ቴዎፍሎስ theophilus
214 subscribers
147 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ሰላም ተወዳጆች ዛሬ አንድ ቃል ላካፍላቹ ብቅ ብያለዉ
የሐዋሳ ሀይቅ ላይ የተተከሉት ቄጤማ ማእበል በሚመጣ ጊዜ የሚያሳልፍት ዝቅ ብለዉ ነዉ በአሁን ዘመን ካለዉ ክፍት ማምለጥ የምንችለዉ ስለዘመኑ ክፍት በማዉራት ሳይሆን በእልፍኝ ዉስጥ ገብቶ ዝቅ በማለት ማለትም በመፀለይ ነዉ
ተባርካቿል #ፀደቀ ነኝ
ሰላም ተወዳጆች
መፅመፍ ቅዱሳችንን የመያዝ ልምድ ይኑረን
ሙስሊሙ ከመስጊድ እንደሚመጡ የምናዉቀዉ በሚያደርጉት ልብስና በያዙት መስገጃ ነዉ ኦርቶዶክሱ ከቤተክርስቲያን እንደሚመጡ ደግሞ የምናዉቀዉ በሚያደርጉት ነጠላ ነዉ እኛ ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ መፅሐፍ ቅዱስ ካልያዝን ቤተክርስቲያን መሄዳችን ወይም ከቤተክርስቲያን መምጣታችን በምን ያስታዉቃል
እኔን ሀጢአተኛዉን እ/ር በማይለቀዉ እጁ ከያዘኝ እኔ ደግሞ መፅሐፍ ቅዱስ ለመያዝ አይከብደኝም
ተባርካቿል #ፀደቀ ነኝ
ብዙዎቻችን ንስሀ የመግባት ችግር የለብንም ተመልሰን ወደ ሀጢአት የመግባት እንጂ በልጅነታችን በጭቃ ተጫዉተን ልብሳችን ከቆሸሸ ቡሀላ እናቶቻችን በደንብ አድርገዉ ያጥቡናል በመቀጠልም ልብስ ይቀይሩልናል ካሰማመሩን ቡሀላ ግን በድጋሚ በዛ ጭቃ እየተጫወትን ብታየን ምን ያክል እንደምታዝን መገመት አይከብደንም እግዚአብሄር ንስሀ ስንገባ የልጁ የክርስቶስ ደም ዛሬም ትኩስ ነዉና ከሀጢአታችን ያነፃናል እኛ ግን በድጋሚ ከወደቀዉ አዳም ጋር በሀጢአት ስንቦራጨቅ ሲያይ እግዚአብሄር ምን ያክል እያዘነብን ይሁን። እግዚአብሄር ይበልጥ የሚደሰተዉ ንስሀ መግባታችን ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰን ወደ ሀጢአት አለመግባታችን ላይ ነዉ።
#ፀደቀ #መንፈሰ
እንኳን ተወለዳችሁ ይህ ያልኩበት ምክንያት የእየሱስ መወለድ የእኛ መወለድ ስለሆነ ነዉ ኢየሱስ በበረት ዉስጥ ሲወለድ የበረቱ ሽታ ለነማርያም ሆነ ለህፃኑ እየሱስ የሚስማማ አይደለም ሰዉ እንኳን በረትን ምርጫዉ ሊያደርግ አይደለም በዛን ለማለፍ እራሱ አፍንጫዉን ይዞ ነዉ የሚያልፈዉ እየሱስም እኛን መምረጡ ልክ እንደዚህ ይገርማል በበደላችንና በሀጢአታችን ሙታን ስለነበርን ከበረቱ ሽታ የበለጠ የእኛ ሽታ ይበልጥ ነበር ሰብአ ሰገዶቹ ለተወለደዉ ህፃን ይዘዉ የመጡት እጣን ከርቤና ወርቅ ነዉ መርጠዉ የሰገዱትም ለሱ ነዉ የእኛ እየሱስ እኮ እንኳን በዙፍኑ ተቀምጦ አይደለም በበረት ተኝቶ እንኳን ተሰግዶለታል እርሱ እንኳን በመላእክት ታጅቦ አይደለም በከብቶች ታጅቦ እንኳን ተሰግዶለታል ወገቡን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቆ አይደለም በጨርቅ መጠቅለያ ተጠቅልሎ እንኳን ተሰግዶለታል እኔን በጣም የገረመኝ ለወደቀዉ አዳም ያማረዉን ኤደን ገነት ለመኖሪያዉ ሰጠዉ ለራሱ ግን የመረጠዉ የከብቶች ማደሪያን በረትን ነዉ ኢየሱስ በከብቶች ማደሪያ መወለዱ ሳይሆን የሚገርመኝ ከእኔ ጋር መኖሩ ነዉ በድጋሚ ልበላችሁ እንኳን ተወለዳችሁ። መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ ይህንን መልእክት ለሌላዉ ያስተላልፉ
ተባርካቿል #ፀደቀ ነኝ
ሰላም ተወዳጆች ዛሬ አንድ መፅሐፍ ላስተዋዉቃቹ ይህ መፅሐፍ በዎችማን ኒ የተፃፈ ሲሆን ስለ ሰዉ ሁለንተና ማለትም ስለ ሰዉ መንፈስ: ነብስና: ስጋ በጠለቀ ሁኔታ ያብራራል። እናንተም እንድታነቡት እጋብዛችኋለሁ።
#ፀደቀ ነኝ
ቃልህን እወደዋለሁ- I.pdf
1.1 MB
ይህ ቃልህን እወደዋለሁ የተሰኘ አጠር ያለ ፅሑፍ ሲሆን ስለ መፅሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ ዳራ ለማወቅ ለሚፈልጉና የመፅሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴዎችን ለመረዳት ፍላጎቱ ላላቸው ጥሩ ጥቆማን ይሰጣል።

#ፀደቀ #መንፈሰ እንደፃፈዉ
ከአንድ ወንድም ጋር ስለ ሴቶች አገልግሎት ሰፍ ባለ መልኩ ከመፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀስን እንወያይ ነበር እሱ የሴቶችን አገልግሎት ብዙም አይቀበልም ነበር በተለይም መስበክና ማስተርን እናም በንግግራችን መሀል ለምሳሌ አለኝ ለወንድ አገልጋይ መጋቢ እንላለን ለሴት ሲሆን መጋቢት ልንል ነዉ? እርሱ ደግሞ ወር እንጂ ፀጋ አይደለም አለኝ😊
እኔም ቀበል አድርጌ ጥያቄ የሆነብኝን ሀሳብ ሰነዘርኩለት
እኛ በአብያተ ቤተክርስቲያን የምናዉቀዉና የለመድነዉ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ በማለት ነዉ እኔ ግን የማዉቃት ከቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል አንዲት ሴት አለች የምትባለዉ ግን የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ነዉ ታዲያ ይህቺን መሪ የቤተክርስቲያን አሮጊት😂 ብለን ብንጠራ ምንድ ነዉ ችግሩ? እስኪ የእናንተንም ምላሽ በ inbox እፈልጋለሁ

#ፀደቀ ነኝ
ለአንድ ጓደኛዬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ አወራዋለሁ መዳን በእርሱ ብቻ እንደሆነና የዘላለምንም ህይወት ለማግኘት በእርሱ ማመን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ መሰክርለታለሁ። የቀመስኩትንም ጣዕም እንዲቀምሰዉ ብዬ ስለ ጣዕሙ አወራዋለሁ። ቃሉስ " ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ አይደል የሚለዉ። ይህንን ጣዕም የቀመሰ የአለም ነገር ይመረዋል። አንድ ጊዜ እንዲህ አለኝ ፀዴ ኢየሱስን ተቀበል አትበለኝ አሁን ያለሁበት life በጣም ተመችቶኛል አለኝ። እንዲህ ሲለኝ በዉስጤ ምናለ ኢየሱስ የህይወት ጣዕም ብቻ ሳይሆን በአፍ የማቀምሰዉ ጣዕም በአፍንጫ የሚሸተት መዓዛ በሆነ ብዬ ተመኘዉ ጣዕሙን ቢያዉቅና መአዛዉን ቢያሸተዉ እርሱ ራሱ ለመቀበል ይጣደፍ ነበር። ልጅ እያለሁ የምማርበት ትምህርት ቤት ከመኖሪያ ቤቴ ስለሚርቅ ሁል ጊዜ ምሳ ይቋጠርልኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ግን የተቋጠረዉን ምሳ ሳልበላዉ እመልሰዋለሁ ምክንያቱም ምሳ የምንበላዉ በአንድ ክፍል ዉስጥ ስለሆነ ያመጣነዉ ምሳ ምን እንደሆነ እርስ በእርስ እንተያያለን የአንዳንዱ ምሳ ሲከፈት መአዛዉ ሲበላ ጣዕሙ ልዪ ስለሆነ የእኔን መብላት ይደብረኝና የእኔን ትቼ ከእነርሱ አንዴ እንዲያጎርሱኝ አይን አይናቸዉን አያለሁ አንዴ ከቀመስኩም የእኔ ምሳ እቃ ይዘጋና ወደ ቦርሳ ዉስጥ ይገባል ሳይበላም ወደ ቤት ይመጣል። ያስቋጠርኩትን ምግብ ጣዕሙን የሚያጠፍ ምግብ ሳገኝ የእኔን መብላት አስጠላኝ። ያኔ ለዛ ልጅ ኢየሱስ ጣዕም ሆኖ ባቀመስኩት ያልኩትን እያሰብኩት ነበር ለካ ኢየሱስም ናፍቆት ይሄ ነበር እርሱን እንድመስልና ሰዎች የእርሱን መአዛ ከህይወቴ እንዲያሸቱ።
አሁን ያለሁበት life ተመችትኛል ያለኝ ልጅ አሁን ጌታን ተቀብሏል በቅርቡ አግንቼዉ ያለኝ ልቤን ገዛዉ ''ጨለማ ጨለማ እንደሆነ የሚታወቀዉ ብርሃንን ስናይ ነዉ ብርሃንን ካየን ደግሞ ጨለማዉ ያስጠላናል'' ። ጌታ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ተገኝቶ እነርሱ ዋነኛ ብለዉ ያዘጋጁትን ወይን ጠጅ መናኛ እንዳስባለዉ ሁሉ አንድ አማኝ ጌታ ኢየሱስ ሲቀበል ዋነኛ ያለዉን መናኛ በማለት ነዉ ክርስትናን የሚጀምረዉ።

#ፀደቀ ነኝ
ጊዜ በሰዎች ሆኖ ለሚጠይቃችሁ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ሁኑ

ጊዜ በራሱ በተለያያ ወቅትና በተለያዩ ሰዎች የሚጠይቃችሁ ጥያቄ አለ ጊዜ ለሚጠይቃችሁ ጥያቄ ሁል ጊዜ በጎ ምላሽ ለመስጠት በተሰጣችሁ ጊዜ መጠቀም መቻል አለባችሁ። ጊዜ በሰዎች ከሚጠይቃቸዉ በጥቂቱ
ተማሪ እያለህ ጊዜ በሰዎች ሆኖ እህህ ትምህርት እንዴት ነዉ? ዉጤትስ እንዴት ነዉ እየሰራህ ነዉ? ሲልህ ምላሽህ አዎ በጣም ጥሩ ዉጤት አለኝ ለማለት በተሰጠህ ጊዜ ማጥናት መቻል አለብህ

ከትምህርት በኃላ ደግሞ ስለ ስራ መጠየቅህ አይቀሬ ነዉ። ጊዜ በሰዎች ሆኖ ከትምህርት በኃላ ስለ ትምህርት አይጠይቅህም ስለ ስራ እንጂ ይሄንንም ምላሽ ለመስጠት ከትምህርት በኃላ ጊዚያችሁን ማጥፍት ያለባችሁ ስራን በሚመለከቱ ጉዳዮች መሆን አለበት ለምሳሌ ተማሪ እያላችሁ አብዛኛዉን ጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ናቸዉ ሰራተኛ ከሆናችሁ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም አብዛኛዉን ጓደኞቻችሁ ሰራተኞች ይሆናሉ። ጊዜ ከሚሰጣችሁ ጓደኛ ጋር መወዳጀት አለባችሁ። በእርግጠኝነት አንድ ተማሪ አብዛኛዉ ጓደኞቹ ነጋዴዎች ከሆኑ ትምህርቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ይከብደዋል። በዚህም ምክንያት ትምህርቱን እስከማቋረጥ ሊደርስ ይችላል። ሁሉም ግን ያቋርጣሉ ማለት አይደለም። ከኔ ጓደኞች እንዳየሁት ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ ተማሪ እያሉ ዉሏቸዉ ከነጋዴ ጋር የነበሩ አሁን ላይ ትምህርት አቋርጠዋል። አንድ ተማሪ እየተማረ በፍፁም መነገድ የለበትም የሚል አቋም የለኝም ነገር ግን ትኩረቱንና አብዛኛዉን ጊዜዉን መስጠት ያለበት ለትምህርቱ ነዉ የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። ደግሞ በስራ ላይ እያላችሁ ጊዜ በሰዎች በተደጋጋሚ የሚጠይቃችሁ ጥያቄ አለ እርሱም መች ልታገባ/ቢ አሰብክ/ሽ? ይሄማ ጥያቄ ከየ አቅጣጫዉ የሚሰነዘር ነዉ በተለይም አህቶች ላይ ይበረታል ከቤተሰብ:ከጓደኛ:ከአካባቢ ሰዉ በተደጋጋሚ ትጠየቃለች አገባሽ? መች ልታገቢ ነዉ? የሚል ድግግሞሽ ጥያቄ ትጠየቃለች። ከአባት ይልቅ እናት የልጆቿን ሰርግ ማየት ትናፍቃለች። እናም እናት ልጅ ባለችበት ወሬዋ ስለ ሰርግ ይሆናል እናት ወሬዋን ትጀምራለች ባለፈዉ ሳምንት የሄድኩት የአቶ ከበደ ልጅ ሰርግ እንዴት ግሩም መሰለሽ ሰርግ ቢሉሽ ሰርግ መሰለሽ? እንደዉ ለአንቺማ የምደግሰዉ ድግስ ይታየኛል በማለት የአግቢልኝ ተማፅኖዋን በተዘዋዋሪ ታቀርባለች። ልጅም ሰምቶ እንዳልሰማ ምላሿ ዝምታ ይሆናል። ደግሞ በ faccebook እና በተለያዩ social Media የጓደኞቿን የሰርግ post መመልከቷ አይቀሬ ነዉ ይሄ ሁሉ አግቢ እንጂ ምን ትጠብቂያለሽ የሚል ንዝነዛ መሆኑ ነዉ። በጊዜ ስትጨቀጨቅ እንቢ ብላ ጊዜ ካለፈ በኃላ
ጠይቁኝ ብላ ሰዎችን ብትጠይቅ እንኳን ጠያቂ ታጣለች። አያችሁ ሰዉ እንኳን የሚጨቀጭቀዉንና የሚጠይቀን ጊዜዉ ሳይመሽ ነዉ አስባችሁታል የ60 አመትን ሴት ማነዉ አግቢ ብሎ የሚጨቀጭቃት?
ማንም የሚኖር አይመስለኝም። ምክንያቱም ከጊዜ ጋር ተላልፍለችና
ምንም ነገር በጊዜዉ ሲሆን ዉበትን ያገኛል።ይሄን ሁሉ መልእክት የፃፍኩት አንድ ሀሳብ ለማስተላለፍ ነዉ ጊዜ በሰዎች አሁን ባለህበት ሁኔታ የሚጠይቅህና የሚጨቀጭቅህ ነገር አለ ለእርሱ ምላሽ ለመስጠት በተሰጠህ ጊዜ ተጠቀም። ከረፈደ ብቻ እንዳትነቃ
ጊዜ ደግ ብቻ እንዳይመስልህ በጣም ጭካኝም ነዉ ደግነቱ ለሁሉም ሳያዳላ በቀን 24 ሰአት መስጠቱ ነዉ ጭካኔዉ ደግሞ ያለፈዉን ትላንት ተጠቀምክበትም አልተጠቀምክበትም ደግሞ በፍፁም አለመስጠቱ ነዉ። ጊዜ ለሚጠይቃቸዉ ምላሽ ላለመስጠት የሚሸሹ በጊዚያቸዉ ያልተጠቀሙ ፈሪ ሰዎች ናቸዉ።

በተሰጠን ጊዜ እንጠቀም መልእክቴ ነዉ
#ፀደቀ ነኝ
ቀን 29 02 2015
አንድ እዉነት እስኪ ላጋራችሁ አብዛኛዉን የሚጨንቃቸዉና እንቅልፍ የሚያጡ ሰዎች ከለሊቱ 8 ሰአት እስከ 9 ሰአት ድረስ አይተኙም ነገር ግን ከለሊቱ 9 ሰአት በኃላ እንቅልፍቸዉ ይመጣል ደግሞም ሰላም ይሰማቸዋል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ታዉቃላችሁ እንደ አለም አቀፍ አብዛኛዉን ክርስቲያን ለፀሎት የሚነሳዉ ከ 9 ሰአት ጀምሮ ስለሆነ ነዉ (universal pray) እንደ አለም አቀፍ አብዛኛዉን ስርቆት የሚከናወነዉ እስከ ለሊቱ 8:30 ባለዉ ሰአት ነዉ እንዲሁም አብዛኛዉን መሸታ ቤቶች የሚዘጉት ከ9 ሰአት በፊት ነዉ።
ፀሎት ጉልበት አለዉ። universal pray ያልተቀላቀላችሁ ካላችሁ እንድትቀላቀሉ ላሳስባችሁ እወዳለሁ ከለሊቱ 9 እስከ12 ባለዉ alarm ሞልታችሁ ነቅታችሁ ፀልዩ

#ፀደቀ ነኝ
በገሊላ ቃና
ጌታ ሆይ በገሊላ ቃና ተአምራትህን ስትገልጥ እድምተኛን አልፈለክም ተመልካችም አላበዛህም። የሰዉን ዉርደት የማትወድ በመናኛዉ ሰዓት ዋነኛዉን የምታቀርብ ሰርገኛዉ ወይን ጠጅ ማለቁን ሳይሰማ ጣፍጭ እንደቀረበ የምታሰማ። ያንተ መኖር የባለ ሰርገኛዉን ሰርግ አድምቆታል አንተ ግን እኔ ባልኖር ምን ትሆኑ ነበር አላልካቸዉም እንዲሁም ዉሀዉን ወደ ወይን ጠጅ ስቀይረዉ ተመልከቱ ብለህ ተአምራትህን በሰርጉ አዳራሽ አላደረክም ምክንያቱም በሰርጉ አዳራሽ ቢሆን ለሰርጉ የመጡ እድምተኞች ሁሉም ትኩረታቸዉን ከባለ ሰርጉ ይልቅ ወደ አንተ ይሆን ነበር ባለ ሰርጉም ትኩረትን ያጣ ነበር። ምንያክል እንደተጠነቀክለት አየዉ
አንተ በጓዳ ተአምራትህን አድርገህ በአደባባይ የምታከብር አፈረን ሲሉ የምታሳርፍ አምላክ ነህ
እኛ ግን ባንተ ድግስ እንደ ደጋሽ መታየትን እንፈልጋለን አንተ በእኛ ስትፈዉስ ልክ እንደፈዋሽ ያደርገናል። የተአትምራት ትልቁ አላማ ተአምረኛ የሆንከዉን አንተን መግለጥ ነዉና አንተን ለማሳየት ሽር ጉድ እንድንልልህ አቅምን ስጠን።🙏


#ፀደቀ ነኝ
ገባኝ ያልከዉን እዉቀት ወደ ታች ወርደህ ቢያስንስ ከ12 እስከ 14 እድሜ ያለን ህፃን በደንብ ማስረዳት ካልቻልክ ያወከዉን በደንብ አልተረዳኸዉም ማለት ነዉ። እንዲህ ሆነ corona በደንብ በተንሰራፍበት ወቅት በlockdown ጊዜ ለምን ህፃናትን መፅሐፍ ቅዱስ አላስተምርም ብዬ ልጆችን መሰብሰብ ጀመርኩኝ ከቤታችን ጀምሬ ጎረቤታችን ያሉትን ልጆች ሰብስቤ ማስተማር ጀመርኩኝ። በማስተምራቸዉ ጊዜ አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ህፃናትን ማስተማር በጣም ከባድ እንደሆነ ነዉ። አንዳንድ ያወኩዋቸዉ እዉቀቶች በደንብ እንዳልገቡኝ ተረዳሁ። ምክንያቱም ህፃናትን ለማስተማር የተለያዩ ምሳሌዎችን መጠቀም የግድ ይላል። አንድ የገባህን ነገር በደንብ ከተረዳኸዉ እርሱን ለማስረዳት የሚሆኑ ምሳሌዎችን አታጣም። በደንብ ካልተረዳኸዉ ግን በየትኛዉ ምሳሌ እንደምታስረዳ ግራ ይገባሀል😊 ገባኝ ያላችሁትን ጠለቅ ያለና ዉስብስብ የሆነን ትምህርት በተለያዩ ምሳሌዎች ተጠቅማችሁ በጣም ቀላል አድርጋችሁ ለ13አመት ልጅ ማስረዳት ካልቻላችሁ በደንብ አልገባችሁም።

እስኪ እናንተም ሞክሩት

#ፀደቀ ነኝ
ቀን 24 5 2015