TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት IGAD ለጤና ሚኒስቴር 800 ሺ ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

የተደረገው ድጋፍ በድንበር ላይ ፤ በተፈናቃዮቸ አከባቢ እና በስደተኞች ካምፕ የሚሰራውን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ተግባርን ለማገዝ የሚዉል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በኬንያ የሟቾች ቁጥር አርባ ሁለት (42) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።

በተጨማሪ 1,486 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አንድ (21) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 758 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ሶስት (3) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 284 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ድንበር ተሻጋሪ ሾፌሮች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊውን ጥንቅቄ ማድረግ እንዳለባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳስበዋል።

በድንበር አካበቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሮች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ነገር ግን በጎረቤት ሀገራት ያለው የቫይረሱ ሥርጭት መጨመሩ ጋር ታያይዞ አሁንም በእነዚህ አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይ በሥራ ምክንያት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በድንበር አካበቢ ያለውን ቁጥጥር ይበልጥ ለማጠናከር አዳዳስ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆኑን ጠቁመው ፤ አሰራሮችን በሚመለከትም በቅርብ ለሕዝብ የተጠናቀረ መረጃ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል።

በሕገወጥ መንገድ ድንበሮችን ተሻገረው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰዎችን በለይቶ ማቆያ ለማስገባት ደግሞ የማኅበረሰቡ ትብብር እጅጉን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመሆኑም የአካበቢው ማኅበረሰብ ይህን ተረድቶ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrFawziyaAbikar

በሱማሊያ ተጨማሪ 65 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 65 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,284 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አምስት (5) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 135 ደርሷል።

በተጨማሪ በሱማሊያ የሟቾች ቁጥር ወደ 53 ከፍ ብሏል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ (1) ሰው ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በደቡብ ሱዳን ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡ ተሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ በአንድ ቀን 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 231 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቡብ ሱዳን ሟቾችን እየደበቀች ነው?

የደቡብ ሱዳን 2 ዶክተሮች ሀገራቸው የኮቪድ-19 ሞቶችን ሪፖርት እያደረገች አይደለም ብለዋል!

ሁለት (2) በኮቪድ-19 ላይ የሚሰሩ ዶክተሮች የሀገሪቱ መንግስት በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎችን ሪፖርት እያደረገ አይደለም ሲሉ ለ #SSNN ተናግረዋል።

አንደኛው የህክምና ዶክተር በጁባ ወታደራዊ ሆስፒታል በኮቪድ-19 ላይ የሚሰሩ ሲሆን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሳይቀሩ በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል ፤ የሀገሪቱ መንግስት ግን ሪፖርት አላደረገም ብለዋል።

ሌላኛው ዶክተር 'የደህንነትና የፀጥታ አካላት' ስለመንግስት የስራ ኃላፊዎች የኮቪድ-19 ሞት ለየትኛውም ሚዲያ እንዳትናገሩ ብለውናል ሲል ለSSNN ገልፀዋል ፤ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ሞት የተመዘገበው ሚያዚያ ወር ነው የቀድሞው የደቡብ ሱዳን የፍትህ ሚኒስትር ፓውሊኒሆ ዋናዊላ ሁናጎ ሲሞት ነገር ግን መንግስት ሪፖርት አላደረገም ሲሉ ለ #SSNN ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት ዛሬ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሞት መመዝገቡን አሳውቋል። ዝርዝር መረጃዎችን ግን አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ! በደቡብ ሱዳን ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ በአንድ ቀን 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 231 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሞት በይፋ መመዝገቡን ሪፖርት ከማድረግ ውጭ ስለሟቹ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

#SSNN ግን ሟቹ የቀድሞ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ጆን ማዴንግ ጋታዴል ናቸው ሲል ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ከተረጋገጠ 4,487,844 ሰዎች መካከል 300,759 ሰዎች መሞታቸውን ዎርልዶሜትርስ ድረገፅ ያሳያል ፤ 1,688,635 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው 5 ሀገራት፦

- አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ 1,439,649 ፣ ሞት 85,764 ፣ ያገገሙ 311,708

- ዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ የተያዙ 233,151 ፣ ሞት 33,614 ፣ ያገገሙ N/A

- ጣልያን በቫይረሱ የተያዙ 223, 096 ፣ ሞት 31,368 ፣ ያገገሙ 115,288

- ስፔን በቫይረሱ የተያዙ 272,646 ፣ ሞት 27,321 ፣ ያገገሙ 186,480

- ፈረንሳይ በቫይረሱ የተያዙ 178,060 ፣ ሞት 27,074 ፣ ያገገሙ 58,673

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AtoAknawKawza

በደቡብ ክልል እስከ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮቪድ - 19 ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ ሲል የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ #አስጠንቅቋል

የቢሮው ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንዳሉት የከፋ የተጋላጭ ሁኔታ አመልካች እንደሚያሳየው አሁን በበሽታው ዙሪያ የሚያታየውን 'የጥንቃቄ ጉድለት' መቅረፍ ካልተቻለ በክልሉ 60 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ በቫይረሱ ሊጠቃ ይችላል።

📹#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 1,818፣ ሞት 90፣ ያገገሙ 198

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,284 ፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 905

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,284፣ ሞት 53 ፣ ያገገሙ 135

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 758 ፣ ሞት 42 ፣ ያገገሙ 284

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 272 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 108

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 231፣ ሞት 1፣ ያገገሙ 3

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 38

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ኮሮና ቫይረስ ሁሉንም የእድሜ ክልል ነው የሚያጠቃው!

(በዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር)

በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የእድሜ ስብጥር ብንመለከት እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 272 ሰዎች ከህፃናት እስከ አረጋዊያን ድረስ በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ተይዘዋል።

ትልቁ ቁጥር 99 ሰዎች ከ15-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው ፤ ከዛ የሚቀጥለው ከ25-34 የእድሜ ክልል ውስጥ (75 ሰዎች) የሚገኙ ሲሆን ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥርም 19 ነው። በህፃናት ላይ አነስተኛ ቁጥር ቢታይም ህፃናትም በሽታው እንደሚይዛቸው ያሳያል።

ይህ በሽታ የማያጠቃው የእድሜ ክልል የለም። በዓለም አቀፍ ደረጃ #ወጣቶች አይጠቁም የሚል #የተሳሳተ ግንዛቤ አለ ፤ በተለይ በእኛ ሀገር ያለው ስርጭት ትልቁ ቁጥር በወጣቶች ላይ የታየ ነው። ስለዚህ እያንዳንዳችን የምንወስደው ጥንቃቄ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የዚህ በሽታ ስርጭት #እየጨመረ የሚሄድ ሊሆን ቢችልም ምን ያህል ይጨምራል የሚለውን የምንወስነው በየዕለቱ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ፣ በየዕለቱ በምንመርጣቸው ምርጫዎች እንዲሁም በምንወስዳቸው እርምጃዎች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 146 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሱዳን)

የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 146 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና 1 ሰዉ ህይወቱ ሲያልፍ 7 ሰዎች ማገገማቸዉን ገልጿል።

ቫይረሱ የተመዘገበበት አድራሻ ፦

1. ካርቱም ግዛት 120
2. ጀዚራ 6
3. ገዳሪፍ 10
3. ከሰላ 7
4. ምስራቅ ኮርዶፋን 3

በዚህ መሰረት ባጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1964 (ካርቱም ግዛት 1594) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 91 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 205 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር!

ሲጠበቅ የነበረው 'የትንሳኤ ሎተሪ' ትላንት በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ወጥቷል አሸናፊ ቁጥሮቹም ከላይ የምትመለከቷቸው ናቸው!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,707 ላቦራቶሪ ምርመራ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 287 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ17 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል (ጉባ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (መተማ ለይቶ ማቆያ) እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 7

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 7

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ ሁለት (112) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለተገኙት 2 ግለሰቦች!

በጤና ሚኒስቴር እንደተገለፀው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት (2) ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው በክልሉ ግንቦት 5/2012 ዓ.ም ከተላኩት 63 ናሙናዎች መካከል ነው።

ሁለቱ (2) ግለሰቦች የ35 እና የ29 አመት ዕድሜ ያላቸው እና #ከሱዳን በጉባ ወረዳ በአልመሀል ቀበሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በፖዌ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የቆዩ ናቸው።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ በመገኘቱ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በጤና ባለሙያዎች የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ራሱንና ህብረተሰቡን መታደግ እንዳለበት አሳስብዋል።

(የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!

በአውሮፓ ለሚዘጋጁ ክትባቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ #ክትባት በቀጣዩ አንድ (1) ዓመት ውስጥ እውን ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል - #AlAin

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

ሱማሌ ክልል ከጅቡቲ ፣ ከሱማሊያ እና ከኬንያ ሰፊ ደንበር ሽፋን የሚዋሰን በመሆኑ በሞያሌ፣ በደወሌና በሱማሊላንድ በኩል የሚገቡ ዜጎች #እየተበራከቱ መምጣት ጋር ተያይዞ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ እንዳይሰራጭ #ሥጋት ፈጥሯል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሥጋቱን ለመቀነስ እንዲሁም ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ የማስተማርና የማስገንዘብ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን 'ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ' ተናግሯል።

ክልሉ አስር (10) ለይቶ ማቆያዎችን አዘጋጅቶ ከአንድ ሺህ 200 በላይ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ማድረጉንም አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ የሟቾች ቁጥር አርባ አምስት (45) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።

በተጨማሪ 2,100 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ ሶስት (23) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 781 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በቃሊቲ ጉሙሩክ ጣቢያ የድንበር ተሻገር አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀምሯል!

#FTA

የድንበር አቋራጭ ከባድ የመኪና አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ለወረርሽኙ ካላቸው ተጋላጭነት አንጻር በወደቡ ገቢ ጭነት ሲያራግፉም ሆነ ወጪ ጭነት ሲጭኑ በሚኖረው ሂደት የዘመቻ ስራው በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከአሁን በፊትም በወደቡ የሰው ንክኪ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እንዲሁም ገቢ ጭነት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ርጭት የማካሄድ ፣ ማንኛውም አሽከርካሪና እና ረዳት ወደ ወደቡ ሲገባ እና ጭኖ ሲወጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የሙቀት ልኬት ማድረግ አስገዳጅ ሆኖ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዛሬ ግንቦት 07 ቀን 2012 ዓ/ም ደግሞ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በአሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተጀመረ መሆኑን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia