TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብሄራዊ ቤተ መንግስት

የብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያቀው ከ300 በላይ #የስልክና #የኢንተርኔት መስመሮችን ጨምሮ ለግለሰቦች በሚውሉ መስተንግዶዎች ምክንያት በየዓመቱ #ከ11_ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱ ተገለፀ።

በአሰራር ክፍተት #ሲመዘበሩ የነበረ በርካታ ሚሊየን ብሮች ግምት ያላቸው ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉንም የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር አስታውቋል።።

በችግሮቹ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 31 ግለሰቦች ላይ #እገዳ የተጣለ ሲሆን፥ ቤተ መንግስቱ አሰራሩን በአዲስ መልክ በማደራጀት ክፍተቶቹን የማስተካከል ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በስሩ ከአስር በላይ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ቤተ መንግስቶችን የሚያስተዳድረው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር በዋነኝነት ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፈጽማል።

ከቤተ መንግስት ጋር ተያይዞ የሚገኙ ቅርሶችን መጠበቅና መከባከብ፣ ትላልቅ መስተንግዶዎችን ማከናወን እና ቤተ መንግስቱ ገቢውን በማሳደግ ራሱን በተሻለ ደረጃ እንዲያስተዳደር የሚሉ ናቸው።

የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር መቀመጫ የሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀላፊነት ሲወጣ ቢቆይም ለረጅም ጊዜያት ከመመሪያና አሰራር ውጪ የሆኑ ተግባራት ሲፈጸሙበት መቆየቱን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል።

ባለፉት 9 ወራት በተሰራው የማጣራት ስራ ቤተ መንግስቱ በአስተዳደር ሂደት ውስጥ የሚያቀርባቸውን የመስተንግዶ አገልግሎቶች ለግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጸሚያነት  እንዲውል በማድረግ በየዓመቱ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሲደረግ ቆይቷል።

ከስልክ፣ ኢንተርኔትና ኢ ቪድዮ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያገቃቸው ከ300 በላይ አካውንቶች በስሙ በየዓመቱ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ሲከፈል መቆየቱም ተደርሶበታል።

እነዚህ በማሳያነት የተነሱት ችግሮችና የተመዘበረ የገንዘብ መጠን ለማሳያነት የቀረቡ እንጂ በገንዘብ ያልተተመነና በአገልግሎት የሚገለጹ ሌሎች ጉድለቶችም እንደነበሩ ማረጋገጥ ተችሏል።

የገንዘቡም መጠን ሆነ የአገልግሎቱ ጉድለት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፥ ይህም ወደ ገንዘብ ሲለወጥ በ100 ሚሊየን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ሲመዘበር ቆይቷል ማለት ነው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት ችግሮቹን ከመለየት ባለፈ ድርጊት ፈጻሚዎች የሚባለኩት በአመራር ላይ የነበሩና ከአመራር የተሰናበቱ 31 ግለሰቦችን ለይቶ አግዷቸዋል።

ድርጊቱን በማስቆም ለተጠያቂነቱ ኮሚቴ በማዋቀር የማጣራት ስራን እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

ሌላው በብሄራዊ ቤተ የግዢ ስርአት ውስጥ የነበሩ ክፍተቶች በርካታ ግዢዎች እየተፈጸሙ ለአገልግሎት ከማዋል ይልቅ በመመጋዘን የማከማቸት ችግር ይታይ ነበር።

የተገዛው እቃ በመከማቸቱ እየተበላሸ ሌሎች በተለይም የውጪ ግዢዎችን በተከታታይ እየፈጸሙ መጠን እየቀናነሱ ማስገባትም ሌላኛው ችግር ነበር።

የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መየሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት የንብረት አያያገዝ ችግሩም ሀብቶቹ እንዲባክኑ እየሆነ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆታቸውን ያስታወቀው የብሄራዊ ቤተ መንግስቱ አስተዳደር፥ አሁን ላይ ወደ መፍትሄው እርምጃ መግባቱንም አስታውቋል።

በሂደቱ ተጨማሪና የተሻሉ አሰራሮችን መዘርጋትና ወደ ተግባር ማስገባነት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት በቅርቡ ለህዝብ ክፈት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩም መሆኑን ሰምተናል።

ቤተ መንግስቱ ያሉትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀምና እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም በማደስ በአጭር ጊዜ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ተጠቋሚዎች የሚለዩባቸውን መመዘኛ መስፈርቶችና #የጥቆማ ጊዜ ይፋ ሆነ።

#የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜ ከመጋቢት 1/07/2011ዓ.ም እስከ መጋቢት 20/07/2011ዓ.ም ድረስ በስራ ስዓት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የእጩ ኮሚሽነር መመዘኛ መስፈርቶችም፦

•እድሜው/ዋ/ ከ 35 ዓመት በላይ የሆነ

•ከደንብ መተላለፍ ውጭ በሌላ የወንጀል ጥፋት ተከሶ ያልተፈረደበት

•ዜግነቱ/ቷ/ ኢትዮጵያዊ የሆነ

•በህግ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሙያ የሰለጠነ ወይም በልምድ ሰፊ እውቀት ያካበተ

•ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተቆርቋሪ የሆነ

•ለህገ-መንግስቱ ተገዥ የሆነ

•ስራውን ለመስራት የሚያስችል የተሟላ ጤንንት ያለው

•በታታሪነቱ ፣ በስነ-ምግባሩና በታማኝነቱ መልካም ስም ያተረፈ
የትምህርት ዝግጅትን በተመለከተ

•ተጠቋሚው ያቀረበው ሰነድ / የልደት ዘመን፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድ እና cv /ግላዊ መረጃዎች/ ወዘተ በግብዓትነት ያቀርባል፡፡

•በቀጥታ በህግ፣ በሰብዓዊ መብት ትምህርቶች እንዲሁም በአመራር፣ ማኔጅመንት፣ ሰላምና ደህንነት፣ የስነ-ምግባርና ስነ-ዜጋ፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ሳይኮሎጅ፣ ሶሾሎጅና ሶሻል ወርክ፣ የሰለጠኑ ሆነው ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው እንደሚሆኑ አቶ ታገሰ በመግለጫቸው ገልጸዋል።

አቅራቢ ኮሚቴ እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ አጠናቆ ለፓርላማ ሪፖርት ቀርቦ እንደሚፀድቅ የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ህዝቡ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ በሚከተሉት ዘዴዎች ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል፡፡
በስልክ 0111241036 ፤በፋክስ 0111241060 ፤ ኢሜል hprhumanright@gmail.comPo box:- 80001 መላክ ይቻላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘውን ጨምሮ 8 ተከሳሾች ክሳቸው እንዲሻሻል ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። እነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ትራክተሮችን ያለጨረታና የግዥ መመሪያ ከሚፈቅደው ሥርዓት ውጭ የጥራት ችግር ያለባቸው ዕቃዎችን በመግዛት 119,856,756.23 ብር በህዝብና በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ተከሰው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ተከሳሾቹ የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ከዚህ ቀደም ይዘውት በቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ የተወሰኑ ክሶች እንዲሻሻሉ ፍ/ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት በቀረበው የክስ መቃወሚያ ላይ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 8 ተከሳሾች ከትራክተር ግዥ ጋር በተያያዘ ክሱ እንዲሻሻል ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በተሸሻለው ክስ ላይ ክርክር ለማድረግ እና ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለመጋቢት 5/2011 ዓ.ም. ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢንፍርሜሽን መረብ ደህንንት አጀንሲ ያዘጋጀው ደራሽ የተሰኘ ሃገር አቀፍ የተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም ነገ ይፋ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡ የክፍያ ፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎች በሚመቻቸው መንገድ እና በመረጡት ቦታ ሆነው የአገልግሎት ክፍያ፤ ግብር፤ ኪራይ እና ቅጣት መከፈል ያስችላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢመደኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የአዲስ አበባ መስተዳድር ም/ከንቲባ የሆኑትን ኢ/ር #እንዳወቅ_አብጤን ከመስተዳድሩ ስራ አስፈፃሚነት "ታገዱ" መባላቸውን አስመልክቶ ማምሻውን ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጋር ቆይታ አደርገው ነበር።

በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ፦

"ውሸት ነው! ባለፈው አንድ የሆነ ንግግር ተናግረህ ነበር እና በሱ ይሆን ወይ ላልከው፣ ሰው መናገር #ይታገዳል እንዴ? በዛ ላይ በዚህ የለውጥ ዘመን። የታገልነው እኮ ስርአቱ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ነው። ስለዚህ አንድ አመራር ተናገረ ተብሎ ማገድ ካለ በእርግጥም ለውጡን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል። ስለዚህ እንደዛ ማረግም ትክክል አይደለም፣ የተደረገ ነገርም የለም።"

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካራማራው ድል‼️

የካቲት 26 1970 አመተ ምህረት ወራሪው የሱማሊያ የዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት 41ኛ አመት የመታሰቢያ በዓል ነው፡፡

በአሜሪካ እና በሶቪየት ሕብረት ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው ወራሪውን የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያን አንድነት ዳግም የታየበት ስለመሆኑም ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የካራማራ ድል ዘንድሮም ለ41ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ(ናይሮቢ)🛫

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር #ለመወያየት በአሁኑ ወቅት ወደ #ናይሮቢ ኬንያ አቅንተዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ በሶማሊያና ኬንያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀ መንበርነታቸው በቅርበት በመከታተል ወደ #ዕርቅ የሚመጡበትን መላ እያፈላለጉ ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኬንያታና የሶማሊያው አብዱላሂ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት በዘለቁ ወቅት ከሁለቱም ጋር ባደረጉት ምክክር፤ ይህንን የኬንያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት ለማመቻቸት ወስነው ነበር። ይህ የውይይት መድረክም በሁለቱ መካከል ያለውን የተካረረ ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይታመናል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ። ለ6 ቀናት የቆየው የዕሳት ቃጠሎ ከ160 እስከ 200 ሄክታር የሸፈነ ቦታ ላይ የሚገኝ አሰታን(Alpine) አውድሟል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ የካቲት 27/2011 በእጣ ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፈው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር እና በዕጣው ለመግባት የሚያስፈልገው የቁጠባ መጠን፦

ሀ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ዝርዝር በቁጥር

1. ባለ 1 መኝታ = 3,060
2. ባለ 2 መኝታ = 10,322
3. ባለ 3 መኝታ = 5,194
በጠቅላላ ለ2ኛው ዙር ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ 18,576 የ40/60 ቤቶች ናቸው

ለ. በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ያሉ ተመዝጋቢዎች

1. በባለ 1 መኝታ = 11,699
2. በባለ 2 መኝታ = 57,277
3. በባለ 3 መኝታ = 56,138
በጠቅላላ 125,114 ተመዝጋቢዎች በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ይገኛሉ።

ሐ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን (ለሁሉም የመኝታ ዓይነት በምዝገባው ወቅት ከነበረው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 40% እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ)

1. ለባለ 1 መኝታ = 162,645x0.4 = 65,058 ብር
2. ለባለ 2 መኝታ =250,000x0.4 = 100,000 ብር
3. ለባለ 3 መኝታ = 386,400x0.4 = 154,560 ብር

መ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የዕጣ ፕሮግራም ብቁ (ዝቅተኛ የቁጠባ መጠንን ያሟሉ) ሆነው ለዕጣው ተወዳዳሪ የሚሆኑ የተመዝጋቢዎች ብዛት በቁጥር
1. በባለ 1 መኝታ = 5,502
2. በባለ 2 መኝታ = 25,634
3. በባለ 3 መኝታ = 26,126

በጠቅላላ 57,262 ብቁ ተመዝጋቢዎች ለ18,576 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ በሚገኘው የአፄ ቴዎድሮስ ሐውልት ላይ ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ #በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው የወንጀል ዐቃቤ ሕግ አቶ ድረስ ዘለለው ለኢዜአ እንደተናገሩት ቅጣቱ የተላለፈባት ነዋሪነቷ በጎንደር ከተማ በሆነው በወይዘሮ መንደሬ እያዩ አባተ ላይ ነው፡፡ ግሰሰቧ የካቲት 5 ቀን 2011 ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ30 ሲሆን፣ ፒያሳ አደባባይ ላይ የቆመውን ሐውልት ቀኝ እጅ ጎራዴ ላይ ጉዳት ማድረሷ በሦስት ምስክሮች በመረጋገጡ ነው፡፡ ግለሰቧ በወንጀል ሕግ ቁጥር 690 ንዑስ ቁጥር ሁለት የሕዝቦች የጋራ ሐውልት በሆኑ ታሪካዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት በማድረስ የተደነገገውን አንቀጽ ተላልፋ መገኘቷንም አመልክቷል፡፡ ተከሳሿ በቀረበባት ክስ በፍርድ ቤት ወንጀሉን አልፈጸምኩም በሚል ክዳ ብትከራከርም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባትን ማስረጃን ባለማስተባበሏ ቅጣቱ ተወስኖባታል፡፡ የጎንደር ከተማ ፍርድ ቤት ግለሰቧ የቤተሰብ አስተዳዳሪና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለባት መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት ተይዞላታል፡፡ ግለሰቧ የፈጸመችው ወንጀል እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን በቅጣት ማቅለያነት እንደያዘላት ዐቃቢ ሕጉ አስረድተዋል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia