TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስታወቂያ09-12-20111.pdf
176.3 KB
#ለደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች

በ2011 የትምህርት ዘመን በቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት የማጠቃለያ ፈተና በራሳቸው ፈቃድ ላልወሰዱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ የቅድመ – ምረቃ ተማሪዎች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ...

"....እንደ ተማሪ #ተቀብሎ እናንተን በሙሉ ኃላፊነት የሚጠብቃችሁ፣ መብታችሁንም የሚያስጠብቅላችሁ በ2012 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና ወቅት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከዚያ ውጭ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመምጣት ከሚደርስባችሁ እንግልት እና አላስፈላጊ ወጭ ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን እድትጠብቁ እንዲሁም ተጨማሪ ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል የበኩላችሁን እንድታደርጉ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ብቻ እንድትቀበሉ በጥብቅ ያስታውቃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱዳን ፖለቲከኞች ሥልጣን ለመጋራት በመስማማታቸው ደስታቸውን ለመግለፅ ወደ ኻርቱም ያቀኑ የአትባራ ሰዎች በተጓዙበት ባቡር አናት ቆመው ሰንደቅ ዓላማ ያውለበልቡ ነበር።

Via #Eshete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዚህ በኃላ ፍትህን ከመንግስት ሳይሆን ከእግዜያብሄር ነው የምጠብቀው"

በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት #ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የወሰነላቸው ቢሆንም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ከእስር እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለTIKVAH-ETH ተናገሩ። ፍርድ ቤቱ ትላንት በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካካል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ እና የጣቢያው የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።

በጉዳዩ ላይ ለTIKVAH-ETH የተናገሩት ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች አንደኛው ይህን ብለዋል፦

"የዋስትና ደብዳቤውን በጊዜ ነው ጨርሰን የሄድነው፤ ፖሊስ ግን ሊፈታቸው ፍቃደኛ አልነበረም። ፖሊስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብዳቤ አስገብቻለሁ አለን፤ ነገር ግን ሄደን ስናይ ያስገባውና የተፈቀደለት እግድ የለም ነገር ግን ልጆቹን አልሠጣችሁም አለን። የፖለቲካ እስረኞች ናቸው ህጉ የሚፈታው አይደለም። ...እዚህ አገር ላይ ከፍርድ ቤትና ከህግ የሚበልጠው እላይ ያለው ደውሎ ልቀቅ የሚል ሰው ነው ይህ እኛ እንደተረዳነው የፖለቲካ ጉዳይ ነው። በሚዲያ ቀርቦ የምናገኘው ፍትህ የለም። ለውጥ የሚባል ነገር የሌለበት ሀገር ላይ ነው ያለነው። ፍትህን ከእግዚያብሄር ጠብቀን እንኖራለን። አሁንም ቢሆን የሲዳማ ህዝብ ልጆቹ ይለቀቃሉ ብሎ ጠብቆ ነበር። በቦታው የነበረው ሰው ሀላሌ ይፍታልን ብሎ ነው የሄደው። የሲዳማ ህዝብ ሲዳማ ብቻ ስለሆኑ የታሰሩ ልጆች ላይ የሚደረገውን ጭቆና አይቶ አሁንም ቢሆን መንግስት ፍትህን ይሰጣል ብሎ አይጠብቅም፤ አይጠይቅም። ከእግዚያብሄር ነው ፍትህን የሚጠብቀው ይህ ህዝብ"

#ቲክቫህ
የኬንያን ባህላዊ የአልኮል መጠጥ በድብቅ ሲያመርቱ የነበሩ ቻይናዊያን በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ቻንጋ የተባለውን የኬንያ ባህላዊ የአልኮል መጠጥ በድብቅ አምርተው ሲሸጡ የተገኙት ቻይናዊያን ዋንግ ያላን እና ዋንግ ሃይጂያን ይባላሉ፡፡

ማቻኮስ በተባለው አካባቢ በሚገኝው የቻይናዊያኑ መኖሪያ ቤት ውስጥ 3ሺህ ሊትር ያለቀለት የአልኮል መጠጥ (ቻንጋ) ፤ 800 ሊትር ሜታኖል ፣ የአልኮል ድፍድፍ የያዙ በርካታ በርሜሎች፣ ትላልቅ የውሃ ማጠራቀሚያዎች እና ለአልኮሉ መስሪያ የሚውሉ የተለያዩ የእህል አይነቶችን ተገኝተዋል፡፡

ፖሊስ ቻይናዊያኑ ባህላዊ መጠጡን በከፍተኛ መጠን ማምረት የሚያስችላቸው ትልልቅ የፋብሪካ መሳሪያዎችን ቤታቸው ወስጥ ተክለው አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ ሜታኖል ሰዎች በቀላሉ እንዲሰክሩ የሚያደርግ አደገኛ ኬሚካል ከመሆኑ ባሻገር ለአይነ ስውርነት እና ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

የኬንያዊያንን ባህላዊ መጠጥ ቻንጋን በፋብሪካ ደረጃ አምርተው በማሸግ ለገበያ እያቀረቡ እንደነበር የተጠረጠሩት ቻይናዊያኑ ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

Via #BBC/AHADU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምዕራብ ኦሮሚያ ሰባት ዞኖች የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዲፒ)ወጣቶች ሊግ ስብሰባ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው። በስብሰባው ከዞኖቹ የተውጣጡ ከ1ሺህ 500 በላይ ወጣቶች በመካፈል ላይ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለስ ተችሏል"- ኮማንድ ፓስቱ
.
.
በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የነበረውን አለመረጋጋት የአካባቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ። ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመቆጣጠር የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት አፈጻጸም ዛሬ ገምግሟል፡፡

በግምገማውም በሀዋሳና በሲዳማ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተዘረፉ ንብረቶችን ህብረተሰቡን በማሳተፍ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን በግጭቱ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬ አቸው እዲመለሱ ተረደርጓል ብሏል፡፡ እንዲሁም የተሰባበሩ ቤቶች እና ንብረቶች እንዲጠገኑ መደረጉንም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።

ኮማንድ ፓስቱ በሀዋሳ ከተማ ፣ በሲዳማ ዞን እና በክልሉ አንዳንድ ዞኖች በህገወጥ መንገድ የተሰቀሉ ሰንደቅ አላማዎች እና ታፔላዎች ወርደው በምትኩ ህጋዊ ሰንደቅ አላማዎች እና ታፔላዎች እንዲሰቀሉ ማድረጉን ከከልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ህገ ወጥ የወጣት አደረጃጀቶች ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ የተጀመረው ስራ አበረታች መሆኑን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡ ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓም በነበረው የጸጥታ ችግር ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት 1 ሺህ 384 ሰዎች ውስጥ የማጣራት ስራ በመስራት 481 ተጠርጣሪዎች የተለቀቁ ሲሆን ቀሪ 903 ተከሳሾች በክስ ሂደት ላይ መሆናቸውን ኮማንድ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ህዝቡ የሚወደው ኢህአዴግን ሳይሆን ዶክተር አብይን ነው፤ ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኢህአዴግን መርታት የሚችሉበት ዕድል አለ ማለት ነው”- ዶክተር ኢንጅነር አድማሱ ገበየሁ የቀድሞው ቅንጅት ምክትል ሊቀመንበር
.
.
• የቀድሞውን ቅንጅት የምርጫ ምልክትም መጀመሪያ ያመጣሁት እኔ ነኝ። ባለቀ ሰዓት አራት ኪሎ ከሚገኙት ፎቶ ቤቶች በአንዱ ገብቼ እጄን ፎቶ አስነሳሁና ወደ ምርጫ ቦርድ ሄድኩ፤ ተሳካልን።

• በቀድሞው በቅንጅት ውስጥ የእኔ ድርሻ ምክትል ሊቀመንበርነት ነበር፤ በቅንጅት ውስጥ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ካደረግናቸው ጥረቶች አንዱ ማኑፌስቶ ማዘጋጀት ነበር። በዚህ ማኒፌስቶ ዝግጅት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ነበረኝ። ይህም ያኮራኛል።

• እንደእኔ እምነት እነ ዶክተር አብይ፥ ኦቦ ለማ፥ እነ ገዱና ሌሎች ቅን አሳቢዎች በመጀመሪያ ደረጃ በአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ያለውን ችግር መረዳታቸው በራሱ የሚያስመሰግናቸው ነው።ይህንን ለውጥ ለማምጣት የተጓዙበት መንገድ ሰላማዊ መሆኑም ሌላ ሊደነቁበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-17-4
ድምፃዊው ከማገገሚ መውጣቱ ተሰምቷል!

ድምፃዊ አበበ ተካ ዛሬ ከማገገሚያ ወጥቶ፣ ተሽሎት ወደ መኖሪያ ቤቱ አቅንቷል። የድንገተኛ የጤና ችግር ላለፋት ወራት በዋሽንግተን ሆስፒታል የገባው አበበ ተካ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ሲደረግለት እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ:- ጌጡ ተመስገን/@AccessAddis
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወጣቶች የሥልጠና ማዕከል ግንባታ የሚሆን 10 ሄክታር ቦታ ለአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተሰጠ!

ወጣትን በመልካም ስነምግባር መገንባት ሀገርን ለጤናማ ትውልድ ማስረከብ በመሆኑ በስነምግባር የታነጹ ወጣቶችን ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጌታሁን ጋረደው አስታወቁ፡፡ ለወጣቶች የሥልጠና ማዕከል ግንባታ የሚሆን 10 ሄክታር ቦታ ለአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተሰጥቷል፡፡

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ለወጣቶች ማዕከል ግንባታ የሚሆን 10 ሄክታር ቦታ በተረከበበት ወቅት እንደተናገሩት ወጣቶች ጥላቻና ቅም አስቀምጠው ሳይሆን ትናንት አባቶቻችን ያቆዩትን መልካም ዕሴቶችን በማስጠበቅ መሆን አለበት፡፡ የወጣቶች የሥልጠና ማዕከል ግንባታ ከወላይታ ሶዶ ባሻገር በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና በሌሎችም አካባቢዎች እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡ የወላይታ ዞን እና የሶዶ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት የወጣቶች የሥልጠና ማዕከል ግንባታ ለማከናወን ፈቃደኛ በመሆን ላደረጉት ቀና ትብብር አገልጋይ ዮናታን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-08-17
#update የደቡብ ክልል የጸጥታ እዝ በሲዳማ ዞን ሐምሌ 11 «በነበረው የጸጥታ ችግር» 1384 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውሎ 481 መልቀቁን 903 መከሰሳቸውን አስታውቋል። በክልሉ ሕገ-ወጥ የተባሉ ሰንደቅ አላማዎችና ታፔላዎች ወርደው በሕጋዊ ተተክተዋል ብሏል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ ሰራተኛው የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦና መንቀሳቀስ የሚስችል መሆኑ ተገለጸ!

.
.

አፈፃፀሙ የደሞዝ ስኬል ሽግግርን አድርጎ የተጠናቀቀው ይህ ፕሮጀክት የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ ወይንም ማስተካካያ የመስራት አለማ የለውም። ሰረተኛው የደሞዝ ልዩነትን ባልተመዘኑ ስራዎችን ለመፈለግ ከመስሪያ ቤት መስሪያ ቤት ወይንም ከዘርፍ ዘርፍ የሚያደረገውን ፍሰት የሚያስቀር መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TIKVAH2-08-17
አሳዛኝ ዜና!

የሶርያ እና የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በኢድሊብ በፈጸሙት የአየር ድብደባ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የሶርያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን አስታወቀ። ካለፈው #ሚያዝያ ጀምሮ የሶርያ መንግሥት እና ሩሲያ የተቃዋሚዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነው #የኢድሊብ አካባቢ እረፍት የለሽ ዘመቻ ላይ መሆናቸውን የዜና አውታሮች ዘግበዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

• "...ውጤቴን ከተስተካከለ በኃላ ነው ትላንት ማታ ያወኩት፤ 32 ነበር አሁን 95 ሆኗል።"

• "ከታች ባሉት ክፍሎች ተማሪ እያለሁ የደረጃ ተማሪ ነበርኩ፤ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ግን 1ኛ ነው የወጣሁት።"

• "ፓይለት መሆን ነው የምፈልገው"

• "በትንሹ 600 ቤት ለመግባት በደንብ አስቤበት ስዘጋጅ ነበር"

#ቃልኪዳን_አስቻለው በአዲስ አበባ ከተማ የካቴድራል ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 643 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት #ከጅማ_ዞን #ጌራ_ወረዳ

"እቅዴ ከዚህም በላይ ነበር፤...ይህን በማምጣቴ ደስ ብሎኛል"

"የአፕቲትዩድ ውጤቴ መጀመሪያ 29 ነበር፤...ተስተካክሎ የመጣው 97 ነው"

"የመጀመሪያ ፈተና ስለነበር ደንግጬ ነበር ፈርቼም ነበር፤ ...ወደ መልስ መስጫ ወረቀቴ በችኮላ ነው የገለበጥኩት በዛ ሰዓት የፈጠርኩት ስህተት ነው ብዬ ገምታለሁ"

"ያለኝን ሰዓት በሙሉ ነበር ተጠቅሜ እያነበብኩ የነበረው"

"የስልክ ተጠቃሚ አይደለሁም፤ የማህበራዊ ሚዲያም ላይ የለሁም፤ ያለኝን ሰዓት በሙሉ ማሳለፍ የምፈልገው በትምህርቴ ላይ ብቻ ነው"

"በራሴ ስለምተማመን ሜዲስን እደምገባ እርግጠኛ ነኝ፤ እዛም ሰቅዬ እንደምወጣ እርግጠኛ ነኝ!"

"ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስካሁን 1ኛ ነው የወጣሁት"

"ለዚህ ፈተና መዘጋጀት የጀመርኩት ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ነው።"

#ነኺማ_ቲጃኒ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን #ጌራ_ወረዳ በሚገኘው የጌራ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 638 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጰያዊያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ #በሱዳን እስር ላይ የነበሩ 105 ኢትዮጰያዊያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፈርማ ስነ ስርዓት አጠናቀው ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን በመያዝ አዲስ አበባ የገቡት፡፡ ኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግት የስራ ሃላፊዎችን ያሳተፈ የጽድት ዘመቻዛሬ ጠዋት በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ ከተማ ተካሄዷል፡፡ በጽዳት ዘመቻው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተሳትፈውበታል፡፡ አሁን ላይም በአካባቢው በኩታገጠም ልማት በአርሶ አደሮች የለማውን የስንዴ ማሳ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአርሲ ዞን በኩታ ገጠም የለማ ስንዴማሳ እየጎበኙ ነው፡፡ በዚሁ ጉብኝት ላይም የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተዋል፡፡ ዛሬ ረፋዱ ላይ 78 ሄከታር ማሳ ላይ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በአርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡ አሁን ላይም በተመሳሳይ መልኩ በኢገሉጢጆ ወርዳ በኩታ ገጠም በአርሶ አደሮች የለማውን የስንዴ ማሳ ለመጎብኘት ወደ ዚያው አምርተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቀጣዩ 4 ወራት ውስጥ 9,000 የ 40/60 ኮንደሚንየም ቤቶች እጣ ይወጣል ተባለ። 200,000 ባለ 20/80 እና 100,000 ባለ 40/60 ቤቶች ግንባታ ለመጀመርም ታቅዷል።

Via Tesfaye Getnet/ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሶሳ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ብሄራዊ ክልሎች መንግስታት የልማትና የጸጥታ ትብብር የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ የምክክር መድረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ አሻድል ሀሰንና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እየመሩት ሲሆን የካቢኔ አባላትም እየተሳተፉ ናቸው፡፡

በምክክር መድረኩ በ2011ዓ.ም በልማትና በጸጥታ ዘርፎች በጋራ የሰሯቸው የጸጥታ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል፡፡ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችና ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ይገመገማል፡፡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለማስወገድ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የ2012 እቅድም ቀርቦ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia