TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ - የሟቾች ቁጥር 2,807 ከፍ ብሏል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 82,220 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,807 የደረሰ ሲሆን 82,220 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 32,914 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

- የሟቾች ቁጥር 2,859 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 83,706

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,859 የደረሰ ሲሆን 83,706 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 36,636 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ጋር የ30 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።

የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና በኢትዮጵያ የዩኤስ አይ ዲ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ ቦርዱ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ይውላል ተብሏል።

#ETHIOFM107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አጫጭር መረጃዎች ከቢቢሲ፦

- ጃፓን እና ኢራቅ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ ትምህርት ቤቶችን ዘግተዋል። ይህ በቻይና የተለያዩ አካባቢዎችም ተተግብሯል።

- ሳውዲ አረቢያ ለመንፈሳዊ ጉዞ ማንም አይምጣ ስትል እገዳ የጣለች ሲሆን እገዳው ቀጣዩን የሃጅ ጉዞ ይመልከት አይመልከት አልታወቀም።

- ኢራን ዜጎቿ የሚያደርጓቸውን አላስፈላጊ የአገር ውስጥ ጉዞዎች እንዲሰርዙ ያሳሰበች ሲሆን በመዲናዋ ቴህራን እና በሌሎች ከተሞች የአርብ ፀሎትን ሰርዛለች።

-አውስትራሊያ ከቻይና የሚነሱ ተጓዦች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ አግዳለች።

- በቫይረሱ 17 ሰው የሞተባት ጣልያን 11 ከተሞችን ዘግታለች።

- ግሪክ ፌስቲቫሎችን በሙሉ ሰርዛለች።

#BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

አስረኛው የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተጀመረ። በጉባኤው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የዘጠኝ ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከቲክቫህ ኢትዮ. መከላከያ ሰራዊት አባላት፦

የደቡብ ዕዝ ስታፍ የሰራዊት አባላት በቶጋ ካምኘ የተሰራዉ የሰራዊቱ መናፈሻ ጋርደን እንዳስደሰታቸዉ እና ከስራ መልስ አረፍ ሲሉ ጥሩ ስሜት እንደፈጠረላቸዉ ገልፀውልናል። መናፈሻውን ከላይ በፎቶው ትመለከቱት ዘንድም አጋርተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አብን ጠርቶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ሰርዟል!

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የአመራሮቹን እና የአባላቱን እስር አስመልክቶ የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ/ም በተመረጡ የአገሪቱ ከተሞች ለማካሄድ ጠርቶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ መሰረዙን አስታውቋል። ሰልፉ "የመንግስት በኩል የታየውን በጎ ጅምርና ሌሎች ተደራራቢ የፖለቲካ ተግባራትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደማይካሄድ" ስለመወሰኑ ነው ያስታወቀው።

https://telegra.ph/NAMA-02-28

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ መንግስት ግልጽ፣ በቂ እና ወቅታዊ መረጃ ለህዝብ እንዲሰጥ እና በፕሮጀክቱ ዙሪያ በሚደረግ ድርድር የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ካለባቸው ሀገራት ከመጣችሁና ትኩሳት ፣ ሳልና የመተንፈስ ችግር ካጋጠማችሁ ላስቸኳይ የህክምና እርዳታ 8335 እንድትደውሉ የጤና ሚኒስቴር አደራ ብሏችኃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ያለባቸው ሀገራት፦

China
South Korea
Cruise ship (Diamond Princess)
Italy
Iran
Japan
Singapore
Hong Kong
United States
Germany
Kuwait
Thailand
France
Bahrain
Taiwan
Malaysia
Spain
Australia
United Kingdom
Vietnam
United Arab Emirates
Canada
Macau
Iraq
Russia
Oman
Switzerland
Austria
Croatia
Greece
India
Philippines
Finland
Israel
Lebanon
Pakistan
Sweden
Afghanistan
Algeria
Belarus
Belgium
Brazil
Cambodia
Denmark
Egypt
Estonia
Georgia
Lithuania
Nepal
Netherlands
New Zealand
Nigeria
North Macedonia
Norway
Romania
Sri Lanka

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የዓለም ደረጃ!

በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች [UAE] የሚገኘው የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ማእከል ሁለት ሺህ ዩኒቨርሲቲዎችን አወዳድሮ ባወጣው ደረጃ መሠረት አምስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተካትተዋል።

ማእከሉ ደረጃውን ለማውጣት ዩኒቨርሲቲዎቹ በየአገራቸው ያላቸውን ደረጃ፣ የሚሰጡትን የትምህርት ጥራት፣ ራሳቸው ያስተማሯቸውን ተማሪዎች የመቅጠር ምጣኔ፣ የፋኩሊቲያቸው ጥራት እንዲሁም በጥናት እና ምርምር ዘርፍ ያላቸው ብቃት በመስፈርትነት ተጠቅሟል።

በዚሁ መሠረት ከሁለት ሺህ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፦

አዲስ አበባ (1 ሺህ 040ኛ) ፣ ጎንደር (1 ሺህ 547ኛ) ፣ መቐለ (1 ሺህ 588ኛ) ፣ ጅማ (1 ሺህ 786ኛ) እና ባሕር ዳር (1 ሺህ 780ኛ) ደረጃ በመያዝ የተካተቱ ዩኒቨርሲቲዎች ሆነዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካኖቹ ሀርቫርድ ፣ ማሳቹስቴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ከ1 እስከ 10ኛ ደረጃ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ከእንግሊዞቹ የኦክስፎርድ (4ኛ) እና የካምፕሪጅ (5ኛ) ዩኒቨርሲዎች በስተቀር በሙሉ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡

[የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ማእከል፣EBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

መቼ ነው ማስክ ማድረግ ያለብኝ ?

የኮሮና ስርጭት ካለባቸው የተለያዩ ሀገራት በተለይም ደግሞ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ቢያንስ ለ14 ቀናት የፊት ማስክ በማድረግ እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ይመከራል። እንዲሁም ከነዚህ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ከማድረግ በመቆጠብ እንዲሁም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወይም በጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ሲታወጅ!

#EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ውድ ቤተሰቦቻችን ራሳችሁን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄዎች ከኤፍ ቢ ሲ ድረገፅ፦

- በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

- ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

- የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

- እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከማጂ ወረዳ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦

በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ የማጂ ወረዳ ባለሥልጣን በመታሠሩ ባለሥልጣኑ መታሠሩ አግባብ አይደለም በማለት የቱም ከተማና የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀዋል።

ከ19/6/2012 እስከ 20/6/2012 ማለዳ ድረስ በርካታ የተኩስ ድምፅ ነበር የሚሉት ቤተሰቦቻችን አርፍዶም በከተማዋ የጎማ ቃጠሎም ታይቷል፤ 2 ሰዎችም በተተኮሰ ጥይት ሞቷል ብለውናል።

ቲክቫህ አትዮጵያ ከማጂ ቤተሰቦቹ የሚመጡ መልዕክቶችን እንዲሁም ስለከተማው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ አሰባስቦ ያጋራችኃል። #TikvahFamily #MajiWoreda

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ እስካሁን ትርጉም ባለው መልኩ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ የገለጹት አቶ አወሉ፤ ነገር ግን አሁን በአዲስ መልክ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተቋቁሞ ሥራውን እየሰራ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ በክልል፣ በዞኖች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#MinistryOfCultureAndTourism

በቅርቡ ከኔዘርላንድስ የተመለሰው የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዘውድ በነገው እለት ለትግራይ ክልል ጨለቆት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተመላሽ ይደረጋል። በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ የርክክብ ሥነ ሥርዓትና ሽኝት እንደሚካሄድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ ፦ 0911360902
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር ተፈተዋል!

የኢትዮጵያ መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰምቷል።

PHOTO : JANO BAND
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል፦

ይህ አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አደባባዩ ላይ ያለዉ የድልድይ አካል ቢወድቅ ከስር ባሉ በተላላፊዎች ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል ይታሰብበት!

#DrivinginAddis #EliasMeseret

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ…
#TPLF #ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

ብልጽግና ፓርቲ ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም፤ ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ።

#EthioFM #አባቱመረቀ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention አሁንም በአንዳድን የማንቡክ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ እየተገለፀልን ከቤተሰቦቻችን እየተገለፅልን ነው። በአካባቢው የተፈጠረውንና እየተፈጠረው ያለውን ዝርዝር ጉዳይ ከቤተሰቦቻችን ጠይቀን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን አካተን እንድታነቡት እናደርጋለን። ለሁሉም ግን የሚመለከታችሁ አካላት [የፀጥታ ኃይሉ] የአካባቢውን ደህንነት እንድታስጠብቁ የቲክቫህ ማንቡክ ቤተሰቦች አሳስበዋል።…
#UPDATE

በዳንጉር ወረዳ ተስተውሎ የነበረው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉን የመከተል ዞን አስታወቀ፡፡ የፀጥታ ችግሩ 3 ሰዎችን ለህልፈት፣ 7ቶችን ደግሞ ለከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ሰለባ ከማድረግ ባለፈ የተወሰኑ ቤቶች እንዲቃጠሉ ምክንያት መሆኑንም ተገልጿል።

በፀጥታ ኃይሎች ፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና በሐይማኖት አባቶች የተቀናጀ ስራ የተስተዋለው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉንና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በአካባቢው የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዘመትም በተቀናጀ መልኩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ያቆየውን አብሮ የመኖር እሴት አክብሮ ለዘላቂ ሰላም መስፈን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

[የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia