TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.6K photos
1.41K videos
203 files
3.86K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በድሬደዋ ዩንቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የTextile Engineering ተማሪ ዛሬ ጠዋት ከፎቅ ወድቆ ሂወቱ ማለፉን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ። የተፈጠረው ክስተት እየተጣራ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እናሳውቃለን ብሏላ። ዩኒቨርሲቲው በተከሰተው ህልፈተ-ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

(ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች!

በነገው እለት በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምክንያት ከንጋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ታላቁ ሩጫ መነሻውና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ በነገው እለት ማለትም ህዳር 7 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዚህም መሰረት በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የጎዳና ሩጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፡-

• ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ለልደታ ፀበል ወደ ልደታ ብሪሞ ሜዳ
• ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ሜክሲኮ
• ከአብነት በጆሳንሰን ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ
• ከሞላ ማሩ ወደ ጨፌ ሜዳ
• ከበርበሬ በረንዳ ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ
• ከተክለሃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ አምባሳደር ቲያትር ፍልውሃ
• ከገብርኤል መሳለሚያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከገብርኤል መሳለሚያ ወደ ካሳንቺስ
• ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ኡራኤል
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ባምቢስ ኡራኤል
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጨርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት
• ከቡልጋርያ ወደ ገነት መብራት ሜክሲኮ አደባባይ
• ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ሜክሲኮ አደባባይ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-11-16

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቅንጅት ባደረጉት ክትትል ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ፡፡

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረገውን ክትትል ተከትሎ ስምንት የውጪ ሀገር ዜጎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሜታ ፋብሪካ አካባቢ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን በመከራዬት በህገ-ወጥ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘብን አስመስለው ሲሰሩ መያዛቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የጉዳዩ መርማሪ የሆኑት ዋና ሳጅን በሪሁን ስለሺ ገልፅዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ በህገ-ወጥ መንገድ አመሳስለው ያዘጋጁት 512 ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ፣ ትክከለኛ የሆኑ 455 ሺ 200 መቶ የኢትዮጵያ ብር እና 1900 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም በብር እና በዶላር መጠን የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው ወረቀቶች ፣ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማዘጋጀት ሲጠቀሚባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ኬሚካሎችና ቁሳቁሶች እንደተያዙ ከዋና ሳጅን በሪሁን ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

https://telegra.ph/ETH-11-16-2

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Channel photo updated
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦

በየዕለቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እየሰማን ያለነው የወንድሞቻችን ሞት፤ የእህቶቻችን ስቃይ ክፉኛ ልባችንን እየሰበረው ነው። በሌላ በኩል ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ወገንተኝነት ወንድሞቻችንን ከማስታረቅ፣ ከማስተቃቀፍ ይልቅ ደም እንዲቀርቡ የሚያደርግ ነው።

ይህ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወንድማማቾች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነገ ሳይሆን ዛሬ፤ በኃላ ሳይሆን አሁን መቆም አለበት። መንግስት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ድምፅ ሰምቶ መፍትሄ ይፈልግላቸው። እኛም የወንድሞቻችንን ድምፅ ማሰማታችንን እንቀጥላለን። የማህበራዊ ሚዲያውን ተጠቅመን ደግሞ ወንድሞችንን የማግባባት፣ የማስማማት፣ የማስታረቅ ስራም እየሰራን ነው። ሁላችንም ከላይ የምንመለከተውን ምስል የፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ ሁላችንም ወንድማማቾች ነን፤ ከፀብ ይልቅ መዋደድ ይበልጣል እንበል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ "ሁላችንም እህትማማቾች ነን!" የፕሮፋይል ፒክቸር እንዳለቀ እናጋራችኃለን። የገፃችን ፕሮፋይል ፒክቸር በየአንድ አንድ ቀኑ የሚቀየር ይሆናል!!

"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ምክር ቤቱ ክቡር አቶ አክሊሉ መኔዶ ሎምበሶ በምክትል ዋና አስተዳዳሪ ማዕረግ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሆኑ የቀረበው ጥቆማ በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል...

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታልን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በዶ/ር ቦጋለች ገብሬ ስም እንዲሰየም በቀረበው አጀንዳ ዙሪያ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ሆስፒታሉ የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ተብሎ እንዲሰየም በሙሉ ድምጽ ተወስኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

"በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ" የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 47 ነጥብ 4 ኪሎግራም ኮኬይን ተብሎ የሚጠራ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ ትናንት በቁጥጥር ስር ውሏል።

አደንዛዥ ዕፁ በቁጥጥር ስር የዋለውም በጉምሩክ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ ክትትል መሪነት ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ጋራ በቅንጅት በተሰራ ኦፕሬሽን ነው። ከድርጊቱ ጋር በተያያዘም አምስት የብራዚል ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ተጠርጣዎቹ በነበራቸው የሆቴል ቆይታ በእጅ በሚያዙ ሻንጣዎችና ቦርሳዎች በድምሩ 47 ነጥብ 4 ኪ.ግ የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ተለያዩ ሀገራት ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

(የገቢዎች ሚኒስቴር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ኮንፈረንስ...

በሲዳማ እና በኦሮሞ ጉጂ ብሔሮች መካከል ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በቦሬ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

(ELU)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአማራና የትግራይ ክልል ምሁራን ለሶስት ቀናት የሚቆይ ውይይት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ ጀምረዋል። የሁለቱን ክልሉች ምሁራን ጉባዔም የሰላም ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ማዘጋጀቱም ተገልጿል።

(EBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!

በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው መደረኩ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት የሚከበረውን 14ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ ላይም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተውጣጡ አፈ ጉባዔዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

(FBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
HT-ማዳጋስካር 1-0 ኢትዮጵያ

የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን ከማዳጋስካር አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በTIKVAH-SPORT በፅሁፍ መከታተል ትችላላችኩ👇

https://t.me/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
#DireDawa_University

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግቢው በር በመዘጋቱ ሳቢያ በጥር እየዘለሉ ለመውጣት መገደዳቸውን እየገለፁልን ነው። መንግስት ምን እንድንሆን ድረስ እንደሚጠብቅ ግራ ገብቶናል ያሉት ተማሪዎች የጠበቃ ኃይሎች ግቢው ውስጥ ቢኖሩም ችግሮች ዶርም ውስጥ ድረስ የሚፈጠሩ በመሆኑ ተማሪውን ስጋት ላይ ጥሏል ሲሉ ገልፀዋል።

መንግስት ወረዳ ድረስ አንከራቶ ያስፈረምን ውል ጥቅሙ አልታያቹ ብሎናል፤ ችግሩ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ ከኃላፊነት ጉድለት ወንድም ከወንድሙ፣ እህትም ከእህቷ እየተቃቃሩ ነው፤ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አሳበዋል። ግቢ ውስጥ እንደልባቸው የሚፈነጩ ፤ ግቢ የሚያተራሙሱ ሰዎችን መቆጣጠር አለመቻችሉ የሚያሳዝን ነው በዚህ ሁኔታ ትምህርት መቀጠል ስለሚያስቸግር መንግስት ተማሪዎችን በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ይሸኝ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጥቂት ሰዓታት በ @tikvahethmagazine በኩል ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረጃዎችን ሰብስበናል። ከሁለቱ (የአማራ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል) ውጭ ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርዓት ነው ያለው።

በሁለቱ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ካለፈው ሳምንት የጀመረው አለመረጋጋት አሁንም ሙሉ ሙሉ ተፈቶ ወደ ትምህርት ስርዓቱ አልተገባም። ጭራስ ስጋቱ ከአንዱ ግቢ ወደላኛው ግቢ እየተዛመተ መጥቷል። ውይይቶች ፍሬያማ ሲሆኑ እያየን አይደለም።

መልዕክት የላኩ ተማሪዎች የሚዲያዎችን ወንገንተኝነት በእጅጉ ተችተዋል። በተማሪው ስቃይ የዩትዩብ ገንዘብ እየለቀሙ ያሉትንም አውግዘዋል፣ የተማሪውን ስቃይ የፖለቲካ መጠቀሚያ ያደረጉ ሰዎችንም በእጅጉ ኮንነዋል።

እኛ ወንድማማቾች፣ እህትማማቾች ነን፤ ባላጠፋነው ነገር ልንሰቃይ አይገባም፣ ለትምህርት እንጂ እርስ በእርሳችን ልንገዳደል አልመጣንም የሀገሪቱ መንግስት ችግሮች ከዚህ ሳይብሱ መፍታት ይኖርባታል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነገሮች ቀለል አድርገው ምንም እንዳልተፈጠረ ለሚዲያ የሚያቀርቡትን ነገር ትተው መፍትሄ ይፈልጉ፣ አጥፊዎችንም ያስጠይቁ ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች እኛንም በር ዘግተው ለአደጋ ከሚያጋልጡን፣ ስጋት ላይም ከሚጥሉን ወደቤተሰቦቻችን ይሸኙን ሁኔታዎችን ሲያስተካክሉና ለህይወት አስጊ ነገር አለመኖሩን ሲያረጋግጡ ይጡሩን ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ(ከቲክቫህ ቤተሰቦች)👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-16

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በአብላጭ ድምፅ ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ።

ኮሚቴው በውህደቱ ማዕቀፍ ውሰጥ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በስፋት አንስቶ መወያየቱንም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢትቪ ተናግረዋል።

በዚህም ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ተጠናክሮ በሚቀጥልበትና የራስ አስተዳደር በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ኮሚቴው በዛሬው ስብሰባው ትኩረት ሰጥቶ በዝርዝር መወያየቱንም ገልፀዋል።

የቋንቋ ብዝሃነት ፣ የብሔር እና ሀገራዊ ማንነትን ሚዛኑን በጠበቀ መልክ እንዲጠናከር የሚሉት ጉዳዮችም በመድረኩ ላይ ምክክር ተደርጎባቸዋል ብለዋል አቶ ፍቃዱ።

በመጨረሻም የውህደቱን ጥናት ኮሚቴው በ6 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። በነገው ዕለትም ለወደፊቱ ውህድ ፓርቲ በተቀረፀው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ እንደሚወያይ አቶ ፍቃድ ተሰማ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

(ETV)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከቀን 08-12/2012 ዓ/ም ትምህርት አይኖርም በማለት አንድ አንድ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ደርሼበታለሁ፤ እንዲያህ ያለ ነገር እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል። በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ግቢው ለቀው እየወጡ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ አረጋግጠናል ብሏል ተቋሙ። የትምህርት ስርዓቱ እንደማይቋረጥ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ጥለው የሄዱ ተማሪዎችም በትምህርታቸው ላይ በሚደርስባቸው እክል ሃላፊነቱን እራሳቸው ይወስዳሉ ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia