TIKUR ANBESSA SCHOOL 2019
1.34K subscribers
542 photos
2 videos
95 files
43 links
Public Channel
Download Telegram
በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019ዓ.ም መክፈቻ መርሃ ግብር በድምቀት ተከናወነ። በዕለቱም የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ቦንሳ ጣሰው ከነአስተባባሪያቸው; የወተማ አመራሮች; የፖሊስ አመራሮች; የት/ቤቱ አመራር መምህራን ሠራተኞች የተማሪ ወላጆች በተገኙበት በድምቀት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርና የችቦ ቅብብል በማድረግ በጋራ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ተከፍቷል።
ቀን 04/2019 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች  ር/መምህራን በሙሉ፡-
በቀን 04/2019 ዓ.ም የትምህርት አጀማመር በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ በነገው ዕለትም (5/1/2019 ዓ.ም) በሁሉም ት/ቤቶች ከዛሬ በተሻለ ሁኔታ የመማር ማስተማር ስራ ማስጀመር ይኖርብናል፡፡
በመሆኑም
·         ከአንደኛ ክፍለ ጊዜ ጀምሮ ትምህርት ማስጀመር
·         የተገኙ መ/ራን  እና ተማሪዎች መረጃ በአግባቡ መያዝ
·         በየክፍሉ የተማሪ መቆጣጠርያ አቴንዳንስ ተዘጋጅቶ የተማሪዎች አቴንዳንስ መያዝ
·         በወረደው አቅጣጫ መሰረት የምገባ አገልግሎት ተግባራዊ ማድረግ
·         ያለምንም ክፍለ ጊዜ ብክነት የመማር ማስተማር ስራ ሙሉ ቀን ማካሄድ
·         ሁሉም ተማሪዎች ዩኒፎርም ለብሰው እንድገኙ ማድረግ (ከአዳዲስ ገቢ ተማሪዎች በስተቀር )
·         መ/ራን ሌሰን ፕላን ይዘው በክፍል ውስጥ መገኘታቸውን ማረጋገጥ
·         የተማሪ አቴንዳንስ በክፍል ደረጃ፣ በፆታ ለይቶ መያዝና መረጃውን ለሱፐርቫይዘሮች መስጠት
ማሳሰቢያ፡- ትምህርት ሙሉ ቀን ይሰጣል፡፡ የትምህርት አጀማመሩ በግልና በመንግስት ት/ቤቶች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ማንኛውም የግል ት/ቤት ከካሌንደር ውጭ መሆን የለበትም፡፡
Channel photo updated
Channel name was changed to «TIKUR ANBESSA SCHOOL 2019»