‹‹እና 20 ሚሊዬን ልትሰጠኝ?››
እንደነገርከኝ ከሆነ እስከአሁን የ205 ሰዎች ኩላሊት በጥቂት ገንዘብ እየገዛችሁ አንዳንዱንም በአደጋ ሆስፐታል ከገብና ከሞቱ ሰዎች ሰርቃችሁ ሸጣችሆል፡፡የ52 ሰዎች ልብ ሸጣችኋል፡..ሌላም ብዙ ብዙ የሚዘገንኑ ወንጀሎች››
‹‹አዎ.ብዙ ጊዜ እኮ ያልካቸውን ወንጀሎች መፈፀማችንን ነግሬሀለው››
‹‹ምነው ታዲያ ስትፈፅሙት ያልደከማችሁ አሁን ስታወራው አንገሸገሸህ፤ስማኝ ከጠቀስክልኝ ወንጀሎች ውስጥ ቢያንስ ግማሹ በእናንተ ታፍነው ልባቸውና በመዝረፍ እንዲሞቱና ሰውነታቸው በአሲድ ቀልጦ ለቀብር እንኳን እንዳይበቁ የተደረጉ ናቸወ፡..እና 20ሚሊዬን ሳይሆን 20 ቢሊዬን ብር ቢኖርህና እንኳን አያድንህም››
‹‹ግን የዚህ ሀሳብ ጠንሳሽም ዋናው አድራጊ ፈጣሪ እኮ ፕሮፌሰሩ ነው፡፡የእኔና የሺኪው ድርሻ ትንሽ ነው››በማለት እራሱን ለመከላከል ሚያደርገውን ጥረት ቀጠለበት፡፡
በንግግሩ አብዬት ተንቀጠቀጠ‹‹ግን ምን አይነት ህሊና ቢስ ሰው ነህ?እንዚህን ቃላቶች ከአንደበትህ ስታወጣ ትንሽ አያደናቅፍህም?ስማ እኔ የእድሜዬን ግማሽ ማጅራት መቺ ሆኜ አሳልፌያለሁ ፡፡በዚህ ሂደት በስህተት አንድ ሰው በእጄ ላይ አልፎል እና ከዛን ቀን ጀምሮ ንፅህ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም… እናንተ ያን ሁሉ ሰው እንዲህ ጨፈጭፋችሁ እንዴት ነው በሰላም መተንፈስ የምትችሉት..ምን አይት አውሬነት ነው በውስጣችሁ ያለው?፡፡አሁን ዝም ብለህ ስማኝ …እኔ እናንተን ለመንግስት አሳልፌ ሰጥቼ በ ፍርድ ቤት እስክትዳኙ መጠበቅ እልችልም፡፡ምን አልባትም የሞት ፍርድም ቢፈረድባችሁ አንኳን አያረካኝም››
‹‹እሸ እንዲሆን የምትፈልገውን ንገረኝ?››
‹‹ኩላሊታቸው ለተዘረፉ 35 ሰዎችን ማግኘት ችለናል.እንሱ አንድ ላይ ሆነው ጠበቃ ገዝተው ሆስፒታላችሁን ከሰዋል፡፡እርግጠኛነኝ ፍርድቤቱ ተገቢውን ካሳ ስለሚበይንላቸው የሚከፈለው ከአንተና ከፕሮፌሰሩ ሼር ተቀንሶ ነው፡፡
‹እንዴ ሼኪውስ…ከዚህ ጉዳይ ከተገኘ አያንዳንዱ ትርፍ ተካፋይ ነበሩ እኮ…››
‹‹ጥሩ .ለጊዜው ግን እሳቸውና ዶዬ እዚህ ወንጀል ውስጥ አይካቱም.. ለአንተ ቤተሰብ የሚሰጠውን ብር ከእሳቸው ነው የምቀበለው….በዛ ላይ ዶክተሯና ጓደኛዬ በእሳቸው እጅ ነው ያሉት..ግን እመነኝ ቀኑ ሲደርስ እራሴው ለሰሩት ወንጀል በደንብ አስከፍላቸዋለው ለዛ ቃል ገባልሀለሁ፡፡አንተ ግን ስለሆስፒታሉ ሼር እርሳው.ምንም አይኖርህም፡፡››
‹‹ቤተሰቦቼ እዚህ ወንጀል ውስጥ የሉበትም.ሚስቴ በጣም ሀይማኖተኛ ና ፈርሀ እግዚያብሄር ያላት ሴት ነች .እና በእኔ ሀጥያት እነሱ መቀጣት የለባቸውም.እንድ ያላቸው መተዳደሪያ ደግሞ ይሄ ሆስፒታል የሚገኝ ገቢ ነው››
‹‹እሱን እኮ አየሁ… ሚስትህንም ልጆችህንም አነጋግሬያቸዋለሁ….ስለአንተ በሚዲያም በሰሙት ነገር ተሳቀውና ተሸማቀው ነው ያሉት…..ብትሞት እራሱ ያን ያህል አያዝኑም…እንዴት አንተን የመሰለ የሰይጣን ታናሽ ወንድም እዛ ቤተሰብ ውስጥ ሊኖር እንደቻላ ማሰብ እንኳን አልቻልኩም፡፡
‹‹አዝናለሁ››
‹‹አይ አንተማ ሀዘኔታ የሚባል ነገር ውስጥህ የለም..ይልቅ አሁን ስማኝ…ለቤተሰብ 20 ሚሊየን ጥሬ በር እንዲደርሰቸው አደርጋለው፡ያንን በስልክ እንድታረጋግጥ ይደረጋል፤ከዛ ቡኃላ ግን ያልከሀውን ታደርጋለህ›
በመጀመሪያ የእያንዳንዱን ሰው ወንጀል በዝርዝር .ምን እንደሰራችሁ ..የእያንዳንዱ ወንጀለኛ ድርሻ ምን እደነበረ፤ በተለይ ፕሮፌሰሩና ባለስልጣኖቹ ላይ አተኩረህ ትተነትናለህ.ያንን በቪዲዬ ይቀረፃል…የራስህንም ወንጀል ሳትረሳ ማለት ነው..ኑዛዜ በለው፡፡››
‹‹ያልከኸውን ማለቴ 20 ሚሊዬን ብር ለበተሰቤ የእውነት እንዲያገኙ ካደረክ ያልከኸውን በደስታ አደረጋለሁ፡››
‹‹ለዛ አትጠራጠር. ቀረፃውን የምታረግው ብሩን እንዳገኙ ካረጋገጥክ ቡኃላ ነው፡፡ግን ከዛ ቡኃላ ደግሞ ሌላ አንድ ነገር ይጠበቅቅሀል፡፡››
‹‹ምንድነው?››
‹‹እኛ በመረጥነው ቦታ ላይ አንተ በመረጥከው መንገድ እራስህን ታጠፋለህ፡፡ ››
‹‹ምን?››
‹‹አዎ .ይሄ እኮ ለአንተ አይነቱ ጭራቅ ትልቅ እድል ነው ….እንደ ወንጀልህ ቢሆን እያንዳንዶን የሰውነትህን ብልት እየተቆረጠ ሞትን እስክትለምን መቃተት ነበረብህ ..እና ግን ያው በአንት ልክ አውሬነት ውስጣችን ስሌለ ምህረት አድርገንልህ ነው እንዲህ አይነት የክብር ሞት አማራጭ የቀረበልህ..እራስህን በራስህ እንድታጠፋ ልንተባበርህ ወስነናል፡፡እንዳልኩህ የመሞቻ ዘዴውን ግድ የለም እራስህ መምረጥ ትችላለህ.ከፈለክ በሽጉጥ ፣ከፈለክ በመርዝ ፣ከፈለክ ደግሞ ተንጠልጥለህ…እኛ የመረጥከውን መሳሪያ ያለምንም ክፍያ እናመቻችልሀለን፤እ ምን ተትላለህ?
‹‹ሌላ ምርጫ የለም..››
‹‹አለ››
‹‹ምን ?››አለ በጉጉትና ፡፡
ኩላሊታቸው ተዘረፈባቸው ያልኩህ 35 ሰዎችን በአንድ አዳራሽ ውስጥ እንዲሰበሰቡ አመቻችና እጅ እግርህን በማሰር መሀከላቸው እንጥልሀለን ፤ከዛ የሚሆነውን ማየት እንችላለን››
‹‹እሺ ፕሮፌሰሩስ እንደእኔ ነው ሚሆነው.እንደእኔ አራሱን እንዲያጠፋ ልታደርጉት ነው?፡፡››
‹‹አይ በፍፅም……እሱ አንተ ያገኘሀውን እድል አያገኝም….በእጆቼ ቀስ በቀስ ነው የምገድለው፡፡ምን አልባት አንድ ወር ሊፈጅብኝ ይችላል.ለማንኛውም ማሰቢያ አንድ ቀን አለህ.ነገ በዚህን ሰዓት ተመልሼ እመጣለሁ..የዛን ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔህን ታሳሳቀኛለህ፡››ብሎ በራፉን ዘግቶበት ወጥቶ ሄደ
ይቀጥላል.... @tibeb145

❤3
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-18
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
//
አቢዬት ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እቤቱን የድግስ ቤት አስመስሎትል።ያልተገዛ መጠጥና ያልተሰናዳ የምግብ አይነት የለም።ይሄ ሁሉ ስርጉድ ዶ/ር ሰጲራን ለመቀበል ነው።አዎ ዛሬ ማታ ከሼክ ጠኸ ሰዎች እጅ ይረከባታል።በህይወቱ በዚህ መጠን ሰው ናፍቆት አያውቅም፡፡ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ቀጠሮ እስኪደርስ አላስችል እንዳለው አዲስ አፍቃሪ አስሬ ሞባይሉን እያወጣ ሰዓቱን ያያል።ካሳ ከ10 ሰዓት በፊት የተለቀቀው ።እንደዛ የሆነበት ምክንያት የአቶ ሙሉን የመጨረሻና ወሳኝ ውሳኔ እንዲቀርፅ ከሼክ ጠሀ ጋር በተደረገ ስምምነት ነው።አብዬት ካሳን ሲረከብ አብሮ ሀያ ሚሊዬን ብር ተቀብሎ ለአቶ ሙሉ ቤተሠብ ሚስጥሩ በተጠበቀ ሁኔታ አስረክቦ አቶ ሙሉ እንድያረጋግጥ ከባለቤቱ ጋር በስልክ አገናኝቶት ነበር።
በወቅቱ የባለቤቱ ስሜት ቅስም ሰባሪ ነበር
"ሙሉ አሁን ለእኛ ገንዘብ ምን ያረግልናል ...የሀገር ሁሉ ብር ብትልክልን እኮ ከደረሰብን ውርደት አያወጣንም...ሙሉ ስለአንተ ከሰማሁ በኃላ ቤተክርስቲያን ሄጄ አላውቅም ፡፡ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? እግዜር ፊት መቅረብ አፈርኩ...ስለባሌ ቢጠይቀኝ ምን ብዬ መልስለታለሁ...?እኚንና መሠል ስሜት የሚያደፈርሱ ንግግሮችን ከማያባራ እንባ አጅባ ተናገረች፡፡
ከዛ ብኃላ አቶ ሙሉ በስምምነታቸው መሠረት እራሱ የሠራውን...የኘሮፌሰሩን..እና የባለስልጣኖችን... እያንዳንድ የፈፀሙትን የወንጀል አይነትና ያገኙትን ብር በመዘርዘር እና ለእያንዳንድም ያለውን ማስረጃ በማቅረብ ተቀረፀ...ከአብዬት ጋር በገባው ውል መሠረት የሼኪውንና የዶዬን ስም አላነሳም።ግን የአቶ ሙሉን የቪዲዬ ኑዛዜና መረጃ ካየ ብኃላ ፓሊስ ምርመራ መጀመሩና ወደእነዶዬ መቅረብ ስለማይቀር..ከአሁኑ ከውስጣቸው ሁለቱ እራሳቸውን ለፓሊስ አሳልፈው በመስጠት በፕሮፌሰሩ የሚታዘዙትን ወንጀሎች ሁሉ እነሱ ብቻ እንደፈፀሙ እንዲናዘዙ ተመቻችቶል።ያው ልጆቹ የእውነትም በእያንዳንድ ወንጀል ስለነበሩበት የሚሰጡት ቃል ከአቶ ሙሉ ቪዲዬ ጋር እንደማይጣረዝ ታምኖል....ከዛ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን ብኃላ ዶክተር ሰጲራ ከፕሮፌሰሩ እጅ እንዳመለጠች ተደርጎ ከጠበቃዋ ጋር ሆና እጆን ትሰጣለች...በተቻለ መጠን መረጃዎች ሁሉ የእሷን ነፃ መሆን ሲለሚረጋገጥ እስር ቤት ሳታድር በዋስ እንድትለቀቅ የተቻለውን ለማድረግ ውሳኔ ላይ ደርሷ ስለዝርዝር ጉዳዩ ከህግ ሰዎች ጋር ከአሁኑ እየተነጋገሩበት ነው።
አብዬት ከካሳ ጋር ዶክተር ሰጲራን ለመቀበል የተቀጠሩበት ቦታ ደርሰው መኪናቸው አቁመው ገቢና ውስጥ ቁጭ ብለው እስኪያመጡላቸው እየጠበቁ ነው።
አቢዬተት"ግን አሞት ነበር ብለኸኝ ነበር አይደል?"በሰላም አላገኛት ይሆን እንዴ የሚል ጥርጣሬ ውስጡን ስላመሠው ካሳን ጠየቀው።
"ካሳ "አይ አሞታል አላልኩህም ግን ፌንት በልታ ነበር "
"ሰው ሳይታመም ፌንት ይበላል እንዴ"
"አዎ በደስታም ሊያረገው ይችላል"
"ግን ሀኪም አላያትም?"
"አንድ ሀኪም መጥቶ አይቶት ሆስፒታል ሄዳ ተጨማሪ ምርመራ ታድርግ ብሎ ኪኒና ሰጥቷት ሄደ...ግን አሁን ስለእሱ እርሳና አሁን ስትመጣ ቀድሞ አቅፎ የሚስማት ማን ነው?"
"ምን ማለት ነው ከማና ከማ?››
"ከእኔና ከአንተ ነዋ?"
"አንተ ደግሞ ለምንድነው የምታቅፋት"
"እንደ አንተ ሰለማፈቅራት ነዋ"
"አይ አንተ ከስሯ የመጣሀው ዛሬ ነው.. ከእኔ ግን ከ5 አስጨናቂና እረፍት የለሽ ቀናት ብኃላ ነው የማገኛት እና የማቅፍትም የምስማትም እኔው ነኝ"አለው ፡፡ምንም እንኳን ንግግሩ ለካሳ ግራ አጋቢ ንግግር የቀልድ መልስ መስጠት ይምሰል እንጂ በእውነትም ማድረግ የሚፈልገውን ትክክለኛ ስሜቱን ነው ያንፀባረቀው
"ንግግሩን እንዳገባደደ አንድ ማርቼዲስ መኪና እየከነፈች መጣችና አጠገባቸው ቆመች ።አብዬት ሽጉጡን በቀኝ እጅ ያዘና ፈጠን ብሎ ገቢናውን ለቆ ወረደ...የመኪናዋ ገቢና ተከፈተ ዳክተሯን አወረዶትና መኪናዋ ተስፈንጥራ ከአካባቢው ተሠወረች ።አብዬት ሽጉጡን ጎኑ ሻጠና ተንደርድሮ ወደእሷ ሮጠ..እንደደረሰ ሙሉ በሙሉ እጆቹን በወገቦ ዙሪያ ጠመጠመና በአየር ላይ አንስቶ አሽከረከራት።እንደተሸከማት ወደመኪናው ይዛት ሄደ..
"አረ አውርደኝ እከብድሀለው"
"አረ በጣም ቀላል ነሽ...ምግብ አይሰጡሽም ነበር እንዴ?"
"አይ ምግብ ነው ሚያወፍረው ብለህ ነው"
መኪናው ጋር ሲደርስ አወረዳት..ካሳ ገቢና እንደተቀመጠ ነው...አልተንቀሳቀሰም።ስታየው ደነገጠች"
"እንዴ ካሳ መጥተሀል እንዴ"
"መምጣት እንኳን መጥቼ ነበር…ይሄ አውሬ እንዳትወርድ..እንዳትስማት ብሎ አስፈራራኝ እንጂ"አለ በቅሬታ
‹‹ማሙሽ ገቢናውን ልቀቅላትና ከኃላ ግባ አለው ››አብዬት ጣልቃ ገብቶ አዘዘው።
አረ ተወው እኃላ ሆናለው ብላ ከፍታ ገባች..አቢዬትም ገባና መኪናዋን አንቀሳቀሰ
"አብዬት በእስፓኪዬ ወደኃላ አየተመለከታት ነው።ከስታለች..መክሳት ብቻ ሳይሆን ገርጥታለች አይኖቾ ጉድጉድ ከማለታቸው በላይ ቁዝዝ ብለዋል...ለቀናት የረባ እንቅልፍ እንዳልተኛች ያስታውቃል...የጤናዋም ሁኔታ አሳስቦታል።
"እንዴ ወደቤት አይደለ እንዴ የምንሄደው ?ነው ወይስ አድራሻ ቀየራችሁ?"ስትል ጠየቀች።የዚህ ጥያቄ መነሻ አብዬት መኪናዋን እየነዳበት ያለው አቅጣጫ ከቤታቸው አቅጣጫ ጋር ስላልገጠመላት ነው።
"አይ እዛው ነን...እግረ መንገዳችንን እዚህ ሰፈር ጉዳይ ቢጤ ስላለችኝ ነው።አያቆየንም።"
"ጉዳይ ካለህ ታዲያ እኛ ምን አገባን ..አውርደን እና በታክሲ እንሄዳለን"አለ ካሳ ተበሳጭቶ
ዶ/ሯ ደነገጠችና "አረ ችግር የለም..እቤትስ ሄደን ምን እንሰራለን ..እንደውም በዚህ ምሽት ነፍሻማ አየር ከተማውን መዞር አስደሳች ነው...በዛ ላይ አንድ ክፍል ውስጥ ታፍኜ መሠንበቴን አትርሳ"
"ላንቺው ብዬ ነው"
"ለእሷ ብለህ ምን...?"
"ይሄንን ያንተን አስቀያሚ ፊት ለረጂም ሰዓት እያየች እንዳትፈራ ብዬ ነው...ይሄንን ፊት ይዘህ ስታፈቅራት ግን ትንሽ አታሳዝንህም?"
በካሳ ሰቅጣጭ ንግግር ዶክተሯ የምትገባበት ጠፋት.. የአብዬትን ንዴት ለማየት አይኖቾን በፈራ ተባ ወደእሱ ስትልካቸውእሱ በካሳ ንግግር እየሳቀ ነው..መኪናውን አቆመ ፡፡
"ሆስፒታል ደግሞ ምን እንሰራለን?"አሁንን በንጭንጭ ቃና ጥያቄውን የሰነዘረው ካሳ ነው
"አስቀያሚ ፊቴን እንዲያስተካክሉልኝ"
ከእግሩ ስር የነበረ ጥቁር ፔስታል አነሳና ለዶክተር ወደኃላ አቀበላት
"ምንድነው...?››
‹‹ወደ ውስጥ አብረን ስለምንገባ እራስሺን ቀይሪ››
ፔስታሉን ውስጥ ያሉ ቁሳቁሶችን ጎኗ ካለ ወንበር ላይ ዘረገፈችና በየተራ አየቻቸው።
"አንተ እነዚ ዕቃዎች አሁንም አሉ?"
"ከዚህ መከራ ሙሉ በሙሉ እስክንወጣ ያስፈልጉናል ብዬ አስቀምጬቸው ነበር ይሄው ዛሬ አስፈለጉን..››እቃዎቹን
ስታይ ከገዳዬቾ ሽሽት እንዴት እሱ እጅ እንደገባቸ እነዚህን እራስን መቀየሪያ የገዛላት ጊዜ ተሠምቶት የነበረው ስሜት ሁሉም ፊቷ ላይ ድቅን አለ..ፀጉሩን አጠለቀች...መነፅሯን ሰካች...በአንገቷ ዙሪያ ሻርፗን ጠመጠመችና አጠናቀቀች
አቢዬትም ከገቢናውን ለቆ ወረደና የዶ/ሯን በራፍ ከፈተ
‹‹ውረጂ ዶክተር››
ወረደች..
ካሳ "እኔም ልምጣ እንዴ..?"
"ቦሮጫህን ቀደው እንዲያስወግድልህ ከፈለክ ና"
"አይ እንደውም ትቼዋለው.. የመድሀኒት ሽታ በጣም ነው የሚያስጠላኝ።
ትተውት ጎን ለጎን ሆነው ወደውስጥ መጓዝ ጀመሩ
"ለምንድነው ግን ወደእዚህ የመጣነው?"ጠየቀችው
"ታመሽና እራስሽን ስተሽ እንደነበር ሰምቼያለው ምክንያቱን ማወቅ አለብን።››
"እና ነገ ተነገ ወዲያ አይደርስም ነበር?"

❤2
"አይ ...የጤና ጉዳይ ለነገ አይባልም...አሁኑኑ መመርመር አለብሽ"
"ታውቃለህ አይደል ...በጣም ምርጥ ሰው ነህ"
"መስሎሽ ነው...ምርጥ መሆን ፈልጌ አይምሰልሽ ..ፈርዶብኝ እንጂ"
‹‹ማለት?›› አለችው የሚለው ስላልገባት
"አይ ምንም እንዲሁ ነው"
በዚህ ጊዜ ካርድ የምትቆርጠዋ ልጅ ፊት ለፋት ደርሰው ነበረ
"ካርድ ፈልገን ነበር"
"ላንተነው ለእሷ"
"ለእሷ"
"እስኪሪፕቶዋን ካርድ ላይ ቀስራ ለመፃፍ እየተዘጋጀች ‹‹ስም ስትል ጠየቀች "
ዶክተሯ ስሟን ለመናገር አፎን ስትከፍት
"እፅብ."ብሎ ነገራት አብዬት
ዶክተሯ በገረሜታ ቀና ብላ አየችው
"እፅብ ማ.."
"እፅብ አብዬት"ካርዳቸውን ተቀብለው እየተስሳሳቁ ወደተዘጋጀው ተራ ወደመጠበቂያ ወንበር ሄደው ጎን ለጎን ተቀመጡ
"እፅብ ማነች አለቺው?"
"እፅብ ልጄ"
"እንዴ ልጅ አለህ እንዴ ?"
"አይ ለአሁኑ የለኝም...ወደፊት ከኖረኝ ብዬ ነው ቀድሜ ስም ያወጣሁላት"
በዚህ ጊዜ ስሞ ተጠራና ለምርመራ ገባች..አጠቃላይ ምርመራው 40 ደቂቃ ፈጀ ጨርሳ ስትወጣ ግን ...ጎብጣ ነበር...እንባዋ ከቁጥጥሯ ወጭ ይረግፋል...አብዬት ሁኔታዋን ሲያይ በጣም ደነገጠ..እንደምንም ደግፎ መኪናው ጋር ወሰደና ወደ ውስጥ አስገባት...ተከትሎት ገባና ከጎኖ ቁጭ አለ፡፡
"እዛ ከጎኖ የተለጠፍከው መኪናውን ማን እንዲነዳልህ ነው?"አለው ካሳ
‹‹ችላ አለውና"አረ ባክሽ ዶክተር ምንድነው የተፈጠረው?"
ደረቱ ላይ ተለጥፋ መንሰቅሰቅ ጀመረች።ካሳ እንዴ አንተ ምን አድርገሀት"እያለ ገቢናውን ለቆ ወረደና እነሱ ወዳሉበት የኃላ ወንበር ገባ ።መሀከል አደረጎት
‹‹ዶክተር ምን አይነት በሽታ ቢሉሽ ነው እንዲህ በአንዴ ማቅ የለበሽው...?ይሄውልሽ አንቺ በዚህ አስራአምስት ቀን ውስጥ ከስንት ወጥመድ ከስንት ሞት አምልጠሻል ...እና ምን አዲስ ነገር መጣ ? እነዛ ጭራቆችን ያሸነፍሽ በሽታ ማሸነፍ ያቅትሻል?››
"ደግሞ ከአሁን ወዲያ እኛም ከጎንሽ ነን ...መቼም ቢሆን መቼ ብቻሽን አንተውሽም..."
"አዎ አንተውሽም ..እንዲ እንደአሁኑ በግራና በቀኝ ደግፈን አስከመጨረሻው እንንከባከብሻለን"ካሳ ቃል ገባ፡፡
"ከጎኔ እንደሆናችሁ አውቃለው..ግን ያልገባችሁ ነገር አለ"
"እኮ እንዲገባን ንገሪና እየለመንሽ እኮ ነው?"አብዬት ነው በጭንቀት የጠየቃት
"አርግዤለሁ"
"አርግዤለሁ ማለት ..?ማርገዝ ምንድነው..?ከእኔ ጋር አድርገን ነበር እንዴ..?.ነው ከእኔ ተደብቃችሁ አደረጋችው...ካሳ አብዬት ላይ አፈጠጠበት
‹አብዬት ተናደደ‹‹እስቲ አሁን እንኳን ቢሆን ዝም በል …ዶ/ር አልገባኝም›
‹እኔም አልገባኝም..የ7 ሰማንት እርጉዝ ነኝ…የዛን አውሬ ልጅ በሆዴ ተሸክሜለሁ››
‹‹የፈጣሪ ያለህ››አለ አብዬት ለ30 ደቂቃ ሁሉም እርስ በርስ እንደተጣበቁ በመቀመጥ ከመተከዝና ከመብሰልሰል ውጭ የተነጋገሩት ነገር አልነበረም፡፡

❤6
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-19
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
‹‹ስጋዬ ነው ነፍሴን በውስጡ አቅፎ የሚዞረው ወይስ ነፍሴ ነች ስጋዬን አዝላ ምትዞረው…?ነፍሴ ባትኖር ስጋዬ እራሱን መሸከም ይችላል?፡፡አይ በመሬት ስበት በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ተሸንፎ ዝልፍልፍ በሎ ከመሬት እንደሚዘረር ጥርጣሬ የለኝም፡፡ አሁን እኔ 56 ኪሎ ነኝ ሰላሳ ኪሎ የሚመዝን እቃ ትከሻዬ ላይ ቢጭኑ አጎብድጄ ልወድቅ እደርሳለሁ፡፡ግን ደግሞ አስቡት እግሬ ከቁርጭምጭሚቴ በታች ስንት ኪሎ ይሆናል? ሰባት ኪሎ ይሆናል ብዬ ባስብ ከላይ ያለውን 50 ኪሎ ሲያረፍበት እንዴት ቅንጥስ ብሎ አልወደቀም…?እንዴት ከበላይ ያለውን ቅጥልጥል ስጋ መሸከም ብቻ ሳይሆን ያለምንም ጫናና መዳከም ይዞ ያለማቋረጥ በኪሎ ሜትሮች ርዝመት ወደተራራው ጫፍ ይዞት ወጥቶ መልሶ ወደሸለቆው ይዞት የሚወርደው?
ለካ በጣም የሚፈልጉት ነገርም ቢሆን በተገቢው ጊዜ ቦታና ሁኔታ በእጅ ካልገባ ደስታው ሙሉ አይሆንም።ይሄን ልጅ ትፈልገዋለች።በጣም ትፈልገው ነበር።ጋብቻን 70 ፐርሰንት ትፈልግ የነበረው እንደቢጤዎቹ ዘመናዊ ሴቶች ለፍቅር ሳይሆን ለልጆች ነበር፡፡ጋብቻም ብቻ ሳይሆን ሀብታም መሆን የምፈልገውና ለዛም ቀንና ሌት ስትባክን ኖራ ያሳካችው ሳትሳቀቅ እስከቻለችው በቂ ልጅ መውለድ እንድትችል ነው።ከፕሮፌሰሩም ጋር ከጋብቻ በፊት ተደጋጋሚ ወሲብ የፈፀመችው ስሜቷን መቆጣጠር አቅቶቷት ወይም እሱን አቅሏን እስክትስት ስለምታፈቅረው ሳይሆን በምትወልዳቸው የልጆች ቁጥር ላይ በጊዜ ካልጀመረች ችግር ያመጣብኛል ብላ ስለሰጋች ነበር።ይሄ ችግር ከመከሰቱ በፊት አረገዝኩ አላረገዝኩ ብላ ብዙ ጊዜ ቼክ ታደርግ ነበር..በዛም ለብዙ ቀናት ተሳቃለች ...ብዙ ቀንም አልቅሳለች ..ተጠራጥራም የመሀንነት ምርመራ ሁሉ አድርጋ ነበር ። አሁን ይህ ችግር ከተፈጠረ በኃላ ግን ስለእንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ ቅንጦት ከመሆኑም በላይ ጊዜ ማባከን ስለሆነ አድርጋውም አስባውም አታውቅም፡፡ግን ማርገዞን አሁን ሰማች?
‹‹ ሊያጠፋኝ ከሚያሳድደኝ ሰው እና ልገድለው ቃታውን ብቻ መሳብ ከሚቀረኝ ሰው ልጅ አርግዤያለሁ ።ይሄ ፅንስ የወላጆቹን ስራ እያየ ምን እያለ ይሆን።?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡
ይህንን እያሰበች ያለችው ከሆስፒታል ወደቤት እየሄደች መንገድ ላይ ሆና ነው፡፡አሁን በዚህ ወቅት ከአደጋ መጠበቅና ከሞት የመትራፍ ፍላጎት አይደልም ያላት..እንደው በሆነ ተአምር ብን ብሎ የመጥፋት…ቢቻል በአስማት ቢሆንም የመሰወር …ወይ ደግማ አቧራ ሆኖ በመላው ምድር የመበትን ፍላጎት ነው ያላት፡፡.ልጅ በጣም ትፈልጋለች፡፡መውለድም ለረጅም ጊዜ ስታልመው የቆየችው ነገር ነው፡፡ሌላው ይቅር ከፕሮፈሰሩ ልጅ እንዲኖራት ስለት እስከመሳል ሁሉ ደርሳ ነበር…..ግን በዛ በምትለምንና በምትሳልበት ጊዜ ሳትፀንስ ለምን አሁን? ››ያ ነው እንቆቅልሽ የሆነባት፡፡፡
እቤት ደርሰው ስለነበረ አብዬት የመኪናውን ጡሩንባ ተጫነው.. ብዙም አላስጠበቋቸውም ..የውጪን በራፍ ከፈቱላቸው፡፡ገብቶ አቆመና …ተሎ ብሎ ከገቢና በመውረድ የእሷን በራፍ ከፈተላት፡፡እንዳለ የቤቱ ሰው እሷን ለመቀበል በረንዳውን ሞልተውታል፡፡የሰብለ ልጅ በእድሉ ድክ ድክ እያለ ከበረንዳ ሮጠና ተጠመጠመባት….ጎንበስ ብላ ጉንጮቹን እያገላበጠች ሳመችው….ሌሎቹም ከበረናዳው እየወረድ በደስታ ከበቧት…በመጠኑም ቢሆን የጨፈገጋት ስሜት እየበረደ ሲሄድ ተሰማት….የእሷ መጥፋት ይሄን ያህል ያስጨንቃቸዋል መፈታቶ ደግሞ ያስደስታቸዋል ብላ ግምት አልነበራም…እሷን ከፊት አስቀድመው ተከትለዋት ሳሎን ስትገባ ማመን አልቻለችም…በቃ አግብታ ወላጆቾ ቤት መልስ የተጠራች ነው የመሰላት..ሳሎኑ በተለያ ድሚ መብራቶችና ዶኮሬሽኖች ደምቆል፡፡ጠረጳዛው በምግብና በመጠጦች ተሞልቶል….ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ በትልቁ
ደ/ር በሰላም ወደቤትሽ ስለተመለሽ ደስ ብሎናል፡፡
እንወድሻለን፡፡ይላል…፡
ቆማ አነበበችና
‹‹በእውነት በጣም አመስጋናሁ… እኔም በጣም ነው የምወዳችሁ…››ሳግ ተናነቃት..ድሮም በቋፍ ነች ..ስቅስቅ ብላ አለቀሰች..በድሉና የእሷ ሰራተኛ ተከተለዋት በለቅሶ አገዞት...አብዬት አንገቱን አቀረቀረ..ሌሎቹ ትከሻዋን መታ መታ እያደረጉ ያፅናኗት ጀመሩ…ወደ መቀመጫዋ ይዘዋት ሄድና የእራት ፕሮግራሙ ተከናወነ ፣ከአብዬት ከካሳና ከዶክተሯ በስተቀር ሎሎቹ በደስታ ወደመጠጡ ተሸጋገሩ…
. ዶክተር ‹‹በጣም ስለደከማኝ ባርፍ ቅር ይላችኋል?››ስትል ሁሉንም በትህትና ፍቃድ ጠየቀች፡፡
‹ችግር የለም..አሁን ነፃ ነሽ ነገም ተነገ ወዲያም አብረን ነን.. ተነሽ ተኚ…››ፈቀዱላት፡፡
በዚህ ጊዜ ከሳ ለንቦጩን እንደጣለ ወደመኝታው ቀድሞ ተንቀሳቀ..ሆስፒታል ዝም ያለ እስከአሁን አንድ ነጠላ ቃል እንኳን አልተናገረም.እንደዛ በመሆኑ አብዬት አስደስቶታል ፡እራት ፕሮግራሙ ላይ የሆነ ነገር ዘባርቆ የልጆቹን ስሜት ልክ እንደነሱ ያደፈራርሰው ይሆን? በሚል ስጋት ሲሳቀቅ ነበር ያመሸው….ዶክተሯ ከኃላ ተከተለችው..፡፡
አብዬትም ‹‹እመጣለሁ ተጫወቱ ››አለና ዶ/ሯን ከኃላ ተከተላት፡፡መኝታ ክፍላቸው ከሚገኝበት አንደኛ ፎቅ ላይ እንደደረሱ ቆማ ጠበቀችውና‹‹አቢ አንድ ነገር ፈልጋለሁ ››አለችው፡፡
‹‹ምንድነው ?ጠይቂኝ ምን ላድርግልሽ?››ተንሰፈሰፈ
‹‹ላናጋረው ፈልጋለሁ››
‹‹ማንን..?ማለት መቼ?››
‹‹አሁን››
‹‹እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ››
ዝም ብሏት ቀድሟት ተራመደ… ከኃላው ተከተለችው…መጫረሻ ከሚገኙት ክፍሎች መካከል አንድን ከፈተና ‹‹አብሬሽ እንድገባ ትፈልጊያለሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ግድ የለም ብቻዬን ብሆን ይሻለኛል፡፡››
‹‹በቃ እዚሁ ኮሪደር ላይ ነው ያለሁት ..ስትፈልጊኝ ጥሪኝ› አላትና የበራፉን መግቢያ ለቀቀላት፤ አልፋ ወደውስጥ ገባች፡፡
ፌት ለፊቷ የምታየው ሰው እሱ መሆኑን ማመን አልቻለችም…ከግድግዳ ጋር ተበይዶ በተያያዘ ግዙፍ ብረት ጋር እጆቹ በሰንሰለት ወዲህና ወዲያ ተሰትረው ተንጠልለዋል፡፡ እግሮቹ ከተቀመጠበት ወንበር ጋር በተመሳሳይ ሰለንሰለት ተጠፍንጎ ስለታሰረ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ፊቱ በቦቅስና በጥፊዎች ብዛት ቆሳስሎና ተቦዳድሶ ሌላ መልክ ሰጥቶታል፡፡እላዬ ላይ የለበሰው ነጭ ሸሚዝ በደም ከመጨማለቁም በላይ ተቦተራርፎ ሲታይ ይቀፋል፡፡እሱ አንገቱን ድፍት አድርጎ ያንጎላጅጃል…፡.
ክፍል ውስጥ ያገኘችውን ባዶ ወንበር ወደእሱ አስጠጋችና በአንድ ሜትር እርቀት ላይ አስቀምጣ ተቀመጠችበት፡፡
‹እሺ….ፕሮፌሰር!!››
ድምፆን ሲሰማ ከገባበት ሰመመን እንደመበርገግ ብሎ ነቃአለና አይኖቹን ከፈተ….
‹‹አለሽ?››በሰለለና በደከመ ድምፅ ጠየቀት፡፡
ፐሮፌሰሩ ዶ/ራን እንዳያት ተገርሞልም ተደስቷልም፡እዚህ ቤት ታግቶ ከመጣበት ደቂቃ ጀምሮ እሷን ከአሁን አሁን ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ ነበር…እሱ ሊገድላት ወስኖ እያሳደዳት የነበረ ቢሆንም በሌላ ሰው ተገደለች ሚለውን ዜና ለመስማት ፈፅሞ ዝግጁ አልነበረም.ደግሞ ነገሮች እንዲህ ዝብርቅርቅ ብለው እሱም በገዳዬች እጅ ከገባ በኃላ የእሷ መገደል ለእሱ ምንም የሚያስገኝለት ፋይዳ እንደሌለ ገብቶታል፡፡ቢሆንም የእሷ የመታገት ዜና ውሎ ሲያድር ተስፋ ቆርጦ ነበር.ገድለው የሆነ ጥሻ ውስጥ እንደቀበሯት እርግጠኛ መሆን ጀምሮ ነበር.፡፡

አሁን ሲያያት አላመነም…እሱም እንዲህ በተአምር ከእዚህ እስር ወጥቶ ነፃ የሚሆንበት እድል እንዳለው ተሰማው.አዎ እሷ እድሉ ነች.፡፡ብቸኛ እድሉ.፡፡ቢያንስ ላሳለፍት በርካታ ጣፋጭ የፍቅር ጊዜያቶች ስትል ከእዚህ ጉድ ታወጣዋለች፡፡በዚህ አመነ፡፡እሷንም ሊያሳምናት ወሰነ፡፡ እንደምንም ተዳክሞና ተንጠፍፍፎ የነበረውን የውስጥ ኃይሉን አበረታ.
‹ይመስገነው እንደአንተ ሳይሆን እንደእግዚያብሄር አለሁ›››አለችው፡፡
‹‹በሰላም ስለተመለሽ ደስ ብሎኛል…አንቺንም እንደእኔ አድርገውሽ ይሆን? ብዬ ሳስብ ነበር››አላት .የተናገረው ከአንጀቱ ነው.እሷ ግን እንደማላጋጥ ነው የወሰደችው፡፡
‹‹አይ ፕሮፌሰር ፤በዚህ አይነት ቅጥፈትህ እኮ ለዘመናት ስታታልለኝና ስትጫወትብኝ ነበር፡፡ቢያንስ አሁን በዚህ ለመሞት ሳዕታት በቀረህ ቅፅበት አውነቱን ተናገር…እኔ እንደሆነ ምንም አይሰማኝም..እንዴት ትጠላኝ እንደነበር፣….ምን አይነት ርካሽ አሻንጉሊትህ እንደነበርኩ.. አዎ ጢባ ጢቢ መጫወቻህ እንደነበርኩና….በደደብነቴ ስትስቅብኝ እንደኖርክ ንገረኝ››
‹‹አረ ተይ…እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ….እውነት ነው ምልሽ ከእነዚህ ሰዎች በሆነ መንገድ ካዳንሺኝ የእድሜ ልክ ባርያሽ ነው የምሆነው››
እሱ የሚያወራውን ችላ አለችና የራሷን ወሬ ማውራት ጀመረች‹‹ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት አሞኝ ስለነበር አብዬት በግድ ሆስፒታል ወሰደኝ…ተመረመርኩ…ምን እንደተከሰተ እስኪ ገምት….?የሰባት ሳምንት እርጉዝ ነኝ…፡፡የሰባት ሳምንት ፅንስ በሆዴ አለ…ከማ ያው ከማን ይሆናል ታውቀዋለህ ካንተ..ያዛሬ15 ቀን በዛ አጋጣሚ ኤልያስ አስጠነንቅቆኝ ከእጃችሁ ባላመልጣችሁና ብትገድለኝ ኖሮ እኔና የአመስት ሳምንት ልጅህን ነበር የምትገድለው..››
ያለቸውን ሲሰማ በፊት እሷን ሲያይ ከነቃው በላይ አሁን ነቃ…..ይሄ ልጅ ለእሱ ተስፋውና ከዚህ ከገባበት ድቅድቅ ጨለማ የሚወጣበት ብቸኛ እድሉ እንደሆነ ተማመነበት…በውስጡ ፈነጠዘ፡፡
እሷ ንግግሮን ቀጠለች‹‹ሰሞኑን በታገትኩባቸው ቀናቶች እዛ የብቸኝነት ጉድጓድ ውስጥ ተወሽቄ ምን እየሠራው ያሰለፍኩ ይመስልሀል?።ስለበቀል ነበር የማስበው።አንተን ስለመበቀል። አዎ ስለአንተ ያለኝ ንዴት ልክ እንደነቀርሳ ሰውነቴን በልቶ ሊጨርሰው ነው። ቀድሞ ከወደድኩህ በላይ አምርሬ ጠልችሀለው።አየህ እድሜ ላንተ ይሁንና ጥላቻ ከፍቅር በላይ ጉልበታምና አስፈሪ መሆኑን ሰሞኑን በደንብ ተረድቼያለሁ። ስመጣ በእንቅፍ ውስጥ ገብተህ እያንጎላጅክ ነበር፡፡ እኔ አንተን ብሆን እንቅልፍ ለመተኛት አይኖቼን አልጨፍንም...በማንኛውም ሰዓት ድንገት ባለህበት ቦታ ደርሰው አንገትህን ቀንጥሰው እስከወዲያኛው ሊገላግሉህ የሚችሉ እኔን መሠል በርካታ ጠላቶች እያሉህ እንዴት ደፍረህ ልተኛ ትችላለህ?እንደሰው እንኳን ነፍሴን ለፈጣሪዬ አደራ ሰጥቼ ነው የማሸልበው አትለኝም፤ ምክንያቱም ከሚያሳድዱህ ሰዎች በፊት ያስቀየምከውና ያሳዘንከው አምላክህን ነው።በዛ የተነሳ አምላክህ ምንም እንኳን ልክ እንደኛ ሊያጠፍህ ባያሳድድህም ልናጠፍህ ስንንቀሳቀስ ግን ጣልቃ ገብቶ እንደማይታደግህ እርግጠኛ ነኝ።
እሱም የእሷን የምሬት ንግግር ችላ ብሎ የራሱን ማውራት ጀመረ፡፡‹‹ይሄ የእግዚያብሄር ተአምር ነው….እኔና እንቺ ለአመታት እንዴት ልጅ መውለድ እንፈልግ እንደነበር ትዝ ይልሻል አይደል፡፡… እኔም በጣም አብዝቼው ነበር..አየሽ ልጅ የተፀነሰው እግዚያብሄር ይቅር ሊለኝ ሲፈልግ ነው፡፡ በቃ አሁን እንደምንም እንዚህን ሰዎች አዘናጊና ከዚህ ይዘሺኝ ውጪ ፡፡ከዛ ይሄን ሀገር ጥለን እንጠፋለን፡፡ከዚህ ሁሉ ግርግር ተገልለን የፈለግሺው ሀገር ልጃችንን በሰላም እናሳድጋለን፡፡ደግሞ አትስጊ ሆስፒታሉ ቢወረስ እንኳን ግቢዬ ውስጥ የቀበርኩት መአት ገንዘብ አለኝ…አረ ገና ሌሎች ብዙ ልጆችም እንወልዳለን፡፡››
‹‹ግን ስንት ልጆች ነው መውለድ ምትፈልገው..?ማለት ከእኔ?››
‹‹ስድስት ልጅ….ገና አምስት ልጅ ይቀረናል፡፡››በራሱ መልስ ፈገግ ለማለት ቢሞክርም የቆሳሰለ ፊቱና ያበባጠ ከንፈሩ የፈለገውን ይህል እንዲፈግ አላደረገውም፡፡
‹‹እና ከእኔ ስድስት ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ?››
‹‹አዎ…ከፈለግሽም እንጨምራለን፡፡››
ንዴቷን መቆጣጠር ተሳናት…አንገቱን አንቃው እስከወዲያኛው ልታሰናብተው ፈለገች..‹‹አይ እሱማ እሱን መተባበር ነው..ከመሞቱ በፊትማ በደንብ መሰቃየት አለበት…ይሄ እንዲህ የመጨረሻ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንኳን ሳለማታለል እና ማጭበርበር ብቻ የሚያስብ ሰው ሊታዘንለት አይገባም››ስትል ወሰነችና ድንገት ከመቀመጫዋ ተነሳች… ወደበራፉ ተራመደች..ከፍታ ወጣች..በረንዳ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሰ ሲጠብቃት የነበረው አብዬት ሮጦ ስሮ ደረሰ›፡፡
‹‹ጨረሽ በቃ…?ልቆልፈውና እንሂድ?››
‹‹አይ የሆኑ እቃዎች ፈለጌ ነበር፡፡››
‹‹ምን ልስጥሽ?››
‹‹ፒንሳ አገኛለሁ?››
‹‹ለምን….?››አለ አብዬት ግራ ገብቶት.. ‹‹ሰንሰለቱን ልትበጥስለት ፈልጋ ይሆን እንዴ…?.የልጇ አባት መሆኑን ስታውቅ አሳዘናት ይሆን….?›ስል በውስጡ አሰበ ከእሷ መልስ ሳይጠብቅ‹‹ቆይ ላምጣልሽ ጠብቂኝ››አለና እዛው ከጎኗ የሚገኘው መሳሪያ ማስቀመጫ ክፍላቸው ውስጥ ገባ… አንድ መለስተኛ ፒንሳ አምጥቶ ሰጣት…ምንም ብታደርግ ምንም በውሳኔዋ ጣልቃ ላለመግባት ለራሱ ቃል ገብቶል፡፡አሁን ፈታው በፊት ለፊቱ ብትለቀው ወይም ተከትላው ብትሄድ እንኳን..በሀዘኔታ ከመመልከት በስተቀር ሊያስቆማት በፍፅም አይሞክርም፡፡ይሄንን ወስኗል፡
ያመጣላትን ፒንሳ ተቀበለችውና ‹‹ይቅርታ ..መቀስ አገኛለሁ?›› ብላ ጠየቀችው፡፡አሁንም ተመልሶ ሄደና ይዞላት መጣ፡፡
አመሰግናለሁ፡፡ብላ ወደውስጥ ገባችና በራፉን ከውስጥ ቀረቀረችው፡፡ከላይ የለበሰችውን ሻርፕ ከላዬ ገፈፈችና ቀጥታ ወደፕሮፌሰሩ በመቅረብ አፉ ውስጥ ጠቀጠቀችው….ምን ልታደርግ እንዳሰበች ግራ ስለገባው ተወራጨ ….ግን ደግሞ እራሱን መከላከል የሚችልበት ምንም አይነት እድል የለውም፡፡ ፀጉሯን ጠቅልላ የሰረችበትን ጨርቅ አነሳችና የጠቀጠቀችውን ሻርፕ ተንሸራቶ እንዳይወድቅ በጭንቅላቱ ዙሪያ አዙር አንድ ላይ አሰረችው፡፡ አሁን ቢጮህም ድምፅ ከዚህ ግቢ አልፎ እንደማይሰማ እርግጠኛ ሆነች፡፡፡

ምዕራፍ-20
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
//
አፉን በትክክል ድምፅ እንዳያወጣ እንዳደረገች እርግጠኛ ሆነች፡፡ ከዛ እግሩ የታሰረባቸውን ሰንሰለት ፈታችና አንድ ላይ ተቆራኝተው ተስረው የነበሩ እግሮቹን ለየብቻ ለይታ ወደግራና ወደቀኝ በለቃቅጣ ለየብቻ መልሳ አጥብቃ አሰረችው፡፡
ፕሮፌሰሩ አይኖች ፈጠው እንደህፃን ልጅ እንባ እያረገፉ ነው፡፡
እሷ ነገሬም ሳትለው…ወለል ላይ ያሰቀመጠችውን መቀስ አነሳችና አስተካክላ ወደ እሱ ቀረበች፡፡ በእግርና እግሩ መሀከል ገባች፡፡ ብልቱ አካባቢ ያለውን ሱሪውን በመቀሱ ተረተረችው፡፡ ሙሉ በሙሉ እስኪለያይና የውስጥ ፓንቱ እስኪታይ ድረስ ..ከዛ ፓንቱን ወደታች ጎተተችና ከላይ ጀምራ መሉ በሙሉ ወደታች ተረተረችውና ብልቱ እስከነፍሬው ወደውጭ ተዘርግፎ መውጣቱን ስታረጋጥ መቀሱን መልሳ ወንበሩ ላይ አስቀመጠችና ፒንሳውን ይዛ ቆመች፡፡እና ማውራት ጀመረች
‹ፕሮፌሰር ይሄንን ነገር ለማድረግ ፈፅሞ አላሰብኩም ነበር…. እንዴትስ ላስብ እችላለሁ?..እንደእዚህ አይነት ስራዎች እኮ በእኔ ሳይሆን በአንተ ተፈጥሮ ውስጥ ነው የሚገኙት..ግን አየህ አይደል..?እንዴት እንደቀየርከኝ..?እንዴት እኔንም ጭምረህ አውሬ እንዳደረከኝ…?አሁን ከእዚህ ቁጭ ብዬ ከአንተ ንግግረር እያደማጥኩ ሳለ ይሄንን ማድረግ አለብሽ የሚል ድምፅ በጆሮዬ ሹክ አለኝ..ምን አልባት አንተ ያስቀየምከው ያንተው ወዳጅ የሆነ ሰይጣን ይሆናል እንደዛ ያደረገው…..አንተ እንደዚህ ህይወቴን አመሰቃቀለህ….ስሜን፤ ስራዬን ገደል ከተህ…እናቴንና እህቴን እንደዛ አሰቃይተህ ካበቃህ በኃላም ከእኔ ስድስት ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ?፡፡ያማ አይሆንም፡፡ነገ ወይም ተነገ ወዲያ የሚገድሉህ ይመስለኛል፡፡ግን ከእነሙሉ ዘርህ ወደመቃብር መውረድ የለብህም..አንተ በቁም መመክን አለብህ..እንደአንተ አይነት አውሬ በሰው ልጆች መካከል ዳግም እንዳይፈጠር ያንተ ዘር መምከን የግድ ነው፡፡››
አብዬት በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ጆሮውን በራፍ ላይ ለጥፎ ያዳምጣል….ፕሮፌሰሩን በሰንሰለት ያሰረው እራሱ ባይሆን እንዲህ ተማምኖ ይሄን ሁሉ ሰአት አይቆይም ነበረ…የእሷ ድምፅ ብቻ ይሰማዋል…ለማንኳኳት ፈለገና የተወሰነ ደቂቃዎች ለመተገስ እራሱን አሰመነ፡፡
//
ዶክተር ፒንሳውን ቀስራ ወዲህና ወዲያ ተበለቃቅጠው በታሰሩ እግሮቹ መካከል ቁጭ አለች..ከአዚህ በፊት ብዙ ጊዜ በእግሮቹ መሀከል እንዲህ ተቀምጣ ታውቃለች..ግን ፍቅር ለመስራት ነበር፤ ደስታና እራካታ ፍለጋ፡፡አሁን ግን ድንበር በጣሰ የሲኦል ጥላቻ ነው በቦታው የተገኘችው፡፡ፒንሳውን በለቀጠችና በብልቱ ፍሬ መካከል አስተካክላ ያዘች፤ሰይጣን ባዋሳት ሀይል አንድ ላይ ጨምቃ ያዘችውና ወደግራና ወደቀኝ እየጠመዘዘች አሸችው፤ ለተወሰኑ ደቂቆች የኤሌክትሪክ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ ሟች ፍርደኛ ተንሰዘረዘረ ተንዘረዘረና እራሱን ስቶ ዝርግትግት በማለት አንገቱና ደፋ፡፡
የቆለጡ ቆዳ ተሞሽልቆ ሲነሳ እጇ በደም ተሞላ.. እጇን እያነከረፈፈችና እንደእብድ እየተወራጨች ከአካሉ የተቦጨቀ ቆዳ የያዘውን ፒንሳ ወለል ላይ ወርውራ ወደ በራፍ ሄዳ ከፈተችና አብዬት ደረት ላይ ተደገፈች..በእጇ የሞላውን ደም ሲያይ ደነገጠ …የሆነ ነገር የሆነቸ ነው መሰለው፡፡
‹‹ምን ሆነሻል ፣ምን አደረገሽ?››
እጇን በማራገፍ ደሙን ወለሉ ላይ እየረጨች ከጥልቅ ማለክለክ ጋር ‹‹ምንም አለደረገኝ ..እኔ ነኝ ያደረኩት››አለችና ሸርተት ብላ እዛው በራፉ ጋር ከውጭ በኩል ግድግዳ ተደግፋ ተቀመጠች..
አብዬት የሆነውን ሊያጣራ ወደውስጥ ገባ..ፐሮፌሰሩን ዝርግትግት ብሎ ፤አንገቱን ደፍቶ፤ አፍ ታሽጎ፤ ልብሱ ተበጣጥቆ በደም ተጨማልቆ ሲያገኘው‹‹..በቃ ገደለችው?››ሲል አሰበ፡፡ ተንደርድሮ ተጠጋውና ጣቶቹን ወደ አንገቱ ልኮ ሲያረጋገጥ ነፍሱ አለች..ቶሎ ብሎ አፍ ላይ የተጠቀጠቀውን ጨርቅ አላቀቀና አየር እንዲያገኝ አደረገ ..የእጅ ሰንሰለቱን ከተንጠለተለበት አላቀቀ….ከወንበሩ አወረደና መሬት ወለል ላይ አስተኛው፡፡ከክፍሉ በመውጣት መልሶ ከውጭ ቆለፈውና እሷን ደግፎ ከተቀመጠችበት አነሳትና ወደክፍሏ ይዞት ሄደ ….፡፡
ገፋ አድርጎ ሲገባ…አልጋዋ እንደተነጠፈ፤ መኝታ ቤቷም እንደፀዳ ነው..ይሄን እራሱነው የመምጣቷ ነገር እርግጠኛ ሲሆን ቀን ያዘዘውና በትክክል መሰራቱን ያረጋገጠው፡፡አሁን ያልጠበቀው ነገር ያጋጠመው ከአልጋው በታች ወለል ላይ ግዙፍ ፍራሽ ተዘርግቶሎ እላዩ ላይ ተጠቅልሎ የተኛ ግዙፍ ሰው ማየቱ ነው›
እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ምንድነው ይሄ?››አብዬት ተበሳጨ...እሷን ደግፎ አልጋዋ ጠርዝ ላይ እንድትቀመጥ ካደረገ በኃላ ወደተጋደመው ሰው ሄዶ የተጠቀለለበትን አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ገፎ ሲያየው ካሳ ነው
‹‹ወይ..!!እንዴት ሳላስበው?..ከዚህ ንክ ውጭ እንዲህ የሚያደርግ ሌላ ሰው ከየት ይገኛል?..አንተ ተነስ ››ቀሰቀሰው፡፡
አይኑን እያሸ ተነሰና‹‹ምን ያስጮህሀል››
‹‹ምን ትሰራለህ እዚህ….መኝታ ቤትህ ምን ሆነ?ጉንዳን ወይስ አይጥ ነው ያባረህ?››
‹‹ከአንተ በላይ አይጥ አለ እንዴ?እሷ ያለችበት ክፍል መተኛት ጥሩ ህልም ለማለም ጥቅም እንዳለው እዛ አብረን በነበርንበት ግዜ ተረድቼለሁ..››
‹‹አና››አለው አብየት ተገርሞ፡፡
‹‹እናማ..ከዛሬ ጀመሮ ከእሷ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ በዚህ አይነት ሁኔታ ነው የምተኛው…ለዛ ነው ፍራሼን ወደእዚህ አምጥቼ የዘረጋሁት፡፡››
‹‹ጅሎ እዚህ ከአንድ ሳምንት በኃላ አንኖርም..ሁላችንም በየቤታችን እንበታተናለን፡፡››
‹‹እናንተ ቅጥረኛ አሽከሮች ሰለነበራችሁ አዎ ጥቅማችሁ ስላበቃ በካልቾ ቂጣችሁ እየተጠለዘ ወደበፊት ድርዬነታችሁ ትበተናላችሁ.. እኔ ግን ከእሷ ጋር እሷ ቤት ነው የምሄደው… ከልሆነም እኔ ቤት ወስዳትና አኔ ክፍል አብረን እንተኛለን፡፡››
በጣም በተናደደበትና ግራ በተገባበት ወቅት ባይሆን አሁን እያየ እና እየሰማው ያለውን ነገር በጣም ያስቀው ነበር…
ዶ/ር በሁሉ ነገር የተሰላቸ በሚመስስ ስሜት‹‹አቢ ተወው ይተኛ››አለችው…
‹‹ይሄው ሰማሀት አይደል.?.ተወኝ አንተ ቀፋፊ….ደግሞ ልብህን መንቅራ አውጥታልህ ነው እንዴ እንዲህ እጇ ደም በደም የሆነው?›› አለና ሌላ መልስ ሳይጠብቅ የተገፈፈውን አልጋ ልብስ መልሶ ሙሉ በሙሉ ተጠቀለለና ወደእንቅልፉ ተመለሰ፡
አብዬትም ለካሳ መልስ መስጡን ችላ ብሎ ወደእሷ ዞረና ‹‹አሁን ግቢና ሻወር ውሰጂ›››እኔ ሰውዬውን አይቼው ልምጣ…በእንዲህ አይነት ሁኔታ መሞት የለበትም››አላትና ወጥቶ ሄደ፡፡
እሷም ቀጥታ ወደ ሻወር ቤት ገባችና ተስተካክላ ቆመች…. የሻወሩን ቀዝቃዛ ውሀ ከፈተችው ከነልብሷ ያረሰርሳት ጀመር… ወደታች በእግሮቾ እየተንኳለለ የሚወርደው ውሀ በደም የተበረዘና የደፈረሰ ነው..ቅፍፍ አላት፡፡

አቢዬት ከእሷ እንደተመለሰ ቀጥታ ወደታች ወርደ ..ሁሉም እየጠጡና እየተጫወቱ ፈንጠዚያ ላይ ናቸው፡፡ ሊረብሻቸው አልፈልገም፡፡ ፈንጠር ብሎ የተቀምጦ የሚቆዝመውን ቶላን በምልክት ጠራው ።ያንን የሠማይ ስባሪ የሚያህል ሰውነቱን ይዞ ሲቆም የሳሎኑን ኮርኒስ በጭንቅላቱ ሊነካ ጥቂት ነው የቀረው አብዬት ፊቱን አዞረና ደረጃውን ወደ ላይ መውጣት ጀመረ...ቶላ ከኃላ ተከተለው..ፕሮፌሰሩ ያለበት ክፍል ደረሱት ከፍተው ወደውስጥ ገብ...ዝርግትግት ብሎ በደም እንደተጨመላለቀ እረሱ ስቶ ወለል ላይ እንደተዘረረ ነው።"አብዬት ጎንበስ አለና እግሩን የታሰረበትን ሰንሰለት ቁልፉን በማላቀቅ ፈታለትና እግሮቹን ነፃ አደረጋቸው።የእጆቹን ሰንሰለት ቅድም ነው የፈታለት ።ቶላ የክፍሉ መአከላዊ ስፍራ እንደቆመ ቁልቁል አዘቅዝቆ እራሱን የሳተውን ፕሮፌሰር ያለምንም የስሜት ለውጥ እያየው ነው።በእሱ ቦታ ማንሞ ቢሆን፤ ምን ሆኖ ነው?ለምንድነው በደም የተሸፈነው? ለምንድነው እራሱን የሳተው ?የሚሉ አያሌ ጥያቄዎችን ያቀርብ ነበር..እሱ ግን እንደዚ አይዳዳውም ፡፡ በማይመለከተው ነገር አይገባ።ካልጠየቁት አይመልስም። እንደውም ጠይቀውት እራሱ ብዙ ጊዜ አይመልስም።በዚህም ባህሪው አብዬት በጣም ይወደዋል።
‹‹ወደእኔ ክፍል እንድንወስደው ፈልጌ ነው"
ስሩ ተንበረከከና እንደሚታቀፍ ህፃን ልጅ እጆቹን በጀርባው ሰቅስቆ ለማስገባት መሞከር ጀመረ‹‹ ምን እያደረክ ነው?"
"እራሱን ስቶ የለ ላቅፈው ነዋ።››
"አይ እንደዛ አይደለም ..እግሩ መሀከል ስለቆሰለ ይበልጥ እንዳይጎዳ አብረን ነው የምንይዘው"
"እሺ"አለና ወደ ጭንቅላቱ ሄደና ግራና ቀኝ ብብቱ ውስጥ ግዙፍ የእጅ መዳፎቹን አስገባና ያዘው።አብዬት ሁለት እግሮቹን እርስ በረስ እንዳይፍተጉ እየተጠነቀቀ ያዘው ፡፡ወደላይ አንጠለጠሉትና ከክፍል ይዘውት ወጡ፡፡ወደአብዬት ክፍል አመሩ ፡፡ደሙ በመንገዳቸው ሁሉ እየተንጠባጠበ የቤቱ ወለል ላይ የራሱ መስመር ሰርቶ ነበር፡፡እንደደረሱ ከፍ አደረጉና አስተካክለው ምቹው አልጋ መሀከል ላይ አስቀመጡት።
አሁን የአንተ ሀላፊነት ይሄን ሰው እስኪነጋ መጠበቅ ነው አለው አብዬት ለቶላ
"ችግር የለም"አለና መግቢያው ጋር ካለች አንድ ደረቅ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ.፡፡. አብዬት ስልኩን አወጣና እየደወለ ወጣ።
‹‹ሄሎ ዶክተር..."
"እባክህ ሆስፒታል መውሰድ የማልችለው አንድ የተጎዳ ሰው እጄ ላይ እራሱን ሳተ"
"አዎ አሁን ልወስድህ እየመጣሁ ነው"
"አዎ እራሴ ነኝ የምመጣው...በሀያ ደቂቃ ውስጥ እቤትህ በራፍ ጋ እደርሳለሁ።
"አመሠግናለሁ ዶክተር..."ዘጋውና መኪና ውስጥ ገብቶ ግቢውን ለቆ ወጣ፡፡ ይሄን ዶክተር የረጂም ጊዜ ወዳጅ ስለሆነ ለእንደ እዚህ አይነት ጉዳይ በሚስጥር ጠባቂነቱ የሚተማመንበት ብቸኛው ሰው ነው።

❤5
ጨረቃ 🌕
ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ
እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ
ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ
አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ
ቀና ብዬ አይቻት
ስላንቺ ነገርኳት
ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት
አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት
@tibeb145
ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ
እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ
ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ
አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ
ቀና ብዬ አይቻት
ስላንቺ ነገርኳት
ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት
አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት
@tibeb145
❤6
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-21
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
ማለዳ 12 ሰዓት ነው ከእንቅልፎ ነቅታ ካሳ እዛው በተኛበት ፍራሽ ላይ ሲገላበጥ ትታው ከክፍሏ የወጣችው…. ከአንደኛ ፎቅ ሳትወርድ ወደባልኮኒው ሄደችና ውጪውን አሻግራ ማየት ጀመረች፡፡የጥዋቷ ጸሀይ ገና ከማደሪያዋ ልውጣ ወይስ ትንሽ ልቆይ እያለች ከራሷ ጋር ሙግት የገጠመች ይመስላል፡ማዶ የሚታዬትን የተገጠገጡ ኮንደሚኒየም ቤቶች በመደመም ፈዛ መመልከት ጀመረች፡፡
‹‹በእውነት መንግስትና ሆነ ግለሰቦች ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የገነቦቸው የቤት ብዛቶች በተለይ በአዲስአባ ከባለፈው መቶ አመት ከተገነቡት ይበልጠሉ፡ግን ደግሞ የቤት ጥሙ የህብረተሰቡን ጉሮሮ እንዲሰነጠቅ ከማድረገግ ባለፈ ጥቂት እንኳን እርካታ ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ ይህ በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሚታይ ሀቅ ቢሆንም በአዲስአባ ግን በመቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡የዚህ ምክንያት መንግስትና ግለሰቦች በአንድ ላይ እቤት የመስራት አቅማቸው ወደ አዲስአባ ከተማ በየጊዜው እየተሰደዱ ከሚገብትና ከሚወለድባት የሰዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር የሀይቅና የኩሬ ያህል ልዩነት ስላለው ነው፡፡
መሀል አዲስ አባ በኪራይ ቤት እየኖረ አራት ልጅ የወለደ ጎልማሳ የቀን ህልሙና የቀን ቅዣቱ የኮንደሚኒዬም እጣ ቢሆን ማን ይፈርድበታል..?ይሄ ሰው በአጋጣሚ እድላም ሆኖ እጣው ቢደርሰውና ልጆቹን ይዞ እዛ ቤት ቢገባ …በሚቀጥሉት 50 አመታት እነዛ ልጆቹ ከተማ ከልቀየሩ አዲስአባ ውስጥ ሌላ ቤት ሰርተው ወይም ገዝተው እቤቱን ለአባታቸው ለቀው መውጣታቸው ስንት ፐርሰንት የሚሳካ ነው?፡አሁንም እኮ በ40 አመቱ ከእናቱ ጋር የሚኖር ወይም የምትኖር የአዲስአባ ጎልማሳ ቁጠራቸው ቀላል አይደለም..እናም ደግሞ አይደፈረድባቸውም..
እስከአሁን ስለምን እያሰበች እንደሆነ ወደቀልቦ ተመልሳ ስታስብ ፈገግ አለች.‹‹.ያሉበትን ሁኔታ መቀየር አስተሳሰብንም እንዲህ ይቀይራል እንዴ?›› አለች..እስከዛሬ እኮ አሁን ከላይ ለረጂም ደቂቆች ያመነዠገቻቸውን ሀሰቧች ከዚህ በፊት እንደው ለሰከንደ ሽርፍራፊ እንኳን በአእምሮዋ በራፍ ሽው ብለው አያውቁም፡፡
ከዛ ከፊት ለፊቷ ግቢ የሚሰማት የቆ.ቆ…ድምፅ ቀልቧን ሳበውና ትኩረቷን ወደእዛ ላከች.ግቢው ጥግ ላይ አንድ ሰርቢስ ቤት አለ.፡፡ፊት ለፊት ወደመውጫው በራፍ ተጠግቶ አንድ የሚሊኒያ ዛፍ ይታያል….ዛፉ እጅግ ተመችቶት ቁመቱ እሷ ባለችበት የፎቅ ወለል ትክክል ሊሆን ትንሽ ነው የቀረው፡፡አዎ ድምፅን ከዛ አካባቢ መስማቷን አረጋገጠች…፡፡እታቸ ቂጡ አካባቢ የዛፍን ዙሪያ እየዞረ በሚያብረቀርቅ መጥረቢያ ባለ በሌለ ጉልበቱ ይለዋል፡፡፡ቋራጩ ከስር በመታው ቁጥር ጉማጅ ጉማጅ የዛፉ አካል እየተቀረፈ መሬቱን ይሞላል… ዛፉን ከስር በመታው ቁጥር የዛፉ ቅርንጫፎች ከላይ ሲላጉና ቅጠሎቹም ከመሀከል እየተቀነጠሱ ሱረግፉ ይታያሉ…
የቅርንጫፎቹ መንቀጥቀጥ ዛፉ ለራሱ ሞት የሚያሰማው ሙሾ መሰላት፤ የቅጠሎቹ መርገፍ ደግሞ ከዛፉ አይን ሚንጠባጠብ የምሬት እናባ አድርጋ ነው የወሰደቻ፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለ፡
ይሄ ዛፍ እዚህ ለመድረስ ብዙ ጥሮል ...ስሮቹን ከምደር ከርስ አርቆ ለመቅበርና አስተማማኝ ውሀና የምግብ አቅርቦት ለማግኘት ምን አልባት አመታት ፈጅቶበታል፡፡ከዛም አልፎ ከስር ውሀና መአድናትን ተሸክሞ ለእያንዳንዱ ግንድ ቅርንጫፍና ቅጠሎች በየቀኑ ለማድረስ ምን ያህል አታካች መንገድ ተጉዞል?፡፡አሁን ደረጃው የዝናብ መዘግየት በቀላሉ የማያጠወልግበት…በሀይለኛ ንፋስ ተገፍቶ የማይወድቀበት የፀና መሰረት ላይ ደርሶ እፎይ ማለት ሲጀምር አንድ ግዴለሽ ዛፍ ቆራጭ ገና ፀሀይ በቅጡ እንኳን ሳትወጣ በዚህ ለሊት መጥቶ በሀያ ደቂቃ ውስጥ እንዳልነበረ ሲያደርገው በእውነት ልብ ይሰብራል…እንባዋ ረገፈ….ሰገነቱን ለቃ ወደታች ወረደች…ይሄ እንግዲህ እሷም የማታውቀው አዲሱ ማንነቷ ነው..በፊት እሰከመፈጠራቸውም የማታውቃቸው ነገሮች አሁን የእሷ ዋነኛ የልብ ህመም መሆን ጀምረዋል…ዞሮ ዞሮ ግን ምክንያትና ሰበብ እየፈለገች የምታዝነው ለራሷ ህይወት ነው….
ሁለት ሰዓት ሲሆን ሁሉም አንድ ላይ ሆነው ሳሎን ተቀምጠው ቁርስ እየበሉ ሳለ ቴሌቪዝኑ እነሱን የተመለከተ ዜና ያወራ ጀመር ..ድምፅን ጨምረው ሲያዳምጡ አቶ ሙሉ በቪዲዬ ተቀርፆ ለሚዲያ ሰዎች፤ለፖሊስና ለሚመለከተው ሁሉ እንዲበተን የተደረገው መረጃ ተተንትኖ እየቀረበ ነው፡፡ከዛ አንድ ሚኒስቴር ..ሁለት ዳሬክተሮች…ከአራት በላይ የፖሊስ አዛዦችና ዘጠኝ ፌዴራል ፖሊሶች ከየቦታው እየተለቀሙ ካቴና እጃቸው ላይ እየተጠለቀ ወደፖሊስ መኪና ሲገቡ ታየ….የሰው ቁጣና ደስታ መቀረብ ጀመረ....ሁሉም ዶ/ር ሰጲራን እንደጀግና ያንቆለጳጵሳታል.. ይህ ሁሉ የእሷ ጀግንነት እና በወንጀል እልተባበርም ብላ የገዛ እጮኛንም ጭምር በመቃወም ህይወትንም ጭምር መስዋዕት የሚያስከፍል ፊልሚያ ውስጥ ገብታ በቆራጥነት በመፋለሞ የተገኘችም ውጤት ተደርጎ ተወሰደ… ለዚህም ጀግንነቷ ዘላለማዊ ሀውልት ሊቆምላት የሚገባ ጀግና እንደሆነች ብዙዎች ተናገሩ …በስተመጨረሻም ሼክ ጠሀ ሆሲፒታሉን ወክለው ሲቃ እየተናነቃቸው ለህዝብ ያግዙን ጥሪ አቀረቡ…ዶ/ሯን በመፈለገ የኢትዬጵያ ህዝብ ሁሉ አንዲተባበሯቸውና አሁንም የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት እየጠበቃቸው እንደሆነ ተነገሩ፡፡…ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ
‹‹ይሄ አጭበርባሪ ሽማግሌ አየህልኝ…?ፍፅም ፃድቅ እኮ ነው የሚመስለው፡፡››
‹‹እሱን ለእኔ ተይልኝ……የሚገባውን ቅጣት በቅርብ እሰጠዋለው….በቅርብ››አላት አብዬት
ቁርስ እንደተጠናቀቀ የቤት ሰራተኛዋን ከበብሽን ጠራችና የመኖሪያ ቤቷን ቁልፍ ሰጥታት እቤት ሄዳ እቃ እንድታመጣለት ላከቻት፤ ተመልሳ ስትመጣ ሰው እንዳልተከተላት እንድታረጋግጥ አብዬት አስጠነቀቃት።ከዛ ሁሉም ወደስራቸው እንደተበታተኑ ሳሎን ውስጥ አብዬትና ዶ/ር ብቻ ቀሩ።ወደእሷ በደንብ ተጠጋትና
"ምን እናድርግ ?"አላት
የደነዘዘ አእምሮዋን ለማንቃት እየጣረች"ስለምኑ?"ስትል መልሳ ጠየቀችው።
‹‹ስለ ሁሉ ነገሮ ነዋ… ሰዎቹን ምን እናድርጋቸው?"በዚህ አይነት ብዙ ልንቆይ አንችልንም።ያንቺን መጨረሻ ለማወቅ ህዝብ በጣም ስለፈለገ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረገ ነው። እያንዳንዶ ሰፈር እየተፈተሸች ነው።በዛ ላይ አንቺን ያገኘ የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት ብለው እኛ ሽማግሌ አውጀዋል።እየዋለ ሲያድር ከእኛው ሰዎች መካከል እራሱ ማን እንደሚያፈነግጥ መገመት አይቻልም...ብር የማያታልለው ሰው የለም...ካልፈጠን ውስብስብ ችግር ውስጥ እንገባለን። ማለት ዛሬ ማታ እነዚህን ሰዎች አንድ ነገር ማድረግ አለብን..."
"ታውቃለህ እኔ እድለኛ ነኝ፡፡"
"እንዴት?"
"አንተ ስላለህልኝ ነዋ...ከጓኔ ሆነህ የእኔን ጦርነት ስለተፋለምክልኝ...ተፋልመህም እንዳሸንፍ ስላደረከኝ በጣም አመሰግናለሁ።››
"ይሄ የአንቺ ብቻ ሳይሆን የእኔም ጦርነት ነበር...ደግሞ አብረን ነው የተፋለምነው፤እና አብረን የመጨረሻውን ስኬት መደምደሚያ እንድናበጅለት እየጠየቅኩሽ ነው።››
"ታውቃለህ በሙሉ ልቤ የምተማመንብህ ታላቅ ወንድሜ ነው የምትመስለኝ፤ደግሞ ወንድም ኖሮኝ አያውቅም ።እና እንዴት አይነት ፀጋ እንዳጣሁ እንዳስብ አዶርገሀኛል።ደግሞም ይሄ ነገር ቢገባደድም፤የእኔና የአንተ ዝምድና የሚገባደድ አይሆንም። ማለት አንድ ላይ የምንሰራው ስራ መኖር አለበት።ጓደኞችህንም የሚያሳትፍ ንፅህና መልካም ስራ..ከአሁኑ አስብበት።››
"የሆስፒታልሽ ሰኪሪቲ እንሁን እንዴ?"አላት በቀልድ

"በፍፅም፤እኔ ዳግመኛ ወደእዛ ሆስፒታል አልመለስም...አእምሮዬ ንፅህ ሆኖ በተረጋጋ መንፈስ በሽተኞችን ማከም የምችል አይመስለኝም።እና ደግሞ ከዛ ሽማግሌ ጋርም የጋራ ቢዝነስ እንዲኖሰኝ አልፈልግም..ሙሉ ያለኝን የአኪሲዬን ድርሻ እሽጥና የእኛ የራሳችን ድርጅት እንከፍታለን።
"ስለእሱ ለማሰብ በቂ ጊዜ አለን …አሁን የሠዎቹ ጉዳይ ነው አሳሳቢው።"
"ምን እናርጋቸው?"
"ውሳኔው ያንቺው ነው ..እናስወግዳቸው የምትይ ከሆነም ችግር የለውም..ለህግ ተላልፈው ይሰጡ የምትይ ከሆነም"
"ግራ ገባኝ እኮ...እነሱን ለህግ አሳልፎ መስጠትም ለእነሱ ድል ነው፤እነሱን መግደልም ያው ከእነሱ ጋር አንድ መሆን ነው››
‹‹እኔ በፍቃደኝነት እራሳቸውን እንዲያጠፍ ነበር እቅዴ ...አሁን ግን ያ ሚሰራ አይመስለኝም… በተለይ ለኘሮፌሰሩ››
"ለምን?››
‹‹ አንደኛ የፅንሱ ጉዳይ አለ (ምንም ቢሆን የልጅሽ አባት ነው) ወደፊት ለልጅሽ ምን ብለሽ ትነግሪዋለሽ።ሌላው እኛም ትንሽ ደብድበነዋል አንቺ ደግሞ አቆሳስለሽዋል..በዚህ አይነት ሁኔታ እራሱን አጥፍቶ ሬሳው ቢገኝ ምርመራ መደረጉ አይቀርም፤ምንም እንኳን የበሰበሰ ወንጀለኛ ቢሆንም በግለሰብ እጅ በዚህ መጠን እንዲሰቃይ ህግ ስለማይፈቅድ ዞሮ ዞሮ መጠየቃችን አይቀርም።"
"ሙሉስ?"
"እሱ እንኳን ጥፊም አላረፈበትም ... "
"እንግዲያው አንተ የመሠለህን አድርግ...እኔ በአንተ ውሳኔ እስማማለሁ…አሁን ደክሞኛል ትንሽ ልረፍ"
"አዎ ተነሽ እረፊ..."
///
አይገርምም ግን አንዳንዴ የእግዜር ስውር እጆች ሳስብ እደነቃለሁ።ጠላቴን ለማጥፍት ቀስቴን አዘጋጅቼ ነበር ። የቀስቴንም ጫፍ ከበረሀ እባብ የተቀመመ በሁለት ደቂቃ ውስጥ አፍርጦ የሚገድለው መርዝ በጥንቃቄ ጫፍን ቀብቼ አነጣጥሬ ኢላማዬ ውስጥ እስኪገባ በእጆቼ ወጥሬ በአይኖቼ አጨንቁሬ እየጠበቅኩት ነበር...ግን ድንገት ደመና በሌለበት ዶፍ ዝናብ ዘነበና መርዙን ከጫፉ አጠበው ..አሁን ምን ላድርግ ?። ተረጋግቼ ማሰብ አለብኝ እቅዴን መከለስ አለብኝ።ይሄንን እያሰበች ያለችው ክፍሏ ቁጭ ብላ ነበር ..ከዛ ከበቡሽ እቤቷ ሄዳ ያመጣችላትን ቦርሳ አነሳችና ከፈተች…ውስጡ ያሉትን እቃዎች በጠቅላላ ውስጡ ተወችና አንድ ኪኒን ብቻ ከመሀከሉ አንስታ መኝታ ከፍሏን ለቃ ወጣች፡፡ቀጥታ ፕሮፌሰሩ ወደሚገኝበት የአብዬት ክፍል ነው ያመራችው፤ገፋ አድርጋ ገባች፤ፕሮፌሰሩ እግሮቹን ወዲህና ወዲያ ማዶ አንፈርክኮ አይኖቹን ወዲህና ወዲያ በፍረቻ የያወራጫ ተጋድሞል....ቶላ በራፉ ጋር ባለ ወንበር ቁጭ ብሎ እየጠበቀው ነው፡፡
‹‹ቶላ አንዴ ይሄንን ሰውዬ ማናገር እፈልጋለሁ ውጭ ትጠብቀኛለህ››አለችው
.ምን አልተናገረም…ብድግ ብሎ ወጣና በረንዳው ላይ ከውጨ በኩል ቆመ፤ እሷ ከውስጥ በራፉን ቆለፈችው … .አልጋው ላይ የተሰተረው ፕሮፌሰር ተስፋ ቆረጠ…. በቃ ልትጨርሰው እንደመጣች እርግጠኛ ሆነ…፡፡
‹‹እሺ ፕሮፌሰር ተሸለህ..?ወንበሩን ይዛ ወደእሱ ተጠጋችና በሁለት ሜትር እርቀት አስቀመጠችው.ረጋ ብላ ተቀመጠችበት
‹‹አረ በፈጠረሽ..አሁን ደግሞ ምን ልታደረጊኝ ነው?››
ምን አደርግሀለሁ.. አሁን ኮ ጥቅም የሌለህ ሙትቻና እሬሳ ሆነሀል…ከወር በፊት በዚህ ሀገር በጣም የተከበረክ ሙሁር….እጅግ የተሳከለት የቢዝነስ ሰው….ሙሉ ጤና የነበረህ ውብና ሽቅርቅር ሰው ነበርክ..ግን ዛሬ ተመልከት… መሁርነትህ መክኖ፤ ዝናህ ተኖ፤ ጤናህ ታውኮ ፤ውበትህ ይሄው እንደማየው ከስሞ አልባሌና ተራ ሰው ሆነሀል…ይሄም ሊሆን የቻለው በማን ነው በአንተው ስግገብግብነት..
አየህ አንዳንዴ የሰላ ጭንቅለትና አሰላሳይ አዕምሮ ስላለን ልዩ ሰዎች ነን ማለት አይደለም..ስለምንድነው የምናሰላስለው ?ችሎታችንን ለምን ጉዳይ እየተጠቀምንበት ነው….?ብለን ቆም ብለን አስበን እንደው በጊዜያዊ ፍላጎታች ተገፋፍተን መንገድ ስተን እንኳን ከሆነ ወዲያው እራሳችንን ገምግመን ወደትክክለኛው መንገድ በጊዜ መመለስ ካልቻልን የእኛ ምሁርነት የእኛ አዋቂነት ምንደነው እርባናው…?
ሰው ያለውን እውቀት ፤ዝናና ስልጣን በአግባቡ ካልተገለገለበት…ፕሮፌሰር ሆነ ሚኒስቴር ፤ሼኪ ሆነ ቄስ….ጀኔራል ሆነ ካፒቴን ያው ሄዶ ሄዶ ለውርደት ተዳርጎ ተራ ሰው ሆኖ እንዲህ እንደአንተ ተልከ ስክሶ መቅረቱ አይቀርም..እነዛ ሰሞች አነዛ ማዕረጎች በሚገባ ለሚጠቀምባቸውና በምስጋና ለሚያገለግልባቸው ብቻ ነው እስከመጨረሻው በክብር አብረውት የሚቆዩት፡፡ዳሩ ይሄንን ሁሉ ለአንተ መለፍለፉ ምን ይረባል….በዛ በሰላሙ ጊዜ በፍቅር እያነባው ከድርጊትህ እንድትታቀብ ስማፀንሀ ጥቂት እንኳን ሰምተሀኝ ቢሆን ዛሬ ባንተም ሆነ በእኔ ላይ ይሄ ሁሉ ጥፋትና ውድመት አይፈጠርም ነበር፡
ፕሮፌሰሩ የደ/ሯ ንግግሯን የደከመ መንፈሱን እየሰባበረው ነው…ምንም ትክክል ያልሆነ ንግግር አልተናገረችም፡፡
‹‹ትክክል ነሸ ..ላደረኩት ነገር ሁሉ በጣም አዝናለሁ…መኝታ ቤቴ አልጋዬ ያለበት ቦታ ላይ ወለሉ የሚነሳ ነው.. እዛ የተቀበረ መቶ ሚሊዬን የሚጠጋ ብር አለ…አንድ ነገር ከሆንኩ አስቆፍረሽ ውሰጂው…እቤቱም ያለው ባንቺ ስም ነው…ለሰርጋችን ስጦታ ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ነበር ባንቺ ስም ያዘዋወርኩት…እና እቤቱም ሆነ ብሩ ለልጄ ይሁንልኝ፡፡
‹‹ልጅህ …››በእጇ የያዘችወን መድሀኒት አሳየችው….አይኑን አፍጦ… .‹‹ምንድ ነው?›› አለት..ከእይታው .ሰለራቀ መለየት አልቻለም፡፡ችግሩን ስለተረዳች ወደ እሱ በደንብ አስጠጋችለት››
የኪኒኑን ምንነት ሲረዳ ሰውነቱ ተንዘረዘረ‹‹አይሆንም…እንዳታደርጊው በፈጠረሽ››
ድምፅንና ጉልበቱን ከየት እንዳመጣው አያውቅም..አጓራ..ተማፀናት፡፡
እሷ ግን በእሱ መቃተት እየተደሰተች… ኪኒኖቹን ከእሽጉ ማውጣት ጀመረች..
‹‹አይሆንም ...በፈጠረሽ..››አልጋው ላይ እንዳለ እጅን ዘርግቶ መድሀኒቱን ሊነጥቃት ቢሞክርም ሊደርስባት አልቻለም… መንጠራራቱን ሲጨምር ከአልጋው ላይ ተንደባለና ወደቀ ..የብልቱን ቁስል በእግሮቹ ስለተጨፈለቀ በስቃይ ድምፅ አጎራ…

ምዕራፍ-22
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
የሻወር ቤቱ በር ተከፈተ..አብዬት ከውስጡ ወጣ…
.ዶ/ር ማንም እቤት ውስጥ ይኖራል ብላ አልጠበቀችም ነበር..ፕሮፌሰሩም ተኝቶ ስለነበረ አብዬት ምን ጊዜ ወደ ሻወር ቤት እንደገባ አያውቅም…ሻወር ቤቱ ተከፍቶ ከውስጥ ሲወጣ ሲመለከተው .. አምላክ መላዐክ እንደላከለት ነው የተሰማው፡፡
አብዬት ሻወር ቤት ለመታጠብ ገብቶ ልክ ጨርሶ ልብሱን እየለበሳ ሳለ ነበር የዶክተሯን ድምፅ የሰማው..ከዛ ወጥቶ ሊረብሻት ስላልፈለገ እዛው መቆየትን ወስኖ ነበር የዘገየው...አሁን ግን ጪኸትና ማጎራት ሲሰማ ሰውየውን የጨረሰችው መስሎት ከሻወር ቤት ወጣ
‹‹ምንድነው? ምን ተፈጠረ…?ተንደርድሮ ፕሮፌሰሩን ለማገዝ ወለሉ ላይ ተንበረከከ…
‹‹እባክህ እኔን ተውና ከእሷ መድሀኒቱን ተቀበላለት?›
‹‹የምን መድሀኒት ነው?›
‹‹ዝም ብለህ ተቀበላት…››ተንደርድሮ ተነሳና ስሯ ደረሰ ..መዳፏ መካከል የኖረቻቸውን አራት ፍሬ ኪኒኖች ለመዋጥ አጆን አየር ላይ አንዳንጠለጠለች ተሸከረከረና እጇን በካራቴ ሲጠልዘው ኪኒኖች ቤቱ ጥጋ ጥግ ተበታተኑ…እሷ ክው ብላ ደነገጠች..እጇን በጣም አመማትና እንዳንከረፈፈች ከመቀመጫዋ ተነስተታ ቆመች
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?ለዚህ አውሬ ብለሽ እራስሽን ልታጠፊ ነው?››
‹‹ለማን ብዬ?››
‹‹ታዲያ ኪኒኑ ምንደነው?››
‹‹የእሱን ልጅ የሚገድል ነበር…ፅንስ ለማስወረድ የሚያግዙ መድሀኒቶች ናቸው››
‹‹አንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ…?.ነይ በይ አግዢኝ.. ሰውዬውን እናንሳው.››
ተጋግዘው ወደ አልጋው መለሱት
በንዴት ‹‹ቁጭ በይ…›ብሎ ወንበሩ ላይ ተመልሳ እንድትቀመጥ.አደረገና እሱ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ..
‹‹ዶ/ር በጣም እያበሳጨሺኝ ነው…አሁን አንድ ነገር ብትሆኚስ? ደግሞ ልጅ ምን ባጠፋ ነው እንዲህ አይነት ቅጣት ሚደርስበት…?ይሄ ልጅ ይወለዳል…ሰምተሺኛል አይደል ይወለዳል… በቃ ይሄ የእኔ ውሳኔ ነው…ይሄ ሰውዬንም ሆነ ሙሉን ዛሬ ማታ ለህግ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡››
‹‹ምን?›› አሉ ሁለቱም፡፡
‹‹አዎ ..ባንተ ውሳኔ እስማማለሁ አላልሺኝም?››
‹‹አዎ ብየሀለው….ግን እንዲህ ቆሳስሎ ፖሊሶች ሲያገኙት ምን ይላሉ..እራስህ እኮ ነህ እንደሚያስጠይቀን የነገርከኝ?›
አዎ ግን ለዚህ መፍትሄ አለው ..እሺ ፕሮፌሰር ምን ትላለህ…?ልጅህ እንዳታስወርደው ከልፈለክ …ይሄ የደረሰብህ ነገር ሁሉ ከዶክተሯ ጋርም ሆነ ከእኛ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ቃልህን ለመስጠት ትስማማለህ?››
‹አዎ.እኔ ልጅ መውለድ ምን ያህል እንደምፈልግ እሷ ታውቃለች…እኔ በዚህ ምድር ብቸኛ ሰው ነኝ…..ወላጆቼንም ዘመዶቼንም አላውቅም… በዘንቢል መንገድ ዳር ተጥዬ የተገኘው..ከዛም በማደጎ ቤት ብዙ ስቃይና ችግር እያየው ያደኩ ሰው ነኝ…በዛም የተነሳ ብዙ ልጆችና ትልቅ ቤተሰብ የመመስረት ከፈተኛ ፍላጎት ነበረኝ….ይመሰለኛል ለዛም ነው እንዲ ስግብግባና ማልጠግብ የሆንኩት..ለማንኛውም ለዚህ ልጅ ስል አደርግ ያላችሁኝኝን ሁሉ ያለማቅማማት አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ሰማሽ አይደል…በቃ በዘርዝር ምን እንደምናደርግ ደግሞ እኔ እቅዱን ጨርሰና ለሁለታችሁም አሳውቃችኋለው….አሁን ተነሽ ከእዚህ አንውጣ ››ብሎ ይዞት ወጣ፡፡ክፍሏ አስገባትና..አሁን እራስሽን አጠንክሪና ተዘጋጅተሸ ጠብቂኝ..1፡30 ሰዓት ላይ የመጨረሻውን ተልዕኮ ለመፈፀም እንንቀሳቀሳለን ብሎት ተለይቶት ሄደ
///
ሰዓቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ሆኖል -አብዬት አቶ ሙሉ ፊት ለፊት ተቀምጦል።
‹‹እሺ ትናንት የተነጋገርነውን አሰብክበት?››
‹‹አዎ እንዳላችሁት አደርጋለሁ"
"ማለት››
‹‹ እራሴን አጠፍለሁ"
"ጥሩ.. በእውነት የጀግና ውሳኔ ነው..ታዲያ በምን ይሁንልህ?"
ትንሽ እንደማቅማማት አለና "በሽጉጥ ይሻለኛል...በሽጉጥ"
"ጥሩ ምርጫ ነው...ምንም ሳትሰቃይ ከዚህ ሁሉ ጣጣ ትገላገላለህ ማለት ነው...ተነስ በል እንሂድ"
"ወደ የት?"
"እንዴ እራሴን ማጥፋት ፈልጋለሁ አላልክም ? ...እዚህ እኛው ቤት ካደረከውማ እኛን ያለስራችን ይጠረጥሩናል...ስለዚህ ሌላ የተመቻቸ ቦታ እንፈልግልሀለን ።
‹‹እና ዛሬውኑ ነው የምትገሉኝ?"
"አንተ ደግሞ.. አሁን እንግደልህ ወጣን ..?.እራስህ ነህ ለመሞት የመረጥከው...መሞትህ ካልቀረ ደግሞ የምን ዛሬ ነገ እያሉ ጊዜ መፍጀት ነው"
ቀድሞት ክፍሉን ለቀቀና ሽጉጥ በጎኑ ጩቤ በእጅ ይዞ በራፍ ላይ ወደሚጠብቀው ቶላ.‹‹.ይሄን ሰውዬ ይዘህ ወደ መኪና ውሰድልኝ መጣሁ›› አለና ወደዶክተር ክፍል አመራ ..ዝግጅ ሆና ስትጠብቀው ነበር።
"ዶክተር እንሂድ"ምንም መያዝ ስይጠበቅባት ብድግ ብላ ለመሄድ ዝግጅ ሆነች።ካሳ ሻንጣውን ይዞ ተከተላት
"እንዴ ወዴት ነው?"አብዬት ጠየቀው
"ልንታገት አይደል?"
"እና ለመታገት ይሄን ያህል መስገብገብ"
"አዎ ከእሷ ጋር አይደለ እንዴ ..?."
"አብሽ ዛሬ ተራው የእኔ ነው ።አንተ ዛሬ እዚሁ ዘና ብለህ እደርና ነገ በጥዋት ተነስተህ ወደቀድሞ ስራህ?ስራ አለህ እኮ እረሳሀው እንዴ?"
‹‹አረሳሁትም...የሦስት ቀን ፍቃድ ይቀረኛል..ሶስት ቀን መታገት እችላለሁ"
"አረ ባክህ ትችላለህ...?።ዶ/ር መሀከል ገብታ ታስረዳው ጀመር..."ይሄ ጉዳይ ለዛሬ ለሊት ብቻ ነው።ነገ ጥዎት እኔ ቤት እንገናኛለን።ብላ ተጠጋችውና ጉንጩን ሳመችው።
ምንም ሳይናገር ሻንጣውን ትከሻው ላይ እንዳንጠለጠለ ወደ ክፍሉ መራመድ ጀመረ...ዶ/ርና አብዬት ጎን ለጎን ሆነው ወደታች ወረድና እቤቱን ለቀው ወጡ።መኪናዋ ጋር ሲደርሱ ቶሌ አቶ ሙሉን መኪና ውስጥ አስገብቶ እሱ ከጎኑ ቁጭ ብሎ ለማምለጥም ሆነ ለመንፈራገጥ እንዳይሞክር ጩቤውን ጎኑ ላይ ሽጦበት በተጠንቀቅ ሲጠብቀው ደረሱ።ሁለቱም ገቢና ገብና በአብዬት ሹፌርነት ከጊቢው ወጥተው መጓዝ ጀመሩ።
///
ቀጥታ የሄድት አቃቂ ድልድዩ አካባቢ 500ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኝ አንድ አዲስ የሚሰራ ቤት ውስጥ ነው።ቤቱ ከቀለም መልስ ያሉ ግንባታዎች ያተጠናቀቁበት ቢሆንም ...ባለቤቶቹ አልገብበትም።እቤቱን ከዘበኛው ጋር በመነጋገር ሁለት ቀን ሊጠቀሙበትና 5000ብር እንደሚከፍሉት ነግረውት 3 ሺ ብር ቅድሚያ ተቀብሎ በደስታ ፈቅዶላቸዋል። ባለቤቶቹ የክፍለሀገር ሰዎች ስለሆኑ ከወር ወደእዚ እንደማይመጡ ተረጋግጦል።
አቶ ሙሉ ይሄ ሁሉ መጓዝና ይሄ ሁሉ ግርግር ለምን እንደሆነ አልገባውም‹‹ ..እዚሁ መንገድ ላይ አውርዳችሁ ሽጉጡን ብትሰጡኝ እኮ.. ግልግል ነው"አለ
‹‹እዚህ መሞት ይሻልሀል?"አብዬት ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ"
"እኛ እኮ የተሻለ ቦታ ...በጥሩ ሴርሞኒ ብታደርገው ይሻላል ብለን ነው።››
"የምን ሴርሞኒ እያሾፋችሁብኝ ነው?..ባካችሁ እዚሁ ልገላገል.. መኪውን አቁሙት››
"እሺ እንዳልክ"አለና ቤት ሆነ የሠው እንቅስቃሴ የሌለበለት ቦታ ሲደርስ መኪናዋን ጠርዝ አሲይዞ አቆመ...የውስጥ መብራቱን አበራ ..ዶ/ር አብዬት ምን እየሠራ እንደሆነ ስላልገባት ግራ ገባት፡፡
"ምን እያደረክ ነው ..የእውነት እሱን ሰምተህ እያቆምክ ነው?።"ስትል ጠየቀችው፡፡
"አዎ ለመሞት እንዲህ ከቸኮለ ለምን እናዘገየዋለን...አለና ከጎኑ ሽጦ የነበረውን ሽጉጥ መዠርጦ አወጣ…
"በሽጉጥ ነበር አይደለ መሞት ፈልጋለሁ ያልከው?››ወደኃላ ዞረና ...በመንጠራራት ሽጉጡን በእጅ አስጨበጠው"
ዶ/ር አብዬት አሁን እያደረገ ያለው ነገር እየገባት ስላልሆነ ተደነጋግራለች ..እንዲህ አልነበረም ንግግራቸው።
"እና ምን ትጠብቃለህ ?አድርገዋ"
"እዚሁ?"

❤4
"አዎ እዚሁ …ቶሌ ደሙ ተፈነጣጥቆ ልብስህን እንዳያበላሽ ራቅ በለው ..ጥግህን ያዝ።››ቶላ እጅ ላይ የነበረውን ጩቤ እያገለባበጠ የታዘዘውን አደረገ።አቶ ሙሉ ሽጉጡን አቀባበለና መሀል ጭንቅላቱ ላይ ደቀነ...ዶክተር በፍራቻ እየተንቀጠቀጠች የሚንጣጣ የሽጉጥ ድምፅ ላለመስማትና የሚበረቀስ የራስ ቅል ላለማየት አይኖቾን ጨፍና ጆሮዎቾን በመዳፏ ሸፈነች።
"ስንት ጥይት አለው?"ሲል ጠየቀ
"አታስብ ይበቃሀል ...እንደውም ትርፍ ነው ..6 ጥይት አለው ..ሁለቱን ከተጠቀም ሌላውን አታባክንብን ጓደኛህም በዚሁ ካንተ በተረፈው ነው እራሱን የሚያሰናብተው።››
አቶ ሙሉ አእምሮውን ማሰራት ጀመረ...‹‹አዎ እድሉን መሞከር አለብኝ፤ ከፈጠንኩ ሊሳካልኛል ይችላል...ቀድሜ ይሄ የሠማይ ስባሪ የሚያህለው ጠረንገሎ ጭንቅላት ላይ ሁለት ጥይት ብለቅበት …ከዛ ያኛው ሌላ መሣራያ ከማውጣቱ በፊት የተቀረውን በጀርባውም በጭንቅላቱም ባንጣጣበት አበቃ ማለት ነው.. ዶ/ሯን በእጄም አያቅተኝ ።ከዛ የሶስቱንም እሬሳ እዚሁ ቅርብ ድልድይ ስር ገልብጬ.. በዚህችው መኪና ወደቤት ሄድና በቀደም ለሚስቴ ከሰጦት ብር ቢያንስ 10ሚሊዬንን ይዤ ከእዚህ አገር ላጥ..በሰከንዶች የጊዜ ልኬት ሁስጥ የወራት እቅድ አውጥቶ ጨረሰ..
"ሰውዬ ፈራህ እንዴ,.?.እየጠበቅንህ እኮ ነው?"አለው አብዬት፡፡
አቶ ሙሉ በጥልቀት ተነፈሰ እራሱን ከዘጋጀ...በህይወቱ ሙሉ ፈጥኖ ከሚያውቀው ፍጥነት በተለየ ሽጉጥ የጨበጠው እጁን ቶላ ጭንቅላት ላይ ቀሰረና ቃታውን ደጋግሞ ሳበ.ቃ... ቃ.. ደገመው"ቃ..ቃ"ምንም የፈነዳ ድምፅ የለም...ምንም ተፈናጥሮ የወደቀ ቀለሀም የለም ..የተፈረከሰ ጭንቅላትም አይታይም፤ አብዬት እየተንከተከተ ተንጠራራና ሽጉጡን ከእጅ መንጭቆ ተቀበለው...
"እንደማስብህ ከርፋፋ ሰው አይደለህም"ብሎ መኪናዋን አንቀሳቀሰ..ዶ/ር ቀስ ብላ አይኖቾንም ገለጠችና የተፈጠረውን ለማየት ወደኃላ ዞረች ሁሉ ነገር ሰላም ነው ..አቶ ሙሉ አይኖቹን በፍራቻ ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ነው።መዳፎን ከጆሮዋ አነሳች። "ምን ተፈጠረ?"አብዬትን ጠየቀችው።
"ሙሉ የሚባለው ሰውዬሽ ገና ለመሞት ዝግጅ አይደለም"
"እና? "
"እናማ ...ቶላ ላይ ደቀነና ቃታውን ሳበ...በጣም ጥሩ ገዳይ መሆኑን በደንብ አረጋገጠልን፡፡"
"እንዴ ቶሌ ተጎዳህ?"መልሳ ባለማመኖ ጠየቀችው..ቶላ እየተደረገ ያለውን ነገር ሁሉ እሱ የማይሳተፍበት ቀሺም ፊልም እንደሚያይ ሰው ነው በቸልተኝነት እየታዘበ ያለው።ሽጉጥ ሲደቀንበትና ቃታ ሲሳብበት እንኳን የስሜት ለውጥ፤ የመፍራት ፤የመደንገጥ ሁኔታ በፊቱ ላይ አልታየም።
"እድሜ ለእኔ ከቤት ስንወጣ ዘንግቼው ሽጉጡ ውስጥ ጥይት አልጨመርኩበትም ነበር...ለዝንጉነቴ ይቅርታ አቶ ሙሉ"አሾፈበት።
"አንተ ክፉ ሰው ነህ ባዶ ሽጉጥ ሰጥተሀው ነው እንዲህ የምታጨናንቀኝ...እርጉዝ እኮ ነኝ "ደነጠ"ውይ ይቅርታ ...ፈፅሞ እንደዛ አላሰብኩም"
"አረ ስቀልድ ነው… የክፉ ሰው ፅንስ እንዲህ በቀላሉ ይሸበራል ብለህ ነው?።ደረሱ ቶሌ ክንድን ጨምድዶ ጎትቶ አወጣው
ቶሌ ቆይ አለና ቅድም ከአቶ ሙሉ እጅ የነጠቀውን ሽጉጥ አወጣ …ኪሱ ገባና ጥይቶች በማውጣት ሞላበት ...
"አሁን ልስጥህ እንደ?"የቀዘቀዘው ና የደነዘዘው አቶ ሙሉ ፀጥ እንዳለ ነው፡፡ቶሌ እሱን ለእኔ ተውልኝ አንተ እዚሁ ቦታህን ያዝና እስክደውልልህ ጠብቅ….ደክተር ተከተይኝ..››አለ
ዶክተሮ ፈራ ተባ ስትል ያያት አብዬት ወደዶክተሯ ጠጋ አለና
‹‹አይዞሽ ዶክተር ችግር የለውም ..ይሄውልሽ እዛ ጥግ ሰብለ ክላሽ ደቅና ገቢ ወጪውን እየጠበቀች ነው ..በተቃራኒው እዛ ደግሞ አቤል እስናይፐሩን ሰትሮ እየጠበቀ ነው እዛ ፊት ለፊት ደግሞ ዛፍ ተከልሎ ባርቾ ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ነው።ቶላም አሁን ቦታን ይይዛል/..ችግር ከተፈጠረ ወዲያው አንቺን ከዚህ ያስወጡሻል"
"አንተ ከጎኔ ካለህ አልፈራም ..››አለችው
‹‹አቶ ሙሉ ቀጥል"መራመድ ጀመረ...ግቢ ውስጥ ተከታትለው ገቡ ...እቤቱ በረንዳ ላይ ባለ አግዳሚ ወንበር ላይ የዶዬ 3 ሰዎች ተኮልኩለው ተቀምጠዋል።
አቶ ሙሉ ግራ ተጋባ ..እነዚህን ሰዎች ያውቃቸዋል ..ለረጅም ጊዜ ለእነሱ ሲሰሩ የነበሩ የዶዬ ሰዎች ናቸው።‹‹እዚህ ምን እየሰሩ ነው?"››እራሱን ጠየቀ ‹‹ከመጀመሪያውም ከእኛ በተቃራኒ ሆነው እየሠሩ ነበር እንዴ?"ጥያቄውን እርግፍ አድርጎ ተወው...አሁን ምንም ሆነ ምንም ለእሱ የሚጠቅመው ነገር የለም ። የእሱ ጉዳይ አብቅቶለታል …ልጆቹ የአብዬትን መሞጣት ሲያዩ ከተቀመጡበት ተነስተው ቆም...አብዬት ምንም ሳይላቸው ሰውዬውን በሽጉጡ አፈሙዝ እየገፋ ወደቤቱ ውስጥ ይዞት ገባ..ዶክተሯ ሁኔታውን እየቃኘች ከኃላቸው ተከትላለች፡፡
ሳሎኑ ውስጥ ሁለት ወንበር፣ አንድ ጠረጰዛ ፣ ምንጣፍ፣ ምንጣፍ ላይ የተዘረጋ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድ ልብስ ፣እሽግ ውሀ በደርዘን.. በቃ ይሄ ነው ያለው...
አብዬት ማውራት ጀመረ‹‹ስማኝ።አንተ ማንም አላገተህም። እስከዛሬ ለአንድ ሳምንት እዚህ ነበርክ...የምትተኛው እዚህ ፍራሽ ነው ፤ውሀውም እነዛ ኩኪሶችና ቆሎዎች ለአንተ የተዘጋጅ ናቸው። ፍራሹን ገለጥ አደረገና አሳየው..አየህ 500 ሺ ብር ነው ..እርግጥ 50 ሺ ብር አካባቢ ተነስቶለታል ..ያንተ ነው።ስትያዝ የተወሰነ ብር በእጅህ መገኘት አለበት ከለዛ አያሳምንም፡፡ በራፍ ላይ ያየሀቸው ካንተ ጋር የሚሰሩ አንተ የቀጠርካቸው ናቸው።እነሱን ስትቀጥር ዶዬም ሆነ ሼኪው አያውቅም። አንተና ፕሮፌሰሩ ብቻ ናችሁ የምታውቁት፡፡ከዶዬ በብር ኃይል ለእነሱ መቶ ሺ ብር ከፍላችሁ ነው ያስኮበለልካቸው።በስምህ በየአካውንታቸው መቶ መቶ ሺ ብር ገብቶላቸዋል፡፡››
ፍዝዝ ሲልበት።"ሰውዬ የምለውን እየሠማኸኝ ነው አይደል?
"አዎ በደንብ እየሠማውህ ነው..ግን አልገባኝም"
"ቆያ ትንሽ ታገስ እያስረዳውህ ያለውት እኮ እንዲገባህ ነው። ከሳሎኑ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከፈተው ..."ዶ/ር ነይ ግቢ፤ እዛ ወንበር ላይ ቁጭ በይ ...ቁጭ አለች..ተጠጋትና ፀጉሯን ያሰረችበትን ፀጉር ማስያዣ ፈታችውና ፀጉሯን ብትንትን አደረገው...፡፡
‹‹ምን እያደረክ ነው?››አለች ግራ ገብቶት፡፡
"ትንሽ መጎሳቆል አለብሽ ...››አለና ከላይ የለበሰችውን ቲሸርት እንድታወልቀው አደረገ፡፡ ወለል ላይ ጥሎ በእግሮቹ በማሻሸት እንዲቆሽሽ ካደረገ በሀላ አንስቶ የለበሰችው ሱሪዋ ላይ አራገፈው.. ሽሮ መልክ ያለው ሱሪዋ በቀላሉ ቆሸሸ… ሸሚዙን ሶስት ቦታ ቀደድ ቀደድ አደረገና መልሶ አለበሳት
"ትናንት ገዝተህልኝ ዛሬ ስትቀደው ትንሽ አያሳዝንህም? አለችው
‹‹አይ የገዛሁበት ብር ያንቺ ስለሆነ አያሳዝነኝም"
እጇን በገመድ አንድ ላይ ጠፍሮ አሰራት...‹‹በጣም አሳመምከኝ .."
‹‹በደንብ መምሰል አለበት እንደውም ክርክር ቢያወጣ ወይም ቢደማ አሪፍ ነው..››.ጎንበስ ብሎ እግሯንም ከወንበሩ እግር ጋር አሰረኸው..ግድግዳውን ተደግፏ ፈዞ ለሚያየው አቶ ሙሉ ..።‹‹ስማኝ አሁን በህይወት ላተርፍህ እየጣርኩ ነው። እድሜ ለዶ/ር በል …እኛ እንደ እነሱ ገዳይ አንሆንም ስላለች ...እጃችሁን ለመንግስት እንድትሰጡ እያመቻቸን ነው።ህግ ፊት ደግሞ የሞት ፍርድ ቢወሰኖብህ እራሱ ገና መረጃ ተሠብስቦ ፤ስንት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ፤ ክስ ቀርቦ፤ የምስክሮች ቃል ተሠምቶ፤የቅጣት ውሳኔ ተላልፎ ፍርድ ታውቆ ፕሬዘዳንቷ ፈርማ እስኪባል ቢያንስ አምስት አመት በህይወት ትኖራለህ..አስርና ሀያ አመትም ልትኖር ትችላለህ።እ ምን ትላለህ?።
‹‹አረ በጣም ነው የማመሰግነው ...እውነት ዶ/ር ላደረግሺልኝ ምህረት አመሠግናለው"አለ

❤1
እንግዲያው የምልህን በደንብ አስተውለህ ስማኝ…..በቪዲዬ ተቀርፀሀ የለቀቅከውን እያንዳንዱን መረጃ እንዳትዘነጋ ..ና ተከተለኝ አለና ዶ/ሮን እዛው ተዋትና ቀጣዩ ክፍል ይዞት ገባ…እዛ ክፍል በተነጠፈ አልጋ ላይ ፕሮፌሰሩ ዝርግትግት ብሎ ተኝቶ ያቃስታል…እነሱ እዚህ ከመድረሳቸው ከ30 ደቂቃ በፊት ነው ከቤት አምጥተው እዚህ ያስተኙት፡፡ከፍተኛ ስቃይ ላይ ቢሆንም ግን ንቁ ነው….ክፍል ውስጥ ሙሉንና አብዬትን ሲያይ ማቃሰቱን ቀነስ አደረገና ትኩረቱን ወደእነሱ አዞረ
‹‹እሺ ፕሮፌሰር ወዳጅህን ይዤልህ መጥቼያለው…..››
አቶ ሙሉ የፕሮፌሰሩን ሁኔታ ሲያይ ዝግንን አለው..ያ ኩሩ ቀብራራ..ያ ሽቅርቅር መሬት አይንካኝ ብሎ በአየር ላይ የሚበር ግለሰብ እንዲህ ተገጣጥቦና ጠቋቁሮ፤ ዝሎና ደክሞ፤ልክ በሰመመን አድክሞ አልጋ ላይ አስተኝቶ እንደሚቀዳቸው በሽተኞቹ እሱም ተሰትሮ ሲያየው የሰው ልጅ ከንቱነት ፍንትው ብሎ ተገለፀለት..እሱን ስላላሰቃዩት በውስጡ አመሰገናቸው፡፡
‹‹አሁን ሁለታችሁም ሱሙኝ….እንደተለመደው..ይሄን ቦታ ከዘበኛው በሌላ ሰው አማካይነት ተከራይታችሁ ነው፡፡ የተከለከራያቸሁት 5 ሺ ብር ሲሆን 3 ሺብር ከፍላችኋል፡፡እዚህ ሳምንት ተቀምጣችኋል….ዶክተሯንና አግታችሁ ሁኔታዎችን እየተከታተላችሁ ነበር….አንተ አቶ ሙሉ ስሜታዊ ሆነህ እራስህን እንደምታጠፋ ገልፀህ የንዛዜ ቪዲዬውን የለቀቅከው…በጎደኛህ እንዲህ መሆን ተስፋ ቆርጠህ ነበር…ምክንያም ፕሮፌሰሩን ከሁለት ቀን በፊት ማታ አራት ሰዓት ላይ ወደከተማ ደርሼ ልምጣ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ ጨለማ ተገን አድርገው እዚህ መግቢያ ላይ ጠብቀው ነው እንዲህ አበለሻሽተው ጥለውት የሄዱት፡፡አንተ ስትገማት እንዲህ ያደረጉት ሰዎች ምክንያታቸው ደግሞ ፕሮፌሰሩ ቀድሞ ከሰራቸው ስራዎች ጋር በተያያዘ ቂም የያዙበት ሰዎች እንደሆኑ ጥርጣሬው ፡፡እነዚህ የህክምና ቁሳቁሶች ይታዩሀል እነሱን ከፋርማሲ ገዝተህ በእናንተ እገታ ስር ያለችውን ዶክተር በግድ እንድታከመው አስገድዳችሁ ከሞት እንዲተርፍ አድርገሀል…ገባህ››
‹‹አዎ የገባኝ መሰለኝ››
‹‹ጥያቄ አላችሁ?››
አቶ ሙሉ ጠየቀ‹‹የመሞት ሀሳብህን ለምን ቀየርክ ካሉኝስ?››
‹‹ያው ፈሪ ስለሆንኩ በላቸዋ››
‹‹ፕሮፌሰሩ በሚርገበገብ ድምፅ‹‹ልጄስ?›ሲል ጠየቀ
‹ፕሮፌሰር እንደውም አስታወስከኝ.. ዶ/ሯን ሳትገድላት እስከአሁን ያቆሀት ልጅህን ማርገዞን ስላወቅክ እንደሆነ ብትናገር በጣም አሳማኝ ምክንያት ነው››
‹‹እሺ አደርገዋለሁ አታስብ…ልጄን ብቻ እዳታስወርደው ተከታተልልኝ…ውለታህን አልዘናጋውም››
‹‹ላንተ ውለታ የመዋል ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም.. ግን ለእሷ ስል ልጆንም ሆነ እሷን እጠብቃቸዋለሁ፡፡››
‹‹እኔም የምፈልገው ያንን ነው….አመሰግናለሁ››
‹‹እንግዲያው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልንገራችሁ….በምንም አይነት ሁኔታ ዶ/ሯን ለአንድ ቀን እንኳን እስር ቤት የሚያስገባትን መረጃ አሳልፋችሁ ብትሰጡና ከስምምነታችን ውጭ ብትንቀሳቀሱ እስር ቤት ሆናችሁ የትም አንድ ቀን አታድሩም፤ምንም አላዝንላችሁም፡፡አንተ ሙሉ ተብዬው…. ቅድም መኪና ውስጥ እንዳደረከው ብልጥ ልሁን ብትል መጀመሪያ ልጆችህን ከዛ ሚስትህን ጨርስና ወደአንተ መጣለሁ… አሁን በሉ ፖሊሶቹ ጥቆማ ይደርሳቸዋል…በሀያ ደቂቃ ውስጥ መጥተው ይከቦችኋል፡፡ በረንዳ ላይ ከእናንተ ጋ እጃቸውን ለመስጠት የተዘጋጁ ጠባቂዎች አሉ፡፡ወጭ ደግሞ የእኔ ልጆች ችግር ከተፈጠረ ..ማለቴ ለማምለጥ የምትሞክሩ ወይም አልማረክም ብላችሁ ፖሊሶችን የምታስቸግሩ ከሆነ በእስናይፐራቸው ይቀልቡና ይገላግላችኋል፡፡በሉ መልካም የእስር ዘመን በጣም ትናፍቁኛላችሁ››ብሎ ወጣና ወደ ዶ/ር ክፍል ተመለሰ፡፡
ዶ/ር እንግዲህ ሰዓቱ ደርሶል፡፡በቃ ልሂድና ፖሊቹን ይዣቸው ልምጣ››
‹‹እንዴ እራስህ ነህ እንዴ የምትጠቁመው››
‹‹አዎ…እንዚህን ወንጀለኞች በመጠቆም እራሴንም ከተጠርጣሪነት ነፃ ማውጣት አለብኝ..በዛ ላይ የሼኪው 5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አለ››
‹‹ትቀልዳለህ አይደል?››
‹‹በይ..ደግሞ ሰውዬሽን እንደዛ ደብድበውና አኮላሽተው እዚ ባራፍ ላይ ጥለውት ሲሄዱ አቶ ሙሉና ጠባቂዎቹ በግድ አስገድደው እንድታክሚው አድርገውሻል..አንቺ ነሽ ያከምሽው››
ዝግንን አላት
‹‹በይ…አልቆይም ፖሊስ ይዤ መጥቼ አድንሻለሁ፡፡››ብሎ ወጣ፡፡
ይቀጥላል....

የመጨረሻ ክፍል
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-23
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
ደ/ር ሰጵራ ከሁሉ ነገር ነፃ ሆኖ እቤቷ ከገባች አንድ ወር ሆኗታል፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ያለምንም እንከንነና የአካል ጉዳት የነፃነት አየር እተነፋሳለሁ የሚል ግምት ፍፅም አልነበራትም..ተስፋ ቆርጣ ነበር፡፡አሁን ማዕበሉ ሁሉ እንዲህ ፀጥ ብሎ ወጀብና መናወጹ ቆሞ ሁሉ ነገር ሰላማዊ ሆነ ማየቷ ማመን ነው ያቃታት፡፡
ወደቤቷ ስትመለስ ሶስት ሰዎች አብረዋት ተመልሰው ከእሷ ጋር እየኖሩ ነው፡፡የመጀመሪያው የቀድሞ ተመላላሽ ሰራተኛዋ የሆነችው ከበብሽ አሁን በቆሚነት ለብቻዋ ከኃላ ያለ አንድ ሰርቢስ ክፍል ተሰጥቶት እዛው እየኖረች የቀድሞ ስራዋን እንድትቀጥል ተደርጎል፡ሁለተኛው ከእሷ ጋር መኖር የጀመረው ሰው ካሳ ነው፡፡ ከፖሊስ ጣቢያ በነፃ ተለቃ እቤቷ በገባች ከሶስት ቀን በኃላ በፒካፕ መኪና ጠቅላላ እቃውን ጭኖ መጣና ግቢው ውስጥ ዘረገፈው... እንደዚህ ያደረገው ለእሷ ምንም ሳይነግራት ምንም ሳያማክራት ነው፡፡ አልከፋትም፤ እንደውም በተቃራኒው ደስታ ነው የተሰማት፡፡ ቤቷ ካለው ሶስት መኝታ ክፍሎች መካከል አንድን ሰጠችው.ከዕቃዎቹ መሀከል ያቻለለትን ያህል ወደክፍሉ እንዲያስገባ ካተደረገ በኃላ የቀሩት ዕቃዎች ታሽገው ወደእቃ ማከማቸ መጋዘን እንዲገቡ ተደረገ፡፡የመጨረሻውን ሶስተኛው አብሮት ለመኖር የመጣውና እሰከአሁን የራሱ መኝታ ቤት ስላልተዘጋጀለት ከእሷው ጋር ጉያዋ ውስጥ ገብቶ እየተኛ የሚገኘው ህፃኑ በድሉ ነው፡፡ይሄ የሆነው ዶ/ር ህጻኑን በተመለከተ ከእናቱ ጋር ከተነጋገረች በሃላ ልታሳድገው ተስማምታ ወደቤቷ ስላመጣችው ነው፡፡በአንድ ጊዜ የሁለት ልጆች እናት ልትሆን በመሆኗ ጥልቅ ደስታ ነው የተሰማት፡፡ የበድሉ እናት ልጇን ማየት በፈለገች በማንኛውም ሰዓት መጥታ ማየትና ልታዝናናውም በፈለገች ጊዜ ወደፈለገችበት ቦታ ወስዳ መመለስ እንደምትችል ተስማምተው በሁለቱም ፍቃድ ነው እንደዛ የሆነው፡
ከአስር ቅን በፊት ጎንደር ሄዳ ለሁለት ቀን በማደር እናቷንና ቀሪ ቤተሰቦቾን ጠይቃና አረጋግታ ነው የመጣችው፡፡
በዚህ አንድ ወር ውስጥ እራሳቸው ለህግ አሳለፈው አንዲሰጡ የተደረጉት ፐሮፌሰሩ፤ አቶ ሙሉና ሶስቱ ጠባቂዎች በአንድ መዝገብ በተከፈታቸው ክስ በከፍኛ የፀጥታ ጥበቃ እስከአሁን ሶስት ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል..እያንዳንዱ የፍርድ ቤት ውሎቸው በሀገሪቱ ሚዲያዎች ሆነ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ትኩረት የሚያገኝ ትኩስ ዜና ሆኗል…በተለይ ከእነሱ ጋር ንክኪ ባላቸው ባለስልጣንና የፖሊስ አባላት አብሮ መታሰር እና በወንጀሉ ተጠያቂ መሆን ለጉዳዩ ተጨማሪ ድምቀት ፈጥሮለታል፡፡ የፓለቲካ ተቃዋሚሆችም ነገሩን በማራገብ መንግስትንና ባለስልጣኖቹን አንዲያጥላሉበት መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡
ሌላው በፍርድ ቤት ውሰኔ የሆስፒታሉን ህልውና ለመጠበቅና የግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ የህክምና አገልግሎት ላይ የማይናቅ ድርሻ ሰላለው እና በዚህም የተነሳ የህዝብ ሀብት ጭምር መሆኑን ከግምት በማስገባት ሆስፒታሉ ሰሙን አድሶ እንደአዲስ ሰራውን እንዲቀጥል በመንግስትም ሆነ በፍርድቤት በኩል ከፍተኛ አርብርብ ተደርጎ ውጤት ተገኝቷል፡፡
በዚህም የተነሳ የዶክተሯን ለፍትህ ያደረገችውን ከፍተኛ ተጋድሎና አስተዋፅኦ ከግምት በማስገባት..የፕሮፌሰሩንና የአቶ ሙሉን የአክሲዬን ድርሻ ለእሷ እንዲተላለፍና እሷ ደግሞ በወንጀለኛቹ ምክንያት ጥቃትና የአካል ዘረፋ ለደረሰባቸው በአካል ቀርበው ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ተጨባጭ መስረጃ ላቀረብ 78 ግለሰቦች እንደጉዳታቸው መጠን የሚከፈል ካሳ 30 ሚ ብር እንድትከፍል ተወሰነ፡፡
በዚህ ውሳኔ ወንጀለኞቹ ፕሮፌሰሩና አቶ ሙሉም ስለተስማሙ የሀግ ሂደቱ ያለምንም እንከን ነው የተከናወነው፡፡.እሷም ሚፈለግባትን ብር እጇ ላይ ያላውን ብር በመሰብሰብ የጎደላትን ከባንክ በመበደር ወዲያው ለተወሰነላቸው ተጠቂዎች እንዲውል ለፍርድ ቤቱ አስረከበች….፡፡
በዚህ ምክንያት የሆስፒታሉ 23ፐርሰንት የራሶ 16 ፐርሰንት የፕሮፌሰሩና 5 ፐርሰንት የአቶ ሙሉ በአጠቃላይ 44 ፐርሰንት ባለድርሻ ሆነች፡፡፡ 10 ፐርሰንት የሞቹ የአቶ ኤልያስ ሲሆን ለቤተሰቦቹ እንዲተላለፍ ተደርጎል…..ግን ከቤቱ ስራውን ለመስራት የደረሰ ልጅ ስላልነበረና ባለቤቱም ለስራ ፍቃደኛ ስላልሆነች…ውክልናዋን ለዶ/ሯ በመስጠቷ ደክተሯ ከሌሎቸ ፅቃቅን ባለአክሲዬኖች ከሰጧት ድምፅ ጋር ተዳምሮ ከ60 ፐርሰንት በላይ በሆነ ድምፅ ሆስፒታሉን የማስተዳደሩን ኃላፊነት ተረከበች፡፡ቀሪው 35 ፐርሰንቱ ደግሞ ቀጥታ የአቶ ጠሀ ድርሻ ሲሆን ሌሎች 5 ፐርሰንት ድርሻ ያላቸው የእሳቸው ደጋፊዎች አሉ ፡፡እርግጥ በምንም አይነት መንገድ እሷቸው ባለንብረት በሆኑበት ሆስፒታል ዳግም እደማትመለስ ድርሻዋንም እንደምትሸጥ ምላ ነበር፡አሁንም ማሀላዋን አላፈረስችም፡እቤቷ በተመለሰች በሶስተኛው ቀን ነበረ ሼክ ጠሀ በልብ ድካም በሽታ ሆስፒታል መግባታቸው የሰማችው፡፡ ወዲያው ከ3 ሰዓት በኃላ ሌላ ስልክ ተደውሎ መሞታቸውን ሰማች፡፡ በማግስቱ ቀብራቸው ላይ ከአብዬት ጋር ተገኘች፡፡እዛው ወደ ግብአተ-መሬታቸው በሚገቡበት ጊዜ ነበር‹‹አንተ ነህ ወይስ እግዜር ነው የወሰዳቸው››ብላ አብዬትን የጠየቀችው፡፡›
እሱም ‹ተጋግዘን ነው›ብሎ መለሰላት፡፡.እንዴት አድርጎ ሀኪሞች እንኳን መለየት በማይችሉበት ሁኔታ እንደመረዛቸው ዝርዝሩን አልጠየቀችውም፤እሱም ሊነግራት ፍቃደኛ አልነበረም፤ግን እንዳለው ቃሉን ጠብቋል፡፡
ከዛ በሃላ ፍፅም የእሳቸው ልጅ የማይመስል መሀመድ የሚባል ከድሮም ጀምሮ የምትወደው የ50 ዓመት ጎልማሳ የተማረና በስነ-ምግባር የታነፀ ልጃቸው የቤተሰቦቻቸውን ሙሉ ፍቃድና ውክልና አግኝቶ ቦታውን ተረክቦ ከእሷ ጋር ለመስራት መጣ…እሷም ከዛ በኃላ ነው የመጣላትን ሁሉ እድል ተጠቅማ 55 ፐርሰንት ድርሻ ወስዳ ሆስፒታሉና በመረከብ ወደቀድሞ ስራዋ በአዲስ ሞራል የተመለሰችው፡፡
///
ዛሬ ይሄ ሁሉ ከሆነ አንድ ወር በላይ ሆኖታል፤ለዚህ ያበቁአትን ሰዎች ለማመስገን ቤቷ የትረፈረፈ ድግስ በማዘጋጀት አቢዬትንና ልጆቹን ጠርታለች ፡፡ምሳ ተበልቶ …ብና ተፈልቶ፤ተጠጥቶ ካበቃ በኃላ ሁሉም ፊቱ የሚፈልጉትን መጠጥ አስቀምጠው እየጠጡ መጫወት እና መሳቃቅ ጀመሩ… ዶክተር ሁሉም እየተደሰቱና እየተፍነከነኩ ስታይ ደስ አላት፡፡
..እና ንግግር ለማድረግ ፈለገች… ትኩረት እንዲሰጧት አጇን በማጨብጨብ በተቀመጠችበት ሆና መውራት ጀመረች፡፡
ዛሬ ይሄን የምሳ ግብዣ ያዘጋጀሁት ሁላችሁንም አመሰግናለሁ ለማለት ነው፡፡እናንተ ለእኔ ነፍሴን መልሳችሁ ሰጥታችሁኛል፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፋችሁ ከገባሁበት የህይወት ማጥ ጎትታችሁ ታድጋችሁኛል..በኢትየጳያ ህዝብ ዘንድ ጀግና ተብዬ በየመንገዱ እንድከበር እድሉን አመቻችታችሁልኛል፡፡ሆስፒታሌን በ44 ፐርሰንት ድርሻ እና በ60 ፐርሰንት የድጋፍ ድምፅ መልሼ እንድቆጣጠር የሆነው በእናንተ ቀና ድጋፍ ነው፡፡
በአሁኑ ሰአት በጣም ሀብታም፤ስኬታማና ዝነኛ ሴት ሆኜያለሁ.. እናንተ እኔን ማዳን ብቻ ሳይሆን እነዚህ ሰዎች በተደላደለ ሁኔታ ቢቀጥሉ ኖሮ አጉል የሚያደርጎቸውን በሺ ሚቆጠሩ ንፅሀንን ከሚደርስባቸው አሰቃቂ የአካል ዘረፋን ህይወት ማጣት አድናችኋል…ስለዚህ ልትኮሩ ይገባል.እኔም በጣም ነው የምኮራባችው፡፡

ግን አሁን ይሄንን የመሰለ የፅድቅና የጀግንነት ስራ ከሰራችሁ በኃላ መልሳችሁ ወደድሮ ህይወታችሁ የምትመለሱ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም፡፡እናንተ ከአሁን በኃላ ልዩ ሰው መሆን አለባችሁ.. በዚሁ ንፅሀንን ምትታደጉ፤ ስውር ወንጀለኞን የምታጋልጡ፤ ለተግፉት ዋስትና …ለተረገጡት ድምፅ የምትሆኑና መቀጣት ያለበትንም ለህግም እያሳለፈችሁ የምትሰጡ ስውር የነፃነትና የፍትህ አርበኞች መሆን አለባችሁ፡፡ዝርዝር ጥናቱ ገና እኔ አበዬትና ካሳ እያዘጋጀነው ሲሆን ሁሉ ነገረ ካለቀ ለእናተ እንድታውቁት ይደረጋል፡፡
ግን ከአሁን ወዲህ ሁላችሁም የአብዬት ሰራተኞች እንደሆናችሁና በየወሩ የራሳችሁ የሆነ ደሞዝ እንዳላችሁ ስናገር ደስ እያለኝ ነው፡፡እቤቱን በጭብጨባ አናጉት
አብዬት ተራውን መናገር ጀመረ‹‹አዎ .ደ/ር እንዳለችው ከአሁን በኃላ ከመካከላችን ማንም የበፊቱን ስራ የሚሰራ አይኖርም...መስረቅ ፤ማጅራት መምታት ወዘተ መሰል ስራዎች አይፈቀዱም..ይሄንን ለማድረግ ሁላችሁም ቃል እንድትገቡልኝ እፈልገላው..››
‹‹ቀለል እንገባለን .ቃል እንገባለን…››
እንግዲህ ዶክተር እንዳለችው ለሁላችሁም በዳይመንድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ውስጥ ቆሚ ስራ ይሰጣችኋል….ማለቴ የጥበቃ ክፍል ፤ጉዳይ አስፈፃሚ የመሳሰለው፡፡ግን ከዛም በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የምንሰራው ሰራ ይኖረናል….ዶ/ር ቅድም ለመነካካት እንደሞከረችው.ልክ እሷ እንዳጋጠማት አይነትቸ ችግር ውስጥ ያሉትን የተገፍትን በወንጀለኞችና ባለስልጣን በደል ደርሶባቸው ከቤታቸው ከንብረታቸው የተፈናቀሉትን ማንኛውንም ግለሰብ ሳንመርጥ በአቅማችን እንረዳለን፤እራሳችንን ሳናጋልጥ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እንደርጋለን፡፡.ሌላው ጠቅላላ የስራችን ይዘት ምንድነው የሚለውን ግን በዘርዝር በቅርብ እንነጋገርበታለን፡፡ ከዚህ አፈንግጦ ወደበፊት ህይወቴ እመለሳለው ሚል ግን የሁላችንም ጠለት ስለሚሆን እኛም አሳልፈን እንሰጠዋለን… እንደማንኛውም ሌላ ወንጀለኛ ጠላታችን አድርገን እንፋለመዋለን፡፡
ካሳ እጁን አወጣ
‹‹እሺ ካሳ››አለው አብዬት የሚናገረውን ነገር ለመስማት በመጓጓት
‹‹ይህ ፊትህ ላይ ያለውን ጠባሳ ሰርጀሪ ተሰራው.. ከቂጥህ ላይ ቦጨቀው ይለጥፉና ያጠፉልሀል.የህክምና ወጪውን እኔ እሸፍናለሁ››አለው፡፡
በተናገረው ነገር ሁሉም ግራ ተጋቡ‹‹ያን ያህል ምን አሳሰበህ?››
‹‹ለአንተ አስቤልህ አይደለም.ለራሴ ብዬ ነው›
‹‹አልገባኝም››
‹‹ያው ከአሁን በኃላም አብረን የምንሰራና ደጋግመን የምንገናኝ ከሆነ ይህንን ፊትህን እያየሁ መፍራትና መሳቅ አልፈልግም››
‹‹እሺ ከፈለክ አሰራዋለሁ..ሌላ የምትለው ነገር አለህ?›አለው እየሳቀ
‹‹አዎ እዚህ ቤት የተጠራቀሙ የተሰባበሩ ነፍሶች በጣም ነው አንጀቴን የሚበሉኝ .አሁን ምን አልባት ቀስ በቀስ እየተጠገኑና እየተስተከካከሉ ይሄዳሉ ብዬ አስባለሁ.እዚህ ቤት ካሉ ነፍሶች ውስጥ የእኔዋ ነፍስ ብቻ ያልተሰባበረች በመሆኗ ኩራት ይሰማኛል፡፡›አለ
አብዬት ፈገግ አለና‹‹አይ ካሳ ብዙም አትኩራራ…የራስ ነፍስ መሰበር እኮ ለራስ አይታይም፤እኔ አሁን ያንተን ነፍስ ሳያት ስንጥቅጥቅ ብላ ነው የምትታየኝ ››አለው፡፡
ዶክተር መሀከል ገባችና‹‹በሉ እንግዲህ እቤታችሁ ነው ..ብሉ ጠጡ፤ ሙዚቃውን ሞቅ አድርጉትና ጨፍሩ.. ተዝናኑ ዛሬ ሁላችንም እዚሁ ነው የምታድሩት…ለሁላችሁም መኝታ ተዘጋጅቷል፤የጎደለ ነገር ካለ ጠይቁ›አለቻቸው ሁሉም በጭብጨባ መስማማታቸቸውን ገለፅ
በዚህ ጊዜ ከእንቅልፍ የተነሳው ህፃኑ በድሎ ፈንደስ ፈንደስ እያለ መጣና ጉያዋ ተሸጎጠ….ዶ/ር አንስታ አቀፈችው…ከወንዶቹ መካከል ሆና ቢራዋን እየላፈች የነበረችው እናቱ በቆረጣ የልጇን እና የዶ/ርን ሀኔታ አየችና በደስታ ፈገግ አለች፡፡
//
ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ዶክተር ሰጵራ ንፋስ ለመቀበል ወደበረንዳ ስትወጣ አብዬት ከኃላው ተከተላት
‹‹ምነው ደ/ር እንደ እኔ ሰከርሽ እንዴ?››አላት
‹‹ምነው አንተ ሰክረሀል እንዴ….?ብዙ ስትጠጣ እንኳን አላየውህም፡፡››
‹‹መጠጥ ብቻ መሰለሽ ደስታም እኮ ያሰክራል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…እንደዛ ከሆነማ እኔም ሰክሬላሁ፡››
‹‹ልጅሽስ?››
‹‹ማለት? ሆዴ ውስጥ ነዋ!!››
‹‹አይ ..አሱን አይደለም የጠየቅኩሽ…ታላቅዬውን… በድሉን ››
‹‹እ ..እናቱ ይዛው ተኝታለች.. ከእሷ ጋር ነው፡፡››
‹እ ..ዛሬ ብቻሽን ነዋ የምታድሪው ››አላት
‹‹ብቻዬን…?አዎ ምነው የተገናኘን ቀን የጀመርከውን ልትጨርሰው ፈለክ እንዴ?›››አለችው
በእፍረት አንገቱን አቀረቀረ…ዶክተር ሁልጊዜ ስለዛች ቀኗ ድርጊቴ ሳስብ ትንሽነት ነው የሚሰማኝ..እባክሽ ይቅርታ አድረግልኝና ሁለተኛ መልሰሽ አታንሺብኘ››
‹‹አይ አንተ..እኔ ደግሞ ስለእዛች ቀን ሳስብ ያንተን ትልቅነት እና ስሜትን የመቆጣጠር ችሎታ እያሰብኩ ነው…ምደነቅብህ….››
‹‹ተይ እንጂ ዶክተር››
‹‹እውነቴን ነው..እንደውም የዛን ቀን የጀመርከውን መጨረስ አለብህ…ና›› ብላ ክንዱን ያዘችና ያለምንም ይሉኝታ ሳሎን ውስጥ እየጨፈሩ ባሉት ጓደኞቻቸው መካከል ሰንጥቃ ወደመኝታ ቤቷ ይዛወ ሄደች…ሲደርሱ ካሳ በራፍ ጋር ተገትሮ..ለንቦጩን ጥሎ እየጠበቃቸው ነበር…አብዬት እርር አለ .. .. .. .. .. ተፈጸመ.. በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ መልካም ጊዜ .. @tibeb145 @tibeb145ተ

“ጤና ትልቁ ንብረት ነው ፡፡ እርካታ እጅግ ውድ ሀብት ነው ፡፡ መተማመን ታላቁ ጓደኛ ነው ፡፡ አለመሆን ትልቁ ደስታ ነው ።”
— ላኦ ቱዙ
— ላኦ ቱዙ
❤4
ይመስለኝ ነበር...
የእኔ የሆነ አካባቢ ላይ መገኘት ለቦታው የሆነ የሚጨምረው ነገር እንደሚኖር አስብ ነበር...
...የሆነ value add እንደማደርግ ይሰማኝ ነበር።
ዋጋ የማይሰጥህ ቦታ መኖር ማለት ፤ እሾህ ላይ በባዶ እግር እንደመቆም ነው።
የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ @tibeb145

አባቷን ያጠባችው ልጅ
በጥንት የሮማዊያን ታሪክ ውስጥ የተፈፀመ እስካሁን ድረስ የፍቅርና መስዕዋትነት መገለጫ ተደርጎ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ነው የአባት ሲመንና የሴት ልጁ ፔሮ ታሪክ
ሲመን በእድሜ ማምሻቸው ለእስር ተዳርገው የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል፡፡ ፍርዱ ግን በስቅላት ወይም ጥይት ተተኩሶባቸው አልነበረም እንዲሞቱ የተወሰነባቸው፡፡ በራብ እንዲሞቱ ነበር።
በዚህን ግዜ ሞታቸውን በጥብቅ ቁጥጥር ስር ባለው እስር ቤት ሆነው እንዲጠብቁ ተደረጉ። በዚህ መሀል ልጃቸው ፔሮ አባቷን ከሞት የመታደግ ሀቅም ባይኖራትም ቢያንስ አባቷ አስኪሞት እየተመላለሰች እንድትጠይቃቸው አዛዦችን ተማፀነች። እነሱም ለአባቷ ያላትን ጥልቅ ፍቅር አይተው ፈቀዱላት ነገር ግን ምግብ በምንም መልኩ ይዛ ብትገባ የአባቷ እጣ እንደሚደርሳት አስጠነቀቋት። በርግጥ ፍተሻውም ሊያሳልፋት የሚችል አልነበረም።
በዚህ ሁኔታ ሳምንታት አለፉ፡፡ ጠባቂዎች ቢጠብቁ ሲመን ሊሞቱ አልቻሉም፡፡ ይባስ ብለው ያብረቀርቁ ጀመር። በዚህን ጊዜ ተደብቀው ነገሩን መከታተል ጀመሩ። ከዚህ በኋላ ነበር ለሰው ልጅ የፍቅርና መስዕዋትነት መለኪያ ሁኖ በታሪክየተሰነደውን ነገር የደረሱበት።
ለካስ ልጅ አባቷን ጡቷን እያጠባቻቸው ነበር ይህን ታክል ጊዜ ያቆየቻቸው።
ጠባቂዎች ይዘው ለአለቃቸው አቀረቧት። ለምን እንዳደረገች ስትጠየቅም እድሜ ልኬን እንዳልራብና እንዳልጠማ ያደረገኝ አባቴ እያየሁት በራብ ሲሞት እንዴት ይቻለኛል፡፡ ቀድሜው ብሞት እመርጣለሁ አለች።
በዚህን ጊዜ አለቆች ልባቸው ተሰበረ። ለአባቷ በከፈለችው መስዕዋትነት ግድያ ሳይሆን ክብር ነው የሚገባት ብለው አባቷንም በምህረት ፈቱላት ።
#ሰላም_ለሀገራችን_ሰላም_ለሕዝባች

👏10❤1🔥1🥰1