የሐቅ መንገድ (the path of truth)የንፅፅር ቤት
1.44K subscribers
157 photos
55 videos
286 links
የንፅፅር እና የአቂዳ ትምርቶች
Download Telegram
ኢየሱስ አምላክ ከሆነ የሚመለስበትን ቀን ለምን አላወቀም?
 
10. ማርቆስ 13፡32 ላይ “ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ከአብ በቀር ፣ የሰማይ መላእክትም ፣ወልድም ቢሆን ፣ ማንም አያውቅም

እንደተባለው ስለ ትንሣኤ ኢየሱስንም ጨምሮ ማንም ከአብ በቀር የሚያውቅ እንደሌለ ተገልጿል፡፡

ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስ ከአብ እኩል ከሆነ እንዴት የትንሣኤን ጊዜ ማወቅ ተሳነው?

አንዱ አምላክ አውቆ ሌላኛው “አምላክ ” ሳያውቅ እንዴት ቀረ? ኢየሱስ ሁሉንም የማያውቅ ከሆነ እንዴት አምላክ ነው ልንል እንደፍራለን?

አንዳንድ ክርስቲያኖች “ወልድ ሰው ስለሆነ ነው የማያውቀው ” ይላሉ፡፡ ግና ሰው ብቻ ነውን?

ኢየሱስ ወደ ምድር ሳይመጣ በፊትና ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ “ወልድ ” አይባልምን ታድያ ጥቅሱ “ወልድም ቢሆን” እንጂ “ምድር ሳለ፣ ስጋ በለበሰ ጊዜ” አይል?


https://t.me/thepath_of_truth
6👌1
https://youtu.be/dOiLwrlkcq8?si=waRA9tTfMZ9r8WhM


አወቅሽ አወቅሽ ሲሉዋት የቄስ ሚስት መጽሐፍ አጠበች አሉ¡

ምሁር ሊቅ ብላችሁ የምትጠሩት ጀለስ ይኸው ሙስሊም አይደለሁም አለ በራሱ አንደበት። አሁንም ጥብቅና ቁሙለት እስቲ

የፈለገ ብትጠበብ እውቀትህ ሞልቶ ቢፈስ እንኳን ሙስሊም አይደለሁም ብለህ መናገርህ የመጨረሻ የወረድክ መሆንህን የሚያሳይ ነው። ድንቄም ቡርሃን

وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
— سورة فصلت (41:33)

ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
— ፉሲለት (41:33)
🤣31👀1🙉1
18 الكهف
الشيخ عبدالله المطرود
سورة الكهف

ሱረቱል ካህፍ   የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያድምጥ

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል።

#የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል


https://t.me/thepath_of_truth
🥰3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሐጅ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن حَجَّ لِلَّهِ فَلَمْ يَرْفُثْ، ولَمْ يَفْسُقْ، رَجَعَ كَيَومِ ولَدَتْهُ أُمُّهُ﴾

“ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣ የአላህን ትዕዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከኃጢእቶቹ ሙሉ ጠርቶ ይመለሳል።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1561

#ይህ ሐዲስ የሐጅን ኢባዳ ታላቅነትና አላህ ለባሮቹ ያዘጋጀውን ሰፊ እዝነት በግልፅ ያሳያል።

#ሐጅ ማለት እንዲሁ አካላዊ ጉዞ ብቻ ሳይሆን፤ ምላስን ከመጥፎ ንግግር (ውሸት፣ ሀሜት፣ ጭቅጭቅ) የመጠበቅ እና ነፍስን ከአመፅ የማንጻት ከባድ የፅናት ጉዞ መሆኑንም ያስገነዝበናል።

¶​በአሁኑ ወቅት ለሐጅ ጉዞ እየተዘጋጁ ላሉ ወይም በአላህ ቤት ዙሪያ ለሚገኙ ሙስሊሞች ሁሉ አላህ ሐጃቸውን ‹‹መብሩር›› (ተቀባይነት ያለው) ያድርግላቸው። ኃጢአታቸው ተሰርዞ፣ ልክ እንደተወለደ ህጻን በንፅህና ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አላህ ይወፍቃቸው።

ረሂሙ ጌታ እኛንም ይወፍቀን


https://t.me/thepath_of_truth
🍓5🥰3🤣1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَالضُّحَىٰ
በረፋዱ እምላለሁ፡፡

وَاللَّيْلِ إِذَا سَجَىٰ
በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤

مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ
ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡

وَلَلْآخِرَةُ خَيْرٌ لَّكَ مِنَ الْأُولَى

መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡

وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ

ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَىٰ

የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡

وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ
የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
5👍1
ከቁርአን ጋር

يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ
وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡

"​ይህ አንቀጽ በሰዎች መካከል ሊኖር ስለሚገባው እኩልነት አንድነትና ልዩነቶቻችንን እንዴት መመልከት እንዳለብን የሚያስተምር መሠረታዊ መመሪያ ነው።

"​የሰው ልጅ አመጣጥ አንድነት፦ ሁሉም የሰው ልጅ የመጣው ከአንድ ወንድና ከአንድ ሴት (ከአዳምና ከሐዋ) መሆኑን በማስታወስ ማንም ከማንም የማይበልጥ እኩል ፍጡር መሆኑን ያበስራል።

"​የልዩነቶች ዓላማ (መተዋወቅ)፦ በቋንቋ በጎሳ በነገድ ወይም በዘር መከፋፈላችን አንዱ ከሌላው ለመበላለጥ ወይም ለመጨቆን ሳይሆን ውበት ሆነው እርስ በርስ እንድንማማርና እንድንተዋወቅ መሆኑን ይገልጻል።

"​እውነተኛው የብልጫ መስፈርት (ተቅዋ) በአላህ ዘንድ ትልቁና ብቸኛው የብልጫ መስፈርት ዘር ሀብት መልክ ወይም ስልጣን ሳይሆን አላህን መፍራት (ተቅዋ) እና መልካም ስነ-ምግባር ብቻ መሆኑን ያስተምራል።

ይህንን ካወቅን ደግሞ ይበልጥ አሏህን በመፍራት ከሰዎች ሁሉ በልጭ ልንሆን እዲሁም በዘር በገዘብ በጎሳ በብሔር መመካታችንን ልተው ይገባል ።

ረሂሙ ጌታ እርሱን ከሚፈሩት ባሮቹ ያድርገን


https://t.me/thepath_of_truth
🥰8
#የአረፋ ቀን ፆም መፆም እንዳንዘነጋ!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ሰ•ዐ•ወ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162


https://t.me/thepath_of_truth
9
እንኳን ለታላቁ ለ1447ኛው ለዒድ አል-አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እህት ወንድሞቼ

ኢዱን በዚክር በዱኣ በደስታ የምታሳልፉ አላህ ያርጋችሁ ዱአቸውን ከተቀበላቸው ባሮቹ አላህ ያድርገን


تقبل الله منا ومنكم


https://t.me/thepath_of_truth
10🥰4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM

🔖ጣፋጭ ቲላዋ

ቁርአን የልብ ብርሀን......
🥰3
#ኢማም ኢብኑል- ቀይም  አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፡-

በስንፍና አልጋ ላይ የተኛ ሰው በፀፀት ሸለቆ ውስጥ ተኝቶ ይነቃል። ቁምነገርም ሁሉ የተግባር ውጤት ሲሆን ፀፀትም ሁሉ የስንፍና ውጤት ነውና!።

📚بدائع الفوائد (١٢١٠/٣)


#አንድ ሰው ዛሬ ጊዜውን በቸልተኝነትና በስንፍና ካሳለፈ፣ የሚነቃው (የሚረዳው) ነገ ነገሮች ካመለጡት በኋላ ነው።

"በፀፀት ሸለቆ ውስጥ ይነቃል" የሚለው አገላለጽ ስንፍና መጀመሪያው ላይ ምቾት ቢመስልም መጨረሻው ግን የከፋ ሐዘን መሆኑን ያሳያል።

#​በህይወት ውስጥ ማንኛውም ስኬት እውቀትም ሆነ መንፈሳዊ እድገት የሚገኘው በምኞት ሳይሆን በተግባር ነው።

ቁምነገር ያለው ሰው የሚለካው በሚያከናውናቸው ተግባራት እንጂ በሚያልማቸው ህልሞች ብቻ አይደለም።

​ኢማሙ "ፀፀት ሁሉ የስንፍና ውጤት ነው" በማለት ያስጠነቅቁናል።

ዛሬ የምንዘራው ስንፍና ነገ ፀፀት ሆኖ ይጎዳናል።
ዛሬ የምንዘራው ጥረት ደግሞ ነገ ስኬትና ደስታ ሆኖ ይገኛል።

​ይህ ትምህርት በተለይ ጊዜያችንን በአግባቡ ለማንጠቀም ሰዎች እንድንጠቀምና ለነገ የምንለውን ስራ ዛሬ እንድንሰራ ትልቅ መነቃቂያ  ነው።

ከባድ ስራ ማለት መስራት ባለብን ሰአት ያልሰራነው ቀላል ስራ ነው ።

ረሂሙ ጌታ ጊዜአቸውን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ባሮቹ ያድርገን


https://t.me/thepath_of_truth
🥰10💯32
سورة الكهف كاملة للقارئ عمر الدريويز | Al-Kahf sorah - Omar Aldarweez
<unknown>
وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا
.
እና ታላቅ መለኮታዊ መጽሐፍ ሲሆን ዘላለማዊ ተአምር የሆነ ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው።


سورة الكهف كاملة
Omer Aldarweez 🎙
#እድለቢስ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐

“እድለቢስ ማለት እኔ እሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሰለዋት ያላወረደ ነው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 3546
🍓42
በችግር በመከራ ያላችሁ ሰዎሽ አብሽሩ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يودُّ أَهلُ العافيةِ يومَ القيامةِ حينَ يعطى أَهلُ البلاءِ الثَّوابَ لو أنَّ جلودَهم كانت قُرِضَت في الدُّنيا بالمقاريضِ﴾

“በቂያማ እለት ዱኒያ ላይ እያሉ ጤናማ (ከመከራ) ነፃ የነበሩ ሰዎች የመከራ ባልተቤቶች የነበሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ምንዳ ሲያዩ እንደነሱ ቢሆኑ ይመኛሉ እዚህ ዱኒያ ላይ እያሉ ቆዳቸው በመቀስ (በስለት) የተቆረጠ በነበር ቢሆን ይመኛሉ።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል፡ 2402

#በአሁኑ ሰዓት በፈተና እና በመከራ ውስጥ ላሉ ወንድም እህቶቻችን ይህ የነቢዩ (ﷺ) ሐዲስ ትልቅ ተስፋ እና ብርታት የሚሰጥ ነው።

እኛ በሰውኛ እይታችን መከራን እንደ ጉዳት ብናየውም በአላህ ዘንድ ግን የመከራ ባለቤቶች የሚሰጣቸው ክብርና ምንዳ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል።

መከራው ሲመጣ በትዕግስት የሚያልፉ ሰዎች የቂያማ እለት ሌሎች የሚቀኑባቸው ደረጃ ላይ ይደርሳሉ።

​አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው በዱኒያ ላይ ይፈትነዋል ይህም ወንጀሉ እንዲረግፍለትና ደረጃው ከፍ እንዲል ነው።

#የዚህ ዓለም ስቃይ ምንም ያህል ቢበዛ አጭርና ጠፊ ነው ለዛ ስቃይ የሚሰጠው ሽልማት ግን ዘላለማዊ ነው።

​አላህ ከሚታገሱትና በቂያማ እለት ያንን ታላቅ ምንዳ ከሚቀበሉት ያድርገን በእርግጥም "ከችግር ጋር ምቾት አለ"

{ إِنَّ مَعَ ٱلۡعُسۡرِ یُسۡرࣰا }


https://t.me/thepath_of_truth
7👍1
እዚህ ጥቅስ ላይ ምን ትረዳላችሁ ወገኖቻችን ???
👨‍💻6👍2
መልስ በማስረጃ ቢሆን ይመረጣል ወገኖች።

ከእንቅልፍ የሚነቃ አምላክ?
የሚነቃውም ሰው ከእንቅልፍ አስነስቶት ከሆነ ምንም አያቅም።ማለት ነው? እንደት ይህ አካል ይመለካል? አይ የተኛው በመለኮቱ አይደለም በስጋው ነው። ካላችሁ ለምን ተኝቶ በመለኮቱ አላስቆመውም? ከእንቅልፍ እስከሚቀሰቀስ ለምን ጠበቀ ሁሉን ካወቀ?
“እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።”
📕 ማርቆስ 4፥38

አንዱን አምላክ ተገዙ ሳይመሽባችሁ ወገኖች
اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡

📖ምዕራፍ البقرة 2:255


https://t.me/thepath_of_truth
👍72
⚡️ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል

ጥያቄ
⁉️
የሱብሂ ሶላት ስንት ረከዓ አለው


🧎‍♂🧎‍♂🧎‍♂
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ረዝቅና ሞት ያለቀጠሮ ነው የሚመጡት
እዚህ ዱኒያ ላይ እስካለህ ድረስ ሪዝቅህን ትጠቀማለህ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لو أنَّ ابنَ آدمَ هرب من رزقِه كما يهرُبُ من الموتِ، لأدركه رزقُه كما يُدرِكُه الموتُ﴾

“የአደም ልጅ ከሞት እንደሚሸሸው ሁሉ ከሪዝቁ (ከሲሳዩ) ቢሸሽ ኖሮ ሞት እንደሚያገኘው ሲሳዩም ያገኘው ነበር።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 952

#እንዴት ያለ ውብ እና ልብን የሚያሳርፍ መልዕክት ነው!

ይህ የነቢዩ (ﷺ) ሐዲስ በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ስላለው የሪዝቅ (ሲሳይ) ዋስትና ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

​በአሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችን ስለ ነገ ስንጨነቅ "ምን እበላለሁ? ምን እጠጣለሁ?" እያልን ስናስብ ይህ ሐዲስ የጭንቀታችንን መፍትሄ እንዲህ ያስቀምጠዋል፡-

#​የሪዝቅ እርግጠኝነት፡ ሞት ለማንም እንደማይቀር ሁሉ ለአንድ ሰው የተጻፈለት ሲሳይም ሳያገኘው አይቀርም።

#​የልብ መረጋጋት፡ ሰው መሞቱ የማይቀር መሆኑን አምኖ እንደሚቀበለው ሁሉ ሲሳዩም ዘግይቶም ቢሆን እንደሚመጣ ማመኑ ከከንቱ ጭንቀት ያርቀዋል።

#​ሰበብ ማድረስ፡ ይህ ማለት ግን ዝም ብሎ መቀመጥ ማለት ሳይሆን ልብን በአላህ ላይ ጥሎ (ተወኩል አድርጎ) አስፈላጊውን ጥረት ማድረግን አለብን።

​ባለንበት ዓለም ላይ ለቁሳቁስ የምናደርገው ሩጫ በዝቶ ሰላም ባጣንበት ወቅት እንዲህ ያሉ መንፈሳዊ ማስታወሻዎች ወደ እውነተኛው የውስጥ ሰላም ይመልሱናል።

ረሂሙ ጌታችን
ባለን ነገር ላይ በረካውን ያውርድልን የሰጠንን ሪዝቅም ለበጎ ተግባር የምናውለው ያድርገን ያረብ


https://t.me/thepath_of_truth
1👍1
ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ

ወደኸይር ያመላከ የሰራውን ሰው አጅር ያገኛል ረሱል (ﷺ)
👍2