TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ካለመናበብ ምክንያት በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ያለፈው የፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ!

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት ም/ኮማንደር ባይህ ጥላሁን መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ስአት አካባቢ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በከተማው ውስጥ የነበረውን የፀጥታ ስምሪት እየመሩ ነበር፡፡

ታዲያ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ባጋጣሚ በሌላ አቅጣጫ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የፀጥታ ሀይሎች ጋር ተገናኝተው ስአቱ ጨለማ ስለነበር ግራ ቀኝ ማነህ ማነህ እየተባባሉ እንዳለ ካለመናበብ በድንገት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል የምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ም/ኮማንደር ባይህ ጥላሁን ስርዓተ ቀብራቸው መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በደብረ ኤልያስ ከተማ ደበረ ገነት ቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን ስርአተ ቀብራቸው ይፈፀማል፡፡

ምንጭ፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዝሆን ሎተሪ ወጥቷል!

ዛሬ ከምሽት 12፡00 በእድል የዕጣ ማውጫ አዳራሽ ላይ የወጣው የዝሆን ሎተሪ ማውጫ ከላይ የምትመለከቱት ነው።

• 1ኛ 7,000,000 ብር - የዕጣ ቁጥር 0315625

• 2ኛ 4,000,000 ብር - የዕጣ ቁጥር 0348089

• 3ኛ 2,000,000 ብር - የዕጣ ቁጥር 1698464

• 4ኛ 1,000,000 ብር - የዕጣ ቁጥር 1605818

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ! መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ የህዝቡን ድምፅ ለማፈን የሚጥሩ ኣካላትን ባስቸኳይ ሕጋዊ እርምት መውሰድ አለበት፡፡ የትግራይ ቴሌቪዥን የዓፋርኛ ቋንቋ ጋዜጠኞች በዓፋር ክልል አብዓላ ከተማ ውስጥ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋዜጠኞች ዑመር ኣሕመድ፣ ኣሸናፊ ዳርጌ የካሜራ ባለሙያ ገ/መድህን ኪዳነማርያምና ሽፌር ሃፍቱ…
#UPDATE

ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ በአፋር ክልል ታስረው የነበሩት የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞች ተለቀዋል።

ምንም እንኳን በእስር ላይ የነበሩት ጋዜጠኞች ከእስር ቢለቀቁም ካሜራቸው፣ መኪናቸው እንዲሁም የሞባይል ስልካቸው ግን እስካሁን አንዳልተመለሰላቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] እስካሁን ድረስ መድሃኒትም ሆነ ክትባት አልተገኘለትም፤ ነገር ግን ቫይረሱን መከላከል ይቻላል።

- ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱ እና ትኩሳት ካላቸው ሰዎች ይራቁ!

- እጅዎን በሳሙናና በውሃ አዘውትረው ይታጠቡ!

- ከሰዎች ጋር አይጨባበጡ!

-ለበሽታው አጋላጭ ሁኔታዎች ከነበርዎ እና ምልክት ከታየቦት በአስቸኳይ 8335 ላይ ያሳውቁ፤ የህክምና እርዳታ ያግኙ!

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

- ዛሬ በሊባኖስ በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሁለተኛው ግለሰብ ሪፖርት ተደርጓል፤ በተጨማሪ በሀገሪቱ 8 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንደተገኙ ተረጋግጧል።

- በኢንዶኔዥያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል። በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ 34 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- በፓናማ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል። በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ 8 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- ፖላንድ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭትን ለመከላከል ትምህርቶችን፣ ሲኒማ ቤቶችን፣ ሙዝየሞችን ለመዝጋት እንደወሰነች ተሰምቷል።

- የዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኬይቭ ከወዲሁ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎችን እና ትምህርት ቤቶችን ለጊዜው ለመዝጋት መወሰኗ ተሰምቷል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 1009 ደርሷል። በ24 ሰዓት ውስጥ 115 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ተመዝግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 31 ደርሷል።

- በቱርክ በሀገሯ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መኖሩ በዛሬው ዕለት አረጋግጣለች።

- ኢራን በከፍተ ሁኔታ ቫይረሱ እየተስፋፋ ነው። በ24 ሰዓት ውስጥ በኢራን 958 አዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ይህም አጠቃላይ የተጠቂዎችን ቁጥር 9,000 አድርሶታል። 63 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሞተዋል።

- በጣልያን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12,462 ደርሰዋል። በ24 ሰዓት ውስጥ 2,313 አዳዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ትላንት የሞቱ 196 ሰዎችን ጨምሮ እስካሁን በቫይረሱ 827 ሰዎች ሞተዋል።

- በኳታር በ24 ሰዓት ውስጥ 238 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 262 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በሞሮኮ በኮሮና ቫይረስ 1 ሰው ሞቷል። በ24 ሰዓት ውስጥ ደግሞ 2 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ በዚህም በሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሰዋል።

- በግብፅ በዛሬው ዕለት አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር 60 አድርሶታል።

- በደቡብ አፍሪካ 6 ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ተመዝግበዋል። በሀገሪቱ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም 13 ደርሰዋል።

- በቱኒዝያ ተጨማሪ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተይዟል። በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችም 7 ደርሰዋል።

- ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዛሬ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መኖሩን ይፋ አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

ዛሬ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። መወያያ አጀንዳዎች የሚመለከቱት ናቸው መሆናቸውን እናስታውሳችሁ፦

1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅ፣

3. የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት መርምሮ ማጽደቅ፣

4. የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ሹመት መርምሮ ማጽደቅ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

"አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች እንዳይገቡ ከአውሮፓ የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ አግደናል" - ዶናልድ ትራምፕ

አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአውሮፓ ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ ማገዳቸውን አስታወቁ። በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት በተላለፈው ንግግራቸው ትራምፕ ከማንኛውም አውሮፓ አገር የሚደረግ በረራ ለቀጣዩቹ 30 ቀናት መታገዱን ገልፀዋል።

ነገር ግን ይህ ጥብቅ እና አስፈላጊ እግድ 460 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ባረጋገጠቸው እንግሊዝ ላይ ተግባራዊ እንደማይሆን አስታውቀዋል። በመላ አሜሪካ 1135 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 38 የሚሆኑ ደግሞ ሞተዋል።

"አዳዲስ ኬዞች እንዳይገቡ ከአውሮፓ የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ አግደናል" ብለዋል ትራምፕ ትናንት ከዋይት ሃውስ በተላለፈው ንግግራቸው። ይህ እገዳ ከነገ አርብ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ግዙፍ የተባለ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚያካሂድ ዋዜማ ራዲዮ ዘገበ። በቅዳሜው መርሀ ግብር ላይ እንዲሳተፉም በርካቶች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው። ባለሀብቶች፣ ምሁራንና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙም ተነግሯል።

የቅዳሜው የሚሊኒየም አዳራሽ መርሀ ግብር “የብልጽግና ፓርቲ የማጠናከሪያ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የመጀመርያው ምእራፍ ማብሰሪያ የእራት ግብዣ” የሚል ስያሜ አለው ነው የተባለው። በቅዳሜው የእራት ግብዣ ላይ ለብልጽግና ፓርቲ በይፋ ገንዘብ የማሰባሰብ መርሀ ግብር የማከናወን እቅድ ይኑር አይኑ መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ ሬድዮ ጣቢው ጨምሮ ገልጿል።

ለምርጫ ዘመቻ የፖለቲካ ስራ ገንዘብን በተለያየ መልኩ በድጋፍ ማሰባሰብ በሌሎች ባደጉ ሀገራት የተለመደ ቢሆንም አሁን በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎች ግን በተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጫና በመፍጠር የተከናወኑ ናቸው በሚል ከዚህ ከዚያም ወቀሳዎች ይደመጣሉ።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የONN ጋዜጠኞች ታስረዋል!

የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ሁለት ጋዜጠኞች በመንግሥት መታሰራቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው አስታውቋል።

የታሰሩ ጋዜጠኞችም ደሱ ዱላ እና ዋቆ ኖሌ እንደሚባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶርሳ ደበላ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የኦሮምያ መንግሥት በበኩሉ ጋዜጠኞቹ የታሰሩት በሞያቸው ሳብያ ሳይሆን ጥፋት በመፈፀም ተጠርጥረው ነው ብሏል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#election2012

ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲካሄድ ቀን የተቆረጠለት የዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ 170 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

- የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኮሎራዶ እና በኔቫዳ የነበራቸውን ፕሮግራም ሰርዘዋል።

- በዛሬው ዕለት በግሪክ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ ሞቷል። ግሪክ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች 99 ደርሰዋል።

- ትዊተር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩ አዟል።

- ኤልሳልቫዶር ትምህርት ቤቶችን ዘግታለች። ወደ ሀገሪቱ የትኛውም የውጭ ዜጋ እንዳይገባም አግዳለች።

- የአሜሪካ ግዛቷ አሪዞና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። በተመሳሳይ በዋሽንግተን ዲሲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

- የጣልያን መንግስት ከፋርማሲና ከምግብ መሸጫዎች ውጪ ሁሉም ሱቆች እንዲዘጉ አዟል።

- በUS ፍሎሪዳ የሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትምህርቶችን በኦንላይን እንዲሰጡ ታዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመቶች አፀደቀ!

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀረቡለትን የአራት ሚኒስትሮች የሹመት ጥያቄ ተቀብሎ አፅድቋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

1. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ - የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

2 . ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር

3. አቶ ላቀ አያሌው - የገቢዎች ሚኒስትር

4. ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው በ21 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸው ፀድቋል።

PHOTO : FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቂት ስለ ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሒ፦

ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሒ 'ነበድ' የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት ናቸው። ከሚኖሩበት ብሪታኒያ የተመለሱት በቅርብ ሲሆን ባለፈው ወር የሰላም ሚኒስቴር "የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም አምባሳደር" ብሏቸዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሳዑዲ ዓረቢያ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ጋር በተያያዘ የአውሮፓ ሀገራትን ጨምሮ 50 በሚደርሱ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች።

የጉዞ እገዳው በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ ዓረቢያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የተጣለ መሆኑ ተገልጿል።

በውሳኔው መሰረት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምሮ 50 ከሚደርሱ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ ብሎም ከሀገሪቱ ወደ ሀገራቱ የሚደረግ ማንኛውም በረራ በጊዜያዊነት ታግዷል።

ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኤርትራን ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል። በጉዞ እገዳው 28 የአውሮፓ እና ስድስት የእስያ ሀገራትም ተካተዋል ነው የተባለው።

More https://telegra.ph/COVID19-03-12

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የቀድሞው የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ፥ የስራ ባለደረባቸው የነበሩት ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

ዶ/ር አሚር በትዊተር ገፃቸው ፥ "ዶክተር ሊያ እጅግ ታታሪ ፣ ቅን ፣ አስተዋይ እና በሳል መሪ መሆንዋን በቅርበት በስራ ባልደረባነት በሰራንበት ጊዜያት በሙሉ ተመልክቻለሁ" ሲሉ አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ከደቂቃዎች በፊት በአልጄሪያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል። በሀገሪቱ ዛሬ የተመዘገቡ 4 ኬዞችን ጨምሮ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አቶ ጌታሁን አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ 5 ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ጉባዔው አቶ ጌታሁን አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እንዲሆኑ እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በአዲስ መልክ ለማዋቀር በወጣው አዋጅ መሠረት ለተቋሙ የቦርድ አባልነት የቀረቡ አዳዲስ እጩ ተሿሚዎችን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት፦

1. አወሉ አብዲ - ሰብሳቢ
2. አበበች ሺከታ
3. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ
4. ማንያዘዋል እንደሻው
5. ዳንኤል ክብረት
6. ኦባንግ ሜቶ
7. ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ
8. ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ
9. ጌትነት ታደሰ አባል

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነር!

አቶ ፀጋ አራጌ የሥነ–ምግባርና ጸረ–ሙስና ኮሚሽነር ሆነው ዛሬ ጥዋት ተሹመዋል። ሹመታቸው 11 ተቃውሞ 6 ድምጸ ተዓቅቦ ገጥሞታል። የሰሜን ወሎ አስተዳዳሪ፣ የአማራ ከልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ ነበሩ።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውዝግብ ያስነሳው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሹመት!

ዛሬ የምክር ቤት አባላት ምክር ቤቱ ሹመት በመስጠትና በመንፈግ ላይ መጠመዱን በማንሳት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል።

ለኢትዮጵያ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነ ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መላውን ኢትዮጵያ የሚያገለግል በመሆኑ በእርሳቸው የቦርድ አባልነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡት አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለብቻው ጉዳያቸው ታይቶ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በ148 ድጋፍ በ126 ተቃውሞ እና 24 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የዲያቆን ዳንኤል የቦርድ አባልነት ፀድቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia