ታላቁ እስክንድር ከመሞቱ በፊት የሰራዊቱን አዛዥ ጠርቶ ሦስት ያልተለመዱ ጥያቄዎችን ጠየቀ
1,“ምርጥ የሚባሉት ዶክተሮች የሬሳ ሳጥኔን ይሸከሙልኝ ”ታዋቂ የተባሉት ዶክተሮች እንኳ በሞት ፊት አቅም እንደሌላቸው እንዲያዩ።
2. “የወርቅ ሳንቲሞችን እና የከበሩ ፈርጦችን ወደ መቃብሬ በሚወስደው መንገድ ላይ እንዲበተን። ” በህይወት የምናከማቸዉ ሀብት ስንሄድ ወደኋላ እንደሚቀር አለም እንድትገነዘብ
3. “እጆቼ ከሬሳ ሳጥኔ ውጪ ይዝለቁ፣ ለሁሉም ይታይ” ሁሉም ሰው እንዲያውቀው — ንጉስ እንኳን ባዶ እጁን ነው የሚሄደው የሚለውን።
አዛዡ ደንግጦ ግራ ገብቶት እንዲህ ያልተለመደ ምኞት ለምን ብሎ ሲጠይቀው ታላቁ አሌክሳንደር እንዲህ አስረዳ፡
“ህዝቡ እውነቱን ይየው። የኃይልንም ልክ፣ የሀብትንም ልክ ፣ የሞትንም አይቀሬነት ያስተውሉ። ግማሽ አለምን አሸነፍኩ...
በመጨረሻ ግን ምንም ነገር ይዤ አልሄድም። ” መንግስታትን የገዛ፣ ሰፊ ሰራዊቶችን ያዘዘ እና ሊታሰቡ የማይችሉ ሀብቶችን የተቆጣጠረ ሰው ከሁሉ የሚበልጠውን ትምህርት ተናገረ...
ህይወት ባከማቸኸው ነገር አይደለም ምንም ማእረግ፤ ምንም ንብረት፣ ምንም ሀብት በመጨረሻ አያደርሰንም አሻራችን ብቻ ነው የኛ እውነት። ስለዚህ አውቀህ ኑር።
በልግስና ስጡ፣በቅንነት ተናገሩ በነፃነት ይቅር በሉ፣በትህትናም ተራመድ። ምክንያቱም የመጨረሻው ሰዓት ሲመጣ ሁላችንም አንድ አይነት መንገድ እንሄዳለን - ከስማችን እና ከሰጠነው ፍቅር በቀር ሌላ ምንም አይኖርም!!
https://t.me/thbigdream

❤1
አንዳንድ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም፡፡ ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል እንኳን፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትናንት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን።
📓አዎ እሱ ጋ ያመኛል
📓አዎ እሱ ጋ ያመኛል
❤1
በጊዜ ውስጥ "ትናንት'' ትዝታ ፡ ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው ፡፡ ካመለጠ ትናንት... ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉ ይበልጣል።
📓ሌላ ሰው
📓ሌላ ሰው
❤1
ሕልም አለኝ? ካለኝ፣ እየኖርኩት ነው? ከሌለኝስ፣ ለምን?
ሕልማችሁን ዓላማ፣ ራእይ ወይም ደግሞ ሌላ ስም እንድትሰጡት ነጻነቱን ለእናንተው ልተወውና፣ እዚህ ጋር እንድታስቡት የምፈልገው ለነገ የምትኖሩለትን ነገርና ከኖራችሁት በኋላ መለስ ብላችሁ፣ “እንኳን ይህንን መንገድ ተከተልኩኝ” የምትሉለትን ነገር ነው፡፡ ይህንን እውነታ በትክክለኛ ስሙ ከጠራነው ምንም እንኳን “ራእይ” ብለን ልንጠራው ቢገባንም፣ የመጠሪያ ስሙን ለእናንተው በመተው ወደ ዋናው ሃሳብ ልግባ፡፡
አንዳንድ ሰዎች “ሕልም የሌለው ሰው እንዴት ሊኖር ይችላል?” በማለት አክርረው ሲሞግቱ ይታያሉ፡፡ ጉዳዩ እንደዚህ በአንድ የአቋም መግለጫ መልስ የሚያገኝ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ሕልምን አስመልክቶ አራት አይነት ሰዎች አለን (የምንነጋገረው ጤናማ ሕልምን አስመልክቶ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም የለንም፡፡ ማለትም፣ በውስጣችን የሚቀጣጠል፣ የወደፊታችንን በጉጉት እንድንጠብቀውና ለዚያ የሚያስፈልገንን ነገር አሁን እንድንሰራና እንድናጠራቅም የሚያደርገን የምናየው ነገር የለንም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ዛሬውኑ ሕልማቸውን የማግኘት ጉዞ እንዲጀምሩ ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻች ሕልም ነበረን ሕልማችን ግን ሞቶብናል (ጥለነዋል)፡፡ ማለትም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በማሳለፋችን ምክንያት ተስፋ ቆርጠን፣ በአጉል ሰዎች ተጽእኖ ስር ከመውደቃችን የተነሳ ጫና ተደርጎብንና አንዳንድ ውስብስብ ፍልስፍናዎች ውስጥ ከመተብተባችን የተነሳ ግራ ተጋብተን ሕልማችንን ትተነዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሕልማቸውን የጣሉት የቱ ጋር እንደሆነ ፈልገው በማግኘት እንደገና እንዲያነሱት ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም ነበረን፣ ሕልሙ አሁንም አለ፣ ነገር ግን ሕልሙ እውን የሚሆንበት ጊዜው ረዝሞብንና ሕልማችን ሌላ፣ የምንኖረው ኑሮ ደግሞ ሌላ ሆኖብን ዝለናል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሕልም ጊዜ እንደሚጠይቅና አጥብቀው ከተከታተሉት በርግጥም እውን እንደሚሆን በማወቅ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም አለን፣ ሕልማችንንም በንቃት እየተከታተልን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች በዚያው እንዲቀጥሉ ይመከራሉ፡፡
ሕልምን ማግኘት ማንነትን የማግኘት አንዱና ዋነኛው ክፍል ነው፡፡ ዛሬ ይህንን ጥያቄ በሚገባ ለመጠየቅና ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ከተጠቀሱት ደረጃዎች በየትኛው ላይ እንዳለህና ምን ለማድረግ እንደምታስብ ሃሳብ ለመጻፍ ሞክር፡፡

#ሕልማችንን እውን ለማድረግ የገበሬ ልብ ይኑረን! 🌾✨
ታላቅ ሕልም አለህ? ከሆነ፣ ዕድገትን እና ስኬትን በትክክል የሚያውቀውን ገበሬውን መመልከት አለብህ።ገበሬው የትምህርት ደረጃው ከፍ ያለ ላይሆን ይችላል፣ ግን የሕይወት እና የፍሬ የማፍራት ጥልቅ ምስጢርን ይረዳል።
#እኛም ሕልማችን እውን እንዲሆን፣ የገበሬው አይነት ጽኑ ልብ ሊኖረን ይገባል።
“የወደፊት ዕጣ ፈንታህ የሚወሰነው በሕልሞችህ መጠን ሳይሆን በዕለታዊ ልማዶችህ ነው።” – ጆን ሲ. ማክስዌል
1. የገበሬው የምርጫ እና የትዕግስት ትምህርት
✓ዘር መምረጥ: ገበሬው ምርጡን ዘር ለላቀ ፍሬ እንደሚያዘጋጅ ሁሉ፣ እኛም ከብዙ ሃሳቦች መካከል፣ በሕይወታችን ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚያመጣውን፣ ምርጡን የተፈጠርንለትን ሕልም መምረጥ አለብን።
✓ትዕግስት፡ ገበሬው ዘሩ ፍሬ የሚያፈራበትን ጊዜ በትክክል ይገምታል። እኛም ሕልማችን እንዲያድግ፣ እንዲያብብ እና ፍሬ እንዲያፈራ ጊዜ መስጠትና ትዕግስት ሊኖረን ይገባል። ሁሉም ነገር የራሱ ጊዜ አለው።
2. የገበሬው የዕለት ተዕለት ተግባር (የእምነት ድርጊት)
ገበሬው ዘሩን ከዘራ በኋላ እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፤ ሕልሙ እውን እስኪሆን ከእምነቱ ጋር የሚመጥን ተግባር ይሰራል።
✓🌱 ያርማል፣ ይኮተኩታል፡ አረም ሰብሉን እንደሚያውክ ሁሉ፣ በየቀኑ የሚመጡትን #አሉታዊ ሀሳቦች እና ስሜቶችን ማረም እና ማስወገድ አለብን።
✓☀️ ማዳበሪያ ያደርጋል፡ አእምሮህን በአዎንታዊ አስተሳሰቦች፣ በአዳዲስ ዕውቀት እና በተነሳሽነት መመገብ አለብህ።
✓ 🛡️ ፀረ-ባክቴሪያ ይረጫል ፡ ልክ ሰብሉን ከበሽታ እንደሚከላከል ሁሉ፣ አንተም ጠዋት እና ማታ ለራስህ ጊዜ በመስጠት አእምሮህን ከፍርሃት፣ ከጥርጣሬ እና ከአሉታዊ ሀሳቦች "ባክቴሪያዎች" ማጽዳት ይኖርብሃል።
✓ 🚧 ያጥራል፣ይጠብቃል፡ ገበሬው ሰብሉን ከብቶችና ሌሎችም እንስሳት እንዳይበሉት በማጠር ይጠብቃል። ሕልምህንም ከሌሎች ሰዎች አሉታዊ ተጽዕኖዎች፣ ከስንፍናና ትኩረት ከሚያስቱ ነገሮች መጠበቅ አለብህ።
3. ያልተጠበቁ መሰናክሎችና እምነት
የገበሬው ሰብል ባልታሰበ አደጋ ሊጠፋ ይችላል። ነገር ግን ገበሬው ተስፋ ሳይቆርጥ መሬቱን እንደገና ያርሳል፣ #አዲስ ዘር ይዘራል። ይህ የሚያሳየን የእምነትና የጽናት ጥንካሬውን ነው።
በሕይወትህ ያልተጠበቁ መሰናክሎች ሲገጥሙህ፣ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በሕልምህ ላይ ያለህን እምነት በመያዝ እንደገና መጀመር እንዳለብህ አስታውስ።
#የሕይወትህ ምርጥ ገበሬ ሁን። የሚበቅለው በረከት እጅግ ታላቅ ነው። ሕልምህን ምረጥ፣ በእምነት ዘርተህ አጥብቀህ ስራ። የገበሬ ልብ ካለህ፣ የምትጠብቀው የመጨረሻው ውጤት አስደናቂ ይሆናል።
👇

Telegram
The Biggest Dream(ትልቁ ህልም
የዚህ ቻናል ዓላማ ሰዎች በመልካም አስተሳሰባቸው የሚፈልጉትን ሕልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ እንዴት እንደሚገነባ እንዲሁም የአዕምሯችንን ምስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና ዘለቄታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የሚረዳ ቻናላችን ነዉ@@https://t.me/thbigdream
ወደ ህልሜ እየተራመድኩኝ ነው? ወይስ ቁጭ ብዬ ሕልሜን እየጠበኩኝ?
እኛ ወደ ሕልማችን እንሄዳለን እንጂ ሕልማችን ወደ እኛ አይመጣም፡፡ ትክክለኛ ሕልም እውን እንዲሆን የእኛን እንቅስቃሴ ይፈልጋል፡፡ ወደፊትና ወደኋላ በሚወዛወዝ ወንበር ላይ ተቀምጦ አይኖችን ጨፍኖ በመወዛወዝ፣ “አንድ ቀን ሃብታም እሆናለሁ፣ አንድ ቀን አዋቂ እሆናለሁ፣ አንድ ቀን ጎበዝ ሯጭ እሆናል . . . ” እያሉ በመዋል ሕልም እውን አይሆንም፡፡
ሕልማችን ጋር እንደርሳለን እንጂ ሕልም እኛ ጋር አይደርስም፡፡ ወደ ሕልም የሚደረሰው ደግሞ ካለሙ በኋላ በማቀድ፣ ወዳቀድነው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ፣ ከዓላማ ግራና ቀኝ ባለማለት፣ ባለመሰልቸት፣ ሲወድቁ በመነሳት . . . ነው፡፡ በአጭሩ፣ ወደፊት ካልተራመድን ወደ ሕልማችን አንደርስም፡፡
ሕልም ማለት ንድፍ (Blue Print) ማለት ነው፡፡ የአንድን ሕንጻ ንድፍ የሰራ መሃንዲስ ያንን ውብ የሆነ ንድፍ ባለው የኮምፒውተር ክህሎት አሳምሮ ካስቀመጠ በኋላ በየቀኑ ያንን እያየ በመደነቅና ለሰዎችም እያሳየ አድናቆት ስላገኘ ሕንጻው አንድ ቀን ብቅ አይልም፡፡ ከንድፍ በኋላ ብዙ ስራ፣ ወጪና መስዋእትነት ይጠብቀዋል፡፡
ሕልምህ፣ ሕልም ብቻ ሆኖ እንዲቀር አትፍቀድለት፡፡ ተነሳና ተንቀሳቀስ፣ መክፈል ያለብህን የመስዋእትነት ተመን አውጣና ተራመድ፡፡ አደጋ ይደርስብኛል ብለህ አትፍራ፡፡ የአደጋው መጠንና አደጋውን የተጋፈጥንበት ምክንያት አስፈላጊነት ይለያይ እንጂ ማንኛውም ምርጫ ከአደጋ ነጻ ሊሆን አይችልም፡፡
አየህ፣ ባለህበት ሕልምን እያመነዠጉ መኖር ባሉበት “የመበስበስ” አደጋ አለው፡፡ ሕልምን ተከትሎ መውጣት ደግሞ ከአዳዲስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚመጣ የተጋላጭነት አደጋ አለው፡፡ የትኛውን እንደምትመረጥ ውሳኔው አንተው እጅ ላይ ነው ያለው፡፡ ባሉበት ሳይንቀሳቀሱ ከማለፍ፣ ሕልምን እየተከተሉ ማለፍ እንዴት የላቀ ነው!
ሕይወት ከሕልምና ሕልምንም ከመከታተል ውጪ ከሞት አትተናነስም፡፡ ዛሬ ሕልምህ ምን እንደሆነ በሚገባ በማሰብ አጣራውና ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ጻፈው፡፡

ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁትን ነው የምኖረው ወይስ እኔ ያመንኩበትን ነገር?
ማንነትህን ለሌላ ሰው አታከራይ! ማንነትን ለሌላ ሰው ማከራየት ማለት እኛ ያመንንበትን ነገር ከመኖር ይልቅ ሰዎች በእኛ ውስጥ ሆነው ከእኛ የሚጠብቁትን ነገር ለመኖር እንዲያስገድዱን መፍቀድ ማለት ነው፡፡ የአንዳንድ ሰዎች ዘመን እንዲሁ የሚባክነው በዚህ ሁኔታ ነው፡፡
በየጊዜው ሰዎች በእነሱ የግል ጉዳይ ገብተው ውሳኔን እንዲወስኑ፣ ምርጫን እንዲመርጡና አቅጣጫቸውን እንዲቀርጹላቸው ራሳቸውን ከፍተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ኑሯቸውን የሚኖሩት ራሳቸው ሳይሆኑ ሌሎች ሰዎች በእነሱ ውስጥ ሆነው ነው የሚኖሩላቸው፡፡ አሳዛኝ ሕይወት!
የማንነትህ፣ የራእይህ፣ የእቅድህ፣ የፍላጎትህ . . . ደጅ ጠባቂ ልትሆን የሚገባህ አንተ ነህ፡፡ ሌሎች ሰዎች በአንተ ውስጥ የራሳቸውን ዓላማ እንዲያራምዱ መፍቀድ የለበህም፡፡ የሌሎች ሰዎች መልካም ተጽእኖ ቢያስፈልግህም እንኳን ትክክለኛውን ሕልምህንና እውነተኛ ማንነትህን ከማገዝ አንጻር እንጂ አንተነትህን ትተህ ሌላ ኑሮንና የእነሱን ፍላጎት እንድትኖር ሊሆን አይገባውም፡፡
ዛሬ ማንነተህን ለሌሎች ከማከራየት የመቆጠብ ውሳኔን አስተላልፍና ፍጻሜህን ፈጣሪህ በሰጠህ የማንነትህ እጅ አስገባ፡፡ ምንም አሰብክ ምንም ሃሳቡን ያሰብከው አንተ መሆንህን እርግጠኛ ሁን፡፡ ምንም አደረክ ምንም የምታደርገው ነገር አንተ ያመንክበት መሆኑን እርግጠኛ ሁን፡፡ ምንም አቅጣጫ ተከተልክ ምንም አቅጣጫውን ለመከተል የወሰንከው ከውስጥ በወጣ እርግጠኛነት መሆኑን አጣራ፡፡
ውስጥህ በማያልቅ ጉልበትና ከምንም እንቅፋት አልፎ በሚሄድ ኃይል ወደፊት የሚዘልቀው ሰዎች ከአንተ የሚጠብቁትን ኑሮ ከመኖር ተላቀህ አንተ ያመንክበትንና ውስጥህ ያለውን ሕልምህን መኖር ስትጀምር ነው፡፡ በአጠገብህ ለማንነተህ ክብር ያለው ጥሩ መካሪና አጋር አድርገህ ከተጓዝክ ይህ አቋም ታሪክህን የሚለውጥ አቋም ነው፡፡
ዛሬ በየትኛው የሕይወትህ አቅጣጫ ሰዎች ጫና እንደሚያደርጉብህ ጊዜ ወስደህ በማሰብ እንዴት መላቀቅ እንደምትችል ጭምር ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ጻፈውና እርምጃ መውሰድ ጀምር፡፡

ደስተኛ ነኝ? ከሆንኩኝ ለምን? ካልሆንኩኝስ ለምን?
ራስን በማግኘት ላይ ታላቅ ተጽእኖ ካላቸው ጉዳዮች አንዱ የውስጥ ደስተኛነትህ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የደስተኛነትህ መጠን በውስጥህ የሚሰማህን የጉልበት መጠን ስለሚወስን ነው፡፡ ደስተኛነትህ ሲጨምር፣ ኃይልህም ከዚያው ጋር ይጨምራል፡፡ የደስተኛነትህ መጠን ሲቀንስ፣ ኃይልህም እንደዚያው፡፡
ብቅ ጥልቅ የሚልና የሚለዋወጥ ደስታ፣ በውስጣችን እንደየሁኔታው የሚለዋወጥን አቅም ይፈጥራል፡፡ ይህ ደግሞ በተራው እንደአቅማችን የመተግባርና ያለመተግባር ተለዋዋጭ እርምጃ ውስጥ ይከተናል፡፡
በማንነቱና በተግባሩ አንድ አይነትነት የማይታይበት ሰው አጋጥሞህ ከሆነ ይህ ሰው ተለዋዋጭ የደስታ ውጣውረድ ውስጥ ያለ ሰው ነው፡፡ ደስ ሲለው ጥሩ ይሆናል፣ ጥሩ ይሰራል፡፡ ደስ ሳይለው ደግሞ ሁለንተናው ይለወጣል፣ ተግባሩም ይቀንሳል፡፡
ደስተኛ ለመሆን ምንም አዲስ ነገር ሊጨመርልህ አይገባም፡፡ ደስተኛነት የዝንባሌና የውስጥ ውሳኔ ጉዳይ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ደስተኛነት የትኩረትም ጉዳይ ነው፡፡ ምን ላይ ለማተኮር እንደወሰንክ ተመልከተውና የስሜትህ ምንጭ ከየት እንደፈለቀ ታገኘዋለህ፡፡
ለምሳሌ የማይቀበሉህ ሰዎች ላይ ያተኮርክ ጊዜ ደስተኛ ልትሆን አትችልም፡፡ ያንን ተወት አድርገህ የሚወዱህና ሊያዩህ የሚናፍቁ ሰዎች ላይ ያተኮርክ ጊዜ ደግሞ ደስተኛነትህ ከፍ ያለ ነው፡፡ ቀላል ስሌት! ይህንን ስሌት ባለህ ወይም በሌለህ ነገር ላይ በማተኮር አንጻር ማጤን ትችላለህ፡፡
ተደሰትክም አልተደሰትክም የዛሬዋ ቀን ታልፋለች፡፡ ተደሰትክም አልተደሰትክም አሁን የምትኖረው ኑሮ ያልፋል፡፡ ተደሰትክም አልተደሰትክም ከዚህ አለም ማለፍህ አይቀርም፡፡ ታዲያ ለምን ደስተኛነትን አትመርጥም?!
እስቲ ዛሬ ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ በሕይወትህ ያሉትን መልካም ጎኖች አንድ በአንድ በመጻፍ ፈጣሪን በማመስገን ደስተኛነትን ምረጥ፡፡ ልጀምርልህና፡- ይህንን ጽሁፍ ማንበብ ስለቻልክ፣ ዛሬ ጠዋት ስለነቃህ፣ ስለሚወዱህ ሰዎች፣ አንተን የማይፈልጉህ ሰዎች አንተን ከመኖር ስላልከለከሉ፣ በልተህ ስለምታድር . . . ፡፡
ደስተኛ ሁን!

🔥1
ችግሩ እናንተ ጋር ባይሆንስ !?
ሰዎች በእናንተ ላይ የሚያንጸባርቁት ባህሪይ የእናንተን ሁኔታ ከማንጸባረቁ ይልቅ የሚያሳየው የእነሱኑ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ መገንዘብ በሄድንበት ሁሉ ሰዎች የሚሰጡንን መስተግዶና የሚሳዩንን ባህሪይ እየተከታተልን ከመደናበር ይጠብቀናል፡፡
በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ሰዎች የሚያሳዩአችሁን አጉል ባህሪይ እያያችሁ ሁኔታው የእናንተን ማንነት መተርጎሚያ ከማድረግ ልቦናችሁን ጠብቁ፡፡
ጥቂት የመንደርደሪያ ሀሳቦች . . .
ሰዎች ከጠሏችሁ የግድ የምታስጠሉ ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሰዎቹ በጥላቻ የተሞሉ አይነት ሰዎች ስለሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡
ሰዎች ከናቋችሁ የግድ መናቅ የሚገባችሁ አይነት ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን የመናቅ ችግር ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡
ሰዎች ካገለሏችሁ የግድ እንድትገለሉ የሚያደርጋችሁ ማንነት ስላላችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን በተለያየ ምክንያት ማግለል የለመደ ባህሪይ ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡
በአጭሩ ሰዎች ለእናንተ የሚያሳዩትን ባህሪ በመመልከት ብቻ ከዚያ አንጻር ለማንነታችሁ ትርጉምና ፍቺ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ በዚያ ምትክ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ሊያዛባ የሚችል አጉል ባህሪይ ካለባች እሱ ላይ ካለማቋረጥ በመስራት የሰዎችን የግል አመለካከትና አጉል በህሪይ ለራሳቸው ተውላቸው፡፡

Forwarded from Dr. Eyob Mamo
“የሕይወታችን ጥራት የሚወሰነው በውሳኔዎቻችን ጥራት ነው” ይባላል!
በጊዜ ሂደት ደጋግመን የምናደርጋቸው ምርጫዎች፤ ግንኙነታችንን፣ ጤናችንን፣ ፋይናንሳችንን (የኢኮኖሚ ደህንነታችንን) እና በመጨረሻም ባህሪያችንንና ማንነታችንን ይቀርጻሉ።
ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ እያንዳንዱ ውሳኔ የራሱ የሆነ ውጤት አለው። አንድ ነጠላ ውሳኔ እምብዛም አስፈላጊ እንዳልሆነ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን የበርከቶች ዕለታዊ ምርጫዎች ድምር ውጤት የሕይወታችንን አቅጣጫ እና ጥራት ይወስናል።
መልካም ውሳኔዎች አወንታዊ ውጤቶችን የማስገኘት ዝንባሌ ያላቸው ሲሆን፣ ደካማ ውሳኔዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ ወደማይፈለጉ መዘዞች ይመራሉ ።
ሕይወት በአንድ አስገራሚ ውሳኔ ብቻ የመቀየር አጋጣሚዋ ጠባብ ነው። ይልቁንም፣ ቀስ በቀስ ወደ ልማድ በሚቀየሩ ወጥ የሆኑ ዕለታዊ ምርጫዎች የምትቀረጽ ናት።
እነዚህ ልማዶች ባህሪያችንን ይገነባሉ፣ ባህሪያችን ደግሞ ዕጣ ፈንታችንን ይወስናል።
ይህንን አንዘንጋ . . .
የወደፊት ሕይወታችን በአብዛኛው ዛሬ የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ውጤት ነው።
የሕይወታችንን ጥራት ማሻሻል ከፈለግን፣ መጀመሪያ የውሳኔዎቻችንን ጥራት በማሻሻል እንጀምር።
ዛሬ እነዚህን ጥያቄዎች ለመጠየቅና ለመመለስ እንሞክር
· እስካሁን በሕይወቴ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳደሩት አስፈላጊ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው?
· ዕለታዊ ምርጫዎቼን ወደ ግቦቼ እያስጠጉኝ ነው ወይስ ከግቦቼ እያራቁኝ?
· ለወደፊት ሕይወቴ አወንታዊ ተጽዕኖ ሊያበረክት የሚችል፣ ዛሬ ልወስነው የምትችለው አንድ ውሳኔ ምንድን ነው?
· የበለጠ ጥበባዊ ውሳኔዎችን የማድረግ ልማድን እንዴት ማዳበር እችላለሁ?
እያንዳንዱ ምርጫችን፣ ወደፊት ለምንሆነው ማንነትና ለምንኖረው ኑሮ እጅግ ወሳን መሆኑን አንዘንጋ፡፡
LIKE & SHARE !!!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የበቀል ወጥመድ
አንድ ሰው ሲጎዳን በቶሎ የሚመጣው ስሜት ያንን ሰው መበቀል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የበቀል ስሜት ብዙ ጊዜ ትክክለኛ ምላሽ ይመስለናል፤ ምክንያቱም እፎይታ፣ ፍትሕ ወይም እርካታ እንደሚያመጣልን እናስባለን። እውነታው ግን በቀል ከምንበቀልበት ሰው ይልቅ ሂደቱ የሚጎዳ እኛንው ነው፡
1. በቀል ካለፈው ጉዳት ጋር አስሮ ያቆየናል
በቀልን የመፈለግ ዝንባሌ አእምሯችሁን ስለሚይዘው ከጎዳችሁ ሰው ውጪ ማሰብ እንዳትችሉ ያስራችኋል። ስለሆነም፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሁልጊዜ ያንኑ ጉዳት እያሰባችሁ ትኖራላችሁ።
2. በቀል የመበቃቀል ዑደት ይፈጥራል
እናንተ የተበቀላችሁት ሰው መልሶ እናንተን ሊበቀል ከፈለገ፣ ሁኔታው በዚያ መልክ ስለሚቀጥል አንድ የበቀል እርምጃ ሌላ የበቀል እርምጃን ይወልዳል። ከመፍትሔ ይልቅ ግጭትን ያባብሳል።
3. በቀል ሰላምን ይሰርቃል
ብዙ ሰዎች ከተበቀሉ በኋላም የልብ ሰላም እንዳላገኙ ይናገራሉ። በቀል ለጊዜው እርካታ ሊሰጥ ይችላል፤ ነገር ግን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን አያመጣም።
4. በቀል ፈውስን ያዘገያል
በሰዎች ጉዳት ከመጣባችሁ ቁስል መዳን የምትምሩት ቁስሉን የሚያባብሰውን የበቀል እርምጃ ተወት አድርጋችሁ ራሳችሁን ማከም ላይ ስታተኩሩ ነው፡፡
የተሻለው አማራጭ
ከበቀል ይልቅ፦
🌠 ፍትሕን መፈለግ፡፡
🌠 ከሁኔታው በመማር ለሰዎች ጤናማ ድንበሮችን (የግል መስመር) ማስቀመጥ።
🌠 ይቅር በማለት የልብን ቋጠሮ መፍታት።
🌠 ኃይልን በፈውስና በግል እድገት ላይ ማተኮር።
በቀል እንዲህ ይላል፦ "እኔን እንዳሰቃየኸኝ አንተም እንደኔ እንድትሠቃይ እፈልጋለሁ።"
ይቅርታ እንዲህ ይላል፦ "ያደረግክብኝ ነገር ሕይወቴን እንዲቆጣጠረው በፍጹም አልፈቅድም።"
የበቀል ተቃራኒው የተፈጸመውን ክፋት እንዳልነበረ ማስመሰል አይደለም። ይልቁንም ከምሬት ይልቅ ነፃነትን እና ከበቀል ይልቅ ጥበብን መምረጥ ነው፡፡
ሰዎች ባደረጉባችሁ በደል ምክንያት በፍጹም ራሳችሁን ከማሳደግና ዓላማችሁን ከመከታተል ጎዳና አትውጡ!

ብርቱ ሁኑ!
💪 ከወደቃችሁ ተነስታችሁ አቧራችሁን አራግፉና መንገዳችሁን ቀጥሉ፡፡ የወደቃችሁበት ሆናችሁ ሰዎች ምን እያሰቡና እያወሩ እንደሆነ ለማሰብ ጊዜው አይደለም፡፡
💪 ሰዎች ላይመለሱ ጥለዋችሁ ከሄዱ እውነታውን ተቀበሉና ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ፡፡ ሰዎቹ ለምን ትተዋችሁ ለመሄድ እንደፈለጉ እያብሰለሰላችሁ ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡
💪 አንድ ተስፋ ያደረጋችሁት የእድል በር ከተዘጋ ሌላ በርን ለማንኳኳት ዘወር በሉ፡፡ ለምን ተዘጋብኝ በማለት የራስ-በራስ ለቅሶ ውስጥ በመግባት አቅመ-ቢስ አትሁኑ፡፡
💪 ማንም ሰው አጠገባችሁ ከሌለና ብቻችሁን እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ ከራሳችሁ ጋር ማሳለፍን ልመዱ፡፡ ለብቻ መሆን ወደ ብቸኝነት ስሜት እንዲለወጥ አትፍቀዱለት፡፡
በርቱ!!