TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ካርታ ይፋ ማድረጊያ ቀንን ከመጋቢት 01 ቀን 2012 ወደ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ማዘዋወሩን አስታወቀ።

ምርጫ ቦርዱ የምርጫ ክልሎች ካርታ ዝግጅትን ያጠናቀቀ ቢሆንም ሂደቱ መከናወን ያለበት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መሆን ስላለበት እና በጉዳዩ ላይ ባለሞያዎች ማብራሪያ መስጠት ስላለባቸው ቀኑን መቀየር ማስፈለጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት የምርጫ ክልሎች ካርታ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 05 ቀን 2012 ዓ.ም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ይፋ የሚደረግ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መሰረታችን ጋሞ ፤ ወላይታ ፤ ጉራጌ ፤ ኦሮሞ ፤ አማራ ፤ ትግራይ ቢሆንም ከፍታችን ግን ኢትዮጵያዊነት ነው" - ኢ/ር ታከለ ኡማ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የጋሞ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ላይ ባደረጉት ንግግር መሰረታችን ጋሞ ፤ ወላይታ ፤ ጉራጌ ፤ ኦሮሞ ፤ አማራ ፤ ትግራይ ቢሆንም ከፍታችን ግን ኢትዮጵያዊነት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የጋሞ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም 'የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌት ለሀገር ግንባታ' በሚል መሪ ቃል ነበር የተካሄደው። በወቅቱ የጋሞ የሰላም አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዳዶች ተገኝተው ነበር።

ምክትል ምከንቲባው የጋሞ የልማት ማህበር በአዲስ አበባ ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የከተማ አስተዳደሩ ከጎናቸው እንደሚሆን ገልፀዋል። የልማት ማህበሩ በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች መልካም ጎዳናን በመከተል የአዲስ አበባን ብልፅግና እውን እናደርጋለን ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HumanRightsWatch

የኢትዮጵያ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ዘግቶ የቆየውን የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ገደብ በፍጥነት እንዲያነሳ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሒውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው ለሁለት ወራት የተዘጋው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቤተሰብ እንዳይገናኝ አድርጓል፤ በአካባቢው የነፍስ አድን ሥራ በአግባቡ እንዳይከናወን አደናቅፏል ሲል ወቅሷል።

መንግስት በአካባቢው እየወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃም መረጃ እንዳይወጣ አስተዋጽዖ ማድረጉንም መግለጫው አመልክቷል።

ከታኅሣስ 24 ቀን፤ 2020 ጀምሮ አንስቶ በምዕራብ ኦሮሚያ በቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ ዞኖች የኢንተርኔት እና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ማመልከታቸውን ያተተው መግለጫው በጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ብቻ የስልክ እና የመልዕክት አገልግሎት ብቻ እንደነበር አስታውቋል።

More https://telegra.ph/HRW-03-10

#HumanRightsWatch #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪዎችን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት አንድ ሺ የሚሆኑ የግል ታክሲዎችን ለማስገባት መታቀዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታውቋል። በመንግሥት ሦስት ሺ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ለማስገባት እየተሠራ መሆኑንም ተሰምቷል።

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃዎች ይገባሉ ስለተባሉት ታክሲዎች፦

- በአዲስ አበባ ከተማ ታክሲዎቹን ለማስገባት የታቀደው በግለሰቦች ሲሆን፣ ታክሲዎቹም አራት እና ሰባት ሰዎች የሚጭኑ ላዳዎች ናቸው።

- የእነዚህ ታክሲዎች መግባት የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍና ለበርካታ ዓመታት ባገለገሉ ታክሲዎች ሲሰጥ የቆየውን የትራንስፓርት አገልግሎት ለማዘመን ያስችላሉ ነው የተባለው።

- ከታክሲዎቹ 80 % አራት ሰዎች የሚጭኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የተቀሩት ደግሞ ሰባት ሰው የሚጭኑ ናቸው። ታክሲዎቹን ለማስገባት የሚያስችለውን ብድር ለማግኘት ለንግድ ባንክ ፕሮፖዛል ተልኳል።

- በአንድ ተሽከርካሪ ታክስን ጨምሮ ወደ 800 ሺህ ብር ብድር ግምት ተይዟል። ከላዳ ኩባንያ ጋር ድርድር ተጀምሯል።

- ታክሲዎቹን ለመግዛት ገዥዎቹ እንደ ቤቶች ልማት የባንክ ሂሳብ ከፍተው እንዲቆጥቡ እየተደረገ ነው። ከ10 ሺ 300 በላይ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለማስመጣት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ለእዚህም ወደ 184 ማኅበራት ተደራጅት ተመዝግበዋል።

- በየክፍለ ከተማው ማኅበራቱን የሚወክሉ ሁለት ሁለት ሰዎች እንዲመርጡ ተደርጎ ከሃያ ተወካዮች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።

[የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኞቹን አገደ!

የኢፕድ ከደቂቃዎች በፊት፤ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎችን ካርታ ቅዳሜ ይፋ ያደርጋል” በሚል ርዕስ በሰራው ዜና ስር የተጠቀመው ምስል የተሳሳተ መሆኑን ገልጿል። ለተፈጠረው ስህተትም ይቅርታ ጠይቋል።

የኢ.ፕ.ድ. ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገፁ ላይ ይህንን ስህተት የፈጠሩ ጋዜጠኞቹን ከስራ ያገደ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃም እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀረር ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የለም!

በሀረር ከተማ በጁገል ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ በሽታ ተገኘ በሚል በከተማው የተሰራጨው ጭምጭምታ ትክክል እንዳልሆነ የሀረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ።

የጉዳዩ ይዘት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑት ከደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከተማ ወደ ሀረር ከተማ ቤተሰብ ጥየቃ ከመጡ ቤተሰብ አባላት መካከል ሁለት ልጆች በሆድ ህመምና ማስመለስ ምክንያት እንደሆነ ነው የተነገረው።

ነገር ግን ሁለቱ ልጆች ሲመረመሩ ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውና ልጆቹም አስፈላጊው ህክምና ተደርጎላቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂምን ጨምሮ የቢሮው የኮሮና ቫይረስ መከላከልና ቅድመ ዝግጅት ታስክ ፎርስ በሆስፒታሉ በመገኘት ጎብኝተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ!

መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ የህዝቡን ድምፅ ለማፈን የሚጥሩ ኣካላትን ባስቸኳይ ሕጋዊ እርምት መውሰድ አለበት፡፡

የትግራይ ቴሌቪዥን የዓፋርኛ ቋንቋ ጋዜጠኞች በዓፋር ክልል አብዓላ ከተማ ውስጥ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ጋዜጠኞች ዑመር ኣሕመድ፣ ኣሸናፊ ዳርጌ የካሜራ ባለሙያ ገ/መድህን ኪዳነማርያምና ሽፌር ሃፍቱ ፅጋብ ከ29/06/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሥራ ከተሰማሩበት ተይዘው ታስረዋል፡፡

ከዚህ በፊትም አሶሳ ከተማ ሁለት ጋዜጠኞች ታስረው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር የዓፋርና የፌደራል መንግስት የሚድያ ባለሞያዎቹን ባስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል፡፡

የትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር
01/07/2012 ዓ/ም
መቐለ-ትግራይ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianPressAgency

በኢትዮጵያ ፕሬስ ደርጅት ዛሬ መጋቢት 1,2012 ቀትር 5: 50 ገደማ የተሰራጨው ፎቶ በስህተት አንደሆነ እና ጥፋትም እንደሆነ ምስሉን የተጠቀመው ጋዜጠኛ ድልነሳው ምንውይለት የተናገረ ሲሆን ይቅርታም እንደጠየቀ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት ታደሰ ለwww.fidelpost.com ተናግረዋል።

”ነገሩ እንደተከሰተ ወዲያው ነው ይቅርታ የጠየቀው። አጥፍቻለው። የሰራሁት ነገር ስህተት ነው።” በማለት ጋዜጠኛው ለድርጅቱ እንደተናገረ አቶ ጌትነት ተናግረዋል።

የተቀነባበረው ፎቶ እንዴት ጋዜጠኛው ኮምፒውተር ላይ ሊገኝ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ጌትነት ”ልጁ ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል። እኛም እንደ አስተዳደር ከስራ አግደነዋል። ሌላውን ጉዳይ ፓሊስ እያጣራ ስለሆነ ከዚህ በላይ ምንም ልል አልችልም ” ብለዋል።

www.fidelpost.com በዘገባው ጋዜጠኛውን ጨምሮ ሌላ የድርጅቱ የድህረገፅ ክፍል ሀላፊ ዛሬ ከሰአት ፓሊስ ጣቢያ ለምርመራ አቅንተው እነደነበር ገልጿል።

ምንጭ፦ ፊደል ፖስት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከአንድ ዓመት በፊት በቢሾፍቱ አቅራቢያ ጊምቢቾ ወረዳ ተከስክሶ ህይወታቸውን ላጡ የቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን መንገደኞች አንደኛ አመት የመታሰቢያ ስነ ስርአት ተከናወነላቸው።

የመታሰቢያ ስነ ሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ፣ የአየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር።

#የትራንስፖርትሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶች ማህበር አባላት የዛሬ አመት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ጓደኞቻቸው የማስታወሻ ፕሮግራም አካሂደዋል።

#EliasMeseret #EliasGJ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው...

የዛሬ አመት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ያሬድ ጌታቸው ይጫወትበት የነበረ ሜዳ በጓደኞቹ እና በሥራ ባልደረቦቹ በስሙ ተሰይሟል።

ካፒቴን ያሬድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ካጡ 157 ሰዎች አንዱ ነው።

ወጣቱ አብራሪ ያሬድ ጌታቸው ቅርጫት ኳስ እና እግር ኳስ ይጫወት እንደነበር ጓደኛው ካፒቴን ቢኒያም ዓለማየሁ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው ከጓደኞቹ ጋር ይጫወትበት ነበር የተባለው ሜዳ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። ዛሬ ጓደኞቹ ሜዳው በስሙ እንዲጠራ አድርገዋል። ፎቶው ከDW የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NISS

ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ያስገባው ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መነሻውን ከቱርክ ሜርሲን ወደብ ያደረገው ህገወጥ የጦር መሳሪያው፤ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ገብቶ በቁጥጥር ስር የዋለው፤ በወደቡ ለአምስት ወራት ያህል በድብቅ ተቀመጦ፤ በረቀቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ከገበ በኋላ መሆኑን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ግምታቸው ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ 501 እሽግ ካርቶኖች፤ ከ18 ሺህ በላይ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ጋር መያዛቸውን የጠቆመው መግለጫው፤ ለሽፋን እንዲያገለግሉ ታስቦ የተዘጋጁና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በውስጣቸው የያዙ 229 እሽግ ካርቶኖችም ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

More
https://telegra.ph/NISS-03-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ሄዶ ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተገኘበት የተባለው ግለሰብ ወደ ሀገሪቱ ከተመለሰ ሳምንታትን ያስቆጠረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከትናንት ጀምሮ በማህበራዊ ድረ ገፆች እየተሰራጨ ያለው እና ከኢትዮጵያ እንደ ሄደ ቫይረሱ ተገኘበት በተባለው አሜሪካዊ ጉዳይ ዙሪያ ለኤፍ ቢ ሲ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም መረጃወን የማጣራት ሰራ እየሰራን ነው ያሉት ዶክተር ሊያ፥ ግለሰቡ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረ ቢሆንም ወደ አሜሪካ ከተመለሰ ግን ሳምንታትን ማሳለፉን ከኤምባሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

- በሊባኖስ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የመጀመሪያው ሞት በዛሬው ዕለት መጋቢት 1/2012 ዓ/ም ተመዝግቧል።

- በቻይና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየቀነሰ ቢመጣም የቫይረሱ ስርጭት አውሮፓን እያመሳት ነው። በጣልያን ብቻ በ24 ሰዓት ውስጥ 977 አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል።

- በጣልያን በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 168 ሰዎች ሞተዋል። በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 631 ደርሷል።

- የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጣልያናዊያን ቤታቸው እንዲቀመጡና የግድ አስፈላጊ ነው የሚሉት ጉዞ ካላቸው ደግሞ የመንግሥትን ፍቃድ እንዲጠይቁ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

- ሌላኛው ኮሮና ቫይረስ የራስ ምታት የሆነባት ሀገር ኢራን ናት። በኢራን በ24 ሰዓት ውስጥ 54 ሰዎች ሲሞቱ፣ 881 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- በኢራን አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር 291 ደርሷል። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 8,042 አሻቅቧል።

- የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የኮሮና ቫይረስ የተቀሰቀሰባትን ውሀን ከተማን ጎብኝተዋል። ይህም አገሪቱ በሽታውን መቆጣጠር ችላለች የሚለውን መልእክት ለዓለም ለማስተላለፍ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠቂዎች ቁጥር 7 ደርሷል። ሀገሪቱ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ በሙሉ አቅሟ እየሰራች እንደሆነ ሰምተናል።

- በቱኒዚያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በዛሬው ዕለት 6 ደርሰዋል።

- በቡርኪነፋሶ ዛሬ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ይፋ ተደርጓል። በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 2 ነው።

- በሞሮኮ ዛሬ 1 አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥእ 3 ደርሰዋል።

- በናይጄሪያ 2፣ በካሜሮን 2፣ በቶጎ 1፣ በሴኔጋል 4፣ በግብፅ 59፣ በአልጄሪያ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

- በአሁኑ ሰአት ከቻይና በተጨማሪ እንደ ጣሊያን፣ ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ እና የመሳሰሰሉ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

- ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሀገራት የሚመጡ መንገደኞችን ቅፅ በማስሞላት እና አድራሻቸውን በመያዝ በስልክ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።

- እስካሁን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 1 ሺህ 20 መንገደኞች ተጨማሪ ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን፥ 1 ሺህ 93 መንገደኞች ደግሞ በስልክ ከትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

- ጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ ቢከሰትም በፈጥነት መቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን፥ የሆስፒታል ዝግጅት፣ የግብአት እና የባለሙያዎች ዝግጅትም በስፋት እየተሰራበት ነው።

- የኮሮና ቫይረስ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን የሚያሳይ እና የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ቫይረስ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ላይ መዘናጋት አንደሌለበት ማሰስቢያ ተሰጥቷል።

- ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ መረጃዎች ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውን በማረጋገጥም የበኩሉን ደርሻ እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- መላው ህብረተሰብ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ቀድሞ ለመከላከል የግል ንፅህናን መጠበቅ እና ንክኪዎችን መቀነስ ላይ ትኩረት ማደረግ አለበት ተብሏል።

- ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር በተያያዘ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት ሆነ መረጃዎችን እና እርዳታዎችን ለማግኘት ወደ 8335 መደወል እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል።

#DrLiaTadesse #ኤፍቢሲ #ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በነገራችን ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ውስጥ የሙቀት መጠናቸው ላይ ጥርጣሬ የታየባቸው ሶስት (3) መንገደኞች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ምንም አይነት የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያለተመዘበ ሲሆን ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረጉን እንዲቀጥል ጥሪ እየቀረበ ይገኛል። በተለይም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 8335 ላይ መደወል እንደሚቻል ተገልጿል።

#DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ዙምባቡዌ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠርጥሮ ሐኪሞች ምርመራ ከማድረጋቸው በፊት ከሆስፒታል ያመለጠ የታይላንድ ዜጋ ተይዞ ምርመራ ተደርጎለት ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን የዚምባቡዌ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት በመርካቶ ባደረገው ቁጥጥር የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን በአግባቡ ባልተጠቀሙና ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ በተገኙ አንድ ሺ 71 ግብር ከፋዮች ላይ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዳደራዊ ቅጣት መጣሉን ማስታወቁ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia