TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ያደረባቸውና በጅማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጠለሉ ተማሪዎች ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከተማሪ ተወካዮች፣ ጋር እየተወያዩ ነው። በነገራችን ላይ በየመስጊዱም የተጠለሉ ተማሪዎች እንዳሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል። በውይይቱ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ የሚለውን ቆየት ብለን እናቀርባለን።

(ቲክቫህ ቤተሰቦች)

@tsegawolde @tikvahethiopia
#UPDATE

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የሰኔ 15 ምርመራ ተጠናቅቆ 68 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት መኾኑን ዐስታወቀ። 68ቱ ተጠርጣሪዎች «ወንጀል መፈጸማቸው በሠነድ እና በቴክኒክ ማስረጃ የተረጋገጠ» መኾኑንም ገልጧል። ክስ ይመሰረትባቸዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎቹ ከባሕር ዳር 55 ከአዲስ አበባ ደግሞ 13 መኾናቸው በመግለጫው ተጠቅሷል። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ «ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ እና በመንግሥትላይ ወንጀል መፈጸማቸው በሠነድ እና በቴክኒክ ማስረጃ የተረጋገጠ ስለኾነ ክስ ለመመስረት ዝግጅት ላይ የምንገኝ ይኾናል» ብለዋል።

(DW)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፌዴራል ደረጃ አዲስ አበባ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማብራሪያ ሰጥቷል!

ጥቃቱ አንድ ወታደር በመመልመል፣ ቃል በመግባትና ገንዘብ በመስጠት ተልዕኮ እንደተሰጠውና በዚያ መሠረት በጄኔራል ሰዓረ እና በጄኔራል ገዛኢ እንደተፈጸመ ዐቃቤ ሕግ ተናግሯል፡፡

ከጄኔራል ሰዓረ በኋላ በጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተልዕኮ መሰጠቱንም ዐቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡

ጥቃቱ ባሕር ዳር ላይ ከተፈጸመ በኋላ ጎንደር ሄዶ ቃል የተገባለትና ስልጠና የተሰጠው ወታደር ለጄኔራል ሰዓረ ጥበቃ ትዕዛዝ እንደሰጠውና በዚያ መሠረት ጥቃቱ በጠባቂያቸው እንደተፈጸመ መረጋገጡን ዐቃቤ ሕግ ተናግሯል፡፡ ጄኔራል ብርሃኑ ግን በጄኔራል ሰዓረ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ ወደ ቦታው እንደተገመተው ባለመሄዳቸው ዕቅዱ መክሸፉ ነው የተብራራው፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-13-3
#DambiDollo_University

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ለታ ሰኞ እለት በተማሪዎች ካፍቴሪያ አካባቢ በተፈጠረው አለመረጋጋት አንድ ተማሪ ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሕይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል። ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩና የተያዙ ሰዎች መኖራቸውንና ሌሎችን በቁጥጥር ስር ለመዋልና እርምጃ ለመውሰድ ከፖሊስ ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወላይታ ዞን ጅብ የሦስት ሕጻናትን ሕይወት አጠፋ!

በወላይታ ዞን ጅብ ባደረሰው ጉዳት የሦስት ሕጻናት ሕይወት ሲጠፋ በሌላ አንድ የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰ።

የወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው በህጻናቱ ላይ የሞትና የአካል ጉዳት የደረሰው በወረዳው “ኮዶ ጋውሊያ” በተባለ የገጠር ቀበሌ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አሳቻ ሰዓታት ጠብቆ የመጣ ጅብ ባደረሰው ጥቃት ነው።

ጅቡ ባደረሰው ጥቃት ሦስት ህጻናት ሕይወታቸውን ሲያጡ በአንዲት የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ስምኦን ጣዲሶ ተናግረዋል።

በቀጣይ ጅቡ መሰል ጥቃቶችን እንዳያደርስ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበል እርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvhaethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoSHE የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል። ከሰሞኑ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፀጥታ ችግር አጋጥሟል፤ የተማሪዎች ሕይወትም አልፏል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በእነዚህ የፀጥታ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ተማሪዎቹ ሳይሆኑ የተማሪዎችን መታወቂያ በመቀማትና ህገወጥ የተማሪዎች መታወቂያ በማዘጋጀት ወደ ግቢው ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች ናቸው!" - ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ

ሰሞኑን በአንድ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ወደነበረበት ለመመለስና የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ሃይሎች የተጠናከረ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት አስታወቀ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በመቱ፣ መዳወላቡ፣ ጅማ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጠረውን ችግር ለማስወገድ ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት አባቶች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-13-5

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbeba

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ "አጠና ተራ አካባቢ" ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን የቤተሰባችን አባላት በቪድዮ በታገዘ መረጃ አሳውቀውናል። የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MoSHE

‹‹የተማሪዎችን መታወቂያ #በመስረቅ ተማሪ በመምሰል ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እየገቡ ሁከት የሚፈጥሩ ግለሰቦች እጃቸውን ከዩኒቨርሲቲዎች ላይ ሊያነሱ ይገባል›› ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ
.
.
ከሰሞኑ በሀገሪቱ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፀጥታ ችግር አጋጥሟል፤ የተማሪዎች ሕይወትም አልፏል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ እንዳለውም ግጭቶች በተነሱባቸው የመዳወላቡ፣ መቱ፣ ወልድያ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ በችግሮቹ ዙሪያ ውይይቶች እየተደረጉ ነው፡፡

መግለጫውን የሰጡት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶክተር) እንዳሉት ተማሪዎች ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል በመስጋት ግቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው፡፡ ‹‹ሁኔታው ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ባለመሆኑ ዛሬ ምሽት ላይ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል›› ብለዋል፡፡ ‹‹መገናኛ ብዙኃን መረጃዎችን በማጤን እና በመመርመር በኃላፊነት ለሕዝብ ማድረስ አለባቸው›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ‹‹ሚዲያዎች ኃላፊነት በሌለው ሁኔታ በሚለቁት መረጃ ሰበብ ጉዳት እየደረሰ ነው›› ብለዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-13-4

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የተፈጠረውን አለመረጋጋት አሁን በፀጥታ ኃይሉ በቁጥጥር ሥር የዋለ ቢሆንም አንድን እኩይ ተግባር ተግባሩን ተጠይፎ ከመቃወም ይልቅ ተግባሩን በሠላማዊ ወንድምና እህት ላይ ለመድገም መሞከር ጭራሽ ሰብዓዊ አለመሆኑንና የንፁህ ወንድምና የእህቱን ደም የሚያፈስ ሰው መቼም ቢሆን የህሊና ወንጀለኛ ሆኖ በፀፀት እየተሰቃየ የሚኖር መሆኑን ስናስብ እጅግ እናዝናለን። ወንጀሉን የሠራውን ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን አጣርቶ ለፍርድ ማቅረብ ፅኑ አቋማችን መሆኑን እንገልፃለን!" መቱ ዩኒቨርሲቲ

ከመቱ ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️
(ማክሰኞ ህዳር 2/2012)

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


አቶ ድንቁ ደያስ ሸራተን ሆቴል ግቢ ውስጥ ትላንት ከሰዓት በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ ተዘርፈዋል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️
(ማክሰኞ ህዳር 2/2012)

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያስተላለፈውን መመሪያ ባልተቀበለ የአትሌቶች ተወካይ ላይ የውል ማቋረጥ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️
(ማክሰኞ ህዳር 2/2012)

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


በሳውዲ አረቢያ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊን ጉዳይ በተመለከተ

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ያዳምጡ⬆️
(ማክሰኞ ህዳር 2/2012)

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


በፌስቡክ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎችንና የሀሰት ዜና ማጋለጥ ላይ የተሰራ አንድ ጥናት ይፋ ተደርጓል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በተነሳ ግጭት በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ። የመንግስት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ተወካይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚካኤል እንዳለ ለቢቢሲ እንደገለፁት በድሬደዋ በተደጋጋሚ ግጭት የሚከሰትባቸው ቀበሌ 6፣ ቀፊራ ደቻቱና መጋላ ፣ በቀበሌ 05 ገንዳ አዳ፣ እንዲሁም ቀበሌ 09 ገንደ ጋራ የሚባሉ ቦታዎች ናቸው።

በድሬዳዋ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ግጭት እንደነበር የተናገሩት ኃላፊው ትናንትናና ዛሬም ግጭት ተቀስቅሶ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ዛሬ በተቀሰቀሰው ግጭት ከፍተኛም መካከለኛም ጉዳት ደርሷል ያሉት አቶ ሚካኤል ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታል ሕክምና አግኝተው እየተመለሱ ነው ብለዋል። ከፖሊስም ከሆስፒታልም የሞት አደጋ መድረሱን ለጊዜው መረጃ እንዳልደረሳቸው የተናገሩት ኃላፊው ግጭቱን ለማብረድ የፀጥታ መዋቅሩ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሚካኤል የግጭቱ ባህሪ ተለዋዋጭ እንደሆነና አንድ ቦታ በቁጥጥር ስር ሲውል ሌላ ቦታ አንደሚቀሰቀስና ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ያስረዳሉ። ግጭቱ የብሔርና የሀይማኖት መልክ እንዲይዝ ሙከራዎች እንዳሉ የገለፁት ኃላፊው ጥፋተኞችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

አሁንም ቢሆን የተፈጠረው ግጭት "ከጸጥታ መዋቅሩ" በላይ አይደለም በማለት ከከተማው አስተዳደር የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ እንደተሰማራ ተናግረዋል። ግጭቱንም ለመቆጣጠር ሁሉም በጋራ እየሰሩ መሆኑን በማስረዳት ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ከሚገኙ ሐሰተኛ መልእክቶች ራሱን እንዲጠብቅ ተማጽነዋል።

https://telegra.ph/ETH-11-13-6

(BBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ህዳር 10 ለሚደረገዉ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ቦርዱ መራጮች በሰላማዊ መልኩ ለድምፅ መስጫ የሚሆናቸውን ካርድ እየወሰዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

በሌላ ዜና...

ሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ገደማ መራጭ መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia