TIKUR ANBESSA SCHOOL 2018
1.3K subscribers
504 photos
2 videos
95 files
43 links
Public Channel
Download Telegram
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ11ኛና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች
የማጠናከሪያ ትምህርት በካቴድራል እየተከታተላችሁ ያላችሁ እና የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የ2019ዓ.ም ምዝገባ የምታከናውኑት ከካቴድራል ት/ቤት ክላስተር ማዕከል የሚሠጣችሁን ማጠናቀቃችሁን የሚያረጋግጥ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውን ሰርተፊኬት የሚሰጥ ሲሆን ሠርተፊኬቱን ያልያዘ ተማሪ መመዝገብ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
የማጠናከሪያ ትምህርቱን ባለመሳተፍና በቀሪ ምክንያት ሠርተፊኬት ለማይሠጠው ተማሪ ኃላፊነቱን ተማሪውና ወላጁ የሚወስዱ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
የማላቂያ ትምህርት ፈተና ከአርብ ጀምሮ መሠጠት ይጀምራል
ለ11ኛና ለ12ኛ ክፍል ለሚመለከታችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በካቴድራል ክላስተር ማዕከል ሲሰጥ የነበረው የክረምት የውጤት ማላቂያ የማጠናከሪያ ትምህርት ነሐሴ 20/2018ዓ.ም ይጠናቀቃል። ፈተና ነሃሴ 18 እና 20 /2018ዓ.ም ይሠጣል።
ምዝገባ ከነሀሴ 21 እስከ 25/2018ዓ.ም ብቻ የሚከናወን ሲሆን በምዝገባ ወቅት ማሟላት ያለባችሁ
1. የክረምት ትምህርቱን መከታተላችሁን የሚያረጋግጥ ሠርተፊኬት ከት/ቢሮ የተሠጠ
2. የማጠናከሪያ ክፍያ የከፈላችሁበት ደረሠኝ እና
3. የትምህርት ማስረጃ; ፋይዳ(የተማሪና የወላጅ) ፎቶ ይዛችሁ በመምጣት መመዝገብ ትችላላችሁ።
ማሣሠቢያ:-
የማጠናከሪያ ትምህርቱን ያልተከታተለና ክፍያ ያላጠናቀቀ ተማሪ መመዝገብም ሆነ መሸኛ መውሰድ አይችል።
Forwarded from Agaziyan no.3 s/s
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ከምሽት 1፡00 ጀመሮ ማየት ይቻላል።
የሀገረ አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የሚታይባቸውን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል።
አገልግሎቱ የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉም አሳውቋል።
ተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
አያይዞም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን ምአገልግሎቱ ያሳውቃል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
የውጤት ማላቂያ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የመዝጊያ መርሃ ግብር አርብ ነሃሴ 22 ቀን 2018ዓ.ም በመሆኑ ትምህርቱን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች በዕለቱ ሠርተፊኬት የሚሠጥ ስለሆነ 2:15 ጀምሮ ካቴድራል ት/ቤት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ለ11ኛና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ሊንኩን በመጠቀም የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርቱ ምን ጥሩ ነገር እና መሻሻል ያለበትን እንድትሞሉ እናሳውቃለን። የምትሰጡት አስተያየት የማስተካከያ ርምጃ ለመውሰድ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ሳትዘናጉ ሙሉ።
Forwarded from Beli Tsegaye
🏆እንኳን ደስ አላችሁ!!!🏆
ክቡራን የት/ቤታችን ተማሪዎች; ወላጆች; የተወማ አመራሮች; መምህራን; የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት በሙሉ በ2018ዓ.ም በቁልፍ ተግባር አመላካችና በሪፎርም ሥራዎች የ1ኛና የ2ኛ መንፈቅ አመት ድምር ውጤት ከፍተኛ አፈጻጸም በማምጣት በክፍለ ከተማው ካሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የ2ኛ ደረጃን በማግኘት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነናል። ይህ ውጤት እንዲገኝ በታታሪነት ተናቦ በመስራትና መረጃ በአግባቡ በማደራጀት ያላሰለሰ ጥረት ያደረጋችሁ አካላትን በሙሉ ከልብ እያመሠገንን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እንላለን።
Forwarded from Beli Tsegaye
መስከረም 4/2019ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይከፈታል።
በዕለቱ መታወቂያ እና ዩኒፎርም ይሠጣል።
መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
🌼መልካም አዲስ አመት🌼