TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰመራ⬆️ለአፋር ህዝብ ፓርቲ ዛሬ በሰመራ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። የተደርገው አቀባበልም #በሰላም ተጠናቋል።

በሌላ በኩል...

ዛሬ 9:00 በሰመራ ሉሲ አዳራሽ Dr. Konte Musa የፓርቲው መስራች እና ሊቀመንበር ከህዝቡ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።

©Samarians ከሰመራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከነዋሪዎቹ ጋር #የሰላም እና #የልማት ዉይይት እያካሄደ ነዉ። ከቀናት በፊት በከተማዋ ተከስቶ የነበረዉን #አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ ከአገር የሽማግሌዎች፤ ወጣቶች ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተወከሉ ነዋሪዎች ጋር በዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነዉ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ #ሰለሞን_ፈየ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና የዜጎች ተዘዋዉሮ መስራት እና መኖር መብት እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና⬆️ከ1997 ጀምሮ ታጥረው የቆዩ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው #ተቋርጦ ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ግዜ ታጥረው የተቀመጡ በመንግስት፣ በግል ባለሀብቶችና በተለያዩ የዲፕሎማቲክ ተቁዋማት ተይዘው የነበሩ አጠቃላይ ስፋታቸው 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ መሬቶች የሊዝ ውላቸው ተቁዋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ከካቢኔ አባላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ነው ውሳኔውን ያስተላለፉት።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግስት የተያዙ 11 ቦታዎችን። ጨምሮ በድምሩ 154 በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎች ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ ይደረጋሉ።

ቦታዎቹ በዝርዝርም:-

1, ከግል ባለሀብቶች 95 ቦታዎችን በካሬ 456,428.00/ አራት መቶ ሀምሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ ስምንት ካሬ/

2, ከመንግስት መስሪያ ቤቶች 19 ቦታዎችን በካሬ 127,140.93/ አንድ መቶ ሀያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አርባ አንድ ካሬ/

3, የሸራተን ማስፋፊያን ጨምሮ ከሚድሮክ ግሩፕ 11 ቦታዎችን በካሬ 549,241.00 /አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ካሬ/

4, ከዲፕሎማቲክ ተቁዋማት 18 ቦታዎችን በካሬ 250,413.89 / ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ አራት መቶ አስራ አራት ካሬ/

5, ከፌደራል ተቁዋማት መከላከያና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽንን ጨምሮ 11 ቦታዎችን በካሬ 2,743,200.00 / ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ካሬ ባጠቃላይ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው
ተቋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።

ቦታዎቹ ከ 1997 እስከ 2004 በተለዬዩ ጊዜያት የተላለፉና እስካሁን ምንም አይነት ልማት ሳይከናወንባቸው ታጥረው የተቀመጡ ናቸው።

📌ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ጨምረው እነዚህና መሰል ቦታዎች የከተማዋን ልማት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆኑ ጠቅሰው ይህ ስራ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን ከዚ በኹዋላ መስተዳድሩ ቦታ ወስደው ወደልማት የማይገቡ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ባለሀብት ላይ ጥብቅ ክትትል አድርጎ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል።

©Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ⬆️

"ሀይ ፀግሽ እንዴት ነህ? ከድሬዳዋ ነው የምልክልህ። ከትላንት ጀምሮ #ሳቢያን የተባለ ሰፈር እኛ ወጣቶች በሰፈራችን ከፖሊስ ጋር በመተባበር በበጎ ፈቃደኝነት በመደራጀት የተጠናከረ ጥበቃ እያረግን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የድሬዳዋ ሳቢያን ፖሊስ ጣቢያ ስላደረጉልን ትልቅ ትብብር ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ። ወጣቱ ላይ ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚፈጥር ስራዎች ቢሰሩ ብዙ የሚፈፀመውን እና ሊፈፀም የታሰበውን ወንጀል በጋራ ተከላክለን ሰላም እና ፍቅር የሰፈነባት ድሬዳዋን መፍጠር እንችላለን ብዬ አስባለሁ። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቀይ መስቀል⬆️

"ቀይ መስቀል:- ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ችግሩ ከተከሰተበት ዕለት አንስቶ በማስተባበር ፣ በመንከባከብ፣ ቤተሰቦቻቸውን በማገናኘት ፣ አምቡላንስ በማቅረብና ህመም የሚያጋጥማቸውን ወደ ህክምና ማዕከላት በማመላለስ ፤ ውሀ በቀይ መስቀል ቦቴ በማቅረብ ፤ የተጠለሉበትን ቦታ በማፅዳት እና የህፃናትን ገላቸውን በማጠብና ንፅህናቸውን በመጠበቅ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር የቀይ መስቀል በጎፈቃደኞች እጅግ በሚደንቅ ወገናዊነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ዛሬም በፎቶ እንደሚታየዉ የመጡ እርዳታዎችን በማሠራጨት ላይ ናቸው። አኩሪ የህሊና እርካታን የሚያስገኝ ሰብዓዊ ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ #ብርሃኑ_ተክለያሬድን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ #ሁከት እንዲፈጠር ረድተዋል በሚል የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮም ተፈቅዶለታል።

በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ሰብዓዊ መብትን #የሚጥስ አያያዝ እየተተገበረባቸው እንደ ሆነ ለፍርድቤቱ ተናግረዋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ የሆኑት ሄኖክ አክሊሉ ደንበኞቻቸው በጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል እንዲታሰሩ መደረጋቸውን፣ ከህገ-መንግስቱ በተፃራሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከ48 ሰዓታት በኋላ መሆኑን እንዲሁም ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በተለይ «የአዕይምሮ ህመም አለበት» ተብሎ ከሚጠረጠር ሰው ጋር እንዲታሰር መደረጉ ለህይወቱ አስጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎች በተገቢው መንገድ እንዲያዙ ፖሊስን ማሳሰቡንም አክለው ነግረውናል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ሁከትን በማስተባበር እና በመፍጠር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ያሳያሉ ያላቸውን ሰነዶች እና የባንክ ደብተር እንዳሉት ሆኖም ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀን ያስፈልገኛል በማለት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ብርሃኑ ተክለያሬድ ከዚህ ቀደም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በነበረው ተሳትፎ ፣ቆየት ብሎ ደግሞ «የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን ሊቀላቀል ሞክሯል» በሚል ለእስር መዳረጉ አይዘነጋም።

ብርሃኑ በቅርቡ ከእስር ከተፈቱ የፖለቲካ እስረኞች መካከል አንዱ ነበር።

ምንጭ ፦ BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሪፖርት📌የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት በዓለማችን በአማካይ ከ20 ሰዎች ውስጥ አንዱ በአልኮል መጠጥ #እንደሚሞቱ ጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2016 ብቻ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች መሞታቸውም በሪፖርቱ ተካቷል።
ከዚህ ውስጥ ከ75 በመቶ የሚበልጡት ወንደች መሆናቸው ተገልጿል።

የአልኮል መጠጡ ለጉዳት በመዳረግ የሚሞቱት ሰዎች 28 በመቶ ሲሆኑ፣ ለምግብ መፈጨት ችግር በመጋለጥ የሚሞቱት 21 በመቶ ያህል ናቸው።

19 በመቶ ያህሉ ደግሞ የአልኮል መጠጡ በሚፈጥረው የልብ ችግር ህይወታቸውን እነደሚያጡ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ቀሪዎቹ ለካንሰር፣ ለቁስ ህመሞች፣ ለአዕምሮ ችግርና ሌሎች በአልኮል ምክንያት ለሚመጡ የጤና መታወክ በማጋለጥ ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውም ተነግሯል።

የአልኮል መጠጥን መጠቀም በዓለም ላይ ከሚገኙ በሽታዎች 5 በመቶ ያህሉ እንዲባባሱ ማድረጉም ነው የተገለጸው።

በዓለም ላይ 237 ሚሊየን ወንዶችና 46 ሴቶች በአልኮል መጠጥ ምክንያት ለአዕምሮ ችግር መዳረጋቸውንም ሪፖርቱ አሳይቷል፤ ለዚህ ጉዳት ከተዳረጉት መካከል አውሮፓውያን ቀዳሚ ሲሆኑ አሜሪካውያን ይከተላሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር #ቴድሮስ_አድሃኖም ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ስጋት የደቀነውን የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም መዛባት ለመከላከል በትጋት መስራት አለብን ብለዋል።

በዓለም ላይ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ያህል ሰዎች አልኮል ይጠጣሉ። በርካታ ታዳጊዎችም 15 ዓመት ሳይሞላቸው አልኮል መጠጣት እንደሚጀምሩ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ምንጭ፦ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia