በትግራይ ክልል 6ኛው ክልላዊ ምርጫ መራጮች ከንጋት (12:00 ሰዓት) ጀምሮ ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።
ከለሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ ለመስጠት ሲጠባብቁ የነበሩ በርካታ ሰዎች ነበሩ።
ድምፅ ሰጭዎች በ2 ሺህ 672 የምርጫ ጣቢያዎች ነው ድምጻቸውን እየሰጡ የሚገኙት።
PHOTO : TIGRAY COMMUNICATION
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ከሀሰተኛ መረጃዎች እራሳችሁን ጠብቁ!
"በኢትዮ - ኤርትራ ድንበር አካባቢ አዲስ ግጭት መከሰቱ ተሰምቷል" በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ እና ሲ ኤን ኤን (CNN) እንደዘገቡ ተደርጎ በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የፎቶ ሾፕ ቅንብር መሆኑን እንዳረጋገጠ 'ኢትዮጵያ ቼክ /Ethiopia Check/ አሳውቋል።

#UPDATE
ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ።
የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረው እና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር።
ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም ስላጋጠማቸው ነው።
ግዙፉ የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ይህ የሚያደናግጥ ሳይሆን የሚያጋጥም ነው ብሏል። ህመም የተሰማቸው ተሳታፊዎች ለምን ህመም እንደተሰማቸው ለማወቅ ጊዜ ይፈልጋልም ሲል ገልጿል።
የኦክስትፎርድ እና የአስትራዜኔካ የምርምር ውጤት የዓለም አገራት ትንፋሻቸውን ውጠው በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ነው።
Via BBC

TIKVAH-ETHIOPIA
ዶክተር ደብረፅዮን የምርጫ ካርድ ወሰዱ! የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው እለት በአደዋ ከተማ በመገኘት የምርጫ ካርድ ተመዝግበው ወስደዋል። በትግራይ ክልል በሚካሔደው ስድሰተኛው ክልላዊ ምርጫ መራጮች ከነሐሴ 15 ጀምሮ እየተመዘገቡ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው። የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ትላንት እንዳስታወቀው ከነሐሴ 15 እስከ…
የትግራይ ክልል ምክትል ር/መስተዳደር እና የህወሓት ሊቀ መንበር የሆኑት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በአድዋ ከተማ ድምፅ ሰጥተዋል።
በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ መራጮች በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አባላት ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
PHOTO : TIGRAY COMMUNICATION
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ መራጮች በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አባላት ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
PHOTO : TIGRAY COMMUNICATION
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ብዙ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጭባቸው የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር እና ታጋይ ኣቦይ ስብሓት ነጋ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ፣ ዓዲ ሓቂ ምርጫ ጣብያ ተገኝተው ድምፅ ሲሰጡ በቴሌቪዥን ታይተዋል።
በትግራይ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በስፋት ወሳጥተው ድምፅ እየሰጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በስፋት ወሳጥተው ድምፅ እየሰጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ማማ - የንግድ ባንክ ህንፃ!
- ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።
- 48 ወለል ያለውና 198 ሜትር ርዝመት አለው።
- ግንባታው በ2008 ዓ/ም ነበር የተጀመረው
- ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና መንግስት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተቆጣጣሪነት እየተሳተፈ ይገኛል።
- መንግስት ለግንባታው ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦለታል።
- ከፕሮጀክቱ የከፍተኛ ትምህርት መምህራርንና ተማሪዎች የዳበረ ልምድ አግኝተውበታል ተብሏል።
- ህንፃው በምስራቅ አፍሪካ በርዝመቱ ትልቅ ይሆናል።
- የህንፃው ግንባታ አሁን በመጠናቀቅ ላይ ነው።
#AlAin

ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል!
ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግና ኮሮናን በመከላከል ትምህርት መጀመር የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እያጠና ይገኛል።
በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ለመረዳት እንደተቻለ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በሌላ በኩል ወላጆች የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለኮሮና ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለው ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
እነዚህን ተቃራኒ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አካባቢዎቹ ወቅታዊ የኮሮና ስርጭት ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ መክፈት የሚያስችሉ መንገዶችን እየገመገመ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው ጥናት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በአንድ ክፍል ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር ፣ የንፅህና መጠበቂያ ለትምህርት ቤቶች ማቅረብ፣ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል።
ሚኒስቴሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ በሚቀርበው ተጨማሪ ምክረ ሃሳብ መሰረት አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል ብሏል።

ሹመት!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።

አቶ ሚሻ አደም ዋስትና ተፈቀደላቸው!
በአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት "ህገ ወጥ የሳተላይት" መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ዋስትና እንደተፈቀደላቸው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። አቶ ሚሻ የ20,000 ብር ዋስትና በማስያዝ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ዛሬ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሠጥቷል።

የአሥራትን ጋዜጠኞች ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የሚል መዝገብ ተከፈተባቸው!
ፖሊስ የአሥራትን ጋዜጠኞች ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት ንብረት እንዲወድም ፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለቱ አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ እንደከፈተባቸው አስራት ቴሌቪዥን አሳወቀ።
አራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ከህዳር 12/2012 ዓ/ም - ሰኔ 12 2012 ዓ/ም ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል መዝገብ ተከፍቶባቸው የነበር ሲሆን በዋስትና ከእስር ሲለቀቁ በሕዳር ወር አሥራትን ከለቀቀው ዮናታን ሙሉጌታ ውጭ ያሉት በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል።
በዛሬው ዕለት ፖሊስ በሶስቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል መዝገብ ያስከፈተ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 6/2013 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
የመንግስት ባለስልጣናት ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ መግለጫ በሰጡበት ወቅት አሥራት ሚዲያ ሁከት እና ብጥብጥ አስነስቷል በሚል የወነጀሉት ቢሆንም አሥራት ሚዲያ ግን ከሀጫሉ ግድያ ቀድሞ ስራ አቁሞ እንደነበር ገልጿል።

ማስታወቂያ!
ለመላው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰብ!
በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ብለን መግለጻችን ይታወቃል።
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
እስከዛው ድረስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከለካል የሚያስችል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ከክፍያ ነጻ በሆነው የዲጂታል ላይበራሪያችን http://ndl.ethernet.edu.et በመግባት አጋዥ መጻህፍትን እያነበባችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

#ዘሓለፉ #ላለፉት #Kandarbaniif
በ2012 ዓ/ም በተለያዩ ምክንያቶች ከጎናችን ያጣናቸውና እና ያለፉ ዜጎቻችንን ዛሬ ጳጉሜ 4 እናስባቸዋለን።
- በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸው ያለፈ
- በ2012 ዓ/ም በነበሩ አለመረጋጋቶች የተገደሉ
- በተለያዩ ህመሞች ታመው ህይወታቸው ያለፈ
- በግድያ ህይወቱ ያለፈ (አርቲስት ሀጫሉን ሁንዴሳ ቦንሳ)
- በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ
- በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ
- በመሬት ናዳ ህይወታቸው ያለፈ
- በበቤሩት አደጋ ህይወታቸው ያለፈ በሌሎችም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ያጣናቸውን ወገኖቻችን 'ነፍስ ይማር' እያልን ዛሬ ጳጉሜ 4 በቲክቫህ ኢትዮጵያ እናስባቸዋለን።
#ዘሓለፉ #ላለፉት #Kandarbaniif
አዲሱ ዓመት ክፉ የማንሰማበት ፣ የሰላም ዓመት ያድርግልን!
#TikvahFamily