#UPDATE
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል!
#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#GERD #ItsMyDam #ItsOurDam
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲሆን ማንኛውም ነገር የኢትዮጵያን ፍላጎትና ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ብቻ እንደሚከናወንና ብሄራዊ ጥቅም የሚነካ ድርድር የኢትዮጵያ መንግስት እንደማያደርግ ገልጿዋል።

#COVID19 #ETHIOPIA
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርጉ ብሄራዊ የሚንስትሮች ኮሚቴ ስለማቋቋም ውይይት አድርጓል። ምክር ቤቱም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚመራና የሚከተሉትን አባላት ያካተተ ኮሚቴ እንዲቋቋም ወስኗል፦
• ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የሰላም ሚኒስትር
• አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትር
• ወ/ሮ አዳነች አቤቤ - የገቢዎች ሚኒስትር
• አቶ ገዱ አንዳርጋቸው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
• ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ - የትራንስፖርት ሚኒስትር
• ዶ/ር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር ዴኤታ

አዲስ ለሚገነባው የሀዲስ አለማየው ልዩ አዳሪ ትምህርት ዛሬ ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ይገኛል!
በአንጋፋው ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ ተሰይሞ በትውልድ መንደራቸው በደብረማርቆስ ከተማ በ100,000 ካሬ ሜትር ላይ ሊገነባ የታሰበውና 2,000 የሚያህሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ለተባለለት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ማስገንቢያ አስመልክቶ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴሩ አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት ትምህርት ቤቱ በአንጋፋው ደራሲ በሀዲስ አለማየው መሰየሙ ስማቸው በራሱ ትምህርት ይሆናል ብለዋል፡፡ አክለውም ሀገር የሚለወጠው በሰው ነው ሰው የሚለወጠው በትምህርት ቤት ነው ሲሉ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት አጉልተው ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም የት/ቤቱ የዲዛይን ገጽታ ለታዳሚው የቀረበ ሲሆን ከ100,000 ካሬ ወደ 200,000 ከፍ እንዲል ምክረ ኃሳብ የቀረበበት ሲሆን አሁን በተሰጠው በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ ላይ ይገነባል ተብሏል፡፡
ዝግጅቱ በቀጥታ ስርጭት በአማራ ቴሌቭዢን እየተላለፈ ይገኛል፡፡ ከውጭ ሀገርና ከሀገር ውስጥ በዚህ ዝግጅት መሳተፍ ለሚፈልጉ ተከታዩን የስልክና የባንክ አድራሻዎች ተጠቅሰዋል፡-
0912005385, 0913066163, 0911814122, 0911953473
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 100294537043
አቢሲኒያ ባንክ፡- 16642134
PHOTO : #TikvahFamily

#የካቲት11 #ሚሊንየምአዳራሽ #ህወሓት
የህወሀት 45ኛ ዓመት የምስረታ በአል የማጠቃለያ ዝግጅት በድርጅቱ ደጋፊዎችና አዲስ አበባ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች በሚለኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ መከበሩን ቀጥሏል።
በበዓሉ ላይም በርካታ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ደጋፊዎች፣ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በትግሉ ወቅት የነበሩ ማነቃቂያ ሙዚቃዎችና ሙዚቃዊ ድራማዎች በበዓሉ ለተገኙ ታዳሚዎች እየቀረበ ይገኛል። የይህም ትግራይ ህዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ የከፈለውን መስዋዕትነት እየተዘከረ ያለበት መድረክ ነው።
#TikvahFamily
የቲክቫህ ቤተሰቦች ከሚሊኒየም አዳራሽ!
PHOTO : የትግራይ ኮሚኒኬሽን

"የህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን ትደግፋለች" - አብደል ቢላል አብደልሰላም
የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም ተናገሩ።
አምባሳደሩ በግድቡ ላይ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን ለግብጽ ወግናለች በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጨውን ወሬ አጣጥለውታል።

በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም ለኢዜአ የተናገሩት፦
በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሱዳን ለግብጽ እንደወገነች ተደርጎ እየተስተጋባ ይገኛል። የሚሰራጨው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው። የዚህ መሰረተ ቢስ መረጃ ምንጮችም መቀመጫቸውን ግብጽ ካደረጉ የማህበራዊና መደበኛ መገናኛ ብዙሃን የሚመነጭ ነው።
ሱዳን ባላት እውነተኛ ፍላጎት ለግድቡ ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ ከኢትዮጵያም ጋር በትብብር ሰርታለች፤ የሱዳን ድጋፍ ባይታከልበት ኖሮ ፕሮጀክቱ እዚህ አይደርስም።
ሱዳን ከቴክኒካል የውሃ ግድብ አሞላል ጉዳዮች ይልቅ በአባይ ወንዝ ዙሪያ የጋራ ትብብር ሁልጊዜም አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች። ሀገራችን የታላቁ ህዳሴ ግድብ በውሃ መጠን ላይ ጉዳት የለውም የሚል እምነት ነው የያዘችው።
ጥቃቅን ልዩነቶች ይፈታሉ የሚል ተስፋ አለኝ። አገሮቹ በጉዳዩ ላይ ረጅም ርቀት የተጓዙ በመሆኑ ያን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል እምነት የለኝም። በህዳሴው ግድብ ላይ በተደረጉ ድርድሮች የተለያዩ ከበድ ያሉ ጉዳዮች በመታለፋቸው ቀሪ ጉዳዮች ከዚህ ግባ የማይባሉ ናቸው።
#ኢዜአ

#ItsMyDam #GERD #ItsOurDam
የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ፦
"አባይን መገደብም ይሁን በምትፈልገው መልኩ መጠቀሙ ሉአላዊት የሆነቸዋ ኢትዮጵያ ምርጫ ነው። የኢትዮጵያ ምርጫ የሌሎች የአባይ ተፋሰስ አገራትን ፍላጎት በእጅጉ እስካልተጻረረ ድረስ በግብጽ እጅ ጥምዘዛ አባይን እንዳትጠቀም የሚደረገው ሴራ በአንዲትን ሉአላዊት አገር ላይ የሚደረግ ድንበር ዘለል ጥቃት ተደርጎ ሊቆጠር ይገባል።"
More https://telegra.ph/GERD-02-29-2

#ItsMyDam #ItsOurdam #GERD
"እኔ እናት ነኝ ለልጄ የተሻለች አገር እፈልጋለሁ! ሰላም እፈልጋለሁ! ለዚህም ካለኝ ላይ ለህዳሴው የምችለውን አድርጌያለሁ። ተማሪ ሆኜ የ3 ወር ቁርሴን፣ ሠራተኛም ሆኜ የ3 ወር ደሞዜን ሰጥቻለሁ። በህዳሴው የመጣ በአይኔ መጣ! ወገኖቼ እኛ እርስ በእርስ ሰንባላ ለጠላት ደስታ ነው፡፡ ሁሉንም ትተን አንድ ሆነን ስለ ህዳሴው እንቁም! የአድዋን ድል ማክበር ብቻ ሳይሆን አድዋን እንድገም መባላት ትተን ለሠላም ለብልፅግና እናብር ያኔ ጠላትም ይፈራናል።" - #GenetHailu
#ItsMyDam #ItsMyBlood

#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD
"የኅዳሴ ግድብ ድርድር ከምርጫ በኋላ ይከናወን" - አቶ ጃዋር መሀመድ
ምርጫ 2012 እስከሚካሄድ ድረስ ኢትዮጵያ ከኀዳሴ ግድቡ ድርድር እንድትወጣ ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ ጥሪ አቀረቡ። ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫውንና በቅርቡ በአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ቃል የተገባውን ብድር በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ጫና ለማሳደር እየተጠቀመችበት ነው ብለዋል ፖለቲከኛው።
በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ መወሰናቸው ትክክል ነበር ያሉት ፖለቲከኛው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአቋማቸው ሊፀኑ ይገባል ብለዋል።
ግብፅና ሱዳን አስቸጋሪ የአገር ውስጥ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ኢትዮጵያ ያሉባትን አንገብጋቢ የአገር ውስጥ ጉዳዮች (ምርጫው 2012ን ጨምሮ) እስከምታጠናቅቅ ድርድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ብለዋል። መንግሥት የድርድሩን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ኀብረት በመውሰድ የአባል አገራቱን ድጋፍ እንዲሰበስብም አቶ ጃዋር መሃመድ መክረዋል።
[አሐዱ ቴሌቪዥን]

#ItsMyDam #GeduAndargachew
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያወጣው መግለጫ "ተቀባይነት የሌለው እና እጅጉን ለአንድ ወገን ያደላ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያወጣው መግለጫ "ተቀባይነት የሌለው እና እጅጉን ለአንድ ወገን ያደላ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #NAMA #GERD
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።
ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡
ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል ብሏል፡፡
#ኢትዮኤፍኤም #ሙሉቀንአሰፋ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ስለተወሰነዉ የቋንቋ ልማትና አጠቃቀም ረቂቅ ፖሊሲ ተጨማሪ ማብራሪያ፦
እንደሚታወቀው አማርኛ የፌደራሉ የሥራ ቋንቋ በመሆኑ እርስ በእርሳችን እንድንግባባ በማደረግ ረገድ ሚናው ትልቅ ነው።
አማርኛ ቋንቋ በሀገር ወስጥ ያለው የተናጋሪዎች ብዛትና የተደራሽነት ስፋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አንድ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ተግባቦትን ለማሳለጥ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎችን መጠቀም አንዱ መንገድ ነው።
ለዚህም በሀገር ውስጥ ያለውን ትሥሥር ከማጎልበት አልፈው ከጎረቤቶቻችን ጋር ጭምር የሚያስተሣሥሩንን ቋንቋዎች ከአማርኛ ጎን ለጎን ብንጠቀም ይበልጥ ተጠቃሚ እንሆናልን።
ይሄንንም የዘርፉ ባለሞያዎች ሲመክሩ ኖረዋል። የአማርኛ ቋንቋን ይበልጥ በማሳደግ ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለፌዴራል የሥራ ቋንቋነት መጠቀም፣ በሌሎች ሀገራትም እንደታየው ሀገራዊ ጠቀሜታው የላቀ ነው።
ስለሆነም አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች ቢሆኑ ልሳነ ብዙ ሀገረ መንግሥት ከመገንባትም ባሻገር ውስጣዊና ቀጣናዊ ትሥሥር ያፋጥናል። ብሎም ኅብራዊውን የብሔረ መንግሥት ግንባታ ያቀላጥፋል። የሕዝቦችንም መግባባት ያሳድጋል።
አራቱ ለተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋነት የታጩ ቋንቋዎች፣ ማለትም አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና አፋርኛ በሀገር ወስጥ ከሽግግር ጊዜ ጀምሮ የክልል መንግሥታት የሥራ፣ የትምህርትና የአስተዳደር ቋንቋዎች በመሆን አገልግለዋል ።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/FBC-02-29
የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት

ተጨማሪ የፌደራል የስራ ቋንቋዎች...
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት 80ኛ መደበኛ ስብሰባ የቋንቋና ልማት የአጠቃቀም ፓሊሲ ማፅደቁ ይታወቃል። ይህም የኦሮሚኛ፣ የአፋርኛ፣ የትግርኛና የሶማሌኛና አፋርኛ ቋንቋዎች ከአማርኛ ቋንቋ ጋር በአንድ ላይ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia

#Mekelle
ከቀናት በፊት በመንግስት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱት የቀድሞው የኢንሳ ም/ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ እንዲሁም ዩኩኖኣምላክ ተስፋይ ዛሬ መቐለ ሲገቡ በመቐለ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
#ቲክቫህ_ቤተሰቦች_መቐለ
PHOTO : BBC