TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETH ከፍተኛ የተማሪዎች ቅሬታን ከሚቀበልባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው። ከመቀሌ የደረሱኝን መልዕክቶች በቀጣይ ቀናት የማቀርብ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግለሰብ ቤት የገባ ነብር በ5 ሰ ዎች ላይ ጉዳት አደረሰ!
ነብር! በአንኮበር ወረዳ ጨፋ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቁልፌ በተባለ ቦታ አንድ ግለሰብ ቤት የገባ አንድ ነብር በአምስት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

እለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 23/2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ ወደ አቶ ደጀኔ በልሁ ቤት ትልቅ አዉሬ እየጮኸ መጣ፡፡ አቶ ደጀኔ በልሁ በአዉሬ ልንበላ ነዉ እርዱኝ ሲል ተጣራ፡፡ በቅርብ ርቀት ላይ በሰንሻይ ንብረት ጥበቃ ላይ የሚገኘዉ ዲያቆን አክሊሉ ማማዬ ከታላቅ ወንድሙ አቶ እንግዳ ማማዬ ጋር ፈጥነዉ ወደ አቶ ደጀኔ በልሁ ቤት ደረሱ፡፡ ሲደርሱም የቤቱ ባለቤት ተነክሻለሁ አዉሬዉም እቤት ነዉ ሲል ተናገረ፡፡

አቶ እንግዳ ማማዬ ወደ ቤት ፈጥኖ ሲገባ ነብሩ ዘሎ ያዘዉ ፊት ለፊትም ተገጣጠሙ በአንድ ጥይትም በሽንጡ ቢመታውም ነብሩ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል፡፡ ነብሩም ተመልሶ ቤት ሸሽቶ በመግባት ገለባ ላይ ተደበቀ፡፡ ዲያቆን አክሊሉ በቀዳዳ በማሾለክ በሦስት ጥይት መታዉ፡፡ አሁንም ሳይወድቅ ወደ ሰዎቹ መጣ ግቢ ዉስጥ ወድቆ ያገኘዉን ቆርቆሮ በመሳብም ተደበቀ፡፡

ዲያቆን አክሊሉም ይህንን ባየ ጊዜ እንዳያመልጥ በማለት ለመቅደም ሲሞክር ነብሩ ዘሎ መሣሪያዉን በማስጣል አንድ እጁን ጐረሰዉ፡፡ ወደ አንገቱ ሄዶ ለማነቅ ሲሞክርም አቶ አለሙ ታደሰ የወደቀዉን መሣሪያ በማንሣት ነብሩን ራሱ ላይ መታዉ፡፡ ነብሩ በእነዚህ ሰዎች ርብርብ የተገደለ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ወደ ጐረቤላ ጤና ጣቢያ በመሄድ እርዳታ የተደረገላቸዉ ሲሆን አቶ እንግዳ ማማዬ ግን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ደ/ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት የህክምና ርዳታ እያገኘ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ የአን/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ መኮንን ትላንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ!
ዜና እረፍት! የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ መኮንን ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። እንደ ህክምና ባለሞያዎች ማረጋገጫ ከሆነ የህልፈተ ህይወታቸው ምክንያት ያጋጠማቸው የልብ ድካም ህመም ነው።

ስርአተ ቀብራቸው ዛሬ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ልደታ ቤተክርስቲያን ይፈፃማል።

TIKVAH-ETH ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው እና ለጎንደር ነዋሪዎች መፅናናትን ይመኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍትሀዊ ነው ፍርዱ? በምዕራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ከእስረኞች ማደሪያ ግቢ ውስጥ ተረኛ ጥበቃ የሆነው ፖሊስ ኮንስታብል እረታ እሸቱ በእስር የነበረችን የ22 ዓመቷን ግለሰብ አዲሴ እሸቴን ሚያዚያ
13/08/2010 ዓ/ም ከእስር ቤቱ አውጥቶ በመሳሪያ በማስፈራራት፣ በመደብደብ ከጥበቃዎች ማደሪያ ክፍል ውስጥ በማስገባት አስገድዶ የደፈረ ሲሆን በአቃቢ
ህግ ተከሶ ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 19/08/2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት 2 ዓመት ከ3 ወር #ቀላል እስራት ተፈረደበት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ለበለጠ መረጃ

📞0919 74 36 30
📧Wtsegab@gmail.com
📧Wtsegab@yahoo.com
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «TIKVAH-ETH ለበለጠ መረጃ 📞0919 74 36 30 📧Wtsegab@gmail.com 📧Wtsegab@yahoo.com»
ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ....

"መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምግብ ምንም ሊስማማን አልቻለም። ተማሪውም ለማን ቅሬታ እንደሚያደርግ ግራ ገብቶታል ስለዚህ እባክህን ይሄን አድርስልን። እና ሽሮ በተደጋጋሚ የሚቀርብልን ሲሆን እሱም ደረጃውን የጠበቀ አሰራር አይሰራም አሁንስ መረረን! ከዚህ በተጨማሪ ምግብ የምንቀበልበት ሳህን የቆየ እና ለማጠብ የሚያስቸግር ሳህን ነው እንዳውም አንዳንድ ጊዜ ራሳችን እንጠበው የምንልበት ሰአት አለ። እና ወንድሜ ይሄን ለሚመለከተው ባለጉዳይ አስተላልፍልን። ከአድሀቂ ካምፓስ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንዲለቀቁ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ኢትዮጵያዊያኑ እንዲፈቱ ወሰኑ፡፡

ምንጭ፦ ETV ዜና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ...

"በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ ከሳምንት በላይ ሆኖናል የመጠጥ እንዲሁም የግል ነፅህናችንን የምንጠይቅበት ውሃ አጥተናል እባካችሁ መልክታችንን አድርሱልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡታጅራ! ከላይ የምትመለከቱት ከሳምንት በፊት ቡታጅራ አካባቢ ዝናብ የሰነጣጠቀው መንገድ ነው።

ፎቶ ምንጭ፦ አቤኑ የሳንጅዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል! ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳዕና ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ ላይ በደረሰ የመሰንጠቅና የመቦርቦር አደጋ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገለጸ፡፡ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ ውስጥ ይህ ክስተት መፈጠሩ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳዕና ቡታጅራ የሚወስደው
መንገድ በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ ተጓዦች ሌላ አማራጭ እንዲጠቀሙ ተገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእሳት አደጋ! በጎሬ ከተማ የሚገኘው የጎሬ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ቤተሙከራ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በ54 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳትና 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ እሳቱን የአካባቢው ማሕበረሰብ በመተባበር በቁጥጥር ሥር ያዋለው ሲሆን የተጎዱ ሰዎችም ሕክምና እንዲያገኙ መደረጉን የጎሬ ጠና ጣቢያ የሕክምና ባለሙያ አቶ ሲሳይ በግዱ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸኙ! የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። ለአዲሷ
አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ደግሞ የአቀባበል ስነ ስርዓት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተደርጓል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ...

"ፀግሽ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገዳም አካባቢ የምንገኝ ፍሬሽ ተማሪዎች በጣም እየተጎዳን ነው። ኮሞሮስ የሚባለው የገበያ ማዕከል ፈርሶ ሱቁ የሚባል ነገር የለም። እና ደግሞ የምግብ ጭማሪ ተደርጎብናል። ስቃይ ላይ ነን። የሚመለከተው አካል ጉዳዩን ይይልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚድሮክ! የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ለሜድሮክ ጎልድ በለገ ደንቢ የወርቅ ማእድን ማውጣት ፍቃድ እድሳት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን እንደሚያይ ገለፀ።

ከፍቃድ እድሳቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ውዥንብር ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ነው የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ቴድሮስ ገብረእግዚአብሄር የተናገሩት።

እንደ አቶ ቴድሮስ ገለጻ፥ ለሜድሮክ ጎልድ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ለገ ደንቢ የወርቅ ማእድን ልማት የፍቃድ እድሳት መደረጉን ተከትሎ የተፈጠረው ችግር ለአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ ከመስጠት አንፃር የተፈጠረ ክፍተት አለ።

ለሜድሮክ ጎልድ የፍቃድ እድሳቱ ከመደረጉ በፊት ኩባንያው የራሱን የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀረበ መሆኑንም አቶ ቴድሮስ ገልፀዋል።

ሚኒስቴሩም በራሱ መንገድ ከኬሚካል አንፃር ናሙናዎችን ወስዶ አውሮፓ ድረስ በመላክ አስጠንቷል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ወገን በመሆን በዚህ ሂደት መሳተፉንም ነው ሚኒስቴር ዴታው ያስታወቁት።

ለሜድሮክ ጎልድ ለ10 ዓመት የተደረገው የፍቃድ እድሳትም በዚህ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ መሆኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ቴድሮስ የተናገሩት።

ከዚህ ውጭ ፍቃዱን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፥ በውይይቱ ሂደት የሚኖሩ ግኝቶች ካሉ ሚኒስቴሩ ያየዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ! በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት መፈታቱን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። በግቢው በነበረው አለመረጋጋት በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
💚 ፍቅር በውስጣችን ካለ ሁሌም ይቅር ባዮች ነን፣ ፍቅር ካለን በደልን አንቆጥርም። ፍቅር ካለን ቂምን ጨርሶ አናውቀውም።

💚 ፍቅር በውስጣችን ካለ አመፅን፣ ክፋትን፣ ምቀኝነትን፣ ክፉ ቅናትን ድባቅ እንመታለን።

💚 ፍቅር በውስጣችን ካለ እየተበደልንም ቢሆን ይቅር እንላለን።

ፍቅር እንዳይጎድለን!
TIKVAH-ETH

@tsegabwolde
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

.ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ጥዋት ባሌ ሮቤ የሚገቡ ሲሆን የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት አብረዋቸው ይጓዛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሮቤ! የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነገው እለት ወደ ኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ያቀናሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ ጋርም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

በነገው እለት ጠዋት ላይም በሮቤ ስታዲየም ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከባሌ ዞን ከተወጣጡ ቁጥራቸው 850 ከሚደርሱ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር የሚወያዩ ይሆናል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይም በዞኑ የኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር እንደሚያካሂዱም ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia