الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
923 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
→ክፍል ሦስት←

↝ቁርዓን በዚና ጉዳይ ለምን ሴቶችን አስቀደማቸው።↜


⑨/ ሴት በዚና ሳቢያ ለተለያዩ ወሲባዊ እብደቶች ልትጋለጥ ትችላለች፡፡ በዝሙተኛውና በዝሙተኛይቱ መካከል ፍቅርና ውዴታ ስለማይኖር እርሱ ፈጽሞ
አይራራላትም፡፡ ከዚህም የተነሳ የፊንጢጣ ወሲብን ሊሠራባት ይችላል፡፡ የአፍ ወሲብንም ሊሠራባት ይችላል፡፡ የነዚህ ወሲባዊ እብደቶች ጉዳት ደግሞ እጅግ የከፋ ነው፡፡ መላውን ወሲባዊ ሕይወቷን ሊያበላሽ ይችላል፡፡

①0/ በተለይ የዘመናችን ዝሙተኞች የተለያዩ የወሲብ ማነቃቂያ ነገሮችን በመውሰድ ሴቶችን እንደሚያሰቃዩ እሙን ነው፡፡ ለምሳሌ ሱስ አስያዥ ዕፅን የወሰደ ወንድ
ሴቷን በአንድ የወሲብ ዙር ብቻ እስከ 40 ደቂቃዎች ሊያሰቃያት ይችላል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሴቷ በቀላሉ ትዳከማለች፡፡ አካሏም ሆነ መንፈሷ ሲበዛ ይጎዳሉ፡፡
ይህም በርሷ ምርታማነት(ልጅ መውለድ ላይ)ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለው፡፡

①①/ ሴት ልጅ በተለይ አሁን ቴከኖሎጂው በብዛት ለመጥፎ ነገር ማስፋፊያነት በሚውልበት አግባብ ውስጥ በለየለት መጥፎ ወንድ እጅ ከገባች እርሱም ዚናውን
እየፈጸመባት በተጓደኝነትም ያንን ትዕይንት ቀርጾት ያስቀምጠዋል፡፡ ወንዱ ይህንን ካደረገ ደግሞ ከዚህ በኋላ የርሷ ነገር በርሱ እጅ ውስጥ ገባ ማለት ነው፡፡ እንደፈለገ ይጫወትባታል፡፡ ያስፈራራታል፤ ያስለቅሳታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሴቷ ለብላክሜይሊንግ(ማስፈራሪያ) ትጋለጣለች፡፡ ይህም ነገር በተውበት ወደ አላህ (ሰብሃነ ወተዓላ) እንዳትለመስ ሁሉ መሰናክል ይሆንባታል፡፡ በዚያ ቪዲዮ ሳቢያም ሴቷ ወደ ጌታዋ ሁሉ መሸሽ የማትችልበት ሁኔታ ያጋጥማታል፡፡

①②/ ዝሙተኛ ሴት ለአስከፊው የሴተኛ አዳሪነትና ለወሲብ ንግድ የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ በተለይ ጅንጀና የሚበዛባት ከሆነ በቀላሉ ወደዚህ ሥራ ልትገባ ትችላለች፡፡ የሴተኛ አዳሪነት ሥራ ጭንቅላት፣ ተያዥ፣ የሕክምና ማስረጃ፣ የሥራ ፈቃድና የመነሻ ካፒታል ስለማይጠይቅም የዝሙት ሱስ ያለባቸውን ሴቶች
የመሳብ ችሎታው ከፍ ያለ ነው፡፡

↝በአጠቃላይ ሴት ልጅ በዝሙተኛ ወንድ እጅ ገባች ማለት የትዳር አጋሯ ባልሆነ፣ በማይወዳት፣ በማያፈቅራት፣ በማይጠነቀቅላትና በማያዝንላት ሰው እጅ ገባች ማለት ነው፡፡ ይህ የወሲብ መንገደኛም ለራሱ ስሜት እንጂ ለርሷ ደህንነት አንዳችም ነገር አይጨነቅላትም፡፡ ለሚመጣው መዘዝም ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ ጉዳት ሲደርስባትም አብሮነቱን አያሳያትም፡፡ ከዚህም የተነሳ በወሲብ መንገደኛ እጅ የገባች ሴት ለአውሬያዊ አያያዝ ትዳረጋለች፡፡ ይህም ሴቶችን በሁሉም መልኩ
ይጎዳቸዋል፡፡ ዚና ሴቶችን የወሲብ ሕይወታቸውን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ማንነታቸውን ጭምር ያራከሳል፡፡ ክብራቸውን ዝቅ ያደርጋል፡፡ በገላቸው እንጂ በጭንቅላታቸው እንዳያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡ እራሳቸውን እንዲያሻቅጡና አስከፊውን የሴተኛ አዳሪነት ሕይወትን እንዲቀላቀሉ ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ይህም በመሆኑ
ሴቶች በዚና ሳቢያ ከወንዶች በላይ ተጠቂዎችና ተጎጂዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ሲባል ነው ቁርኣን በዚና ጉዳይ ሴቶችን ያስቀደማቸው፡፡

(ወሏሁ አዕለም)

اللهم صل وسلم علي سيدنا محمد
❁════❃ •• ❃════❁
★★★★★

ትክክለኛ ውዴታ ሚገለፀው በዚህ ነው የእውነት የእህቶቻችን ጉዳት(እምባ)የሚያስጨንቀን ከሆነ ይሄን ውድ ምክር ለእህቶቻችን እናካፍል።

👉ፁሁፉ ልብን ይቆረቁራል ይሄን ፁሁፍ አምብባ ጥንቃቄ አታደርግም(ወደ ዚና ትሄዳለች) ማለት ይከብዳል።


👉 እኔ የእህቶቼ እምባ ያመኛል! እናንተስ እኛም ያመኛል ከሆነ መልሳችሁ
በውስጥ መስመር ለእህቶቻችን እና በምናውቃቸው ግሩፖች(ሚዲያዎች) እንልቀቀው።

Co๓๓ent↠
@Jezakellah
👇👇👇↡↡↡↡👇👇👇

ይሄን ውድ አዲስ ቻናል የላችሁም ብየ አላስብም
ግን ምን አልባት ከሌላችሁ በደስታ ተቀላቀሉን።
ብዙ የምንወያይባቸው አዳዲስ ርዕሶች አሉን
ይቀላቀሉን
Join us On
TelegraM Channel

👇 👇 👇 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል አንድ←

↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶቹ↜

አነስ ቢን ማሊክ ባወሩት ሐዲሥ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
↝«የሃይማኖታዊ ዕውቀት መነሳት (በዑለሞች ሞት ምክንያት)፣ የመሃይምነት መንሰራፋት፣ የኸምር (በስፋት) መጠጣትና የዝሙት ይፋ መውጣት ከቂያም
ምልክቶች መካከል ናቸው፡፡» (ቡኻሪና ሙስሊም)

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ሐዲሥ ነብዩ (ﷺ) ከዛሬ 1400 ዓመታት በፊት ስለመጪው ጊዜያት ክስተቶች ከተናገሩት ትንቢቶች መካከል ነው፡፡ እነዚህ ትንቢቶችም ከበቂው በላይ በገቢር ተፈጽመው የርሳቸውን ነብይነት ይበልጡኑ የሚያረጋግጡ መረጃዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡ ያለ ምንም ጥርጥር ዛሬ ዛሬ ዝሙት በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ እንደ መደበኛ የሕይወት ዘዬ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ ዝሙት
የበለጠ በተስፋፋ ቁጥርም ጉዳቱም የዛኑ ያህል አብሮ ሥር ይሰዳል፡፡

ከጌታው ጋር መገናኘትን ተስፋ የሚያደርግ ሰው፣ የጌታውን ምሕረትና እዝነቱን የሚከጅል ሰው፣ እንዲሁም ነገ በኣኼራ የጀነት በሮች ተከፋፍተው እንዲጠብቁት የሚሻና እንኳን ደህና መጣ መባልን የሚፈልግ ሙስሊም ሁሉ የዝሙትን ጉዳቶች ጠንቅቆ ማወቅና ከርሱም መራቅ አለበት፤ ምክንያቱም ብልትን ከሐራም መጠበቅ ከመዳኛ መንገዶች አንዱ ነውና፡፡ ሙስሊሙ በሕይወቱ እስካለ ድረስም የዝሙትን መዘዞች በሚገባ ማወቅና ከዚህ ጸያፍ ነገር በመራቅ የጌታውን ትዕዛዝ አጥብቆ መከተል ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ ርዕስ ሥር እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ በርካታ የዝሙት መዘዞች በዝርዝር ይቀርባሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት እያንዳንዱ ሙስሊም እራሱን ከዝሙት ይበልጥ አርቆ ለመጠበቅ ይቻለው ዘንድ እነዚህን ጉዳቶች
በቅድሚያ ለራሱ በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡ በመቀጠልም አንዱ ሙስሊም ሌላውን በተደጋጋሚ በዚህ ነገር መገሰጽና መምከር አለበት፡፡ የዝሙትን ጉዳት ማወቅ ከርሱ ለመራቅ ትልቁ መንገድ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ነጥብ ላይ የበዛ ትኩረት ሰጥተን ግንዛቤያችንን ማዳበር ይጠበቅብናል፡፡ በተለይ ዛሬ ዛሬ ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል በቀለለበት ዘመንና የዝሙት ማጥመጃዎች በየቦታው በተዘረጉበት ጊዜ ሙስሊሙ የዝሙትን ጉዳቶች በሚገባ ካልተረዳ ሰቀላሉ ዝሙት ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን አብዛኛውን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በዝሙት መዳረሻ መንገዶች ዙሪያ ለማንበብና እዚያም እዚህም በመዋለል ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የዝሙትን ጉዳቶች በዝርዝር ማወቁ አንገቢጋቢና ወቅታዊ ነው፡፡


የዝሙት ዋና ዋና ጉዳቶች በየፈርጁ

በዚህ ርዕስ ሥር ወደ 15 የሚሆኑ የዝሙት ጉዳቶች በምድብ ተከፋፍለው ይቀርባሉ፡፡ ነገር ግን የዝሙት ጉዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፤
ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚሁ በየፈርጁ ተከፋፍለው የሚብራራ የዝሙት ጉዳቶችም ሥነ-ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ጤና ነክ ጠንቆችና መንፈሳዊ ጉዳቶ ናቸው፡፡ ከዝሙት ሥነ-ልቦና ጉዳቶችም እንጀምራለን፡፡

ኢንሻ አላህ በቀጣይ ከዝሙት ስነ ልቦናዊ ጉዳቶቹ እንጀምራለን።

👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉በጣም ወሳኝና ትልቅ ትምህርት ያለው ማስታዎሻ ነው። ሁላችንም ልናውቀው ይገባል ምክንያቱም አብዛሃኞቻን አለማወቃችን ነው ወንጀልን እንደቀላል እንድንዳፈረው ሚያደርገን።
👉 እናም ከእናንተ ያለውን በረካ ለሌሎችም ማድረስ አትርሱ ለራሳችን ብቻ ምንኖር ከሆነ የኢማንን ጥፍጥና አናገኝም።
👉 #ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር👈


JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል ሁለት←

♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
👉①/ ↝የዝሙት ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች↜

በዝሙት ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች ሥር ሁለት ጉዳቶች ይቀርባሉ፡፡ እነዚህም በዝሙት ሳቢያ የሚከሰት የማይቋረጥ ጭንቀትና በዚሁ ጸያፍ ድርጊት ሳቢያ
የሚመጣው ቋሚ የሆነ የጥፋተኛነት ስሜት ነው፡፡!

↠ሀ/ ዚና ግለሰቡን ቋሚ የሆነ ጭንቀት ውስጥ ይከተዋል

«ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር(ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነው፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ 12፡33)

የዝሙት የመጀመሪያው ሥልቦናዊ ጉዳት ጭንቀት ነው፡፡ በልቡ ውስጥ የአተምን ከብደት ያህል ኢማን ያለው ሰው ዝሙትን ከሠራ በውጤቱም ምቾትን ከሚነሱት ስሜቶች ጋር ተቆራኝቶ ይቀራል፡፡ ይህም እርሱ የፈለገውን ያህል ከአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ ምሕረትን ቢማፀንም ያው ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፤ ምንም እንኳ አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ) ለነዚያ ምሕረቱን ለሚለምኑት ቢቸራቸውም፤ ግና ያ አካላዊ ንኪኪው አይፋቅም፡፡ ትዕይንቱ ከአዕምሮው ጓዳና ከመረጃ ቋቱ አይረዝም፡፡ ለምን በተለይ ይህንኑ ፀያፍ ድርጊት በተደጋጋሚ የሠራ ሰው ከሆነ ከጌታው የሚያገኘው ምሕረት ወንጀሉን ቢያብስለትም ግለሰቡ ግን ኃጢአቱን አይረሳውም፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የሌላን ሰው ክብር ጭምር ያካተተ ነበርና፡፡ ግለሰቡ የሚሠራው ዝሙት የአንድን ሰው ሴት ልጅ ያካተተ ነበር፡፡ በውጤቱም አርግዛለች፤ አስወርዳለች፡፡ የአንድን ሰው እህት፣ ሚስት ወይም እናትን ያካተተ ነበር፡፡ በተለይ ሴቷ ትዕይንቱን ፈጽሞ አትረሳውም፤ ምክንያቱም ሴቶችና ዝሆኖች ጠባሳቸውን ፈጽሞ አይረሱምና፡፡

ግለሰቡ ከወንጀሉ ቶብቶ ይበልጥ ወደ አላህ(ﷻ) በተቃረበ ቁጥር ደግሞ ይኸው ቀጣይነት ያለው የጭንቀት ስሜት የበለጠ እያደገ ይመጣል፡፡ ምክንያቱም እርሱ ጌታውን የበለጠ ባወቀው ቁጥር ለጌታው የበለጠ ሐያእን ያዳብራልና፡፡ በዚህን ጊዜ ይበልጥ ከአላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ፊት ምቾት የማይሰማው ሆኖ ይቀራል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዴ ዝሙትም ልክ እንደ ስርቆት ሁሉ በፍጥነት የመከሰት ዕድል አለው፡፡ ልክ ሌባ ማንኛውንም ለመስረቅ የሚያስችለውን አጋጣሚ ሲያገኝ በፍጥነት እንደሚጠቀምበት ሁሉ ዝሙተኛውም አንዳንድ ጊዜ በፍጥነት ፀያፍ ድርጊቱን ሠርቶ መሰወር ይፈልጋል፡፡ በመሠረቱ ዝሙትም ቢሆን ስርቆት እንደመሆኑ መጠን አንዳንድ ጊዜ በአሳፋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ይከሰታል፡፡ የመኪና የኋላ መቀመጫዎች ላይ፣ በጓሮ ውስጥ፣ በቤት ግድግዳ ሥር፣ በመፀዳጃ ቤቶች ውስጥ፣ በመንገድ ዳር፣ በሕንፃዎች መካከል፣ በዛፎች ሥር፣ ወዘተ ይከሰታል፡፡ እንደዚህ ያሉ ቦታዎችና ሁኔታዎች ለአንድም የዝሙት ጥንዶች የበለጠ የፍቅር ወዳጅነትን ለመፍጠር በቂ አይደሉም፡፡ ዝሙተኞቹ መልካም ጊዜ ሊኖራቸውና ቁርኝታቸው ሊጠናከር አይችልም፡፡ በርግጥ ቀድሞ ነገር ግንኙነቱ ሕገወጥ እንደመሆኑ መጠን ምንም ሕጋዊ የሆነ ፆታዊ ትስስርና ወዳጅነት ማደግ የለበትም፡፡ የዚህ ዓይነቱ የዝሙት ድርጊት ደግሞ ከእንስሳዊ ወሲብም የባሰ አስቀያሚና አሳፋሪ ነው፡፡ ለምሳሌ ውሾች በጎዳናዎች ላይ ወሲብ ያደርጋሉ፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ወሲብን ብቻ ነውና፡፡ ወዳጅነት፣ ትስስር፣ ቁርኝት፣ ፍቅር የሚል ነገር እነርሱ ዘንድ የለም፡፡ ዝሙትም ቢሆን ይኸው ነገር ይንጸባረቅበታል፡፡

የአንድ አዳጊ ወንድ ወይም ሴት የመጀመሪያው ወሲባዊ ሕይወቱ በዝሙት የተጀመረ ከሆነ፣ ዝሙቱ እርሷ ላይ ከላይ ባለው ሁኔታ ውስጥ ይበልጥ የመከሰት ዕድል አለው፡፡ ከዚያም ያ ዝሙቱ የተካሄደበት ትዕይንት በርሱም ሆነ በርሷ አዕምሮ ውስጥ ታትሞ ይቀራል፡፡ በውጤቱም መላው የወሲብ ሕይወቱ በዚህ ይጠቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተራው የግለሰቡን የጋብቻ ሕይወት አብዝቶ ይጎዳዋል፡፡ ታዲያ የግለሰቡ የጋብቻ ሕይወት ይበልጥ በተጎዳ ጊዜ እርሱም የበለጠ ጭንቀታም እየሆነ ይመጣል፡፡ በጭንቀት ውስጥም ይኖራል፡፡ ይህ ቀጣይነት ያለው የጭንቀት ስሜትም በሂደት ወደ ጥፋተኛነት ስሜት ያድጋል፡፡ ያም በተራው ግለሰቡን ሁሌም ያሳድደዋል፡፡

አላህ ይጠብቀን❗️
👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈
👉ይ ቀ ጥ ላ ል

ወላሂ በጣም ወሳኝ ማስታዎሻ ነው ሁላችንም ልናውቀው(ልናነበው)ይገባል።
ከኛጋ ያለውን በረካ ለሌሎችም ማድረስ አንርሳ ለራሳችን ብቻ ምንኖር ከሆነ የኢማንን ጥፍጥና አናገኝም።
👉 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር👈


JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል ሁለት← ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ 👉①/ ↝የዝሙት ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች↜ በዝሙት ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች ሥር ሁለት ጉዳቶች ይቀርባሉ፡፡ እነዚህም በዝሙት ሳቢያ የሚከሰት የማይቋረጥ ጭንቀትና በዚሁ ጸያፍ ድርጊት ሳቢያ የሚመጣው ቋሚ የሆነ የጥፋተኛነት ስሜት ነው፡፡! ↠ሀ/ ዚና ግለሰቡን ቋሚ የሆነ ጭንቀት ውስጥ ይከተዋል «ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር(ከዝሙት)…
→ክፍል ሦስት

♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
↠ለ/ ዚና ግለሰቡን ሁሌም በሚያሳድደው የጥፋተኛነት ስሜት ውስጥ ይከተዋል

«እንደ ሕሊናድብቅጠላት የለም፡፡»

«የትም ሂድ፤ ምንም ሥራ፤ ሁሌም የሕሊና እስረኛ ነህ፡፡» ዝሙት በሕገወጥ ጥንዶች መካከል በሚከሰትበት ጊዜ አንደኛው ወገን የድርጊቱ ቆስቋሽ ይሆናል፡፡ ይህም ግለሰብ ይህንን ድርጊት ሲቆሰቁስና ሌላውን ግለሰብ በዚህ ረገድ ለማሳመንና ለማግባባት ሲሞክር በርካታ መጥፎ ነገሮችን ይሠራል፡፡ ያኛውም ወገን አብረው ሕገወጥ ነገርን ሊፈጽሙ ከተስማማ ኃላፊነቱን ይጋራል፡፡ ምክንያቱም እርሱ ወይም እርሷ እምቢ ቢሉ ኖሮ ይህ ጸያፍ ነገር አይከሰትም ነበርና፡፡ በሁለቱም መንገድ ሁለቱም ወገኖች እነርሱ ጸያፍ ነገርንና የገዘፈ ኃጢአትን እየፈጸሙ እንደሆነ በሙሉ ልባቸው ያውቃሉ፡፡ ጉዳዩ እነርሱ በዚያ ደረጃ ላይ ሆነው የሚኖራቸው የሀፍረት ስሜት ደረጃቸው የመግፈፍ እውነታ ነው እንጂ ሁለቱም ድርጊቱ ከባድ ኃጢአት መሆኑን መቼም አያጡትም፡፡

ታዲያ ይህ ሁሉ ድርጊትና ሴራ ግለሰቡን በመደበኛነት ያሳድደዋል፡፡ በተለይ አንድ ሰው በርሱ ድርጊት ሳቢያ ከተጎዳ የገዛ ሕሊናው ይበልጥ ጠላት ይሆንበታል፡፡ በዝሙት ድርጊት ደግሞ በርግጠኝነት ቢያንስ አንድ ሰው ይጎዳል፡፡ እንዴት ነው ሌባው ያንድን ሰው ቤት ሰብሮ፣ የርሱን ጌጣጌጦች ሰርቆበት፣ የርሱን ንብረት ወስዶበትና ከዚያም ማንም በዚህ ድርጊቴ ሊጎዳ አይችልም ብሎ ሊጠብቅ የሚችለው? ለዝሙትም ተመሳሳይ ነገር እውነት ነው፡፡ ዝሙተኛው የአንዲትን ሴት ድንግልናዋን በሚገሰርስበት ጊዜ እርሷ አትጎዳምን? አዎን! ግለሰቡ የአንድን ሰው ሴት ልጅ፣ እህት፣ ሚስት ወይም እናትን ወደ ዝሙት በሚጎትትበት ጊዜ ይህ ድርጊቱ ጉዳትን እንደሚያስከትል ሕሊናው ፈጽሞ አያጣውም፡፡ እርሱ በወቅቱ ስለዚያ ሳያስብ እንኳን የኃጢአቱ ጥላ በሰፊው ያጠልበታል፡፡ ዝሙቱን ከሠራ በኋላም ተሸከሞት የሚቀረው ወንጀል ግለሰቡን ይመርዘዋል፡፡

ዝሙተኛው አንዲት ሴት ለባሏ ያላትን ቃልኪዳን አፍርሳ ከርሱ ጋር እንድትማግጥ በሚያደርግበት ጊዜ ይህ ድርጊቱ በዚያ ሰው መብት ላይ ድንበር አላፊነት መሆኑ መቼም አይሰወርበትም፡፡ ይህ ድርጊት በሴትዮዋ ክብርና የትዳር ሕይወቷ ላይ ትልቅ መዘዝን እንደሚያስከትል ያውቃል፡፡ በርሷ ቤተሰባዊ ሕይወት ላይም በትንሹ አለመረጋጋትን እንደሚፈጥር ጭምር ያውቃል፡፡ ይህንን ሁሉ ሕሊናው ያውቀዋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጥሰቶች በተጨማሪ ይበልጥ አደገኛው ግለሰቡ በዝሙት ድርጊቱ የአላህን ድንበር ማለፉ ነው፡፡ የአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ) ድንበር ደግሞ የሚጣለው በድንበር አላፊዎች ብቻ ነው፡፡ ይህም አምላካዊ ቁጣን ያስከትልበታል፡፡

ሁለቱም የማይቋረጥ ጭንቀትና ቋሚ የጥፋተኛነት ስሜት በተለይ ያገባች ሴት በዝሙት አርግዛ ስታበቃ የልጁን የዘር ሐረግ ከንጹሕ የባሏ ቤተሰብ ውስጥ ስትቀላቅል የበለጠ ከባድ ይሆናሉ፡፡ ይህም ማለት ሴትዮዋ ከምስጢራዊ ፍቅረኛ ላይ አርግዛ እርሷ ምኑንም ለማያውቅ ባሏ ልጅህ ነው ትለዋለች፡፡ ይህም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማንም መገመት ይችላል፡፡ ይህም የዝሙት አደገኛው መዘዝ ነው፡፡

አላህ ይጠብቀን❗️

ኢንሻ አላህ በክፍል አራት የዝሙት አካላዊ ጉዳቶችን ይዤላችሁ እመጣለሁ።

ዝሙት ምን ያክል እንደተስፋፋ ሁላችንም እናውቃለን። መስፋፋቱ የማያሳስበው ይኖራል ብየ አላስብም ምን አልባት ስለ እምነቱ ምንም ስሜት የሌለው ሰው ካልሆነ በቀር።

👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።


ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል ሦስት ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ↠ለ/ ዚና ግለሰቡን ሁሌም በሚያሳድደው የጥፋተኛነት ስሜት ውስጥ ይከተዋል «እንደ ሕሊናድብቅጠላት የለም፡፡» «የትም ሂድ፤ ምንም ሥራ፤ ሁሌም የሕሊና እስረኛ ነህ፡፡» ዝሙት በሕገወጥ ጥንዶች መካከል በሚከሰትበት ጊዜ አንደኛው ወገን የድርጊቱ ቆስቋሽ ይሆናል፡፡ ይህም ግለሰብ ይህንን ድርጊት ሲቆሰቁስና ሌላውን ግለሰብ በዚህ ረገድ ለማሳመንና…
→ክፍል አራት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
②/ የዝሙት አካላዊ ጉዳቶች

«ኵራትን ብንወስድ መለኮታዊ ወንጀል ነው፡፡ ምቀኝነት ሰይጣናዊ ወንጀል ነው፡፡ ደም ማፍሰስ እውሬያዊ ወንጀል ነው፡፡ ዝሙት እንስሳዊ ወንጀል ሲሆን የወሲብን አስፈልጎት ለማርካት ሲባል የሚፈጸም ኃጢአት ነው፡፡ እናም ዝሙት በዚህ ባህሪው አካልን የመጉዳት ተጽዕኖው ወደር የለውም፡፡» (ታላቁ ሊቅኢማም ኢብኑል ቀይም)

«ወንጀሎች ሁሉ እንደ በሽታ ሲሆኑ መፈወስ ያለባቸውም እንደየ ዓይነታቸው ነው፡፡»

በዝሙት አካላዊ ጉዳቶች ሥር አራት አበይት የዝሙት ጉዳቶች ይብራራሉ፡፡ እነርሱም የዝሙተኛው ሰውነት መዳከም፣ ከዚና የተነሳ የበረካ መነሳትና መጥፋት፣ በዚና የተነሳ በሐላል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ውስጥ ለመሳተፍ የፍላጎት እጦት እና ምናልባትም ለዝሙት ሱሰኛ መሆን አልያም የሴሰኝነት በሽታ መከሰት ናቸው፡፡❗️

↠ሀ/ ዝሙት ግለሰቡን በአካል ደካማ ያደርገዋል።❗️

እንዲሁ በተለምዶ ሕጋዊ የሆኑ ወሲባዊ ድርጊቶች እንኳን ወንዱንም ሆነ ሴቷን የሰው ዘር ሁሉ በአካል እንደሚያዳክሙ ይታወቃል፡፡ ያ እንዳለ ሆኖ፣ ዝሙት
ከሌብነት አይለይም የሚለውን እውነታ ስናከልበት ደግሞ ዝሙተኛው የበለጠ የመዳከም ዕድል አለው፡፡ አንድ የጌጣጌጥ ቦታን ሰብሮ ለመግባት የቻለ ሌባ በዚህ
ድርጊቱ «ወርቃማ ዕድልን እንዳገኘ ያውቃል፡፡ ይህም በተራው እርሱ የግድ መጠቀም ያለበት ምርጥ አጋጣሚ ስለሆነ የሚችለውን ያህል እንዲሰርቅ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ እርሱ የሚችለውን ያህል ጌጣጌጥ ተሸክሞ እንደሚሄድ ግልጽ ነው፡፡

ልክ እንደዚሁ ዝሙት ሠሪውም ድርጊቱን በሚፈጽምበት ጊዜ ያቺን ከርሱ ጋር ዚና የምትሠራውን ሴት ለተመሳሳይ ድርጊት ዳግም ላያገኛት እንደሚችል ያውቃል፡፡ ሌላው ቢቀር በማንኛውም አስቸኳይ በሆነበት ወቅት አያገኛትም፡፡ ስለዚህ እርሱ አዕምሮውን አስቀድሞ ፕሮግራም ያደርገዋል፤ በተገኘው የዝሙት አጋጣሚ የሚችለውን ያህል በርካታ ዙር ለመሄድ፡፡ እናም ይህ የክብርና የድንግልና ሌባ የሆነው ዝሙተኛ በርካታ ዙሮችን ለመሄድ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ በውጤቱም ወሲባዊ ኃይሉን አሟጦ ይጠቀምበታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ዮዝሙተኛው አካል ይዳከማል፤ ወሲባዊ ኃይሉም ይቀንሳል፡፡ ታዲያ ይህ ዝሙተኛ ግለሰብ ሕጋዊ የወሲብ አጋር(ትዳር)ካለው እርሷን ገብቶ እንደ እንግዳ ሰው ማየት ይጀምራል፡፡ ሴቷ ዝሙተኛም ባሏን እንደ እንግዳ ማየትና መያዝ ትጀምራለች፡፡ ሁለቱም በየፊናቸው ከሕጋዊ የወሲብ አጋሮቻቸው ጋር ዳግም ወሲብን ለመፈጸም ስሜቱም ሆነ አቅሙ አይራቸውም፡፡ ፍላጎታቸውም ይቀንሳል፡፡

በሌላ አነጋገር ሕጋዊ የወሲብ አጋሮች በሚሄዱት ዙር መካከለኞች ናቸው፡፡ ይህም ሆኖ ሳለ እካላቸው ይዳከማል፡፡ ዝሙተኞች(ሕገወጥ የወሲብ አጋሮች)ግን በሚሄዱት ዙር ከልክ ያልፋሉ፤ ምክንያቱም ድርጊታቸው ስርቆት ነውና፡፡ ከዚህም የተነሳ አካላቸው የበለጠ ይዳከማል፡፡ ይህ አካላዊ መዳከምም ሁለቱንም ወንዱንም ሴቷንም ይጎዳቸዋል፡፡ የነርሱ ምርታማነት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል፡፡ የነርሱን ማህበራዊ ትስስርም ይጎዳል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ዝሙተኞቹ በአምልኮ ተግባሮቻቸው ላይ ይውላሉ፤ ይንሸራተታሉ፡፡ ይህም የነርሱን መንፈሳዊ ኃይል በማዳከም ምርታማነታቸውን የበለጠ ይቀንሳል፡፡


ዝሙት ኢኮኖሚን ያቃውሳል፤ ከገቢ ላይም በረካን ያነሳል

ኢንሻ አላህ በክፍል አራት👆👆ይዤላችሁ እመጣለሁ።


ዝሙት ምን ያክል እንደተስፋፋ ሁላችንም እናውቃለን። መስፋፋቱ የማያሳስበው ይኖራል ብየ አላስብም ምን አልባት ስለ እምነቱ ምንም ስሜት የሌለው ሰው ካልሆነ በቀር።
👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።


ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል አራት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ②/ የዝሙት አካላዊ ጉዳቶች «ኵራትን ብንወስድ መለኮታዊ ወንጀል ነው፡፡ ምቀኝነት ሰይጣናዊ ወንጀል ነው፡፡ ደም ማፍሰስ እውሬያዊ ወንጀል ነው፡፡ ዝሙት እንስሳዊ ወንጀል ሲሆን የወሲብን አስፈልጎት ለማርካት ሲባል የሚፈጸም ኃጢአት ነው፡፡ እናም ዝሙት በዚህ ባህሪው አካልን የመጉዳት ተጽዕኖው ወደር የለውም፡፡» (ታላቁ ሊቅኢማም ኢብኑል…
→ክፍል አምስት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
↠ለ/ ዝሙት ኢኮኖሚን ያቃውሳል፤ ከገቢ ላይም በረካን ያነሳል

«… አንዳንዱ የጫት ሱስ አለው፡፡ አንዳንዱ የመጠጥ ሱስ አለው፡፡ አንዳንዱ የወሲብ ሱስ አለው፡፡ አንዳንዱ የምግብ ሱስ አለው፡፡ ዝም ብሎ መብላት በራሱ ችግር ነው፡፡ ወሲብ ሰዓቱን ጠብቆ መደረግ ያለበት ነው፡፡ ያለሰዓት፣ በተገኘው አቅጣጫ ሁሉ የሚነጉድ ከሆነ ቤት የተቀመጠችዋንም ይጎዳል፡፡ አልጋ ሲይዝ፣ አብሯት የምትወጣውን ሲያበላ፣ ሲያጠጣ፣ በየቦታው ሲሄድ ኢኮኖሚው ይጎዳል ብቻ ሳይሆን ሥራም አይሠራም፡፡ ለከፍተኛ ውድቀት ይዳርጋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ አይበረታታም፡፡»

አንድ ዝሙተኛ ለዝሙት ሲሄድ በርካታ የሥራ ሰዓቱን ያቃጥላል፡፡ ከሥራውም ላይ ይፈናቀላል፡፡ በዚህን ጊዜ ሥራው ላይ ቢሆን ኖሮ ሊያገኝ የነበረው ረድኤትና በረካ ያመልጠዋል፡፡ አምላካዊ ቁጣንም ያተረፈ ሆኖ ይመለሳል፡፡ አምላካዊ ቁጣን የወረሰ ሰው ደግሞ ረዳት የለሽና ደካማ ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ ግለሰቡ በዝሙት ላይ በርካታ ዙሮችን ስለሚሄድ አካሉም ተዳክሞና እራሱን እየጎተተ ወደ ሥራው ይመለሳል፡፡ ይህም ይበልጥ ገቢውን ይቀንስበታል፡፡

ማንኛውም ግለሰብ የዝሙትን ሂደት ለማመቻቸት የሚያወጣው ነገር ሁሉ ሐራም ነው፡፡ ድርጊቱን መፈጸም በራሱ አንድ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡ ገንዘብን በዚህ
እኩይ ድርጊት ላይ ወጪ ማድረግም ሌላው ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ እናም ዝሙት ሠሪው ይህንን ሁሉ ወንጀሉን ተሸክሞት ቁጭ ይላል፡፡ እንደሚታወቀው የኣደም ልጅ ሁሉ በቂያም ቀን ከሚጠየቅባቸው አራት መሠረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ገንዘቡን እንዴት እንዳገኘውና ከምን ላይ እንዳዋለው ነው፡፡ እርሱም ለዚህ ሁሉ ምላሽ ሳይሰጥ ከመቆሚያ ስፍራው እግሮቹን ማነቃነቅ አይችልም፡፡ ይህም የዚያ በዝሙት ላይ ገንዘቡን የሚያወጣው ግለሰብ ሁኔታ ነው፡፡ በእውነቱ ይህ ከባድ ነው፡፡ ታዲያ እርሱ ያ ከዚና ገቢን የሚያገኝ ወይም ድርጅቱን የሚያንቀሳቅስበት፣ በአካል ወይም በኦንላይን ዝሙትን የሚያመቻች ግለሰብ ሁኔታ ምንኛ ሊከፋ ይችላል? እርሱ ያ ለዝሙት ቢዝነስ ሙያዊ ግልጋሎቶችን የሚያቀርብስ ምን ሊሆን ነው? የወሲብ ደላላውና አቃጣሪውስ? የነርሱ ገቢ ሐራም ከመሆኑም ባሻገር እነርሱ ከደንበኞቻቸው ኃጢአት ሁሉ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ በማንኛውም ሰዓት ማንም ሰው የነርሱን አገልግሎት በመጠቀም ዝሙትን ከፈጸመ እነርሱም የወንጀሉ ተጋሪዎች ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም በወሲብ ንግድ ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች ቤተሰቦቻቸውን በሐራም ገቢ ለማስተዳደር ይገደዳሉ፡፡ ልጆቻቸውም የወላጆቻቸውን ሙያ ቀርጸው የማደግና ቢዝነሱን የመረከብ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ግለሰቡንና ቤተሰቡን የማይወጡበት የኃጢአት ቀለበት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ የኃጢአቱ ጥላም በረጅሙ ያጠልባቸዋል፡፡

 👉ይ ቀ ጥ ላ ል👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇
↠ሐ/ ግለሰቡ ለሐላል ወሲብ ያለው ፍላጎት በዝሙት ምክንያት ይቀንስበታል።

👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።


ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል ስድስት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

↠ሐ/ ግለሰቡ ለሐላል ወሲብ ያለው ፍላጎት በዝሙት ሳቢያ ይቀንስበታል።

ከዝሙት ፈጣን ጐዳቶች መካከል አንዱና ግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው ዝምተኛው ከሕጋዊ የወሲብ አጋሩ ጋር ወሲብን የመፈጸም ፍላጎቱ ቀንሶበት መግኘቱ ነው፡፡ አዎ! በዝሙት ውስጥ የሚዘፈቁ ግለሰቦች ከራሳቸው ሕጋዊ የወሲብ አጋሮች ጋር የፍላጎት እጦት ትግል ውስጥ እንደሚገቡ በግልጽ የታወቀ እውነታ ነው፡፡ ማንም አመንዝራም የዚህ ሰለባ ከመሆን አያመልጥም፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ሁለቱም በየፊናቸው በሐራም ድርጊት ውስጥ በሚያባከኑት የበዛ ኃይል ምክንያት ነው፡፡ ዝምተኛው ወሲባዊ ፍላጎቱንና በተለይ ወሲባዊ ኃይሉን በዝሙት ላይ አፍሶ ስለሚመለስ ከዚህ ወዲያ አካሉም ይዳከማል፤ ስሜቱም ይቀንሳል። እብዛኛው ኃይሉ በዝሙት መንገድ ስለፈሰሰ ከዚህ ወዲያ ለሕጋዊ ወሲብ የሚያውለው እምብዛም ፍላጎትና ኃይል አይኖረውም፡፡ እራሱን ጎትቶ እቤት ከገባም አንድ ነገር ነው፡፡

አንድን ባል ወደ ዝሙት የሚገፋፋው የአጅነቢ ሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ በርሱ ሕጋዊ የወሲብ አጋር ዘንድ ላይታይ ይችላል። በዚህን ጊዜ ባልየው በዝሙት ማጥመጃ ውስጥ የበለጠ ይዘፈቅና ለሕጋዊ አጋሩ ፍላጎትን እያጣ ይመጣል፡፡ ከዚህም የተነሳ በርካታ የቤት ውስጥ ችግሮች ብቅ ብቅ ይላሉ፡ ይህም በተራው በርካታ ትዳሮችን ለማናጋትና ለማፍረስ ይመራል። ጃቢር ቢን ዐብዱሏህ (ረድየላሁ ዐንሁ) ባወሩት ሐዲሥ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-

↝ሴት ከቤት እንድትወጣ (ምትገፋፋው) እና እቀባበልን የሚያደርግላት ሸይጧን ነው። እናም ከናንተ አንዳችሁ ሴትን በሚያይበት ጊዜ እርሱ ወደሚስቱ ይመለስና ከሚስቱ ዘንድም እሷ ያላትን ተመሳሳዩን ነገር ያግኝ፤ ምክንያቱም ያ እርሱን በልቡ ውስጥ የሚሰማውን ነገር ይገፍለታልና፡፡» (ቡኻሪና ሙስሊም)

መልዕክተኛው (ﷺ) በሌላም ሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡-

↝ሴት አውራህ ናት፡፡ ወደውጭ በምትወጣበት ጊዜ ሸይጧን ያጎላታል።» (እት ቲርሚዚ፡ ኢብን ሂብባን እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል)

ሴቶች በተፈጥሮ ለወንዶች የተዋቡ ናቸው፡፡ ሸይጣን ደግሞ ከቤታቸው የሚወጡትን ሴቶች በሁለት እጆቹ ተቀብሏቸው ሲያበቃ ወንዶችን የበለጠ በነርሱ አድርጎ ይፈታተናቸዋል፡፡ ስለዚህ ግለሰቡ ለርሱ ሕጋዊ ባልሆነች ሴት ድንገት ከተሳበ እርሱ ወደቤቱ መመለስና ከሕጋዊ ሚስቱ እርካታውን ማግኘት አለበት፡፡ እነዚያ ያንን እርካታ ከነዚያ በየመንገዱ ከሚያዩዋቸው እንስቶች ለማግኘት የሚሹት ግን እነርሱ ሕጋዊ ሚስቶቻቸውን በሚገናኙበት ጊዜ ያንን እርካታ ማግኘት አይችሉም፡፡

↠መ/ ዝሙት በግለሰቡ ላይ ሱስ ሊሆንበት ይችላል።

በተለምዶ «የተከለከለ ነገር ተፈላጊ ነው» ሲባል እንሰማለን፡፡ ዝሙትም ከዚህ ውጭ አይሆንም፡፡ አንድ ሰው በተደጋጋሚ ዝሙት ላይ ከወደቀ እርሱም ለዚያ ነገር ሱሰኛ እየሆነ ይመጣል፡፡ የዝሙት ሱሰኝነትም ወደ ሴሰኝነት(ልክስክስነት)ይቀየራል፡፡ ሴሰኛ ግለሰብም መወሰንና ወሲባዊ ስሜቱን በሕጋዊ መንገድ ማርካት ይሳነዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ዝሙት ለግለሰቡ እርካታን ሰጥቶታል ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ልክ የወሲብ ፊልምን የመመልከት ሱስ ያለበት ሰው ፊልሙን ካላየ ፋታን እንደማያገኝ ሁሉ ሴሰኛ ሰውም እዚያም እዚህም ካልተልከሰከሰ ፋታን አያገኝም ማለት ነው፡፡ እርሱም እርካታዬን ከዚህ ነው የማገኘው በሚል ይታለላል፡፡ ዝሙትን የበለጠ በሠራ ቁጥርም የበለጠ ከርሱ መልሶ ይፈልጋል፡፡ ዝሙትን የበለጠ በፈለገው ቁጥርም ግለሰቡ የሚያገኘው እርካታም የበለጠ አነስተኛ እየሆነበት ይሄዳል፡፡ ከዚያም ቀጣይነት ያለው ሱስ ይሆንበታል፡፡

👉ይ ቀ ጣ ላ ል👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ ክፍል
👉የዝሙት ማህበራዊ ጉዳቶች በሚል ርዐስ እንመካከራለን።

#በዱዓችሁ_አትርሱኝ

አሰተያየት ጥያቄ ወይም ከዝሙት መውጣት ፈልጋችሁ እንዴት መውጣት እችላለው ካላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ተመካከረን እንፈታዋለን። በአላህ ፍቃድ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው። inbox👇
👉@Jezakellah @Jezakellah



👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።

ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል ሰባት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
↝ የዝሙት ማህበራዊ ጉዳቶች

የዝሙትን ማህበራዊ ጉዳቶችን በተመለከተ በዚህ ርዕስ ሥር አምስት ጉዳቶች ይብራራሉ፡፡ እነርሱም መጥፎ አርአያ መሆን፣ የቤተሰብ ማፈሪያ መሆን፣ ውርጃ፣
የጎዳና ልጆችን ማፍራት እና የፍቺ መጠን ከፍ ማለት ናቸው፡፡

↠ሀ/ ዝሙት ሠሪው ለሌሎች መጥፎ አርአያ ይሆናል

አንድ ሰው ምን ያህል በርሱ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖን እንደሚያደሳድር ላያውቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን እውነታው፣ ማንም ሰው በዙሪያው ባሉት ሰዎች ላይ ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተጽዕኖን ያሳድራል፡፡ ምክንያቱም በማህበረሰቡ መካከል ያሉ ልጆችና አዳጊዎች ሮል ሞዴላቸውን የሚሠሩት በዙሪያቸው ካሉት ጎልማሶች ነውና፡፡ ከጎልማሶች መካከል የተወሰኑት መልካም ነገሮችን በመሥራት መልካም አርአያ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ጸያፍ ነገሮችን በመሥራት መጥፎ አርአያ ይሆናሉ፡፡ሁለቱም ወገኖች ግን በተለያዩ ልጆችና አዳጊዎች ተከበዋል፡፡ ልጆቹም ለየትኛው ወገን የበለጠ ቅርብ በሚሆኑት ላይ ተመሥርቶ ተጽዕኖ ያድርባቸዋል፤ ጫናም ውስጥ ይገባሉ፡፡ ልጅን ለማሳደግ መንደሩ ሁሉ እንደሚያስፈልግ እሙን ነው፡፡ እናም ዝሙተኛው በርሱ ጸያፍ ድርጊት ለመንደሩ ልጆችና አዳጊዎች መጥፎ አርአያ ሆኖ የመገኘት ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡!

በተለይ ዝሙተኛው ለቤተሰቡ አባላት መጥፎ አርአያ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ የግለሰቡ የዝሙት ድርጊት በቤተሰቡ ዘንድ ባይታወቅ እንኳን የግለሰቡ ንግግር እርሱን ከመግለጽ ወደኋላ አይልምና፡፡ ያካበተው የብልግና ልምድ እርሱን ይፋ ከማውጣት አይቆጠብም፡፡ ግለሰቡ መልካም ጓደኞችንም አይዝም፡፡ ለቤተሰቡ የሚያስተላልፈው መልካም ነገርም አይኖረውም፡፡ ቤተሰቡን ከዝሙት ማስጠንቀቅ አይችልም፡፡ እንዴት ነው አንድ ዝሙተኛ ሰው የገዛ ልጁን ከዝሙት ጉዳቶችና ጠንቆች መምከርና ማስጠንቀቅ የሚችለው? ቤተሰብን ከመስበክ ይልቅ በተግባር መምራት የበለጠ ተጽዕኖን ያሳድራል፤ የበለጠም ውጤታማ ነው፡፡ የዝሙት ሱሰኛ (ሴሰኛ ደግሞ እራሱን መደበቅ አይችልም፡፡ ከዚህም የተነሳ መላው ቤተሰብ የርሱን ድርጊት ያውቃል፡፡ እርሱም ለነርሱ መጥፎ አርአያ ይሆናል፡፡

👉ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
ለራስ ቤተሰብ ማፈሪያና ውርደት ስለመሆኑ እንመካከራለን።

👉በዱዓችሁ አግዙኝ


አሰተያየት ጥያቄ ወይም ከዝሙት መውጣት ፈልጋችሁ እንዴት መውጣት እችላለው ካላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ተመካከረን እንፈታዋለን። በአላህ ፍቃድ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው። inbox👇
👉@Jezakellah @Jezakellah


👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ እና ሃ
ላፊነት ሚሰማችሁ ከሆነ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።!

👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።

ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል ሰባት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ↝ የዝሙት ማህበራዊ ጉዳቶች የዝሙትን ማህበራዊ ጉዳቶችን በተመለከተ በዚህ ርዕስ ሥር አምስት ጉዳቶች ይብራራሉ፡፡ እነርሱም መጥፎ አርአያ መሆን፣ የቤተሰብ ማፈሪያ መሆን፣ ውርጃ፣ የጎዳና ልጆችን ማፍራት እና የፍቺ መጠን ከፍ ማለት ናቸው፡፡ ↠ሀ/ ዝሙት ሠሪው ለሌሎች መጥፎ አርአያ ይሆናል አንድ ሰው ምን ያህል በርሱ ዙሪያ…
→ክፍል ስምንት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
↠ለ/ ለራስ ቤተሰብ ማፈሪያና ውርደት መሆን

አንድ ሰው በማንኛውም አዋራጅ ድርጊት ውስጥ በሚዘፈቅበት ጊዜ በትንሹ በዙሪያው ያሉ አምስት ዓይነት ሰዎች የመሸማቀቅ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ እነዚህ
አዋራጅ ድርጊቶችም ሙስና፣ ስርቆት፣ ብልግና እና ማንኛውም ዓይነት ኢሞራላዊ ጥፋቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚያ በግለሰቡ ጸያፍ ድርጊት ሳቢያ የሚዋረዱና
የሚሸማቀቁ አምስት ዓይነት ሰዎችም ወላጆቹ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹ፣ የቅርብ ዘመዶቹና ጓደኞቹ ናቸው፡፡ በተጨማሪነትም ጎረቤቶቹ፣ ሌሎችም እርሱን የሚወዱትና በቅርበት የሚያውቁት ሰዎችም መሸማቀቃቸው አይቀርም፡፡

በአብዛኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ግለሰቡ እነዚህን አምስት አካላት በሙሉ ወይም ከፊሎቹን በሕይወቱ ውስጥ እጅጉን አስፈላጊ የሆኑ ሰዎች አድርጎ ያያቸዋል፡፡ ይህም እነርሱ በግለሰቡ መላው ሕይወት ውስጥ የጥንካሬው ማዕዘናት እንደሆኑ ያስረዳል፡፡ እናም የነርሱ መኖር ግለሰቡ በሕይወቱ ውስጥ በሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ላይ ከባድ ተጽዕኖ አለው፡፡ እነዚህም አካላት በግለሰቡ ጨዋነትም ሆነ ብልግና ሳቢያ ከባድ ተጽዕኖ ይደርስባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ግለሰቡ በጨዋነት ወደተቀደሰው ጋብቻ ሲያመራ የርሱ የቅርብ ተጠሪዎች፣ ረዳቶች፣ ደጀኖችና ምስክሮች እነዚሁ ሰዎች ናቸው፡፡ በዚህን ጊዜ በዚህ ቅዱስ ተግባር የበለጠ የሚኮሩበትም ራሳቸው ናቸው፡፡ የሠርጉን ሂደት የሚያቀለጣጥፉትና ምቹ አካባቢን የሚፈጥሩትምና ለትዳሩ ስኬት ትልቁን ሚና የሚጫወቱትም እነዚሁ ናቸው፡፡ ግለሰቡ ላይ ማንኛውም ችግር ቢደርስበት፣ በትዳር ሕይወቱ ላይ አደጋ ቢጋረጥበትና ብሎም ግለሰቡ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ችግር ቀድመው የሚደርሱለትና የሚከላከሉለት እነዚሁ ናቸው፡፡ ግለሰቡ ወልዶ ለመሳምና ለመክበድ የበቃ እንደሆነም በርሱ ልጆች ላይ ትልቅ ተጽዕኖን የሚያሳድሩት እነዚሁ አካላት ናቸው፤ ምክንያቱም ልጆቹ በነዚህ አካላት የተከበቡ ናቸውና፡፡

ይህም በመሆኑ እነዚህ ሰዎች እነዚያ አብዛኞቻችን የርሱ የጥንካሬው ማዕዘናት ብለን የምናያቸው ናቸው፡፡ ታዲያ እነርሱም ግለሰቡ ጋብቻን ትቶ ወይም የጋብቻ ቃልኪዳንን አፍርሶ ዝሙትን ሲመርጥ ፈጽሞ አይቀበሉትም፤ እነርሱም በዝሙት ባህል ውስጥ ያደጉ ካልሆኑ በስተቀር፡፡ እናም የነርሱ ተወዳጅ ሰው በዝሙት ላይ መውደቁን ሲያውቁና ሌሎችም ባወቁት ጊዜ እነርሱ የውርደቱ ተሸካሚዎች ይሆናሉ፡፡ እናም ወደድንም ጠላንም፤ አንድ ግለሰብ በተለይ በዝሙት ሱሰኛ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች በትንሹ በርሱ ማፈራቸው አይቀርም፡፡ ይህም ዝሙት ምን ያህል ማህበራዊ ጉዳትን እንደሚያስከትል አንዱ ማሳያ ነው፡፡


👉ይ ቀ ጥ ላ ል👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ
ዝሙት ንጹሕ ነፍስን ለመግደል(ለውርጃ)ይመራል በሚል ርዕስ ይጠብቁን።

👉በዱዓችሁ አግዙኝ


አሰተያየት ጥያቄ ወይም ከዝሙት መውጣት ፈልጋችሁ እንዴት መውጣት እችላለው ካላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ተመካከረን እንፈታዋለን። በአላህ ፍቃድ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው። inbox👇
👉@Jezakellah @Jezakellah


👉አንተ 👉አንቺ ዝሙትን ከሚቃወሙት ከሆኑ እና ሃ
ላፊነት ሚሰማችሁ ከሆነ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ላሉት ጓደኞቻቹሁ እንደምትልኩላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።!

👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።

ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል ዘጠኝ←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️


↠ሐ/ዝሙት ንጹሕ ነፍስን ለመግደል(ለውርጃ) ይመራል።

ወሲብ የሰው ልጅ የሚራባበትና የሚተካካበት መንገድ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነቱ ሐራምም ይሁን ሐላል የጽንሰትና የመዋለድ ሂደቱ ይካሄዳል፡፡ እናም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ተከትሎ ጽንሰት ይፈጠራል፡፡ ሕጋዊ ጥንዶች ደግሞ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ከፈጸሙ በኋላ የሚፈጠረውን ጽንስ ለማስወረድ ሲታገሉ ማየት አልተለመደም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሕገወጥ ጥንዶችም ዝሙትን ፈጽመው ሲያበቁ በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን ጽንስ እንዲወለድ ሲፈቅዱ ማየት አልተለመደም፡፡ በተቃራኒው ለማስወረድ ሲጣደፉ ነው የሚታዩት፡፡ ያንን የሕይወት እስትንፋስ የተነፋበትን ጽንስ ማስወረድ ደግሞ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ማጥፋት ነው፡፡ ንጹሕን ነፍስ መግደል ደግሞ በኢስላም ከባድ ወንጀል ነው። ከሺርክ(ባዕድ አምልኮ) ቀጥሎም አውዳሚ ወንጀል ተብሎ የተቀመጠው ይሄው ነው። ከዚህም የምንረዳው ዝሙትን ተከትሎ የሚመጣው ውርጃ ጥንዶቹን ቢያንስ ሁለት ታላላቅ ኃጢአቶች ውስጥ ይከታቸዋል -የዝሙት ድርጊቱ አንዱ ነው። ንጹሕን ነፍስ በውርጃ አማካኝነት መግደሉ ሌላው ነው፡፡ በተለይ ሴቷ ሁለቱንም ወንጀሎች ተሽክማ የመቅረት ዕድሏ ከፍ ያለ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱም ኃጢአት ከሺርክ ቀጥሎ በሁለተኛና በሦስተ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡!

↠መ/ ዝሙት ያልተፈለጉ ልጆችን በጎዳና ላይ ይበትናቸዋል።

ዝሙት በወግ አጥባቂም ሆነ በሌላው ማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ፈርጀ ብዙ ነው፡፡ በእውነቱ የዝሙት ጉዳትና መዘዝ ቁጥር ስፍር የለውም፡፡
ለዚህም ነው ሁሉን ዐዋቂው አምላካችን አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)«ዝሙትን አትቅረቡ» ሲል እንደ ከፍተኛ ኤሌክቲሪክ ቮልቴጅ ከሩቁ ያስጠነቀቀው፡፡ ዝሙተኛው ባልተፈቀደለት ማሕፀን ውስጥ የሚረጨው የዘር ፈሳሹ ወደ ጽንሰት ይለወጣል፡፡ አንዴ ጽንሰቱ ከተከሰተ ከዚያም አዲስ ሰብአዊ ፍጡር ይጠበቃል፡፡

በዝሙት ሂደት ውስጥ ጽንሰት የመከሰቱ ዕድል ሁሌም እንዳለ ነው፡፡ ጥንዶቹ የፈለጉትን ያህል ጥንቃቄ ቢያደርጉም የአላህን ሕግ ግን ፈጽሞ መቀየር
አይችሉምና፡፡ ባሴሩ ቁጥርም አላህም ሴራቸውን ይመልስባቸዋልና፡፡ እናም ማንኛዋም ሴት እርግዝናን መቶ በመቶ መከላከል አትችልም፡፡ በተራቀቀ ቴክኖሎጂ የተመረቱ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችም ሲሆኑ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ እንኳን ማክሲማም ከ98% በላይ መከላከል አይችሉም፡፡ በዚህ ላይ በስሜት መሸነፍ፣ መሳሳት፣ መግደድና ስካርም አለ፡፡

ከጋብቻ እልጋ ውጭ የሚወለዱ ሕፃናት ተገቢውን እነጻና በቂ ትምህርት ማግኘት አይችሉም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሲያድጉም ለማህበረሰቡ ጠንቅ ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ መካከል የተወሰኑት(ብዙዎቹ ባይሆኑ እንኳን) ወደ ጎዳና የመውጣት ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ከነዚህ የጎዳና ልጆች መካከል አብዛኞቹ ለዝሙት፣ ለግብረ ሰዶማዊነት፣ ለልዩ ልዩ ደባል ሱሶች፣ ለአስገድዶ መድፈርና ለሌሎችም ወንጀሎች የተጋለጡ ናቸው፡፡ በዚህም ማህበራዊ ችግሮችን ይበልጡኑ ያባብሱታል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በዚያው እነርሱ በተወለዱበት መንገድ ተመሳሳይ የችግር ቀለበት ውስጥ በመግባት ይዋለዳሉ፡፡ ልክ እነርሱም ኃላፊነት በጎደለው መንገድ እንደተወለዱ ሁሉ እነርሱም ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ይዋለዳሉ፡፡ በዚህም በነርሱ ትውልድ ላይ የማንነት ውድቀት ሁሉ ይከሰታል፡፡ ይህም ቀስ በቀስ የማህበረሰቡን ማንነት ሁሉ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል፡፡!

👉ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
ዝሙት የፍቺን መጠንን ከፍ ያደርገዋል በሚል እንመካከራለን።

👉በዱዓችሁ አግዙኝ


👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።

ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል አስር←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

↠ሠ/ ዝሙት የፍቺ መጠንን ከፍ ያደርገዋል

«ምንዝርነት ለሺህ ትዳሮች መፍረስ ትልቁ ምክንያት ነው፡፡»!

ወሲብ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የሚያሳካው ዋና ዓላማና ግብ አለው፡፡ ለተቀደሰው ጋብቻ መመሥረትም ወሲብ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ አንድ ቤተሰብ በፍቅር መሠረት ላይ እንዲገነባም ወሲብ የሚጫወተው ሚና ቀላል አይደለም፡፡ በአጭሩ የጥንዶች የጋራ ዓላማ ከወሲብ ይፈነጥቃል ማለት ይቻላል፡፡ ምንም እንኳን ወሲብ በጋብቻ ሕይወት ውስጥ እጅግ አነስተኛ የሆነውን አኃዝ ሲይዝም ግና በጥንዶቹ መካከል ጉድኝቱ፣ ሞሳሳቡ፣ ትስስሩ፣ቁርኝቱ፣ ወዳጅነቱና ፍቅሩ እንዲዳብር ቅመም በመሆን የሚያገለግለው ወሲብ ነው፡፡ በጥንዶቹ መካከል ፍቅር፣ አብሮነት፣ የመተዛዘንና የመተሳሰብ ሁኔታዎች የሚመነጩት በዚህ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በሚፈጸመው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላይ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም እንደተጠቀሰው አንድ ግለሰብ ወሲብን በዝሙት በኩል የሚፈልግ ከሆነ እርሱ ሕጋዊ ሚስቱን በሚገናኝበት ጊዜ የወሲብ ፍላጎቱ ወርዶበት ያገኘዋል፡፡ ወሲባዊ ፍላጎቱንና ኃይሉን በስርቆት ባገኘው የዝሙት ድርጊት ላይ አብዝቶ ስለሚያፈሰው ዝሙተኛ ባል ለሕጋዊ ሚስቱ የሚኖረው ፍላጎት፣ እንዲሁም ዝሙተኛ ሚስት ለሕጋዊ ባሏ የሚኖራት ፍላጎት ያለ ምንም ጥርጥር ይቀንሳል፡፡ በስርቆት በተፈጸመው ወሲብ ላይ ብዙ ዙሮችን ስለሚሄዱ ለሕጋዊ ወሲብ የሚቀራቸው ኃይል አነስተኛ ሆኖ ያግኙታል፡፡ ይህ ፍላጎት በቀነሰበት አግባብ ውስጥ ደግሞ ጥንዶቹ አንዱ ከሌላው የሚፈልገውን ስሜታዊ እገዛዎችን በሚፈለገው መጠን አያገኙትም፡፡ የትዳር ሕይወት ቅመሙ ወሲብ እንደመሆኑ መጠን የወሲባዊ ፍላጎት መቀነስ ትዳሩን ያናጋዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ዝሙተኛው ወገን ሕጋዊ አጋሩን እንደ እንግዳ ማየት ይጀምራል፡፡ ባልም ሚስቱን የሳሎን ቤት ዕቃ አድርጎ ያያታል፡፡ እንደ እንግዳ ኢንተራክት ይደራረጋሉ፡፡ እንግዳ ደግሞ የፈለገውን ያህል ቢሰነባብት መለየቱ አይቀርም፡፡ እናም የኋላ ኋላ ጥንዶቹ ጣሪያ መጋራታቸውን ይቋጫሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እነዚያ እስከ ጋብቻ ድረስ ወሲብን በዝሙት በኩል ከማድረግ የሚታቀቡ ጥንዶች ከነዚያ እንዲህ ከሚያደርጉት ይበልጥ ማራኪ የወሲብ ሕይወት አላቸው፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ ዝሙት ምን ያህል በትዳር ሕይወት ላይ የእርካታ መቀነስን እንደሚያስከትል ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ወሲብ ለጥንዶቹ ቁርኝት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ እንደዚሁም በጥናቶች እንደተረጋገጠው እነዚያ ድንግል ሆነው የተጋቡ ጥንዶች ከነዚያ ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው ከሚጋቡ ጥንዶች ያነሰ የፍቺ መጠን አላቸው፡፡ በጥቅሉ ከትዳር አጋሮች መካከል አንዱም በዝሙት ላይ ከወደቀ ከዚያም በትንሹ እርሱ ለሕጋዊ አጋሩ የሚኖረው ፍላጎት ይቀንስበታል፡፡ ይህም በተራው የሚስትን ወሲባዊ ሕይወት ይጎዳዋል፡፡ እርሷም ፍላጎቷ የማይጠበቅላት ከሆነ ትዳሩ ይመራታል፤ ቅመሙ የለምና፡፡ እናም የሰማይን ያክል እሩቅ መስሎ ሲታይ የነበረው ፍቺ በዝሙት ሳቢያ ቅርብ ሆኖ ይሰየማል፡፡

👉ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉 ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
ከጤንነት ጋር የተያያዙ የዝሙት ጉዳቶች በሚል እንመካከራለን።

👉በዱዓችሁ አግዙኝ


👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።

👇👉ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል አስር← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ↠ሠ/ ዝሙት የፍቺ መጠንን ከፍ ያደርገዋል «ምንዝርነት ለሺህ ትዳሮች መፍረስ ትልቁ ምክንያት ነው፡፡»! ወሲብ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የሚያሳካው ዋና ዓላማና ግብ አለው፡፡ ለተቀደሰው ጋብቻ መመሥረትም ወሲብ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ አንድ ቤተሰብ በፍቅር መሠረት ላይ እንዲገነባም ወሲብ የሚጫወተው ሚና…
→ክፍል አስራ አንድ←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

④/↝ከጤንነት ጋር የተያያዙ የዝሙት ጉዳቶች↜

ወደ ጤና ጉዳይ ስንመጣ፣ ዝሙት በፈፃሚዎች ላይ በርካታ ጤና ነክ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)የርሱን ድንበር በማለፍ በጸያፍ ድርጊቶች ውስጥ የሚሳተፉትን ግለሰቦች በተለያዩ በሽታዎች ይቀጣቸዋል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ በሽታዎች ወጥነት አይደሉም፤ ይልቁንም ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ይለያያሉ፡፡ እናም አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ዝሙተኛውን ግለሰብ በፈለገው በሽታ ሊቀጣው ይችላል፡፡ አልያም በሽታ ሳያመጣበት በሌላ መንገድ ሊቀጣው ይችላል፡፡

በርካታ የአባላዘር በሽታዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ እንደ ኤች.አይቪ/ኤድስ፣ ሄፓፓታይስ(የጉበት መቆጣት)፣ ጨብጥና ቅጢኝ ያሉትን በሽታዎች ብንመለከት በርካታ ሰዎችን እንዳጠቁና እንደፈጁ ያደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በርግጥ በነዚህ በሽታዎች የተጠቃ ሰው ሁሉ ዝሙትን ፈጽሟል ብለን መደምደም አንችልም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ጥቂት ሰዎች ምንም እንኳን ዝሙት ላይ ፈጽሞ ባይወድቁም በተወሰኑ የአባላዘር በሽታዎች ግን ሊጠቁ ይችላሉና ነው፡፡ ግና ከሞላ ጎደል ዝሙተኞች በነዚህ በሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡

በሌላ በኩል ሁሉም ዝሙተኛ በነዚህ የአባላዘር በሽታዎች ላይጠቃ ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የለየላቸውን ሴሰኞች ብንወሰድ በኤችአይቪ/ኤድስም ሆነ በሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ሳይጠቁ ሰርክ ሲልከሰከሱ ይታያሉ፡፡ ከዚህም የምንረዳው ሁሉም ዝሙተኛ በአባላዘር በሽታዎች የማይጠቃ መሆኑን ነው፡፡ ያ ማለት ግን ግለሰቡ ከዝሙት ጉዳቶችና መዘዞች ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡ አላህም ይህንን የለየለት የዝሙት መንገደኛን ዝም ብሎታል፤ ሌሎች ከርሱ ያነሱትን ተራ ዝሙተኞች ደግሞ በበሽታዎች ክፉኛ ይዟቸዋል ብለን አላህን(ከሁሉ ጉድለት ጥራት ይገባውና)ረሺ ወይም ኢ-ፍትሓዊ አምላክ አድርገን ማሰብ የለብንም፡፡ አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ፈጽሞ ይህንን ሴሰኛ ገና ከመነሻው ሳይቀጣው የተወዉ እንዳይመስለን፡፡ በእውነቱ ምናልባትም አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)እርሱን የያዘበትን መንገድ ቢያውቁ ምናልባትም የአባለዘር በሽታ ሰለባዎች በራሳቸው ላይ በደረሰው ቅጣት ይጽናኑ ይሆናል፡፡! ግለሰቡ የዝሙት መንገደኛ ሆኖ መቅረቱ በራሱ በአባላዘር በሽታ ከተጠቃው ሰው በላይ ተቀጥቷል፤ ምክንያቱም የወንጀሉ ሸክም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረበት ነውና፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ያንን በአባላዘር በሽታ ያልቀጣውን የዝሙት መንገደኛን ምናልባትም በሥነ-ልቦናዊ ወይም በአካላዊ ወይም በመንፈሳዊ የዝሙት ጎዳቶች ቀጥቶት ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ ደግሞ እኛ ከምናስባቸው የአባላዘር በሽታዎች መካከል ከየትኛውም በበለጠ ሁኔታ ሴሰኛውን ግለሰብ እንደሚጎዱት እሙን ነው፡፡ከዚህም በላይ ሴሰኛው ግለሰብ ከአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ረሕመት የተባረረ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ ከዚህ የከፋ ሌላ ምን ኪሳራ አለ!? እጅግ አዛኝና ሩኅርህ ከሆነው ከአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ገደብና ወሰን የለሽ አምላካዊ እዝነቱና በረከቱ ከመባረር የበለጠ ሌላ ምን የከፋ ቅጣት አለ!? በእውነቱ ያ በአባላዘር በሽታዎች ያልተጠቃ ሴሰኛ ከዚህ ቅጣት ግን አያመልጥም፡፡ ስለዚህ አንድ የዝሙት መንገደኛ በዚህ መጥፎ ድርጊቱ ምንም የሚታይ ጉዳት ስላልደረሰበት ብቻ በርሱ መንፈላሰስ ፈጽሞ ልንታለል አይገባም፡፡ አንዲት አመሻሽ ላይ በመንገድ ዳር ዝሙትን የምትሠራ ሴት ምንም የሚታይ ጉዳት ስላደረሰባት ብቻ በርሷ ወቅታዊ መንፈላሰስ መሸንገል የለብንም፡፡ አንድ የዝሙት ተንሸራሻሪ(ወሲብ ቱሪስት)ከአገር አገር እየተዘዋወረ የሴቶችን ጭን ሲጎበኝ ምንም የሚታይ ጉዳት ስላልደረሰበት ብቻ በርሱ የላይላይ ሁኔታ መሳብ የለብንም፡፡ በጥቅሉ የተለያዩ ግለሰቦች በልዩ ልዩ ኃጢአቶች ላይ ሆነው ስለተንፈላሰሱ ብቻ በነርሱ ወቅታዊ ሁኔታ መታለል የለብንም፡፡ ይህንኑ እውነታም አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ) በሚቀጥለው አምላካዊ ቃሉ በአንክሮት አስገንዝቦናል፡-

Surah Ghafar (غافر), verses: 4

مَا يُجَٰدِلُ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَلَا يَغْرُرْكَ تَقَلُّبُهُمْ فِى ٱلْبِلَٰدِ

በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ)አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡

👉ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉 ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
የዝሙት መንፈሳዊ ጉዳቶች በሚል እንመካከራለን።

👉ዱዓ እያረጋችሁልኝ ነዋ¿

👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።

👇👉ይህ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል ይቀላቀሉን የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።
JOIN US ONNN
T/G CHANNEL
👇👍👇👇👇👍👇
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል አስራ ሁለት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

↠ሀ/ ዝሙትን መሥራት ትልቅ ኃጢአት ነው፤ ይህ ብቻውን በቂ አይደለምን

የዝሙት ትልቁ ጕዳትና መዘዝ ይኸው ድርጊት ከታላላቅ ኃጢአቶች አንዱ መሆኑ ነው፡፡ ዝሙት ታላቅ ኃጢአት መሆኑን አስመልክቶ ታላቁ ኢማም ኢማሙ
አሕመድ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡-

«እኔ ከሺርስ ጦባዕድ አምልኮ)እና ነፍስን ከመግደል በኋላ ሕገወጥ ወሲባዊ ግንኙነትን(ዝሙትን)ከመስራት ይበልጥ የከፋን ሌላ ነገር አላውቅም፡፡

የዝሙትን አደገኛነትና የገዘፈ ኃጢአትነቱን አስመልከቶ አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ) እንዲህ ይላል፡-

Surah Al-Furqan (الفرقان), verses: 68 -70

وَٱلَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ ٱلنَّفْسَ ٱلَّتِى حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا يُضَٰعَفْ لَهُ ٱلْعَذَابُ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِۦ مُهَانًا
إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَٰلِحًا فَأُو۟لَٰٓئِكَ يُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِهِمْ حَسَنَٰتٍ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል፡፡ ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡


አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ነፍስን መግደልና ዝሙት መሥራትን አቆራኝቷቸዋል፡፡ የዚህንም ቅጣት ዝንተ ዓለም በጀሀነም-እሳት ውስጥ አድርጓል፤ ግለሰቡ ወንጀሉን በተውበት፣ በኢማንና በመልካም ሥራ ካላስወገደው በስተቀር፡፡ እናም ዝሙተኛው በድርጊቱ ከባድ ወንጀልን ተሸክሞ ይቀራል፡፡ ዝሙትን መፈጸም ለአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ቁጣ ይዳርጋል፡፡ ዝሙትን ጤናማ የሕይወት አካሉ የሚያደርግ ማህበሰረብ በበርካታ ቅጣቶች ይመታል፡፡ እነርሱ ዝሙትን በዚያ መንገድ ማወደስን ካላቆሙ ደግሞ ለጥፋትም ይዳረጋሉ፡፡ ይህ ማህበረሰብ ሙስሊምም ይሁን ሌላ ያው ነው፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው ዝሙትን ያልሠራ ሆኖም ሳለ ከላይ ከተዘረዘሩት ጉዳቶች መካከል በየትኛውም ሊጠቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በዝሙት ውስጥ ከተዘፈቀ ወዲያው ተውበት ካላደረገ በስተቀር ለዝሙተኛውና ለአመንዝራው የተገባው አምላካዊ ዛቻና የቅጣት ጥላው እርሱን ያሳድደዋል፡፡ እናም እርሱ ተውበትን አድርጎ እስከሚመለስ ድረስ ከዒባዱር-ረሕማን ምድብ ወጥቶ ከዲያብሎስ ሕዝቦች ምድብ ውስጥ ሆኖ ይቀራል፡፡


👉ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉 ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
ዝሙት ግለሰቡን ከሸይጧን ሕዝቦች ምድብ እንዴት እንደሚጨምር እንመካከራለን።

👉አደራ በዱዓችሁ

👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።
Co๓๓ent⇢ @Jezakellah @Jezakellah


JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል አስራ ሁለት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ↠ሀ/ ዝሙትን መሥራት ትልቅ ኃጢአት ነው፤ ይህ ብቻውን በቂ አይደለምን የዝሙት ትልቁ ጕዳትና መዘዝ ይኸው ድርጊት ከታላላቅ ኃጢአቶች አንዱ መሆኑ ነው፡፡ ዝሙት ታላቅ ኃጢአት መሆኑን አስመልክቶ ታላቁ ኢማም ኢማሙ አሕመድ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡- «እኔ ከሺርስ ጦባዕድ አምልኮ)እና ነፍስን ከመግደል በኋላ ሕገወጥ…
→ክፍል አስራ ሦስት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

↠ለ/ ዝሙት ግለሰቡን ከሸይጧን ሕዝቦች ምድብ ይጨምረዋል

ዝሙትን መፈጸም ጸያፍ፣ ነውርና አስቀያሚ ነገር ከመሆኑም በላይ መንገድነቱ የከፋ ነው፡፡ ይኸው እውነታም በሱረቱል ኢስራእ አንቀጽ 32 ላይ በግልጽ ተጠቅሷል፡፡ ይህ የከፋ መንገድ ደግሞ ግለሰቡን ከዒባዱር-ረሕማን ምድብ አውጥቶት ከኢብሊስ ሕዝቦች ይቀላቅለዋል፡፡ በእውነቱ ዝሙት ላይ መውደቅ የአር- ረሕማን ባሮች መግለጫ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው አንድ ሰው ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ እርሱ ሙእሚን ሆኖ አይደለም የሚባለው፡፡ ይህንኑ አስመልክቶም ነብዩ (ﷺ)እንዲህ ማለታቸው ይታወሳል፡-

‹‹ዝሙተኛው ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ እርሱ ሙእሚን ሆኖ አይደለም፡፡»

አዎ! ግለሰቡ ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ ሙእሚን ያለመሆኑ እውነታ የዝሙት መንገድ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ከነዚያ ከተመረጡ የአላህ ባሮች(ዒባዱር-ረሕማን) ባህሪያት መካከል አንዱ እነርሱ ዝሙትን አለመሥራታቸው ነው፡፡ እንዲሁም ከሙእሚኖች ባህሪያት መካከል እነርሱ ከጋብቻ በፊት ክብረ ንጽሕናቸውን መጠበቃቸውና በትዳር ሕይወት ውስጥ ደግሞ ታማኝነታቸውን ጠብቀው መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህን ለመጠበቅ የሚሳናቸው ሰዎች ደግሞ ከመጥፎዎች ባልደረባነት ውስጥ ይወድቃሉ፡፡

↠ሐ/ በዝሙት ሳቢያ ግለሰቡ የአላህን ድንበር ይተላለፋል

አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)የሰውን ልጆች ወንድና ሴት አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ መልካሙንና መጥፎውንም አሳውቋቸዋል፡፡ ከዚህም በላይ በመልካምና በመጥፎ
መካከል ለይቶ የሚያውቁበትን ሕሊና ሰጥቷቸዋል፡፡ የሰማያትና የምድር፣ በመካከላቸው ያለው ነገር ሁሉ ንግሥናው የርሱ ነው፡፡ ማንም ንጉሥ የራሱ ክልልና ድንበር እንዳለው ሁሉ የንጉሦች ሁሉ ንጉሥ የሆነው አላህም(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)የራሱ የሆነ ድንበር አለው፡፡ እነዚህም እርሱ ከልክልና ሐራም ያደረጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ በነዚህ ነገራት መካከልም አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)የራሱን አምላካዊ ድንበሮቹን አብጅቷል፡፡ ባሮቹም እነዚህን አምላካዊ ድንበሮች የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህም በመሆኑ የአላህን ድንበር በዳዮች እንጂ አይተላለፉትም፡፡ በእውነቱ በዳዮችም አይድኑም፡፡
Surah At-Talaq(الطّلاق),verses:1
وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ

«የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፡፡ »

Surah Al-An’am (الانعام), verses: 21
إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

«እነሆ በደለኞች አይድኑም፡፡»

የአላህን ሕግጋት የሚተላለፍ ሰው እራሱን ከመበደሉም በተጨማሪ ቤተሰቡንም ይበድላል፡፡ በዝሙት ድርጊት የሚታወቅ ሰው በራሱ ልጆች ላይም ድንበርን ተላልፏል፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው ከርሱ ቤተሰብ ጋር የጋብቻ ትስስሩን ለመፍጠር አይፈልግምና፡፡ የአመንዝራ ዘር እየተባለ ዘሩም ይሰደባል፡፡!

ከምንም በላይ ግለሰቡ ዝሙት ላይ ከመውደቁ በፊት የሄደባቸው መንገዶች ሁሉ በአምላካዊ ድንበር ዙሪያ የማንዣበብና የመዋለል አካላት ናቸው፡፡ በአላህ
(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ድንበር ዙሪያ ማንዣበብም የኋላ ኋላም አምላካዊውን ሕግ ለመተላለፍ አበቃው፡፡ እናም አንድ ሰው ዝሙት ላይ ከመውደቁ በፊት ተላልፋቸው የሚሄደው የዝሙት መዳረሻ መንገዶችም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ የተከለከለው ዕይታ፣ ዕይታውን ተከትሎ የመጣው ሐሳብ(ምኞት)፣ ሐሳቡን ተከትሎ የወጣው ንግግር፣ ንግግሩን ተከትሎ ለዝሙት የተራመደው እርምጃና በመጨረሻም ዝሙት ላይ የወደቀበት አግባብ ሁሉ የተከለከሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ደረጃዎች በየፊናቸው የተከለከሉና ግና በዝሙተኛው የተጣሱ አምላካዊ ገደቦች ናቸው፡፡ እናም የአንድ ዝሙተኛ ሰው ድንበር አላፊነት በውስጡ በርካታ ጥሰቶችን ያካትታል፡፡ ለዚህም ነው በአላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ) ድንበር ዙሪያ አታንብቡ የሚባለው፡፡

በነገራችን ላይ ዝሙትን አትቅረቡ ሲባል ዋናውን የዝሙት ድርጊት ብቻ ሳይሆን የዝሙት መዳረሻ መንገዶቹንም ጭምር ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ዝሙትም ሆነ የዝሙት መዳረሻ መንገዶችም እንደ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ቮልቴጅ ከሩቅ የመሳብ ኃይል አላቸውና፡፡ ለምሳሌ ዕይታን ብንወስድ ግለሰቡ በተመኛት ሴት ላይ እንደ ማግኔት የመጣበቅ ኃይል አለው፡፡ የተምኔት ዕይታን ተከትሎ የሚመጣው ሐሳብም ቢሆን የግለሰቡን በነፃነት የማሰብ መብቱን ክፉኛ ይቀናቀነዋል፡፡ ሐሳቡን ተከትሎ የሚመጣው ንግግርም ቢሆን የግለሰቡን ፍላጎት ፈንቅሎ ለማውጣት ሰርክ ይታገለዋል፡፡ ንግግሩን ተከትሎ ወደ ዝሙት የሚሄደው እርምጃ ደግሞ ይበልጥ እየተፋጠነ ይመጣል፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ የብልቱ የማጽደቅ አዝማሚያው ይበልጥ ይፋጠናል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁሉ ጥሰቶች የሚፈነጥቁት ሲታይ አነስተኛ ከሚመስል የተምኔት ዕይታ ነው፡፡ እናም ዝሙት ለነዚሁ ሁሉ ድንበሮች መተላለፍ ስለሚዳርግ ከሩቁ መጠንቀቅ ግድ ይላል፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭም የለውም፡፡ በእውነቱ አላህ ይጠብቀንና ዝሙት ላይ የወደቀ ግለሰብም በአምላካዊ ድንበሮች ላይ በርካታ ታላላቅ ጥሰቶችን ፈጽሟል፡፡

👉የ መ ጨ ረ ሻ ው ክፍል ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

👉 ኢንሻ አላህ በቀጣይ 👇👇👇
ዝሙት ከቆሻሻ እንደተቆጠረ እንመካከራለን።

👉በዱዓ አንረሳሳ

👉ለአላህ ብለው ይሄ ትልቅ ማስታዎሻ ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ።
Co๓๓ent⇢ @Jezakellah @Jezakellah

👉ይቀላቀሉን ከዚህ ኒዕማ ራሰዎን አይከልክሉ👈
JOIN US ON
TELEGRAM CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል አስራ ሦስት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ ↠ለ/ ዝሙት ግለሰቡን ከሸይጧን ሕዝቦች ምድብ ይጨምረዋል ዝሙትን መፈጸም ጸያፍ፣ ነውርና አስቀያሚ ነገር ከመሆኑም በላይ መንገድነቱ የከፋ ነው፡፡ ይኸው እውነታም በሱረቱል ኢስራእ አንቀጽ 32 ላይ በግልጽ ተጠቅሷል፡፡ ይህ የከፋ መንገድ ደግሞ ግለሰቡን ከዒባዱር-ረሕማን ምድብ አውጥቶት ከኢብሊስ ሕዝቦች ይቀላቅለዋል፡፡ በእውነቱ…
→ክፍል አስራ አራት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️

↝ዝሙት ከቆሻሻ ተቆጥሯል

ዝሙት በሚከሰትበት ጊዜ ሁለቱም ጥንዶች ወንዱና ሴቷም በራሳቸው ላይ ታላላቅ ጉዳቶችን አድርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን ሴቷ ከወንዱ የበለጠ የጉዳቱ ሰለባ ትሆናለች፡፡ ለምሳሌ ወንዱ ያበላሻትንና በዝሙት ላይ የጣላትን ሴት ከተዋት በኋላ ድንግል ሴትን ፈልጎ ሊያገባ ይችላል፡፡ ይህንኑ ማየትም የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ሴት ድንግል ወንድን ለጋብቻ ስትፈልግ ማየት የተለመደ አይደለም፡፡ በትንሹ በሴቷ ላይ በዝሙት ሳቢያ የማይታይ ጠባሳ ይደርስባታል፡፡ ይህንኑ የማይታይ ጠባሳን መፈወስ ደግሞ ከባድ ነው፡፡ ሆኖም ግን ወንዱ ያበላሻትን ሴት ከታዋት በኋላ ድንግል ሴትን ለማግባት ቢፈልግም አያገኝም፤ ምክንያቱም እርሱ መጥፎ ወንድ በመሆኑ ለርሱም የምትገባው የራሱ ዓይነት መጥፎ ሴት ናትና፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ዶ/ር ሙሐመድ ሐሰን እንዲህ ይላሉ፡-

«(መጥፎዎቹ ወንዶች ልጃገረዶችን ያበላሻሉ፡፡ ከዚያም ማግባትን ሲያስቡ ሷሊሕ(ጥሩ)ሚስት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ ግና ሁለተኛ ላይ የምታገኛት ሚስት ያንተው ዓይነት ምግባር ያላት ትሆናለች፡፡ አብዛኛው ወጣት ገርልፍሬንድ ብሎ የያዛትን ሕገወጥ የወሲብ አጋን በፍጹም አላገባትም ይላል። ታዲያ እኔ የምልህ ነገር ቢኖር የዝሙት ጓደኛህን ባታገባትም አንተ የምታገባት ሚስት የሌላ ሰው የዝሙት አጋር እንደነበረች ቅንጣት ታክል አትጠራጠር፡፡!
ከፈለክ ይህንን የአላህ ተባረከ ወተዓላ ቃልን አንብብ፡-

መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡(እንኑር 24:26)

አዎ! የማይታይ ጠባሳ አይፈወስም፡፡ ዝሙትም በባህሪው የማይታይ ጠባሳን ጭምር ያስወርሳል፡፡ የተሰነዘረ ስድብ ማርታን ሊያገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ቃላቱን መፋቅ አይቻልም፡፡ ለደረሰው ጉዳት ይቅርታን ማስባል ይቻላል፤ ነገር ግን ጉዳቱን እንዳልተከሰተ ማድረግ አይቻልም፡፡ ለተሠራው ዝሙት ከአምላከ ምሕረት ሊገኝበት
ይችላል፡፡ ነገር ግን በዝሙት ሳቢያ የተገረሰሰውን ድንግልናና የጠፋውን ጥብቅነት መመለስ አይቻልም፡፡! ዝሙተኞቹም በጸያፍ ድርጊት ውስጥ በመሳተፋቸው ያጡትን ክብር መልሰው ማግኘት አይችሉም፡፡ ብልግናን ሠርተው ሲያበቁ ጨዋነት ይገባናል ብለው መልሰው መጠየቅ አይችሉም፡፡ ክብርን በማጣት የደረሰው ውርደት መልሶ ሊገኝ አይችልም፡፡ መሓሪው አምላክ ለዝሙተኛው ምሕረቱን ሊለግሰው ይችላል፤ የርሱን ድንበር በመተላለፉ፡፡ ነገር ግን የድርጊቱ ሰለባዎችና ተጠቂዎች የሆኑት የግለሰቡ ሕጋዊ የትዳር አጋር፣ ልጆቹና ወዳጆቹ፣ ወዘተ፣ በጥቅሉ እነዚያ በግለሰቡ ድርጊት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አካላት ምናልባትም ይቅር ላይሉት ይችላሉ፡፡ እናም እነዚህ ሁሉ የማይታዩ ጠባሳዎች አይፈወሱም፡፡

ይህም ማለት አንድ ሰው የዝሙትን መዘዞች በወጉ አውቆ ከርሱ ከመራቅ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም ማለት ነው፡፡ ማንም ሰው ተውበትን ተስፋ በማድረግ ወደ ዝሙት ቢሄድ የሚያገኘው አምላካዊ ምሕረት የአምላኩን ድንበር በመተላለፍ ለፈጸመው በደል እንጂ የችግሩ ሰለባዎችን ምሕረትና ይቅርታን አያስገኝለትም፡፡ የነርሱን ጠባሳም አያሽርላቸውም፡፡ በጥቅሉ የዝሙትን ጉዳቶች በምንም ማካካስ አይቻልም፡፡ ይህም በመሆኑ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ነገር ቢኖር ዝሙትን ከመራቅ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለውም፡፡!


ስለተከታተላችሁኝ ከልብ አመሰግናለው።
አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው።
በነብያችን ላይ ሰለዋትና ሰላም ያውርድ።
اللهم صل وسلم علي سيدنا محمد
★ ★ ★ ★ ★

የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ ለኔ ለራሴ ምወደውን ለናንተም እወዳለሁ እኔ በዱንያም ደስተኛ እንድንሆን በአኼራም ደግሞ የከፍተኛው የፊርደውስ ሰዎች እንድንሆን ነው ምኞቴ።
ስለዚህ ለራሴና ለወንድሞቼ አደራ የምለው ባስታወስኳቹህ ነገር ላይ እንድንማርበትና እንድንፀና ነው። በዱዓም እንተጋገዝ።
አላህ በዱንያ ላይ ኸይርና በረካን ይስጠን
በአኼራ ደግሞ ሙሉ ጣፋጭና ከፍተኛ ምንዳን አላህ ያድርግልን።
አላህን በመልካም ስሞችና በላቁ ባህሪያቶቹ እንለምነው።
  አላህ ልባችንና ቤታችንን በደስታ በኸይርና በበረካ እንዲሞላው አንማፀነው።

የተውሂድ የሱናና የመልካም ስራ ሰዎች እንዲያደርገን እንለምነው።❗️

ይህ በዝሙትን አንዘምን የሚል አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል። አልሃምዱሊላህ በምናቀርባቸው ማስታዎሻዎች ብዙዎች እየተማሩበት ነው። አላህ ፅናቱን ይስጠን።

→እናንተም በጉሩፖችም በፌስቡክ በውስጥ መስመርም በተለያዩ ሚዲያዎች ለማሰራጨት ሞክሩ ሀላፊነት ሚሰማን ሰው እንሁን።❗️

ስለ ዝሙት በሰፊው ተወያይተናል ከዝሙት መውጣት የፈለገ ፁሁፎቹን መረዳት ብቻ ይበቃዋል። ምን አልባትም ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ ጀዛከላህ በሚለው ሊንክ አናግሩኝ።
Co๓๓ent↠ @Jezakellah @Jezakellah

በጣም አስተማሪና አዳዲስ ደስ የሚሉ ፁሁፎችን እናቀርብላችኋለን
ተቀላቀሉን ቤተሰብ ይሁኑን
👇👇👇
Join us on
👇telegram channal👇

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
ቁጥር ሁለት

→ክፍል አንድ←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜

የዝሙት መንሰራፋት፣ የብልግና ይፋ መውጣት፣ የሁኔታዎች መመቻቸትና ዝሙት ላይ የመውደቁ ነገር በቀላሉ የመከሰቱ እውነታ ሲታይ ስለዝሙት አደጋዎችና ጠንቆች የበለጠ ማወቅና ግንዛቤን መጨበጥ በሙስሊሞች ላይ የበለጠ ግዴታና አንገብጋቢ ይሆናል፡፡ የአንድ ሰው የትምህርት ደረጃው(ጉብዝናው፣ ብሩህነቱና የማሰብ ችሎታው)ከፍ ማለቱ እርሱን ከዝሙት ማጥመጃዎች ነፃ ለማድረግና በዝሙት መዘዞች አይነኬ እንዳይሆን ዋስትናን አይሰጠውም፡፡ የአንድ ሰው የሃይማኖተኛነት ደረጃው ከፍተኛ የመሆኑ ሁኔታም እርሱን ሙሉ በሙሉ በዝሙት ማጥመጃዎችና መዘዞች አይነኬ አያደርገውም፡፡ ከዚህም በላይ ማንም ሰው ዝሙትን ካሁን በኋላም ቢሆን ይበልጥ ከመስፋፋትና ይፋ ከመውጣት ሊያስቆመው አይቻለውም፡፡ ይህም ፈተናውን የባሰ ከባድ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ከዝሙት ለመጠበቅ የተወሰኑ የመከላከያ ግንቦችን መሥራት ይችላል፡፡ ከነዚህ የመከላከያ ግንቦች መካከልም የዝሙትን ጉዳቶችና መዘዞቹን በአግባቡ በማወቅና በመገንዘብ የዕውቀት ኃይልን መታጠቅ ነው፡፡!

ዝሙት በቀላሉ የሚንሰራፉና የሚዛመቱ ታላላቅ ጉዳቶችንና ጥፋቶችን ያስከትላል፡፡ የዝሙት ጉዳቶች በፈፃሚ ግለሰቦች ላይ ብቻ ተገድበው የሚቀሩ ሳይሆኑ ማህበረሰቡንም ለታላቅ ጥፋት የሚዳርጉና የመጪውን ትውልድ የማንነት እሴቱንም የሚበክሉ ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ ዝሙት ዓለማችን ላይ እጅጉን የተዛመተ በሽታ እንደመሆኑ መጠንና ብሎም ወደዚህ ጸያፍ ነገር የሚያደርሱ መንገዶችም ከመብዛታቸው የተነሳ ከዚህ ወንጀል ጋር ተያይዘው የሚመጡ መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶችም በዚያው ልክ እየተስፋፉ መጥተዋል፡፡ በጥቅሉ ዝሙት ለሚቀጥሉት ጉዳቶች ያጋልጣል፡-

①/ ዝሙት የበርካታ መጥፎ ስራዎች መጠራቀሚያ ሲሆን በዋናነትም የግለሰቡን የኢማን ኃይል ክፉኛ ያዳክመዋል፤ የመንፈሳዊነት ጎኑን ይሸራርፍበታል፤ የቀናተኛነት መንፈሱንም ያጠፋበታል፡፡

②/ ታላላቅ ስብዕናዎችንና ጥሩ ምግባራትን ያጠፋል፡፡ ለምሳሌ ይሉኝታን፣ ዓይነ-አፋርነትንና ሀፍረትን ይገድላል፡፡ ከዚህም የተነሳ ዝሙተኞች ዓይን አውጣዎችና ኃፍረተ-ቢሶች ሆነው ይቀራሉ፡፡!

③/ ዚና የዝሙተኛውን ፊት ደብዛዛ፣ ጨለምለም ያለና ቀፋፊ ያደርገዋል፡፡ ይህንንም እነርሱን በአስተውሎት የተመለከተ ሰው ሊታዘበው ይችላል፡፡!

④/ ዝሙት ልብን ያጨልማል፤ የልቦና ብርሃንን ያጠፋል፡፡ ሐሳብን ይበታትናል፡፡ ትኩረትን ይሰርቃል፡፡ ልብን ይመርዛል፡፡ ቋሚ የሆነን ጭንቀትና የጥፋተኛነት ስሜትን ያስወርሳል፡፡!

⑤/ ዝሙት ድህነትን ያስወርሳል፡፡ ዝሙተኞች በድህነትና በበረከት እጦት ይሰቃያሉ፡፡ በሐዲሠል ቁዱስ አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)እንዲህ ማለቱን ነብዩ(ﷺ) ነግረውናል፡- «እኔ አምባገነኖችን አጠፋቸዋለሁ፤ ዝሙተኞችንም በድህነት እቀጣቸዋለሁ፡፡»

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

በዚህ ርዕስ 27 የሚሆኑ ጉዳቶችን እንጠቅሳለን።


ለአላህ ብላችሁ በቻላችሁት ፁሁፍን ለማሰራጨት ሞክሩ የአንድ ሰው የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው።!
ከኛ ሚጠበቀው ሀቁን ማድረስ ብቻ ነው የፈለገውን ሚመራው የፈለገው ሚያጠመው አላህ ብቻ ነው።❗️


አላማችን ከዝሙት የፀዳ ማህበረሰብ መፍጠር ነው።❗️
ኢንሻ አላህ እንፈጥራለን!


ቤተሰብ ይሁኑን አብረን ወደ አላህ ከፍ እንበል!
👇 👇 👇 👇 👇
Join us on
👇telegram channal👇

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
→ክፍል ሁለት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜

⑥/ዝሙተኛው በአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ዘንድ ቦታ የለውም፤ የተዋረደ ነውና፡፡ በሰው ልጆች ዘንድም ክብርንና ቦታን የተነፈገ ይሆናል፤ በሰዎችም ዘንድ ለውርደቱ ይቅርታ አይደረግለትም፡፡

⑦/ ዝሙተኛዋ ድንግልና፣ ጥብቅነት፣ ክብረ ንጽሕና፣ ንጽሕት፣ ወዘተ ከሚሉት የተወደሱ መገለጫዎች ውጭ በመሆን የውርደት፣ የኃፍረትና የነውር መገለጫዎችን ትከናነባለች፡፡ ለምሳሌ ዝሙተኛ፣ አመንዝራይቱ፣ ሸርሙጣ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ሸሌ፣ ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስያሜዎችን
ታገኛለች፡፡ ወንዱ ዛኒያም ዝሙተኛ፣ ሂያጅ፣ አመንዝራ፣ ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ የሚሉትን መጥፎና አስቀያሚ
መጠሪያዎችን ያገኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ መጠሪያዎች በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ የርክሰትና የብልግና መገለጫዎች ተደርገው ይታያሉ፡፡

⑧/ ዝሙት ሰዎችን የተጣሉ፣ ባይተዋሮች፣ ብቸኝነት የሚሰማቸውና የተወረወሩ ዕቃዎች እንደሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል፤ ምክንያቱም በወንድና በሴት ዝሙተኞች መካከል ፍቅርና ውዴታ የለምና፡፡ አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)በባለትዳሮች መካከል ፍቅርንና እዝነትን ያደርጋል፡፡ ነገር ግን በዝሙት ጥንዶች መካከል ጥላቻንና ጭካኔን ያደርጋል፡፡ ይህም የቅርቢቱ ዓለም ቅጣታቸው አካል ነው፡፡ ይህም በተራው በነርሱ ፊትና ባህሪ ላይ ይንጸባረቃል፡፡ ከዚህም የተነሳ ዝሙተኞች በትንሽ ነገር ሳይቀር ይከፋሉ፡፡ ስሜታዊነታቸው ይጎላል፡፡ መረጋጋትና ማስተዋል አይታይባቸውም፡፡ በተቃራኒው ግን ጥብቅ ሰዎች፣ ንጽሕት እንስቶች፣ ደናግላት፣ ጥብቅ ወንዶች በሻሻ ፊትና ደስተኛ ልብ አላቸው፡፡ ከነርሱ ጋር የተቀመጠ ሰው ሁሉ ይደሰትባቸዋል፡፡ ይህ ግን በዝሙተኞች ዘንድ ሙሉ በሙሉ የተገላቢጦሽ ሆኖ ይገኛል፡፡

⑨/ሰዎች ዝሙተኞችን በጥርጣሬ እንዲመለከቱና ከከዳተኞች ጎራ እንዲመድቧቸው ያደርጋቸዋል፡፡

10/ አብዛኛውን ጊዜ ነገራት የሚሄዱት ዝሙተኞች ከሚመኙትና ከሚያስቡት በተቃራኒ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ እነርሱ ለከፍተኛ ጭንቀት የተዳረጉ ይሆናሉ፡፡ አንድ ሰው አላህን(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)በማመጽ(በእምቢኝነት) ደስታን የፈለገ እንደሆነ እርሱም በአጸፋው ግለሰቡ ካለበው ነገር በተቃራኒ እንዲገጥመው በማድረግ ይቀጣዋል፡፡ በመሠረቱ መልካም ነገር ሁሉ የሚገኘው ለዓለማቱ ጌታ በመታዘዝ ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)በርሱ ላይ ማመጽን ወደ መልካምነት የሚመራ መንገድ አላደረገውምና፡፡ አዎ! ዝሙተኞች ጥብቅ ሆነው በመገኘት የሚገኘውን ደስታ ብቻ ቢያውቁት ኖሮ እነርሱ በዚህ ኃጢአት ውስጥ በመዘፈቅ ያገኙትን ጊዜያዊ ደስታን ከንቱ ሆኖ ያገኙት ነበር፡፡

11/ ለዝሙተኖች በጀነት ውስጥ ሑረል ዐይን(የጀነት ቆንጆ ወንዶችና ቆነጃጅት ሴቶች አይዳሩላቸውም፡፡ በዚህም ከዚህ ዝንተዓለማዊ ደስታ የተነፈጉ ይሆናሉ፡፡


🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

በዚህ ርዕስ 27 የሚሆኑ ጉዳቶችን እንጠቅሳለን።


ለአላህ ብላችሁ በቻላችሁት ፁሁፍን ለማሰራጨት ሞክሩ የአንድ ሰው የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው።!
ከኛ ሚጠበቀው ሀቁን ማድረስ ብቻ ነው የፈለገውን ሚመራው የፈለገው ሚያጠመው አላህ ብቻ ነው።❗️


አላማችን ከዝሙት የፀዳ ማህበረሰብ መፍጠር ነው።❗️
ኢንሻ አላህ እንፈጥራለን!


ቤተሰብ ይሁኑን አብረን ወደ አላህ ከፍ እንበል!
Join us on
👇telegram channal👇

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል ሁለት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜ ⑥/ዝሙተኛው በአላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ዘንድ ቦታ የለውም፤ የተዋረደ ነውና፡፡ በሰው ልጆች ዘንድም ክብርንና ቦታን የተነፈገ ይሆናል፤ በሰዎችም ዘንድ ለውርደቱ ይቅርታ አይደረግለትም፡፡ ⑦/ ዝሙተኛዋ ድንግልና፣ ጥብቅነት፣ ክብረ ንጽሕና፣ ንጽሕት፣ ወዘተ ከሚሉት የተወደሱ መገለጫዎች ውጭ በመሆን የውርደት፣ የኃፍረትና…
👉ክፍል ሶስት👇

↝የትንሹ ዚና አደገኝነት↜

👉⑤/ የእግር ዚና አደገኛነት

አንድ የአላህ (ﷻ) ባሪያ መልካም ነገርን ለመሥራት ሲሄድ በተራመደ ቁጥር አጅር ያገኛል፡፡ የእግሮቹ ዱካ ያረፉበት ቦታ ሁሉ ይጻፍለታል፡፡ ይህንኑም ቀጥሎ ካለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መረዳት ይቻላል፡፡

Surah Ya-Sin (يس), verses: 12

إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا۟ وَءَاثَٰرَهُمْ وَكُلَّ شَىْءٍ أَحْصَيْنَٰهُ فِىٓ إِمَامٍ مُّبِينٍ

እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ «ወኣሣረሁም» (ፈለጎቻቸውንም) የሚለውን ቃል አንዳንድ ዑለሞች ሲተረጉሙት የእግሮቻቸውን ፋና (ዱካ) ማለት ነው ይላሉ፡፡
በዚሁ መሠረት አንድ ሰው ወደ ኸይርም ሆነ ወደ ሸር ሲራመድ እርምጃው ሁሉ ይመዘገባል፡፡ ግለሰቡ ወደ ሸር ሲራመድም የእግር ወለምታ አጋጥሞታል ይባላል፡፡ የእግር ወለምታ ደግሞ ልክ እንደ ምላስ ወለምታ ሁሉ ከባድ ነው፡፡ አላህ (ﷻ) በሱረቱል ፉርቃን ውስጥ ስለ ዲባዱር-ረሕማን ባህሪያት በተናገረባቸው አንቀጾች ውስጥ እነርሱ በንግግራቸውም ሆነ በእርምጃቸው ትክክለኞችና ቀጥተኞች እንደሆኑ ግልጿል፡፡ አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፡-

Surah Al-Furqan (الفرقان), verses: 63

وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًا
የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡

👉⑥/ የልብ ዚና አደገኛነት

አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፡-
يَعْلَمُ خَائِنَةَ الْأَعْيُنِ وَمَا تُخْفِي الصُّدُورُ

«(አላህ) የዓይኖቸን ከዳት፣ ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡»
(ጋፊር 40፡19)
  
ትኩረት አድርጉ❗️
⇨ ልብ መረጃውን የሚቀበለው ከዕይታ ነው፡፡ ግለሰቡ በስርቆሽም ይሁን በግልጽ ባዳ ሴትን ሲመለከት የርሷ ምስል በቀጥታ ከልቡ ላይ ያርፋል፡፡ ይህ በምኞት የተሞላ የዕይታ ጦርም ልቡን ያቆስልበታል፡፡ ግለሰቡም በመጀመሪያ ዕይታው ብቻ ስለማይረካ ደጋግሞ ያያል፡፡ ልቡም በተደጋጋሚ ይቆስላል፡፡ የቆሰለ ልብ ደግሞ ውስጡ ያለውን ነገር ይዞ መንፈቅፈቁ አይቀርም፡፡

ይህንኑ አስመልከቶ የሕያ ቢን ሙዓዝ እንዲህ ብለዋል፡-ልቦች በውስጣቸው ካሉባቸው ነገሮች ጋር ይንፈቀፈቃሉ ይንተከተካሉ። ምላሶችም ለቀልቦች ትልልቅ ጭልፋዎች ናቸው፡፡»
(እድ-ዳእ ወ አድ-ደዋእ)

ከዚሁ ጋር አያይዘው ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ)
እንዲህ ብለዋል፡- «አንታ ልብ ውስጥ ያለው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ ከፈለክ፣ ይህንኑ በምላስ እንቅስቃሴ መደምደም አለብህ፡፡»
(ኢድ ዳእ ወ ኢድደዋእ)

አነስ ቢን ማሊክ (ረድየላሁ ዐንሁማ) ባወሩት ሐዲሥ
↝ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«የባሪያው ኢማን አይስተካከልም፤ ቀልቡ ቀጥተኛ እስከሚሆን ድረስ፡፡ የርሱም
ቀልብ ቀጥተኛ እይሆንም፤ ምላሱ ቀጥተኛ እስከሚሆን ድረስ፡፡»
↠የአንድ ሰው ቀልብ በዚና ምኞት ከተሞላ ቀጥሎ ፍላጎቱ ይመጣበታል፡፡ ፍላጎቱን ተከትሎ ወደ ድርጊት ያመራል፡፡ ድርጊቱ እንኳን ባይሳካ የግለሰቡ አስተሳሰብ በዚና የተላወሰ ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ በትንሹ የግለሰቡን በነፃነት የማሰብ ችሎታው መካከል ጣልቃ በመግባት ይፈታተነዋል፡፡

🍂🍂🍂🍂

በክፍል አራት⇨ ከአጅነቢ (ባዳ) ሴት ጋር አብሮ የመቀመጥ አደገኛነት። ይቀጥላል

ሼር ማድረጋችሁ መብት ሳይሆን ግዴታ ነው። ሃላፊነት ሚሰማን ሰው እንሁን።
👉ነብዩ ﷺ ከኔ አንዲትም አያ ብትሆን አስተላልፏት አላሉምንእ
እና ምን እንጠብቃለን ባይሆን ሼር እናድርገው እንጂ ንግግራቸውን።


ቀጣዩንና ሌሎችንም የተረሱ የአላህ ትዕዛዛቶችና ሱናዎች እያነሳን እንተዋወሳለን
ቤተሰብ ይሁኑን

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
👉ክፍል ሶስት👇 ↝የትንሹ ዚና አደገኝነት↜ 👉⑤/ የእግር ዚና አደገኛነት አንድ የአላህ (ﷻ) ባሪያ መልካም ነገርን ለመሥራት ሲሄድ በተራመደ ቁጥር አጅር ያገኛል፡፡ የእግሮቹ ዱካ ያረፉበት ቦታ ሁሉ ይጻፍለታል፡፡ ይህንኑም ቀጥሎ ካለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መረዳት ይቻላል፡፡ Surah Ya-Sin (يس), verses: 12 إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا۟…
→ክፍል አራት←

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜

17/ በዝሙት ምክንያት የጥብቅ፣ ድንግልና ንጽሕት ሴቶች ስም፣ ክብርና የወደፊት ሕይወታቸው ይበላሻል፡፡ ይህም ለነርሱ ሳያገቡ ቆሞ-ቀር ለመሆን ትልቅ ምክንያት ሊሆናቸው ይችላል፡፡

18/ ዝሙት በሴቷ ቤተሰቦች ዘንድ ጠላትነትን ያነሳሳል፤ ብሎም በውስጣቸው የበቀል እሳትን ያቀጣጥልባቸዋል፤ ምክንያቱም የሴቷ ቤተሰቦች በዚህ ብልግና ሳቢያ የሚሰማቸው ውርደትና ነውር ከወንዱ አንፃር ሲታይ ከፍተኛ ነውና፡፡

19/ በዝሙተኛ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች (በተለይም ሴቶች)በተመሳሳይ ወንጀል ውስጥ የመውደቅ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ መላው ቤተሰባቸውም ከኢስላማዊው አስተዳደግና እነጻ እየተራቆተ ይሄዳል፡፡

20/ ዝሙተኛው በዝሙት ሳቢያ ታክሞ ለመዳን አስቸጋሪ የሆኑና ለሞት በሚዳርጉ የአባላዘር በሽታዎችና በኤድስ ደዌ ይጠቃል፡፡ በተለይ ሴተኛ አዳሪዎች ላይ በብዛት የሚከሰቱ የማሕፀን መድማት፣ የማሕፀን ሽታ፣ የብልት ካንሰር፣ ከዚህም የተነሳ ቋሚ ጭንቀት፣ ወዘተ የመሳሳሉት የወሲብ ንግድ መዘዞች ናቸው፡፡

21/ ዝሙት ለአንድ መንደር መጥፋት ሰበብ ይሆናል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ኢብን መስዑድ(ረድየላሁ ዓንሁ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንድ መንደር ውስጥ ዝሙት በሚንሰራፋበት ጊዜ አላህ ያቺን መንደር እንድትጠፋ ያዛል፡፡» ዝሙት የዚህ ዓይነት ከባድና ለታላቅ ውድመት የሚዳርግ ወንጀል መሆኑን የሚያረጋግጥልን አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)በዝሙተኞች ላይ የደነገጋቸው ኮስታራ የዚና ወንጀለኞች መቅጫ ሕግጋት የመኖራቸው እውነታ ነው፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም(ረሂመሁሏህ) በአድ-ደእ ወ አድ-ደዋእ ውስጥ እንዲህ ይላሉ፡-

«አላህ ከዚና ጋር በተያያዘ የደነገጋቸውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግጋትን በሦስት መንገዶች ልዩ አድርጓቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ለምንዝርነት የሞት ቅጣትን የደነገገ ሲሆን ይህም በተቻለ መጠን እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንዲከናወን አዛል፡፡ ሁለተኛው ባሮቹ ዝምተኞችን በሚቀጡበት ጊዜ ለነርሱ ምንም ሐዘኔታ እንዳይሰማቸው ከልከሏቸዋል፡፡ እንዲሁም ሦስተኛው የዝሙተኞች ቅጣት በአደባባይ በሙእሚኖች ፊት እንዲፈጸምና በድብቅ እንዳይተገበር አዟል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ነገራት በስተጀርባ ታላቅ ጥበብ እንዳለ እሙን ነው፤ ምክንያቱም ይህ ሁሉ ነገር ሌሎች ዝሙትን እንዳይቀርቡት ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡»

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል
👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 👈

በዚህ ርዕስ 27 የሚሆኑ ጉዳቶችን እንጠቅሳለን።


ለአላህ ብላችሁ በቻላችሁት ፁሁፍን ለማሰራጨት ሞክሩ የአንድ ሰው የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው።!
ከኛ ሚጠበቀው ሀቁን ማድረስ ብቻ ነው የፈለገውን ሚመራው የፈለገው ሚያጠመው አላህ ብቻ ነው።❗️


አላማችን ከዝሙት የፀዳ ማህበረሰብ መፍጠር ነው።❗️
ኢንሻ አላህ እንፈጥራለን!


ቀጣዩንና ሌሎችንም የተረሱ የአላህ ትዕዛዛቶችና ሱናዎች እያነሳን እንተዋወሳለን
ቤተሰብ ይሁኑን

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
→ክፍል አራት← 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜ 17/ በዝሙት ምክንያት የጥብቅ፣ ድንግልና ንጽሕት ሴቶች ስም፣ ክብርና የወደፊት ሕይወታቸው ይበላሻል፡፡ ይህም ለነርሱ ሳያገቡ ቆሞ-ቀር ለመሆን ትልቅ ምክንያት ሊሆናቸው ይችላል፡፡ 18/ ዝሙት በሴቷ ቤተሰቦች ዘንድ ጠላትነትን ያነሳሳል፤ ብሎም በውስጣቸው የበቀል እሳትን ያቀጣጥልባቸዋል፤ ምክንያቱም የሴቷ ቤተሰቦች…
→ክፍል አምስት←

የመጨረሻው ክፍል
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
↝የዝሙት መጥፎ መዘዞችና ጉዳቶች በጥቅሉ↜

22/ ይህንን ኃጢአት በተመለከተ ሰዎችም የተለያዩ መሆናቸውን መጥቀሱ አግባብ ነው፡፡ እርሱ ያ ከበርካታ ግለሰቦች ጋር ዝሙትን የሚፈጽም ከዚያ ከአንድ ግለሰብ ጋር ከሚፈጽመው ሰው ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ ልክ እንዲሁ የወንጀሉ ግዝፈትም እኩል አይሆንም ማለት ነው፡፡ እርሱ ያ ዝሙትን በድብቅ የሚሠራ ሰው ከዚያ ይህንኑ ጸያፍ ነገርን በግልጽ ከሚሠራው ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ አንዴም ሲሆን አግብተው የሚያውቁ ግለሰቦች የሚፈጽሙት ዝሙት ከነዚያ ፈጽሞ አግብተው ከማያውቁ ላጤዎች ጋር ተመሳሳይ አይደሉም፡፡ በሌላ ሰው ሚስት ላይ የሚፈጸም ዝሙት ባላገባች ሴት ላይ ከሚፈጸመው ዝሙት ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ የመጀመሪያው የበለጠ የከፋ ነው፤ ምክንያቱም ይህ
የሌሎች መብትን መጣስና የጋብቻ ሕይወትን ማናወጥን ያካትታልና፡፡

23/ ከዚህም በተጨማሪ በጎረቤት ሚስት ላይ የሚፈጸም ዝሙት ከሌሎች ሴቶች ጋር ከሚፈጸመው ዝሙት የበለጠ አደገኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ የጎረቤትን መብት መንካት ሲሆን በኢስላም ደግሞ በጎረቤት ላይ ጉዳትን ማስከተል በራሱ ከታላላቅ ወንጀሎች ተርታ ይመደባል፡፡ በተጨማሪም ከጎረቤት ሚስት ጋር የሚፈጸም ዝሙት የመደጋገም ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡

24/ በተመሳሳይ ሁኔታ ሚስቱን ትቶ ለጂሃድ ከወጣው ሰው ሚስት ጋር ዝሙትን መፈጸም ከሌሎች ሴቶች ጋር ከመፈጸም እጅጉን የከፋ ነው፡፡

25/ ልክ እንደዚሁ የወንጀሉ አደገኛነት አብሮ ከሚተኛቸው ሴቶች ጋር እንደሚለያይ ሁሉ ዝሙቱ ከተፈጸመበት ወቅትና ቦታ አኳያም ክብደቱ ይለያያል፡፡ እርሱ ያ በተከበረው የረመዷን ወር ውስጥ ዝሙትን የሚፈጽም ከዚያ ከረመዷን ውጭ ከሚፈጸመው ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ እንደዚሁም እርሱ ያ በተቀደሰ ስፍራ
የሚፈጸመው ዝሙት በሌላ ቦታ ከሚፈጸመው ይበልጥ ከባድ ነው፡፡

26/ በአዛውንት አልያም ምራቁን በዋጠው ሰው የሚፈጸመው ዝሙት ከዚያ በወጣት ሰው ከሚፈጸመው ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ የዓሊም ዝሙት ከተርታው ሰው የከፋ ነው፡፡ ሀብታምና እርሱ ያ የጋብቻን ጣጣ መሸከም የሚችል ሰው ከዚያ ለማግባት አቅም ካነሰው ዝሙተኛ የበለጠን ወንጀል ፈጽሟል፡፡

27/ ከምንም በላይ ዝሙትን የሠራ ሰው መዘዙ በትንሳኤው ዕለት አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)ዝሙተኛውን በመላው ፍጥረት ፊት ያዋርደዋል፡፡ ይህንኑም ቀጥሎ ከሚቀርበው ሐዲሥ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ኻሊድ ቢን ወሊድ እንዳወሩት እንድ አዕራብይ ወደ ነብዩ (ﷺ)መጥቶ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- «እምነቴ የተሟላ እንዲሆን እፈልጋለሁ?» ሲላቸው ነብዩም(ﷺ)«ሥነ-ምግባርን አሳምር፤ እምነትህ የተሟላ ይሆናልና» አሉት፡፡ ቀጥሎም «የምጽአት ቀን ጌታዬ(የቂያም ቀን)እንዳያጋልጠኝ እውዳለሁ?» ሲላቸው ነብዩም(ﷺ)«ከዝሙት ተጠበቅ፤ የምጽአት ቀን ጌታህ እያጋልጥህም!» አሉት፡፡ቀጥሎም «ከአላሁ ተዓላ ዘንድ ትልቁ በጎ ሥራ ምንድነው?» ሲላቸው ነብዩም(ﷺ)ጥሩ ፀባይ፣ ትሕትና እና ትዕግስት ናቸው» አሉም፡፡ ቀጥሎም « አላሁ ተዓላ ዘንድ ትልቁ ወንጀል ምንድነው? ሲላቸው ነብዩ(ﷺ)መጥፎ ምግባርና(ለመጥፎ)ፍላጎት(ለስሜት)መገዛት ናቸው» አሉት፡፡
★ ★ ★ ★ ★

አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው።
በነብያችን ላይ ሰለዋትና ሰላም ያውርድ።
اللهم صل وسلم علي سيدنا محمد


ይህ በዝሙትን አንዘምን የሚል አዲስ የቴሌግራም ቻናል ነው ባጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፏል። አልሃምዱሊላህ በምናቀርባቸው ማስታዎሻዎች ብዙዎች እየተማሩበት ነው። አላህ ፅናቱን ይስጠን።

→እናንተም በጉሩፖችም በፌስቡክ በውስጥ መስመርም በተለያዩ ሚዲያዎች ለማሰራጨት ሞክሩ ሀላፊነት ሚሰማን ሰው እንሁን።❗️

ስለ ዝሙት በሰፊው ተወያይተናል ከዝሙት መውጣት የፈለገ ፁሁፎቹን መረዳት ብቻ ይበቃዋል። ግን ምን አልባትም ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ ጀዛከላህ በሚለው ሊንክ አናግሩኝ።
@Jezakellah @Jezakellah

በጣም አስተማሪና አዳዲስ ደስ የሚሉ ፁሁፎችን አዘጋጅተናል እናቀርብላችኋለን።
ተቀላቀሉን ቤተሰብ ይሁኑን

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam

Onther channel👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina


#የ_YOU_TUBE_አድራሻችን 👇#SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🌹🌹👌👌👌👇👇

https://youtube.com/channel/UCbYoBgogrqZB8VJEkAGWyhA