TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዛሬ ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው ክርስቲያን ታደለ፤ ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ እና ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ይገኙበታል፡፡ [አሐዱ ቴሌቪዥን] @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር አልተፈቱም!
[ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8]
መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው 63 ተከሳሾች ውስጥ እስካሁን ያልተፈታው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ መሆኑ ተገለጸ።
ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር መለቀቃቸውን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል። ኤርሚያስ አመልጋ ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ቢሆኑም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም።
ያልተፈቱበት ምክንያት ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኤርሚያስ አመልጋ ከአስር እንዲፈቱ ደብዳቤ ባለመጻፉ ምክንያት መሆኑን በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው ተናግረዋል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጉዳይ በመንግስት በኩል ለውጥ የለም፣ ይፈታሉ ብሏል ደብዳቤውም ለማረሚያ ቤቱ ይላካል እስካሁንም የዘገየው የሚጣሩ ጉዳዮች ስላሉ ብቻ ነው እንጂ መፈታታቸው አይቀርም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
#ኢትዮኤፍኤም #ሳሙኤልአባተ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#COVID19
ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ መካ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች። የጉዞ እገዳው ሐይማኖታዊ እና መደበኛ ተጓዦችን የሚያካትት ሲሆን፥ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ካለው የኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ተሰምቷል።
ይህን ተከትሎም ወደ ሳዑዲ ለሐይማኖታዊ የፀሎት ስነ ስርአትም ይሁን ለጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎች መታገዳቸውን ገልጻለች። ከዚህ ባለፈም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ከተገኙባቸው ሃገራት የሚነሱ መንገደኞች ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡም እገዳ ተጥሏል።
አመታዊው የሃጅ እና ዑምራ ጉዞ ከአምስት ወራት በኋላ ይካሄዳል፤ በአመታዊው ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ ያቀናሉ። የአሁኑ የጉዞ እገዳ እስከ ሃጅ ዑምራ ጉዞ ስለመቆየት አለመቆየቱ ግን የተባለ ነገር የለም።
#አልጀዚራ #ኤፍቢሲ

'የጋዜጠኞች ወግ' መፅሀፍ የካቲት 21 ይመረቃል!
'የጋዜጠኞች ወግ' መፅሃፍ የፊታችን የካቲት 21 በባህር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት እንደሚመረቅ የመፅሃፉ ፀሃፊ ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። ከመፅሃፍ ምርቃው በተጨማሪ ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅት እንደተዘጋጀም ተገልጾልናል።
በዕለቱ አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከረጅም ጊዜ በሗላ መድረኩን እንደሚቆጣጠር የተነገረን ሲሆን ብርቱካን፣ ሀረገወይን፣ ጌጡ ተመስገና እ መሳይ ወንድሜነህ ደግሞ የመድረኩ ፈርጦች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባህር ዳር ከተማ ቤተሰቦችም የካቲት 21 በአቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ እንድትገኙ በክብር ተጋበዛቸሗል፡፡

#SolveITAccelerator
5 ሚሊዮን ብር ለሥራ ጀማሪዎች ማጠናከሪያ!
iCog labs,JICA ከኩዱ ቬንቸር በተገኘው የ5,000,000 ብር [አምስት ሚሊዮን ብር] የገንዘብ ድጋፍ ሥራ ላይ ያሉ እና ምርትና አገልግሎታቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ላይ ለተሰማሩ ሰባት ድርጅቶች የአቅም ማበልጸግ ፣ የገበያ ትስስር መፍጠር እና በትንሹ 250,000 ብር ከፍ ካለ እንደ ፕሮጀክቱ ታይቶ የሚጨመር ድጋፍ ለመስጠት ጀምሯል።
የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ ህሩይ ፀጋዬ እንደገለጹት ሥራ ጀማሪዎቹ ከፕሮግራሙ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ፕላናቸውን ይበልጥ እንዲያሻሽሉ የሚደረግ ይሆናል።
ከ7ቱ ፕሮጀክቶች መካከል 5ቱን በመውሰድ 10 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር ልምድ ልውውጥ እና የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ገበያው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡
"ይህንን መሰሉን ሥራ ስንሰራ በዋናነት ማወቅ የምንፈልገው የቴክኖሎጂው ዘርፍ በኢትዮጵያ ምን አይነት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለውን ነው" ያሉት አቶ ህሩይ "የወጣቱን አቅም ማጎልበትና ትርፋማ ማድረግም ሌላው ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ብለዋል፡፡
በዚህ ስራ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፣ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲና ጥቃቅ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በአጋርነት ይሰራሉ ተብሏል፡፡
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በSolve IT Accelerator ለሚሳተፉ ቤተሰቦቹ ምን ምን ሟሟላት እንዳለባቸው አዘጋጆቹን ጠይቆ ተከታዩን መልስ አግኝቷል፡፡
በመጀመሪያ የራሳቸውን ሥራ የጀመሩ ፣ ሥራ ለመስራት ዝግጅት ጨርሰው በሙከራ ደረጃ የሚገኙ ለምንሰራው ሥራ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ፣ የልምድ እና የገበያ ትስስር የሚፈልጉ መመዝገብ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ከሰባቱ ውስጥ ለመካተት ደግሞ የሚከተሉት መስፈርቶች ይታያሉ፡-
- በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ
- ምርታቸው በገቢያ ውስጥ ገብቶ ውጤታማ መሆኑ ከታመነበት
- የተጠቀሙት ቴክኖሎጂ፣ ያላቸው የማደግ ፍላጎት፣ ህጋዊ ጉዳዮች፣ ለውጥ ማምጣት የሚፈልጉበት ዘርፍ ታይቶ ከሰባቱ ውስጥ ይካተታሉ፡፡
እስካሁን ከሃያ በላይ ሥራ ጀማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን አሁንም በዚህ እድል መጠቀም ለሚፈልጉ ምዝገባው ለተከታታይ 20 ቀናት ክፍት መሆኑን ተገልጿል፡፡
Apply Online http://www.icog-sa.com

#Election2012
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ ፓርቲዎችን ብቁ የማድረጉ ሥራ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ለመመዝገብ እና ለምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስብ እንዲሁም ግንባር/ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርቧል።
ቦርዱ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ከተቀመጠው ጊዜ ገደብ በኋላ የሚመጡ የምዝገባ ማመልከቻዎች በተለመደው አግባብ የሚስተናገዱ ቢሆንም፣ ያለው የአሠራር ሂደት ከሚወስደው ጊዜ አንጻር መጪው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ መሆኑን ገልጿል።
ምንጭ:-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#GAMBELA
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።
ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።
#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።
ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።
#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ!
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
ታራሚዎች ይቅርታ የተደረገላቸውም የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው ተብሏል።
#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
ታራሚዎች ይቅርታ የተደረገላቸውም የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው ተብሏል።
#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የምሽት ሩጫ ሊካሄድ ነው ተብለን ቲሸርት ከገዛን በኃላ ረጫው ሳትደረግ ቀርቷል" - የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
'ኢትዮጵያ አትተኛም' በሚል ሩጫ ሊካሄድ ነው ተብለን፤ ቲክቫህ ላይም ማስታወቂያቸውን አይተን በዳሽን ባንክ በኩል ትኬቱን ገዝተን ነበር።
አዘጋጆቹ በተደጋጋሚ የተለያዩ ምክንያቶችን እየዘረዘሩ ሩጫው መራዘሙን ሲነግሩን ቆይተው ነበር፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም እኛም ስልክ እየደወልን ስንጠይቃቸው ነበር አሁን ግን ስልካቸውም አይሰራም። ስለጉዳዩም ምንም አላሉም።
ረጅም ጊዜ ሆኖታል፤ ሩጫው አልተካሄደም፤ እኔን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ነበርን ቲሸርት የገዛነው ከምን እንደደረሰ ሳይነግሩን ዝም ብለዋል። ይህ ተገቢ አይደለም። ማድረግ ካልተቻለ ምክንያቱ ለህዝብ ማሳወቅ ይገባ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ 'ኢትዮጵያ አትተኛም' ሩጫ ጋር ተያይዞ የቤተሰቡን አባላት ያነሱት ጥያቄ ላይ ምላሽ ለማግኘት ከዚህ ቀድም አዘጋጆቹ ባስቀመጡት ስልክ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም።
ለመጨረሻ ጊዜ ከአዘጋጆቹ የተሰጠው መረጃ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ፍቃድ ካገኘ በኃላ መሰረዙን የሚግልፅ ነው።
አዘጋጆቹ በወቅቱ ለተፈጠረው የፕሮግራም መዛባት ይቅርታ ጠይቀው ነበር። አሁንም ምላሻቸውን በቴሌግራም የሚያደርሱን ከሆነ መልሰን እንድታነቡት እናደርጋለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለመጨረሻ ጊዜ ከአዘጋጆቹ የተሰጠው መረጃ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ፍቃድ ካገኘ በኃላ መሰረዙን የሚግልፅ ነው።
አዘጋጆቹ በወቅቱ ለተፈጠረው የፕሮግራም መዛባት ይቅርታ ጠይቀው ነበር። አሁንም ምላሻቸውን በቴሌግራም የሚያደርሱን ከሆነ መልሰን እንድታነቡት እናደርጋለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
ቢሾፍቱ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የያዘው ሰው ተገኝቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት መረጃ ከቻይና ከተመለሰች 12 ቀን የሆናት እና የቫይረሱን የሚመስሉ ምልክቶች ያሳየች አንድ ግለሰብ ቢሾፍቱ ውስጥ ተገኝታ እንደነበር አንስተው ግለሰቧ ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስዳ፣ ምርመራ ሲደረግላት ነፃ ሆና ተገኝታለች ብለዋል።
#EliasMeseret

#HAWASSA
ከሲዳማ ዞን ግጭት ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የነበሩት እና ከሰሞኑን በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረጉት የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ [SMN] አመራሮች፣ እና ሌሎች ምሁራን ከእስር ተፈተዋል። በሀዋሳ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰቦች ጠቁመዋል።
- ዶ/ር ማቴ ማንገሻ ታሪኩ ለማ
- አቶ ጌታሁን ዳጉዬ
- አቶ በላይ በልጉዳ
- ታረኩ ለማ
- ሪ/ፕ/ር አመሉ ጣሚሶ
- ተፈራ ቄንፈቶ
- ረዳት ፕሮፈሰር ተሰማ ኤልያስ
- አቶ ሳሙኤል በላይነህ
- አቶ አዲሱ ቃሚሶ

#UPDATE
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ከእስር እንዲፈቱ የሚያዝ ደብዳቤ መላኩን ሌማት ሚዲያ ዘግቧል።

ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር አልተፈቱም! [ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8] መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው 63 ተከሳሾች ውስጥ እስካሁን ያልተፈታው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ መሆኑ ተገለጸ። ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር መለቀቃቸውን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል። ኤርሚያስ አመልጋ ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ቢሆኑም እስካሁን…
62 ግለሰቦች ከእስር ተለቀዋል ?
ዛሬ ጥዋት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጠው መረጃ ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር ተለቀዋል፤ የሚቀሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ ናቸው ቢሉም ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሌሎች ግለሰቦችም ከእስር እንዳልተፈቱ አረጋግጧል። የግለሰቦቹ የቅርብ ሰዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደነገሩን ከሆነ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተቋም ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሰጠው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ጥዋት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጠው መረጃ ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር ተለቀዋል፤ የሚቀሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ ናቸው ቢሉም ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሌሎች ግለሰቦችም ከእስር እንዳልተፈቱ አረጋግጧል። የግለሰቦቹ የቅርብ ሰዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደነገሩን ከሆነ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተቋም ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሰጠው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ እንደተደረገበት የከተማ አስተዳደሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
በአዲሱ ማሻሻያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።
እስካሁን በነበረው ህግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።
#MayorOfficeAA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ እንደተደረገበት የከተማ አስተዳደሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
በአዲሱ ማሻሻያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።
እስካሁን በነበረው ህግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።
#MayorOfficeAA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
የብስክሌት ትራንስፖርት መንገድ🤔 በየት በኩል ነው ብስክሌት ተገልጋይ የሚያልፈው ? ለብስክሌት ነው የተሰራው ወይስ ለመኪና ማቆሚያ ? ይህን ነገር የታዘቡት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚሰሩትን መልካም ስራዎች እንደራሳችን አድርገን መጠበቅ ካልቻልን በምንፈልገው ያህል ማደግ አንችልም ብለዋል። ህብረተሰቡ ቢያንስ የሚሰሩ ስራዎችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። ቪድዮው ትላንት ምሽት የቲክቫህ…
መንግስት ሰርቶ ዞር ማለቱ ተገቢ አይደለም!
በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞና ለቡ አከባቢ ለብስክሌት መተላለፊያ ተብሎ የተሰራው መንገድ 2 ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ቦታ ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት አሳዛኝ ነው ሲሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች ትዝብታቸውን አካፍለዋል፦
- ብሎኖቹን እየተፈቱ ነው።
- አሽከርሻሪዎች እየገጩ ይጥላሉ።
- በለቡ አከባቢ የባጃጅ ማጠቢያም ሆኗል።
- በግለሰቦች እየተቀሉ ነው።
ይህ ሁኔታ መንግስት ሰርቶ መሄድ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርግና ህዝቡም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት እንዳለበት የሚያሳይ ነው። ሚዲያዎችም በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።
ሌሎች አስተያየታቸውን ያካፈሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ይህ ገንዘብ ወጪ ተደርጎበት የተሰራው ስራ ምን ያህል ታስቦበታል፤ ምን ያህልስ አገልግሎት ይሰጣል የሚለው በጥልቀት ተጠንቶ መሰራት ነበረበት ብለዋል።
ለመኪና እንኳን መንገዱ እንደሚጠብ የሚያነሱት ቤተሰቦቻችን ከተሰራ በኃላ ደግሞ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ መስራት ያስፈልግ ነበር ፤ ህብረተሰቡም እንደራሱ ንብረት ሊጠብቅ ይገባው ነበር ሲሉ ገልፀዋል።
በተለይ የብስክሌት ተጠቃሚዎች አስተያየት አካፍሉ @tikvahethiopiaBot
#TikvahFamily

#NewsAlert
የኢራን ምክትል ፕሬዘዳንት Masoumeh Ebtekar በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መጠቃታቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ከቀናት በፊት የኢራን ምክትል ጤና ጥበቃ ሚንስትር ኢራጅ ሀሪርቺ ኮሮና ቫይረስ [#COVID19] እንዳለባቸው መገለፁ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የሰልፉ አስተባባሪ እና የዲሲ ግብረ ኃይል ተወካይ አቶ ጣሰው መላከሕይወት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ ነው። አሜሪካ እንዲሁም የዓለም ባንክ ከአደራዳሪነት ወደ ታዛቢነት እንዲመለሱ እንደሚፈልጉም አክለዋል።
"ሰልፉን የጠራነው የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ሲል በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት ለመግባት ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እየፈጠረ ስለሆነ፤ ያንን ተጽዕኖ ከኢትዮጵያ እንዲያነሳ ለመጠየቅ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
#BBC

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ክልል የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ተጠርጣሪ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዞ በምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተያዘው ተጠርጣሪ በሀሰተኛ መንገድ ካዘጋጃቸው፦
- መንጃ ፍቃዶች፣
- የትምህርት ማስረጃዎች፣
- የተለያዩ ማህተሞች ፣
- ፓስፖርቶች፣
- ቲተሮች፣
- የልደት ካርዶችና ሌሎች የተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም ለማተሚያነት ከሚጠቀምበት ኮምፒዩተርና የማሸጊያ ማሽን ጋር በህብረተሰቡ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።