TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️አንኮበር ወረዳ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ዘንቦ ነበር። አካባቢውን ከላይ ባሉት በፎቶዎች ተመልከቱ።

ፎቶ📸Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ!" አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (#ሕወሓት) እና የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ) ቅራኔን በተመለከተ “በአዲሱ ዓመት ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጠን ተወያይተንና ተግባብተን ለመፍታት ዝግጁ ነን” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ ተናገሩ። አቶ ተመስገን ይህን ያሉት አዲሱን 2012 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ብሔር ብሄሰቦችና በተለይም ለአማራ ክልል ህዝብ የመልካም ምኞት መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ።

እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ችግሮችንን ለመፍታት ዝግጁ ነን ያሉት አቶ ተመስገን ፤ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከ(ሕወሓት) ወገንም ተመሳሳይ ፍላጎት ይኖራል ብለው እንደሚያምም ገልፀዋል፡፡ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር መኖሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በአዲሱ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ይፋ አድርገዋል። አዲሱ ዓመት ለመላው ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በተለይ ለአማራ ክልል ህዝብ የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎርብስ የ2019 የአለም ሀብታም ዝርዝር ይፋ በሚያደርግበት ገጹ እንዲህ በቅደም ተከተል አስቀምጧቸዋል፦

1🇺🇸 ጄፍ ቤዞስ : 131 ቢሊየን ዶላር
2🇺🇸 ቢል ጌት: 96.5 ቢሊየን ዶላር
3🇺🇸 ዋረን ቡፌት : 82.5 ቢሊየን ዶላር
4🇫🇷 በርናልድ አርኑሌት: 76 ቢሊየን ዶላር
5🇲🇽 ካርሎስ ስሊም ሄሉ: 64 ቢሊየን ዶላር
6🇪🇸 አርማኒኮ ኦርቴጋ : 62.7 ቢሊየን ዶላር
7🇺🇸 ላሪ ኤሊሰን: 62.5 ቢሊየን ዶላር
8🇺🇸 ማርክ ዙከንበርግ: 62.3 ቢሊየን ዶላር
9🇺🇸 ሚካኤል ብሉምበርግ: 55.5 ቢሊየን ዶላር
10🇺🇸 ላሪ ፔጅ: 50.8 ቢሊየን ዶላር

(Forbes)

#ቲክቫህ_ልዩ_ልዩ

Join👇
@tikvahethmagazine
#ጅማ #JIMMA

•በጅማ ከተማ ምንም ቤተክርስቲያን አልተቃጠለም
•የሃይማኖት አባቶች አልታረዱም፤ አልተገደሉም
•ከፍተኛ እልቂት እየተፈፀመ ነው የሚባለውም ሀሰት ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን👇

√በጅማ ከተማ በሃይማኖት ሽፋን ብጥብጥ ለመፍጠር ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴ በሕዝቡ እና በፀጥታ አካላት ተሳትፎ ከሽፏል።

√በከተማው በሃይማኖት ሽፋን ክልሉን እና ሀገሪቱን ለማመስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በሕዝቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ ሴራቸው ሊከሽፍ ችሏል።

√"በጅማ ከተማ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ" በሚል የሐሰት ወሬ ሕዝቡን በመቀስቀስ ብጥብጥ ለመፍጠር እና ክስተቱም ወደሌሎች ከተሞች እንዲስፋፋ በተቀናጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር።

የተለያዩ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለTIKVAH-ETH የተገሩት፦

ስለውጥረቱ መነሻ ተመሳሳይነት ያለው መረጃ አላገኘንም! የሚመለከታቸውን አነጋግረን እናቀርባለን!

•ከትላንት 7:00 ጀምሮ ውጥረት ነበር።

•ቁጥራቸው ብዙ ባልባልም በመኪና ሆነው የሚንቀሳቀሱ አካላት ነበሩ።

•ወጣቶች ቤተክርስቲያን ሲጠብቁ ነው ያደሩት። አሁንም እዛው ናቸው።

•ፖሊስ በከተማው ውስጥ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲታይ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጠም።

•የተቃጠለ ቤተክርስቲያን የለም፤ ግን ሙከራ ነበር ብለን እናምናለን።

•በፌስቡክ ላይ የሚነገረው ግን በተሳሳተ ምልኩ ነው።

•ፖሊስ ይህን ያህል ውጥረት ሳይፈጠር በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን መቆጣጠር ይችል ነበር።

•አመሻሹን ከቤተክርስቲያን የሚመለሱ አካላት በሚመለሱ ወቅት ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

•አንዳንድ ወጣቶች በግርግሩ ውስጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

•የከተማይቱን ሁኔታ መንግስት ትኩረት ይስጠው።

•ዛሬም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እየሰማን ነው። ውጥረት አለ!

•የከተማው ፀጥታ ኃይል ነገሮች እንዲ ስሳይባባስ ማስቀረት ይችል ነበር፤ ትኩረት አልተሰጠውም።

•ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ቤተክርስቲያን እየጠበቀ ነው።

•ያለውን ስጋት ለመቅረፍ መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት ይስጥና ይስራ።

•ሚዲያዎችም ከአንድ ወገን ብቻ የሚያቀርቡትን መረጃ ማስተካከል አለባቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ!

በመጪው የ2012 ዘመን መለወጫ በዓል የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ ዝግጅት የተደረገ መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

የኃይል መቆራረጥ ዜሮ ማድረግ ባይቻልም የመቆራረጥ ሁኔታን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቅደመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።

ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ሊያጋጥም ስለሚችል፤ የድንጋይ ወፍጮ፣ የብረታ ብረት፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የሲሚንቶ፣ የፕላስቲክ፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት ፋብሪካዎች ከጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 እስከ መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽቱ 12፡00 ድረስ ከዋናው የኃይል ቋት /ከግሪድ/ የምታገኙትን ኃይል እንድታቋረጡ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብለዋል ኃላፊው፡፡

እንዲሁም ኤሌክትሪክ በሚቋረጥበት ጊዜ የጥገና ስራ ለማከናወን የተቋሙን መታወቂያ ወይም የስራ ትዕዛዝ የያዙ ባለሞያዎቻች በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ፤ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ህብረተሰቡ የሃይል መቆራረጥና ሌሎች ችግሮች ሲከሰቱ በነፃ የጥሪ ማአከል 905 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ብለዋል ዳይሬክተሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

መስከረም 4/2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መግለጫ ሰጡ፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2/2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጹት ኮሚቴዎች፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ⬆️

"ዛሬ በሶዶ ከተማ የማጠቃለያ የክረምት በጎ ስራ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም ፕሮግራም ላይ የከተማው ከንቲባና ሌሎች የመንግሥት ሀላፊነት ላይ የተሰማሩ ሰዎች ተገኝተዋል። በዚህም የማጠቃለያ ፕሮግራም ለአዲሱ አመት አቅም ለሌላቸው የመማሪያ ቁሳቁስ ተዘጋጅቷል። ትልቁ ነገር በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ የተሰራው ለአዛውቶች የቤት ስራና ጥገና ተደርጓል።" ቾምቤ ከወላይታ ሶዶ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዶላ⬆️

"እኔም ለወገኔ" በማለት አዶላ ወዮ "እኛው ለኛው" መረዳጃ ማህበር አስተባባሪነት ለ84 አቅመ ደካማ ተማሪዎች #የመማርያ ቁሳቁስ እና #ዩኒፎርም ዛሬ ድጋፍ አርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስከረም 4ቱ ሰልፍ ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ አይደለም!

መስከረም 4 ይደረጋል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ #እንዳልሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች አስታውቀዋል። ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን ገልፀዋል።

Via #ETHIOFM

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እድሜዋ ትንሽ ሀሳቧ ትልቅ---ሰላም⬆️

ሀዋሳ ከተማ ኦሲስ ሆቴል አጥገብ ፌደራል አጥሩ ስር ቡና የምታፈላና ጎን ለጎን መጽሀፎችን ለሚያነቡ #በነጻ እንዲጠቀሙ መልካም የንባብ ባህልን አስተዎጽኦ የምታደርግ ሰላም የምትባል ልጅ አለች። በዚህ ብቻ አላበቃችም ለጎዳና ልጆች እዛው አካባቢ ዘንቢልና የተለያዩ ማጌጭዎችን በመያዝ በቀላሉ እንዲሰሩ እያደረገች ትገኛለች።

አሁንም ቡናዎን እየሸጠች ባዶ ካርቶን አስቀምጣ (1ደብተር፣ 1 እስክሪብቶ፣ 1 እርሳስ፣ ለእኛ ብዙ ነው) የሚል ጽፋ ካርቶን ላይ በ4 አቅጣጫ ለጠፈችበት ሰው አልተጠራጠራትም ካርቶን ላይ የቡና መልስ ወይም ከኪስ በማውጣትና፣ ማቴሪያሉን ገዝተው በማምጣት፣ ትላንት ለፍሬ በቅቶ ብዙ ልጆችና እናቶቻቸው ጭምር በመገኘት ተረክበዎል። ለ1 ሰው ከ6 ያላነሰ እስክርቢቶና እርሳስና ደብተር ተከፉፋሏል።

ለታሰበው አላማ ከጎኗ የነበሩ ልጆችም ቲሸርት አሳትመው ለብሰው ደብተሮቹን በመቁጠርና በማስተካከል ተወጥረው ነበር። ብራቮ ሰላም ቡና በሏት "ግን ትንሽ ልጅ ነች ሀሳቧ ትልቅ ነው" ምስጋና ይገባታል።

Yared Tassew/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ ከባልደራስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም!

ማኅበረ ቅዱሳትንን ጨምሮ አስር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተለያዩ ተቋማት መስከረም አራት የሚካሄደዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያስተባብሩ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል። ተቋማቱ በመግለጫቸዉ በቤተክርስትያኒቱና በምዕመናኑ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ ከኦሮምያ ቤተ ክህነት ጋርም ይሁን፤ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ እስክንድር ነጋ ከሚመራዉ ባልደራስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለዉ አስታዉቀዋል። ጥያቄ ለመንግሥት አቅርበን የእንወያይ ጥያቄ ቀርቦልናል፤ የፊታችን አርብ መስከረም ሁለት ድጋሚ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን ሲሉ ተቋማቱ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ተቋማት የጠሩትን ተቃዉሞ ተከትሎ በአዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ መስከረም አራት ተመሳሳይ ሰልፍ ሊያካሂዱ ዝግጅት ላይ መሆናቸዉ እየተዘገበ ነዉ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopai
#update የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የቀረቡለትን ጉዳዮች የመለየት ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። ኮሚሽኑ የዝግጅት ምዕራፉን #አጠናቆ ወደ ትግበራ ምዕራፍ በመስከረም ወር 2012 ዓ.ም እንደሚገባም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ለ7 መቶ 35 አባላት የማዕረግ እድገት ሰጠ። ከዚህ ውስጥ ዐስሩ ከመስመር መኮኖንንነት ወደ ከፍተኛ መኮንንነት የማዕረግ እድገት ያገኙ ናቸው።በተቋሙ ውስጥ ለ ረጅም ዓመታት ላገለገሉ እንዲሁም አገራቸውን እና ሕዝባቸውን አገልግለው ጡረታ ለወጡ 56 የቀድሞ አባላቶቹም የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷል።

Via ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በነቀምቴ ከተማ ለችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ። የምዕራብ ሸዋ ዞን ሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተማሪዎቹ የተበረከተው ድጋፍ 813 ሺህ 400 ብር ግምት ያለው ነው። በእዚህም ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ችግረኛ ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING

የ2012 የዩንቨርሲቲ #መግቢያ_ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል ተብሏል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ ነገ ረፋድ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

ምንጭ፦ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ነጥብ ነገ ይፋ ይደረጋል!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን በነገው ዕለት ይፋ ያደርጋል።

ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Verified! የዶክተር አሚር አማን የፌስቡክ ገፅ በፌስቡክ ድርጅት #verify ተደርጓል። #ETHIOPIA
ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ #CBE⬆️
የህግ ያለህ!

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች መንገድ ላይ በሚያጋጥማቸው የተደራጀ ዘረፋ ምክንያት በወታደር ታጅበው ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል። በባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ 2 ሾፌሮች የተገደሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት የፋብሪካው ሰራተኞች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ኮርፖሬሽኑም ሆነ መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ግፊት ካልተደረገ አደጋ ላይ ነን ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የአደጋ አድራሾቹ ጥቃት በተለይ የስኳር ሰራተኞችን እና የመሥሪያ ቤት መኪኖች ላይ ያነጣጠረ ነው፣ በተለይ የደሞዝ እና የበአል ሰሞን ብለዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia