TIKUR ANBESSA SCHOOL 2019
1.34K subscribers
542 photos
2 videos
95 files
43 links
Public Channel
Download Telegram
Forwarded from Beli Tsegaye
🏆እንኳን ደስ አላችሁ!!!🏆
ክቡራን የት/ቤታችን ተማሪዎች; ወላጆች; የተወማ አመራሮች; መምህራን; የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት በሙሉ በ2018ዓ.ም በቁልፍ ተግባር አመላካችና በሪፎርም ሥራዎች የ1ኛና የ2ኛ መንፈቅ አመት ድምር ውጤት ከፍተኛ አፈጻጸም በማምጣት በክፍለ ከተማው ካሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የ2ኛ ደረጃን በማግኘት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነናል። ይህ ውጤት እንዲገኝ በታታሪነት ተናቦ በመስራትና መረጃ በአግባቡ በማደራጀት ያላሰለሰ ጥረት ያደረጋችሁ አካላትን በሙሉ ከልብ እያመሠገንን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እንላለን።
Forwarded from Beli Tsegaye
መስከረም 4/2019ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይከፈታል።
በዕለቱ መታወቂያ እና ዩኒፎርም ይሠጣል።
መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
🌼መልካም አዲስ አመት🌼
በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019ዓ.ም መክፈቻ መርሃ ግብር በድምቀት ተከናወነ። በዕለቱም የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ቦንሳ ጣሰው ከነአስተባባሪያቸው; የወተማ አመራሮች; የፖሊስ አመራሮች; የት/ቤቱ አመራር መምህራን ሠራተኞች የተማሪ ወላጆች በተገኙበት በድምቀት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግርና የችቦ ቅብብል በማድረግ በጋራ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ተከፍቷል።