TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር በተያያዘ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ያሉ መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሰረት ህብረተሰቡ 6244 ነጻ የስልክ መስመርን ከዛሬ ጀምሮ በመጠቀም ቫይረሱን በሚመለከት መረጃዎችን ማድረስ ይችላል ብለዋል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብዛዕባ ሕማም ኮሮና ኣመልኪቱ ብቋንቋ ትግርኛ ሓበሬታ ንምልውዋጥ ዘኽእል ነፃ ስልኪ መስመር ካብ ፅባሕ ንግሆ 3:00 ጀሚሩ ሰርሑ ብዕሊ ክጅምር እዩ።

ናብዛ ቑፅሪ ይደውሉ #6244

A toll-free telephone number in Tigrigna.
#6244 #Tigray #Ethiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስለኮሮና ቫይረስ ማወቅ ያለባችሁ እውነታዎች፦

(ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋው)

- በብዛት የሚታዩ ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስምታት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ደረቅ ሳል አብዛኛው የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚያሳዩት ምልክቶች ናቸው። መደበኛ ባይሆንም የመገጣጠሚያ ህመም፣ ጤንነት አለመሰማት፣ ተቅማጥ፣ ማስመለስ ባይበዙም አብረው ሊታዩ ይችላሉ።

- ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች የታየበት ግለሰብ ጋር ንክኪ ያደረገ፣ በአንድ ቤት ውስጥ አብሮ ያሳለፈ፣ በአንድ መኪና ወይም አውሮፕላን አብሮ የተጓዘ እንደሆነ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል። አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጠቃ ጀምሮ እስከ 14 ቀን ድረስ ምልክቱን ሊያሳይ ይችላል።

- ቫይረሱ ከእድሜ አንፃር ሲታይ አብዛኛውን ሞት እና የህመም ደረጃ ከ50 በላይ የእድሜ ክልል ባሉ ሰዎችንና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለበሽታው ከፍተኛ ተጋላጭ መሆናቸው ይታያል። የበሽታው፣ የሞት መጠንም በነዚህ ሰዎች ላይ ከፍ ይላል።

- ቫይረሱ ህይወት በሌላቸው ነገሮች ላይም ይቆያል። ከአንድ ቀን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ህይወት በሌላቸው ነገሮች ላይ ይቆያል። ስርጭቱ የሚቆይበትን ጊዜ አሁን ላይ መገመት ከባድ ነው። እንደ WHO ከሆነ ስርጭቱ እስከአንድ አመት ሊቆይ ይችላል።

- ህይወት በሌላቸው ነገሮች ላይ ቫይረሱ ከ1-6 ቀን ይቆያል፤ ሰው ላይ ሲሆን የመተንፈሻ አካል ላይ፣ አይን ላይ ህክምና እስካልተሰጠ ድረስ፣ እስኪያገግም ድረስ፣ ሊቆይ ይችላል። የተለየ ህክምናም የለውም፤ ህክምና እርዳታ ግን ይደረጋል። በመሆኑም ሰውነት ላይ የሚቆይበትን ጊዜ እንዲህ ነው ተብሎ አይገለፅም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአውሮፓ አገራት ቫይረሱን ተቆጣጥረው ነፍስ ለማዳን መጠነ ሰፊ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

"ይሄ እሳት እንዲነድ አትተዉት" በማለት በአውሮፓ እየታየ ያለው የኮሮናቫይረስ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢነትን ለመግለፅ ሞክረዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ይህን ያሉት በርካታ የአውሮፓ አገራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን እንዲሁም ሞትን እያስመዘገቡ ባለበት በዚህ ወቅት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማትረፍም ሀገር ስትኖር ነው!

በነገራችን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ በህክምና ቁሳቁሶችና በፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተጋነነ ዋጋ የሚጠይቁ ድርጅቶችን ለመቆጠር እና የተፈላጊ ምርቶችን አቅርቦት ለማሻሻል የተደራጀው ግብረሃይል ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል። ትላንት ምሽት እንደተገለፀውም መንግስት ተገቢውን እርምጃ ይወሰዳል።

#AtoMelakuAlebel

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምክንያት አፍሪካ ከፍተኛ ምጣኔ ሃብታዊ ድቀት ሊገጥማት እንደሚችል በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ የወጪ ገቢ ንግድ ፣ ነዳጅ ግብይት፣ እና ቱሪዝምን ጨምሮ በስድስት የተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ከተቀሪው አለም ክፍል ጋር አላት።

በወረርሽኙ ምክንያት በተያዘው በጀት አመት በአማካይ 3 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድግ የሚጠበቀው የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት በግማሽ አሽቆልቁሎ በ1 ነጥብ 8 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፥ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረገው የምርጫ ክልልን እንደገና ማካለል ወይም ማሻሻል አይደለም ብለዋል። ቦርዱ ተበታትኖ የነበረውን የቃላት የካርታ መረጃ በዘመናዊ መልክ አሰናድቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ካርታነት መለወጡን ነው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ያስረዱት።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 547 የምርጫን ክልሎች ይፋ አድርጓል!

ትግራይ 38፣ አፋር 8፣ አማራ 138፣ ኦሮሚያ 178፣ ሶማሌ 23፣ ቤኒሻንጉል 9፣ ደቡብ 123፣ ጋምቤላ 3፣ ሀረሪ 2፣ ድሬዳዋ 2 እንዲሁም አዲስ አበባ 23 ለፌደራል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ይኖራቸዋል።

አሁን ያሉት የምርጫ ክልሎች በ1976 ዓ.ም በደርግ ዘመን የተካሄደውን የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት በማድረግ በ1985 ዓ.ም መካለላቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል።

#FBC #EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የደቡብ፣ የጋምቤላ፣ የሶማሌ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የሀረሪ ክልል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection2012
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

መቼ ነው ማስክ ማድረግ ያለብኝ ?

- የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ካለባቸው የተለያዩ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ቢያንስ ለ14 ቀናት የፊት ማስክ በማድረግ እና አስፈላጊውን ሁሉ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ይመከራል።

- የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ካለባቸው ሀገራት ከመጡ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ከማድረግ በመቆጠብ እንዲሁም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወይም በጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ሲታወጅ።

#EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia