በተጨማሪ ባለሀብቱ አቶ ብርሃን ተድላ በድርጅቶቻቸው ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞቻቸውን እንዳላሰናበቱ ገልፀውልናል።
ግምሽ ሰራተኞች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የዓመት ፍቃድ እንዲያገኙ በማድረግ እረፍት እንዲወጡ ተደርጓል።
በአዲስ አበባ በተከራዩት 'ቀነኒሳ ሆቴል' ውስጥ የሚሰሩ ግማሽ ሰራተኞች ደግሞ ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለመከላከልና ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል በዛው ሆቴል ውስጥ ደህንነታቸው ተጠብቆ፣ ማደሪያም ተዘጋጅቶላቸው እየሰሩ ይገኛሉ።
በሀዋሳው ኦሲስ ሆቴል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ ከቤታቸው እየተመላለሱ እየሰሩ ቢገኙም ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ በቂ ጥንቃቄ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#StateofEmergency
የተጣሉ ግዴታዎች!
- ማንኛውም በስራ ላይ ያለ ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት።
ተጨማሪ የተጣሉ ግዴታዎችን ይህን ተጭነው ያንብቡ : https://telegra.ph/DrAbiyAhemed-04-11

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራት!
- ለሀይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ አላማ፣ ለመንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው፤
- ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው፣
- ማንኛውም ሀገር-አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- ማናቸውም የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤ 8. የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው፤
ተጨማሪ የተከለከሉ ተግባራትን ይህን ተጭነው ያንብቡ
https://telegra.ph/DrAbiyAhemed2-04-11

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ይህን ብለዋል፦
"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ 16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"
https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ 16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"
https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦
- ህንድ ውስጥ በእድሜ ትንሹ የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ ተመዝግቦ የነበረው የ10 ወር ህፃን ከበሽታው አገግሞ ከሆስፒታል መውጣቱ ተሰምቷል።
- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ20,000 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት ከ1,300 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። አሜሪካ በሟቾች ቁጥር ከዓለም ሀገራት ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች።
- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት 635 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ13,800 በልጧል።
- በሩሲያ ባለፉት 24 ሰዓት 1,667 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 12 ሰዎች ደግሞ መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- በሩዋንዳ 842 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁለቱም ቀድሞ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 120 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 11 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም 18 ደርሰዋል።
- በዩጋንዳ 555 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ከበሽታው አገግመው ከህክምና ማዕከል የወጡ ሰዎች ደግሞ 4 ደርሰዋል።

#StateOfEmergency
የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች ፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች እና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ #ግዴታ አለበት።
የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል።
#PMOEthiopia

የጨርቅ ማስክ አዘገጃጀትና ለመስራት የሚመረጡ የጨርቅ አይነቶች፦
ይህንን በተመለከተ ጥቂት ጥናቶች ቢኖሩም አንዱ ካንዱ እንደሚሻል በእርግጠኝነት መናገር ያስቸግራል፡፡ የጨርቁ ውፍረት በጨመረ ቁጥር የተሻለ የመከላከል አቅም አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ጨርቁን በመያዝ በደንብ የሚያበራን የመብራት ብርሀን ምን ያህል እንደሚያስተላለፍ በመመልከት (light test) የጨርቁን ውፍረት መመዘን ይቻላል፡፡ በቀላሉ ብርሃን የማያስተላልፉ ጨርቆች የተሻለ ይመረጣሉ ማለት ነው፡፡
በአገራችን ሁኔታ ቀላሉ እና ለመተግበር የሚመቸው የጥጥ (cotton) ጨርቆችን መጠቀም ሲሆን በቂ ውፍረት እንዲኖረው ሁለት ተመሳሳይ ልኬት ያላቸውን ጨርቆች መደረብ የተሻለ ነው፡፡
የጨርቅ ማሰክ አስተጣጠብ የጨርቅ ማስክ እንዴት መታጠብ አለበት ከሚለው አንፃር ጥናቶች ባይኖሩም እንደተለመደው በሳሙናና የሞቀ(ትኩስ)ውሃ ማጠብ ቫይረሱን እንደሚገድለው ይጠበቃል፡፡
መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ማስክ ማድረግ ብቻውን ከኮቪድ19ም ይከላከላል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ማስክ መልበስ ከመሰረታዊ ጥንቃቄዎች ጋር ሲቀናጅ የተሻለ ውጤታማ ያደርጋል፡፡
እነዚህም፦
• አካላዊ መራራቅን መተግበር
• አካላዊ ንክኪዎች ማስቀረት
• በተደጋጋሚና በአግባቡ እጅን መታጠብ/በአልኮል ማፅዳት
• ሰዎች በሚበዙባቸው/በሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች አለመገኘት
የጤና ባለሙያዎች ካላቸው የተጋላጭነት ደረጃ አንፃር የጨርቅ ማስኮችን እንዲጠቀሙ ፈፅሞ አይመከርም፡፡ በተቻለ መጠን እንዳስፈላጊነቱ ሰርጂካል ማስክ ወይም N-95 ማስክ መጠቀሙ የተሻለ ነው፡፡
https://yetenaweg.home.blog/2020/04/10/አዲስ-መረጃ-update-ስለ-የፊት-ማስክ/amp/?__twitter_imp
ምንጭ፦BROOK ALEMAYHU

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#GovtofEthiopiaCOVID19
ኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] በሚመለከት በጣም ብዙ ሀሰተኛ መረጃዎች አሉ፤ እውነታዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
🔢 በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ ይችላሉ፤ በእድሜ የገፉ ሰዎች እና አስቀድሞ እንደአስም፥ ስዃር እና የልብ በሽታ አይነት በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች በዚህ ቫይረስ በጠና የመታመም አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላሉ።
❄️ ቀዝቃዛ አየር እና በረዶ ኮሮና ቫይረስን መግደል አይችልም።
☀️ ኮሮና ቫይረስ የአየር ንብረታቸው ሞቃትና እርጥበት አዘል በሆኑ አካባቢዎች ሊተላለፍ ይችላል።
🦟 ኮሮና ቫይረስ በትንኞች ንክሻ አይተላለፍም።
🐶 እንደ ውሻ እና ድመት ያሉ የቤት እንስሳዎች ኮሮናን እንደሚያስተላልፉ አልተረጋገጠም።
🛀 በሙቅ ውሀ መታጠብ ቫይረሱን አይከላከለውም።
💨የእጅ ማድረቂያዎች ኮሮና ቫይረስን መግደል አይችሉም።
🟣 ቫይረሱን ለመከላከል የጰሀይ ጨረርን መጠቀም የለብንም፤ የቆዳ መቆጣትን ሊያስከትል ይችላል።
🌡️ የሙቀት መለኪያዎች ሰዎች ትኩሳት ካላቸው ሊለዩልን ይችላሉ እንጂ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው አይለዩም።
💦 ክሎሪን ወይም አልኮል ልብሶት ላይ መርጨት አስቀድሞ ወደ ሰውነትዎ የገባን ቫይረስ አይገድልም።
💉 እንደ ኒሞኮካል እና ሄሞፊለስ ኢንፍሉዌንዛ ያሉ ፀረ ኒሞኒያ ክትባቶች ከኮሮና ቫይረስ መከላከያ ሊሆኑ አይችሉም።
👃 በተደጋጋሚ አፍንጫን በጨው ውሀ መታጠብ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዙ እንደሚያደርግ የተረጋገጠ መረጃ የለም።
🧄 ምንም እንዃን ነጭ ሽንኩርትን መመገብ ጤናማ ቢሆንም ነጭ ሽንኩርት የተመገቡ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳልተያዙ አልተረጋገጠም።
💊 አንቲባዮቲክስ ቫይረስን አያጠፉም፤ አንቲባዮቲክስ የሚሰራው ለባክቴሪያ ነው።
🧪 እስካሁን ድረስ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልም ሆነ ለማከም ይረዳል የተባለ መድሀኒት የለም።
እነዚህን መረጃዎች የአለም የጤና ድርጅት ድህረ ገፅ ላይ ይዩዋቸው: https://www.who.int/emergencies/diseases/novel-coronavirus-2019/advice-for-public/myth-busters
https://api.whatsapp.com/send?phone=251962228565&text=hi&source=&data=

ለኮሮና ቫይረስ በፍጥነት ክትባት ይገኝለት ይሆን ?
በአሜሪካ የጤና ተቋም CDC በኃላፊነት የሚሰሩት ዶክተር ኤርሚያስ በላይ #ETHIOTUBE ላይ ቀርበው ይህን ተናግረዋል ፦
ክትባትን ለመፍጠር ብዙ ሰዎች በተለያዩ ሀገሮች ብዙ ስራ እየሰሩ ነው ያለው። ይሄ ክትባት ሊገኝ እንደሚችል ብዙ ተስፋ አለኝ። በቫይረስ ጥቃት ለሚመጡ በሽታዎች ክትባት ማግኘት በአብዛኛው ጊዜ ብዙ አይከብድም። የሚከብድባቸው ሆኔታዎችም ግን አሉ።
የኢንፉሌንዛ ቫይረስን ብንመለከት በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚተላለፈው፤ ለኢንፉሌንዛ ቫይረስ ክትባት በየአመቱ ይሰራል። ለዚህኛውም ቫይረስ ክትባት እንደሚገኝለት #ተስፋ አደርጋለሁ። ግን ይሄን ክትባት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ከ8-12 #ወራት ሊወስድ ይችላል።
ቫይረሱ ቢጠቃ በክትባት ሊሸነፍ የሚችልበትን ቦታ ማግኘት ያስፈልጋል፤ ይሄ በላብራቶሪ ጥናት ከተደረገ በኃላ ለዛ ክትባት ተዘጋጅቶ በእንስሶች ውስጥ ሙከራ ማድረግ ይፈልጋል፣ ከዛም በሰዎች ላይ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፣ ከዛም ቁጥሩ በዛ ያለ ህዝብ ላይ ይሄ ክትባት ከበሽታው መከላከል መቻሉ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይሄ ሁሉ ሂደት ረጅም ጊዜ ይወስዳል።
አንዴ በጥናት ከተረጋገጠ በኃላ እንኳን ለብዙ ሰዎች እንዲሆን አድርጎ በስፋት ማምረት እንኳን ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ቢያንስ ቢያንስ ሁለትና ሶስት ወራት ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ ክትባት ማግኘቱን ቀላል ነገር ተደርጎ ቢታሰብም ለግለሰቦች እንዲባዛ አድርጎ ማቅረቡ በጣም ጊዜ ይወስዳል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት (2) ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 286 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሳወቁት ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም (2) ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ፤ አንዷ የ24 ዓመት እድሜ ያላትና ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውሳኔ በፊት ከዱባይ የተመለሰች መሆኗን ገልፀዋል።
ሌላኛዋ ግለሰብ የ35 ዓመት እድሜ ያላትና ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ናት።
እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ3 ሺህ 863 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑም ዶክተር ሊያ አሳውቀዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#DrLiaTadesse
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው ተጨማሪ 286 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረዱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
• ታማሚ 1 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውሳኔ በፊት ከዱባይ የተመለሰች።
• ታማሚ 2 - የ35 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከቱርክ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።

ከኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 197 ደረሱ!
የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሠዓት ውስጥ 766 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው አረጋግጧል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 197 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት አንድ ተጨማሪ ሰው መሞቱም ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሠዓት ውስጥ 766 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው አረጋግጧል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 197 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት አንድ ተጨማሪ ሰው መሞቱም ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሴኔጋል ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 171 ደረሰ!
ከወደ ሴኔጋል እየተሰማ ያለው መረጃ ትንሽ ለየት ይላል፤ በሀገሪቱ በየዕለቱ በቫይረሱ ከሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይልቅ የሚያገግሙት ቁጥር ከፍ እያለ ነው። በአሁን ሰዓት ሴኔጋል ውስጥ 280 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 171 ሰዎች አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከወደ ሴኔጋል እየተሰማ ያለው መረጃ ትንሽ ለየት ይላል፤ በሀገሪቱ በየዕለቱ በቫይረሱ ከሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይልቅ የሚያገግሙት ቁጥር ከፍ እያለ ነው። በአሁን ሰዓት ሴኔጋል ውስጥ 280 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 171 ሰዎች አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቻይና ተጨማሪ አዲስ 99 ኬዞች ሪፖርት ተደረጉ!
ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሯ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አደርጋለች። በቫይረሱ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ከተረጋገጠው ዘጠና ዘጠኝ (99) ሰዎች መካከል ዘጠና ሰባቱ (97) ከውጭ ሀገር ወደ ቻይና የገቡ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሯ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አደርጋለች። በቫይረሱ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ከተረጋገጠው ዘጠና ዘጠኝ (99) ሰዎች መካከል ዘጠና ሰባቱ (97) ከውጭ ሀገር ወደ ቻይና የገቡ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶች ወደ ሸማች ማህበራት ሱቆች መግባት መጀመሩ ተገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ምርቶቹን በተመጣጠነ ዋጋ ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።
ምርቶቹ ወደ 800 ሸማች ማህበራት ሱቆች በብዛት እየገቡ ያሉት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያየዘ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር እና ህብረተሰቡም በዝቅተኛ ዋጋ ማግኘት እንዲችል ነው።
#MayorOfficeAA

ከሰሞኑን 'አዲስ አድማስ' ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ 'ከዱባይና ከሳኡዲ አረቢያ ፣ በርካታ ሺ ኢትዮጵያውያን ለበሽታ በሚያጋልጥ ሁኔታ ወደሀገራችን እየገቡ መሆናቸው፤ ከባድ ስጋት ላይ ጥሎናል' ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር ሊያ - ከሳዑዲ በሁለት (2) ሳምንት ውስጥ ወደ አገራቸው የሚገቡ ከ3 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ፣ ለበሽታ በሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ናቸው ሲሉ ሁኔታው ክፉኛ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።
ያለ ምንም የጤና ምርመራ የሚመጡ መሆናቸው ደግሞ አደጋውን እንደሚያከብደው ሚኒስትሯ ለጋዜጣው ገልፀዋል፡፡በዚህም ምክንያት በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጪዎቹ ሁለት (2) ሳምንታት ከሳውድ አረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱት ከ3 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት የጤና ምርመራ ሳያደርግላቸው የሚመለሱና የቆይታቸው ጊዜም ጥንቃቄ የተሞላበት ባለመሆኑ ትልቅ ስጋት ላይ ጥሎናል ብለዋል፡፡
እነዚህን ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆየት የሚቻልባቸውን ቦታዎች የማዘጋጀቱ ሥራ መጠናቀቁን የገለፁት ዶ/ር ሊያ ፤ ተመላሽ ዜጎቹ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንድ ክፍል ለአንድ ሰው ብቻ እንዲሆን ለማድረግና የምግብ አቅርቦትና የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንዲቆዩ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

#FightCOVID19
- በወረዳ 14 አስኮ አዲስፈር በሚባለው ቦታ ላይ የሚገኙ አቶ ቶፊቅ ጀማል የተባሉ ባለሀብት ለ21 ተከራዮቻቸው የ268,000 ሺ ብር የአንድ ወር የቤት ኪራይ በመተው ለወገን ደራሽነታቸዉ አሳይተዋል።
- በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ውስጥ የሚገኘው የኪዳነ ምህረት አካባቢ አብሮ አደግ ወጣቶች ማህበር ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር ከተለያዩ የህህበረሰብ ክፍሎች ያሰባሰቡትን ከ100,000 ብር በላይ የሚገመት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በአካባቢው ለሚገኙ ከ100 በላይ አካል ጉዳተኞችና ደጋፊ ያጡ አረጋዊያን የማከፋፈል ስራ ተሰርቷል።