TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜጀር ጄነራል ክንፈ‼️

የብረታብረትና ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን ከተፈጸመ የመርከብ ሽያጭና የሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ የተከሰሱት እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ከአምስት ገጽ በላይ መቃወሚያ አቀረቡ።

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 ተከሳሾች ያለአግባብ በተፈጸመ በሆቴል ግዢና በመርከብ ሽያጭ በርካታ ብር እንዲባክን ሆኗል ሲል አቃቢ ህግ የመንግስት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት ሙስና ወንጀል በሁለት መዝገብ ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

ይህን ክስ ተከትሎም ተከሳሾቹ ከአምስት እስከ 10 ገጽ የሚደርስ የክስ መወቃወሚያ አቅርበዋል።

ያቀረቡትን መቃወሚያ አቃቢ ህግ ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ለጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ከሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ ተከሰው ያልቀረቡ 2ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾችን እንዲሁም ከመርከብ ግዢ ጋር ተያይዞ ያልተያዙ 2ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ፣ 13ኛ እና 14ኛ ተከሳሾችን ፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ:- fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል፤ ዕዳ ላለባቸውም ዕዳ ሰርዟል፡፡ ለኢትዮጰያ ዐይን ባንክ ደሞ 250 ሺህ ብር መለገሱን የገለጸ ሲሆን የሚደሮክ ፕሮጄክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶችም እንዲሁ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የሚድሮክ ንብረት በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችም ላንድ ወሰነ ትምህርት #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

Via wazemaradio(walta)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሚድሮክ ሰራተኞቹን አንበሸበሸ‼️

የሚድሮክ ግሩፕ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ከእስር #መፈታትን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹን #አንበሸበሸ

Via waltainfo
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀድሞው የኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ ሃላፊ ለነበሩት ተጠርጣሪ ከሳምንት በፊት በዋስትና እንዲፈቱ ማዘዙ ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪው ከብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በተያያዘ ሙስና ወንጀል ነበር ተጠርጥረው የታሰሩት።

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahiopia
ዶ/ር ዐብይ~ብሄራዊ ትያትር ናቸው🔝

ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ በአሁኑ ሰዓት #በብሄራዊ_ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት እየተካፈሉ ነው:: ለተሳታፊዎቹ ባስተላለፉት መልእክት ስለ መስጠት ባህልና የበጎነት ምግባር አንስተዋል::

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ‼️

ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 20/2011 ዓ.ም.

የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ፍራንክ_ዋልተር_ሽቴይንሜይር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
.
.
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አቶ #ዳዊት_ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
.
.
ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የEuropean Tourism Academy Membership ሽልማት ሊሠጥ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4 ሚሊየን 234 ሺህ 856 መቶ ተሸከርካሪዎች በማስተናገድ በአጠቃላይ ብር 124 ሚሊየን 578 ሺህ 594 መቶ ብር መሰብሰብ መቻሉ ተሰምቷል።
.
.
#አለን_ኢትዮጵያ የበጎ-አድራጎት ድርጀት የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል ህጋዊ እውቅና በማግኘት ትላንት በ19/05/01 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ሥራ ጀምሯል።
.
.
በአንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጋር #መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
የሚድሮክ ግሩፕ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ከእስር #መፈታትን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹን #አንበሻብሿል
.
.
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሙስና ተጠርጣሪው የጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም #ኢሳያስ_ዳኘው ፈቅዶት የነበረውን የዋስትና መብት ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሻረው ካፒታል ዘግቧል፡፡
.
.
ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ምሽት #በብሄራዊ_ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት ተካፍለዋል።
.
.
ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ፦ የሚድሮክ ንብረት በሆነው #ዩኒቲ_ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ላንድ ወሰነ ትምህርት(1 ሴሚስተር) #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡
.
.
ምንጭ፦ ዋልታ፣ ፋና፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ሬድዮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ለስብሰባ የሚያወጡት ወጭ አሻቅቧል፡፡ ለመስተንግዶ የመደቡትን ወጭ አሟጠው ጨርሰው ከሌላ በጀት እንዲዘዋወርላቸው የጠየቁ መስሪያ ቤቶች መኖራቸውን ሸገር ዘግቧል፡፡ በተለይ ስብሰባዎች ባብዛኛው ቢሾፍቱ እና አዳማ ባሉ ሆቴሎች መካሄዳቸው ለነዳጅ፣ መስተንግዶ፣ ሆቴል ኪራይና አበል የሚወጣውን ወጭ ስላናረው በጀቱ እየተዛባ ነው፡፡ አስተዳደሩ በዚህ አያያዙ የበጀት እጥረት እንዳይገጥመው ተሰግቷል፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው። ድርጅቱና የኢትዮጵያ መንግሥት ከአስር ዓመታት በላይ በባለቤትነት ይገባኛል ሲነታረኩ ቆይተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጤፍ ጉዳይ ፍርድ ቤት የሚሟገተው 'ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል' የተባለ የሆላንድ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱም እንግሊዝ፣ ጣልያን፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያ እና ሆላንድ ውስጥ የጤፍ ባለቤትነት ፈቃድ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በብዙ የአውሮፓ ሃገራት እውቅና የተሰጠውን የዚህን ድርጅት ጤፍ የማከፋፈል መብት ለማስነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት ለ14 አመታት ሲታገል ቆይቷል። በፈረንጆቹ 2000 አካባቢ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር ስምምነት ስትፈራረም የጤፍ ምርትን ማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነበር። ነገር ግን ለድርጅቱ የተሰጠው ፈቃድ ኢትዮጵያ የጤፍ ምርትን ወደ ውጪ ከመላክ ያግዳታል።

Via AHADU RADIO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የአማሮ ወረዳ አስተዳደር የኦነግ ታጣቂዎች ካምፕ እየገቡ ነው የተባለው መንግሥት እርምጃ መውሰድ ስለጀመረ የማታለያ ዘዴ ሲል ይከሳል፡፡

የ"ኦነግ" ልቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት መረጃው የለኝም ብለዋል፡፡

በቦታው ያለው የመከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ጥቃት አድራሹ የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው ይላል፡፡

እስከአሁን በአካባቢው በተፈፀመ ጥቃት 78 አርሶ አደሮች መገደላቸውን ፣ ከ114 አካል ጉዳተኛ ሲሆኑ ከ21 ሺህ በላይ ዘጎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው መንግሥት ይናገራል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሄዱ። በልምምዱ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia