TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት 1ኛ ዓመት አስመልክቶ በሚሊኒየም አዳራሽ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

• በዚህ አመት በሄድኩበት ስፍራ የደገፋችሁን ወገኖች የሞታችሁልኝ የቆሰላችሁልኝ ወገኖች ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እፈልጋለሁ

• እናንተ ያለ እኔ መኖር ትችላላችሁ እኔ ግን ያለ እናተ የማልረባ ነኝ

• ለውጡ እንደ ደራሽ ውሃ ሳይሆን በብዙ ዋጋ የመጣ በመሆኑ ለውጡን ማስቀጠል ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚተው አደራ ነው

• አምና በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ቀጣይነት በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ከጨለማ ጊዜ መውጣት መቻሉን መዘንጋት ተገቢ አይሆንም

• ለህዝባችን ያለፈውን ድል ብቻ በመናገር ሳይሆን ተደጋጋሚ ድሎችን ማስመዝገብ ይኖርብናል

• ባልተለወጠ ባህል እና ባልታደሰ ተቋም ለውጥ መጀመር ከባድ ነው

• ላለፉት 100 አመታት ኢትዮጵያ በአንድ አመት አምጥታ የማታውቀውን ባለፉት 7 ወራት ብቻ 13 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ተችሏል

• 8 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት 7 ወራት ለግሉ ሴክተር ተሰጥቷል

• 8 አመቱን ያከበረውን የህዳሴ ግድብ እንዲቀጥል ቁርጠኛ አመራር ተሰጥቷል

• በኢትዮጵያውያን መካካል አንገት የሚቀላውን ሳይሆን የሰላም ሰይፍ በመምዘዝ ሰላምን ማስከበር ያስፈልጋል

•ለውጡ በድል ብቻ የታጀበ አይደለም፣ ኢትዮጵያውያን ሊሰሙት የማይፈልጉት መፈናቀል ተከስቷል

•ድሉን በጋራ እንዳመጣነው ሁሉ ችግሩንም በጋራ እንፈተዋለን

•አቅፎ ማለፍ ሳይሆን ጥሎ ማለፍ ላይ የተመሰረተው የሀገራችን ፖለቲካ ለለውጡ እንቅፋት እየሆነ ነው

•እኛ ሀላፊነት መውሰድ ባለመቻላችን የሚያድጉ ልጆች ተጧሪ እንዳይሆኑ ሁለም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል

•የምንሰራውና የምንነጋገረው ኢትዮጵያን ትልቅ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ ጉልበታች ለኢትዮጵያ ልማት አንጂ ህዝብ ለማፈናቀል መዋል የለበትም

•መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ የሚፈልገው አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ ብሎ ኢትዮጵያ ከሌለ ሙሉ መሆን አንችልም

•ሁላችንም ማወቅ ያለብን ኢትዮጵያ ለማኝ አገር ናት፤ ድንቅ ሳይንቲስት፣ አርቲስት፣ ባለሃብት ብንፈጥር የለማኝ አገር ሳይንቲስት፣ አርቲስት፣ ባለሃብት መባሉ አይቀርም

Via etv
@tsegabwolde @tijvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት 1ኛ ዓመት አስመልክቶ በሚሊኒየም አዳራሽ ባደረጉት ንግግር በቀጣይ አመት ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎችን አመላክተዋል፦

• መላው ኢትዮጵያውያን ይቅር በመባባል በጋራ ወደ ፊት እንዲጓዙ ማድረግ

• የተጀመረው ተቋማዊ ለውጥ ያልተሟላ በመሆኑ ተቋማት የመገንባት ስራ አጠናክሮ መቀጠል

• በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ሰራዎች ይሰራሉ

• በግብርና ዘርፍ በተለይም በትናንሽና መካከለኛ መስኖ ስራዎች ውጤተማ ስራዎችን ማከናወን

• የማዕድን ዘርፍ በማስፋፋት ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር

• የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ፍጻሜውን ለመቋደስ ወሳኝ በመሆኑ ህግ የሚያስከብሩ እና የሚተገብሩ አካላት በጠንካራ መሰረት የሚገነቡበት ጊዜ ይሆናል

• የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲቋቋሙ ይሰራል

• በቀጣይ አመት የሚደረገው ምርጫ ለአፍሪካ አርአያ በሆነ መልኩ የሚደረግ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ይህን አንዲጠበቁ እፈልጋለው

• የጎደለ ነገር ካለ ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብዬ ይቅርታ መጠየቅ ፈልጋለሁ

• የጎደሉ ነገሮች ባለማወቅ እና ሁኔታዎች በለመመቻቸታቸው እንጂ ዳተኛ በመሆን የተከሰቱ አይደሉም ብለዋል

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ተቃውሞ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ🔝

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትናንት፣ ሰኞ መጋቢት 23/2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።

በተቃውሞው ሁለት ተማሪዎች መጎዳታቸውን የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲው ከአመሻሽ ጀምሮ #መረጋጋቱን ገልፀዋል።

በተቃውሞ ሰልፉ ኦሮምኛ ፌደራል ቋንቋ እንዲሆን እና ሌሎችም ጥያቄዎች መነሳታቸውን ቪኦኤ ያነጋገራቸው አመልክተዋል።

Via VOA 24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲው ከአመሻሽ ጀምሮ #መረጋጋቱን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልአዚዝ ቡቶፍሊካ ስልጣናቸውን ለቀቁ። የሀገሪቱ ቴሌብዥን እደዘገበው አብዱልአዚዝ ቡቶፍሊካ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄቸውን ለሀገሪቱ ህገመንግስታዊ ምክርቤት አቅርበዋል። አልጀሪያን ለ20 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሯት የ82 ዓመቱ ዕድሜ ባለፀጋ ቡቶፍሊካ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው የጤና እክል ላይ እያሉ እንኳን ለ5ኛ ዙር ምርጫ ለመካፈል ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ ነው።
አዛውንቱ እ.አ.አ 2013 ጀምሮ በስትሮክ በሽታ ተይዘው ህክምና ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል የሚደረገውን የቀጥታ በረራ ጀምሯል፡፡ በዚህም ኢስታንቡል በአውሮፓ የአየር መንገዱ 19ኛ መዳረሻ ሆናለች፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
መጤ-ጠል ጥቃት በደቡብ አፍሪካ‼️

በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ አካባቢ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች የገቡና እዚያው የሚኖሩ ሰዎችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት #ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዪቱ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል።

ባለፈው ሣምንት በጀመረው በዚህ ጥቃት ማንዲኒ በምትባል ቦታ ያሉ የኢትዮጵያዊያን ሱቆች መዘረፋቸውን ገልፀዋል። ፕሪቶሪያ የሚገኘው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

#ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ታራሚዎች "ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት" እንደሚፈጸምባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ይኸ የተገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የእንባ ጠባቂ ተቋም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ካደረገው ጉብኝት በኋላ ነው። ቋሚ ኮሚቴው "ታራሚዎች ያለበቂ ምክንያት ከአንድ ማረሚያ ቤት ወደ ሌላ #ከማዘዋወር ባለፈ አሁንም በክልሉ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች ዘንድ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሆነ" ማረጋገጫ ማግኘቱን ምክር ቤቱ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በታራሚዎች ላይ የሰብዓዊ መብት #ጥሰት ይፈፀምባቸዋል የተባሉ ማረሚያ ቤቶች ግን አልተገለጹም።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ውሎ...

ዛሬ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች #ሰልፎች ተደርገዋል። በአፋር ክልል "ለውጡ ወደ እኛ አልደረሰም" ያሉ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ከአዋሽ ከተማ ወጣ ብሎ መንገድ በመዘጋቱ የአዲስ አበባ ጅቡቲ ትራንስፖርት ለሰዐታት ተቋርጦ ነበር። የመንግስት ወታደሮችም ባንክ ቤቶችን በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ሲጠብቁ ታይተዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሊቾ ወሪሮ🔝

በስልጤ ዞን የአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው መንገድን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ጥያቄ በማንሳት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍኖተሰላም🔝

በአማራ ክልል #ምዕራብ_ጎጃም_ዞን #የፍኖተሰላም ከተማ ነዋሪዎች የመሬት ወረራን #በመቃወም ድምፃቸውን አሰምተዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia