TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FightCOVID19

ከፌም ኢምፔክስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሴፍ ወይ ሱፐር መርኬት) የተላከ መልዕክት ፦

- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በዝቅትኛ ኑሮ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለህፃናት ለአዋቂ የሚሆን የታሽጉ ምግቦች እና የፅዳት እቃ ፣ እገዛ አድርጓል። ዋጋው 105,000.00 ብር በላይ እንደሚሆንም ተነግሮናል።

- በተጨማሪም የድርቅ ጭነት ለማጓጓዝ የሚያገለግል ቫን ተሽከርካሪ ጥሪ በተደረገለት ወቅት የነዳጅ ወጪን በመሸፈን አገልግሎቶች እንዲሰጥ ተውስኗል። የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተርም ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሴንትራል ሆቴልና ከሴንትራል ግራንድ ሞል ሀዋሳ ባለቤት ወ/ሮ አማረች ዘለቅ የተላከ መልዕክት ፦

- መጪው የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ በሴንትራል ሆቴልና በሃዋሳ ግራንድ ሞል በኩል አቅም ለሌላቸው ወገኖች የበአል ስጦታ ተበርክቷል።

- ድጋፉ ለበአል ፍጆታ የሚውሉ ዘይት ፣ ዱቄት፣ እንቁላል ፣ ፓስታ፣ እሩዝ እና ሳሙናዎችን ነው ለአካባቢው ነዋሪዎችና በድርጅቱ ለሚገኙ ሰራተኞች ነው የተሰጠው።

ይህ የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ከ150 ሺህ ብር በላይ እንደሚተመን ደግሞ የሴንትራል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍትህ ወልደሰንበት ነግረውናል።

ከዚህ በፊት ወ/ሮ አማረች የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ገበያ ስለማይኖራቸው ኪራይ መክፈል ይቸግራቸዋል በማለት 1 ሚሊየን ብር የሚያገኙበትን የሁለት ወር ኪራይን ለሃዋሳ ሴንትራል ግራንድ ሞል ተከራዮቻቸው ነፃ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

በተጨማሪ ሰራተኞቻቸው ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስኪገታ ድረስ 'ያለምንም እቀነሳለሁ ስጋት' ስራቸውን ከነሙሉ ደሞዛቸው ይዘው እንደሚቀጥሉ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 602 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። በሌላ በኩል 2,972 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ቁጥሩ ከMARCH 13 በኃላ ሪፖርት የተደረገ ዝቅተኛው ኬዝ ነው።

- በፈረንሳይ ተጨማሪ 762 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 15,729 ደርሷል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ25,500 በልጧል። በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 603,488 ሆኖ ተመዝግባል።

- የቱርክ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል 90 ሺህ የሚደርሱ እስረኞች ለመልቀቅ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።

- በሩዋንዳ በ24 ሰዓት 983 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጣል። በቫይረሱ የተያዙ አጠቀላይ ሰዎች ቁጥር 134 ደርሷል።

- በኤርትራ አንድ (1) ተጨማሪ ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የ25 ዓመት ወጣት ነው። በኤርትራ አጠቃላይ የታማሚዎች ቁጥር 35 ደርሷል።

- የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት 194 እስረኞች በምህረት እንዲለቀቁ ውሳኔ አሳልፈዋል።

- በሱዳን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሷል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 35 መድረሳቸውን የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ዛሬ 2 ፖዘቲቭ ኬዞች ሪፖርት ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከል የሚቻለው በሕግ እና በስርዓት ስንመላለስ ብቻ ነው' - ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተላለፈ መልዕክት!

በዚህ ፈታኝ የአደጋ ወቅት ህዝብን የሚያሸብሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት ፣ በዜጎች ላይ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲደርስ ማድረግ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትል ወንጀል ነው።

መንግስት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመጣስ ተላላፊ በሽታዎችን የሚያሰራጭ፣ የህዝብን ጤና ለአደጋ የሚያጋልጥ፣ ህዝብን የሚያሸብር ሰው በወንጀል ህግ አንቀፅ 514 ፣ አንቀፅ 830 እና አንቀፅ 485 መሰረት እንዲሁም በምግብ ፣ በመድሃኒትና በጤና አዋጅ መሰረት ከቀላል እስራት እስከ #ሞት ድረስ ሊቀጣ ይችላል።

በአንዳንድ ሰው ስህተት ምክንያት ህዝብ እንዳይጠቃ የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] አስመልክቶ የህግ መተላለፎችን ሲመለከቱ 6044 ላይ በመደወል ጥቆማ ይስጡ። ይህን በማድረግ እራሶን፣ ወገኖንና ሀገሮን ይታደጉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WorldHealthOrganization

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ የሰጠው ምላሽ ቀርፋፋ ነው፤ በአካሄዱም ቻይናን ማዕከል አድርጓል ላሉት የዓለም ጤና ድርጅት አገራቸው የምታበረክተውን የገንዘብ መዋጮ እዲቋረጥ አዘዋል።

ይህም ማለት አሜሪካ ለድርጅቱ በየዓመቱ ለድርጅቱ ትሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቆም የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትራምፕን ውሳኔ "ጊዜውን ያላገናዘበ እርምጃ" ሲሉ ተችተውታል።

የማይክሮሶፍት መስራች የሆኑት ቢልጌትስና ባለቤታቸው ሚሊንዳ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያደርጉትን መዋጮ ለማቋረጥ መወሰናቸው " አደገኛ" ነው ሲሉ አውግዘውታል።

"ዓለም የጤና ድርጅቱን ከምን ጊዜውም በላይ ይፈልገዋል" ብለዋል። የጥንዶቹ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው ጌትስ ፋውንዴሽን የዓለም ጤና ድርጀት ትልቁ ለጋሽ ተቋም ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው!

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2,000,000 በላይ ሆኗል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 485,304 ሺህ ደሷል። የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 126 ሺህ 811 ደርሷል፡፡

- ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ባለው መረጃ ከ614 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ በዚሁ በሽታ ሲያዙ ከ26 ሺህ በላይ ያህሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። በትላንትናው እለት ብቻ በአሜሪካ 2 ሺህ 385 ሰዎች በበሽው ሂወታቸው አልፏል፡፡

- በካናዳ የሟቾች ቁጥር ከ900 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 123 ሰዎች ሞተዋል። በሀገሪቱ በቫይረሳ የተያዙ ሰዎች ደግሞ ከ27 ሺህ በላይ ሆኖ ተመዝግባል፤ ከዚህ መካከል 1,383 የሚደርሰው ኬዝ በአንድ ቀን የተመዘገበ ነው።

- በቱርክ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው። ባልፉት 24 ሰዓት 4,062 አዲስ ኬዝ ሲመዘገብ፤ 107 ሰዎች ሞተዋል።

- በተመሳሳይ በሩሲያም ቫይረሱ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት 2,774 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ በአፍሪካ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 790 ደርሷል።

#ETHIOFM #BBC #AFP #SKYNEWS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የስድስት ወራት የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ!

በዓለም ላይ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገራችን ውስጥም በመከሰቱ መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ማሰማራት አስፈልጓል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሙያዎች የተመረቃችሁ እና ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ ሊንኩን በመጫን ለአንድ ወር ያህል እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን፡፡

1. Medicine
2. Public Health Officer
3. Nurse
4. Environmental Health
5. Health Education
6. Pharmacy
7. Medical laboratory
8. Midwife
9. Other Health professionals

ለቅጥር የተመረጣችሁ የጤና ባለሙያዎች ወደፊት በጤና ሚኒስቴር ድረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡ይህንን መረጃ ለሌች የጤና ባለሙያዎች ያጋሩ!

http://www.moh.gov.et/ejcc/am/job-application-form

ከጤና ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 85 ደረሱ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 431 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ43 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ፤ ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“በቤትዎ ይቆዩ”

ኢትዮ ቴሌኮም “በቤትዎ ይቆዩ” በሚል የጥቅል አገልግሎት የቅናሽ ማሻሻያ አድርጓል። ቅናሽ የተደረገባቸው ዕለታዊ አገልግሎቶች:-

1. በ5 ብር 30 ደቂቃ የድምጽና 20 አጭር መልዕት - ይህም ከቀድሞው አንጻር የ53 መቶ ቅናሽ አለው።

2. በ5 ብር 100 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር መልዕክት ወይም በ10 ብር 250 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 የአጭር የጽሁፍ መልዕክት - ይህም ከቀድሞ አንጻር የ56 በመቶ ቅናሽ አለው፡፡

3. በ15 ብር ደግሞ 30 ደቂቃ የድምጽ፣300 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር የጽሁፍ መልዕክት በአንድነት -ይህም ከቀድሞው አንጻር የ45 በመቶ ቅናሽ አለው።

ከጧቱ 12 ሰዓት እሰከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ያለው ትራፊክ መጨናነቁ ሻል ያለ በመሆኑ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ቅናሹ ተደርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚል በጥቅል አገልግሎቱ ላይ ያደረገው ማሻሻያ ከነገ ሚያዝያ 8፣ 2012 ጀምሮ ለ2 ወራት ያህል እንደሚቆይም አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ፣ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጊፍት ሪል እስቴት በላከልን መልዕክት ቃል የገባውን 1,500,000 ብር ለኮቪድ መከላከያ ብሔራዊ ኮሚቴ ማስረከቡን ገልጾልናል።

ይህ ገንዘብ ድርጅቱ ሌሎች ባለሀብቶችን እና የጊፍት መንደር ቁጥር 2 ነዋሪዎችን በማስተባበር በአይነት ካበረከተው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ ግብአቶች ድጋፍ በተጨማሪ ድርጅቱ በግሉ ያበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በላከልን መልዕክት ይህን ወቅት በመደጋገፍ ለማለፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ አሳውቆናል። በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጾልናል።

ድጋፍ እና እገዛን በሚመለከት ፦

- ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠርን በተመለከት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

- ድርጅቱ በሚገኝባቸው ወረዳዎች እና አጎራባች ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ለ400 ሰዎች እገዛ እና ድጋፍ አድርጋል።

- ተቋሙ ለሚያሳድጋቸው 15 ወላጅ አልባ ህፃናት በየወሩ የሚያደርገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የዘይትና የዱቄት ድጋፍ አድርጋል።

የእርድ እና የስጋ ስርጭት አገልግሎትን በሚመለከት ፦

- የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ቀዳሚ የነበረው ሰራተኞችን ማሰልጠን፣ ግንዛቤ መስጠት፣ በተለይም ሚኒ ሚዲያውን በመጠቀም ተሰርቷል።

- ድርጅቱ የሙቀት መለኪያ አስገብቶ ሰራተኞች ሲገቡ ሙቀታቸው እንዲለካ፣ የእጅ ጋንት፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች የንፅህና መጠበቂየዎች እንዲሰጥ ተደርጓል።

- ተሽከርካሪዎች ከከተማ ሲመጡ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ ይገኛል። ኬሚካል ርጭቱ ሊያገኛቸው የማይችሉ የመኪና ክፍል (በተለይም የጎማ ክፍል) 'ማለፊያ ቦታ' ተሰርቶ መኪናዎች ጎማቸው በኬሚካል እንዲፀዳ እየተደረገ ነው።

- እንስሳት ሲገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎ እየተሰራ ነው፣ የእርድ ክፍሎች ሴራሚክ ተደርገዋል፤ ክፍሎቹ ፅዳታቸውን በየጊዜው ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጊኒ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የፊት ጭምብል መልበስን አስገዳጅ ማድረጓን ገልፃለች፡፡ የጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ትናንት ለህዝባቸው ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ዜጋ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ የፊት ጭምብል ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ጭምብል መልበስን ግዴታ ያደረገችው ጊኒ ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ የማያደርጉ አካላት የ 3 ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ፕሬዝዳንት አልፋ የንግድ ተቋማት፤የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ሌሎች ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የፊት ጭምብል እንዲያዘጋጁም ጠይቀዋል፡፡ የሚዘጋጀው የፊት ጭምብል ሀገር ውስጥ የሚመረት እና ብዙ ወጪ የማያስወጣ መሆን አለበት ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia