TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ...

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ #የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

(AlAin Amharic)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
📸በትላንትናው ዕለት በብሄራዊ ቤተ መንግስት ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ 'የጋራ ታሪካዊ ምዕራፍ እናክብር' በሚል መሪ ቃል የተደረገው የእራት ግብዣ!

PHOTO:FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPolice #University #Ethiopia

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በዩኒቨርሲቲዎች አጋጥመው ለነበሩ ግጭቶች እጃቸው አለበት የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እየተለዩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ተጠርጣሪዎችን የመለየት ስራውን አሁንም እንደቀጠለ ነው ተብሏል። የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች ብዛት አሁን ላይ መናገር ባንችልም ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራርንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውስጥ ግጭት አነሳስተዋል የተባሉት ተለይተው እየታሰሩ ነው ብለዋል።

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#Hawassa #AddisAbeba #Wolkite

በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን የመስጂዶችና የንብረት ቃጠሎ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በጅማ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ በጅማ ከተማ ስታዲየም ተገኝቶ ድርጊቱን አውግዟል። በሃዋሳ ከተማ በመስጂደ-ራህማ ፣ በወልቂጤ ፣ በአሰላ ፣ በአዲስ አበባ ኑር መስጂድ፣ በኢሊባቡር እና ሌሎች ከተሞች ህዝበ መስሊሙ "ድምፃችን ይሰማ" በሚል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል።

በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ ህዝቡ መንግስት አጥፊዎችን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ፤ የንብረትም ሆነ ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸውና በክልሉ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ የተቃጠሉ መስጂዶችን በአፋጣኝ በማስገንባት የዘወተር አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ እንዲደረግ ተጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው። በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል። ክሱ የተመሰረተው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ በተካሄደ የደን ምንጣሮ ስራ ጋር ተያይዞ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KombolchaIndustrialPark

ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአምስት ወራት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አስግኝቷል!

ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለፉት አምስት ወራት ወደ ተለያዩ የውጭ ሃገራት ከላካቸው ምርቶች ከሦስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማስገኘቱን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ መኮነን እንደገለጹት በፓርኩ ውስጥ የተገነቡት ዘጠኝ ሼዶች በሙሉ ለስድስት የውጭ ባለሃብቶች ተላልፈዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም አራቱ ምርቶታቸውን ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት መላክ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የሁለቱ ባለሃብቶች ኩባንያዎችም ማምረት መጀመራቸውንና በቅርቡ ምርታቸውን ወደ ውጭ ለመላክ በሂደት ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ሌሎች ባለሃብቶችም ሸዶች እንዲሰጧቸው፤ ፖርኩ ውስጥ ስራ የጀመሩት ደግሞ ማስፋፊያ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ መሆኑን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

ኦነግ ከኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሌሎችም ኃይሎች ጋር ግንባር በመፍጠር በመጪው #ምርጫ "ጥሩ ተፎካካሪ" ለመሆን በሂደት ላይ እንደሚገኝ የኦነግ ቃል አቃባይ ቶሌራ አደባ ለፋና ተናግረዋል። ጥምረቱ "እስከ ውህደት" ሊዘልቅ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የበዓሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ እንዲመጡ እጋብዛለሁ!!" - አቶ ጥራቱ በየነ (ምክትል ከንቲባ)

በሀዋሳ ከተማ ከሚስተናገዱ ታላላቅ መንፈሳዊ በዓል አንዱ የሆነውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ሲከበር ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ቅድመ ውይይት ተደርጓል።

በተለይም በሀዋሳ ከተማ በቅርቡ የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ በሰላም ከመጠናቀቁ በኃላ የሚከበር በዓል በመሆኑ የከተማው ጸጥታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል።

በከተማዋ በርካታ ስብሰባዎች መካሄድ፣ የከተማው ገቢ ማደግ እና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ጥያቄ እየጨመረ መምጣት የሰላም መኖሩ አረጋጋጭ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ጥራቱ በየነ አክለውም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ የከተማው ነዋሪ ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ የጽዳት ዘመቻ እያደረጉ መሆኑን የገለፁ ሳሆን የበዓሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ጋብዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ...

በማንኛውም ሁኔታና ጊዜ የጸጥታ ኃይሉን ድጋፍ የሚፈልግ ሁሉ ከዚህ በታች በተቀመጠ የስልክ ቁጥር በመጠቀም መፍትሄ ማግኝት እንደሚቻል የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።

1. ታቦር ክ/ከተማ.............046-212-8782
2. መናኸሪያ ክ/ከተማ.......046-221-0371
3. ባህል አዳራሽ ክ/ከተማ...046-220-7140
4. ሀይቅዳር ክ/ከተማ.......046-221-0086
5. አዲስ ከተማ ክ/ከተማ... 046-220-4031
6. መሀል ክ/ከተማ............046-212-3704
7. ምስራቅ ክ/ከተማ............046-212-4078
8. ቱላ ክ/ከተማ.............046-229-0225
9. ሀ/ከ/ፖሊስ መምሪያ.....046-220-1046

በተጨማሪም፦

- የከተማ ወንጀል መከላከል ሀላፊ (0916378829)
- የከተማ ፖሊስ አዛዥ (0916828073)

#HAWASSA #ታህሳስ19 #የቅዱስገብርኤልበዓል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

ለመጪው #ምርጫ ወደ 300,000 ገደማ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንደሚመለመሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ብዙወርቅ ከተተ ተናግረዋል። ቦርዱ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል እና ለማሰልጠን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ለፋና ገልጸዋል።

(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#ETHIOPIA

መስጂድ አይፈርስም!
ቤተክርስቲያንም አይፈርስም!
ኢትዮጵያም አትፈርስም!
አፍራሾች ግን ይፈርሳሉ!

📸በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች የተደረጉ ሰልፎች!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia