TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህር ዳር🔝ለ7 ሚሊዮን ህዝብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው "ጥበበ ግዮን" ሆስፒታል ዛሬ በ3 ሀግራት መሪዎች #ተመረቀ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ሆስፒታሉን ሆስፒታሉን መርቀውታል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ከ40 በላይ የሚሆኑ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት #በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ፡፡

የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት ትናንትና ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለስብሰባ ከተጠሩበት ስፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ከፍተኛ አመራሩና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር የዋሉት ገርጂ አካባቢ በሚገኘውና ቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ ይጠራ በነበረውና አሁን የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሆነው አሞራው ሕንፃ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ምክንያት ባይነለጽም፣ የፌዴራል ፖሊስ ጌዜያዊ እስር ቤት በሆነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ቤት መታሰራቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቦንጋ ከተማ‼️
ቦንጋ⬆️ዛሬም ለተከታታይ ቀን በቦንጋ ከተማ የተቃውሞ #ሰልፍ ሲደረግ ተስተውሏል። በከተማይቱ የንግድ አገልግሎት እንደቆም እንዲሁም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደተቋረጠ ነው። የቡና መገኛነታችን ይከበር በሚል ነው ተቃውሞው እየተካሄድ ያለው። ከአንድ የከተማይቱ ነዋሪ ጋር በስልክ ባደረኩት ቆይታ በቡና መገኛነት ዙሪያ የተሰራጨው መረጃ #ስህተት በመሆኑ የሚመለከተው አካል በሚዲያ ወጥቶ በግልፅ #ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ብሎኛል። ችግሩ ከዚህ ሳይሰፋም የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሊፈቱት ይገባል ሲል አክሏል።

©ESA(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE የኢትዮጵያ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ቀጣይ የሶስትዮሽ ውይይታቸውን #ሞቃዲሾ ላይ ለማካሄድ መስማማታቸው ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር⬆️

ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው በባሕር ዳር የአካል ተሃድሶ ማዕከል በመገኘት ለአካል ጉዳተኞች 15 ዊልቼር ድጋፍ አደረጉ፡፡

የክልሉን መንግስት በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ አንዷለም አካል ጉዳተኞችን ማዕከል ያደረገ ስራ መሰራቱ ጥቅሙ ላቅ ያለ በመሆኑ ቀዳማዊት እመቤቷ ያደረጉትን ድጋፍ የክልሉ መንግስት በአድናቆት ይመለከተዋል ነው ያሉት፡፡

የአካል ጉዳተኞቹን ወክለው ድጋፉን የተቀበሉት አቶ ይመር መልካሙ ባለፈው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ.ር ዐብይ መጥተው በጎበኙን ወቅት የገቡትን ቃል ቀዳማዊት እመቤቷ ተግባራዊ ስላደረጉልን ደስታችን ለመግለፅ እንወዳለን ብለዋል፡፡

በማዕከሉ የምንኖር ጉዳተኞች በጠቅላይ ሚኒስትር ስንጎበኝ ዶ.ር ዐብይ የመጀመሪያው ናቸው ያሉት አቶ ይመር በቀጣይም ተከታታይ ድጋፍ ሊደረግልን ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ‼️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አመራሮች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ከ20 በላይ የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ናቸው #በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

ፖሊስ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቀው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ሥራም እንደቀጠለ ነው የተገለጸው፡፡ አመራሮቹ እና ሰራተኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት #ምክንያት በይፋ #አልተገለጸም፡፡

በጉዳዩ ላይ የፊታችን ሰኞ ፖሊስ ዝርዝር #መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጾልናል፡፡

ምንጭ፦ የአማራ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ ተሸኙ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ መሀመድ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሽኝት አደረጉላቸው፡፡ መሪዎቹን የአማራ ክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሸኝተዋቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦንጋ⬆️

"ፀግሽ እንደምታየው በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ህዝቡ እየመጣ ተቃውሞውን እያስተጋባ ነው። የከተማው ህዝብም ንፍሮ ቀቅሎ ለሰልፈኞች በማቅረብ ድጋፍ እያደረገ ነው። ደስ የሚለው ግን ከስራና ከሰው መጉላላት ውጪ እስካሁን በንብረትም ሆነ በሰው ላይ የደረሰ #አደጋ የለም። ጥያቄያቸው፦
1, የቡና መገኛነታችን ይከበር
2, ክልል የመሆን ጥያቄያችን ይመለስ
3, የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ችላ ብሎናል
4, ዞኑን ወክለው በክልል እና በተወካዮች ም/ቤት ያሉት አመራሮች የህዝቡን ጥያቄ እያስተጋቡ አይደለምና....ሌሎችም ናቸው። መነሻው ግን አንደኛው ነው። esa ከቦንጋ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር❤️

ቆይታ ከቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር #አብይ_አህመድ ጋር ባህር ዳር!

ፎቶ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ፈረጃ ቶነር! የተለያዩ የኘሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ቀለምች በተሻለ ዋጋ አሉን። በ+251911276145 ይደውሉ