የእንዚራ ስብሐት ነገረ ድኅነት
ሰዎቻችን በቤተ ክርስቲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ አዳኝ የለም የሚል ውሸት ይዋሻሉ፡፡ ይኼን ውሸታቸውን ግን መጻሕፍቶቻቸውን ገልበጥ ገልበጥ ያደረገ ሰው ሳይቸገር ያገኘዋል፡፡
ድኅነት በፍጡር በኩል እንደሚገኝ በማስመሰል አጉል ተስፋ ከሚሰጡት መጻሕፍት መካከል አንዱ እንዚራ ስብሐት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በተከታታይ ይኼን ለማሳየት ጥረት አደርጋለኹ፡፡ ለዛሬ ወደ ብሉይ ኪዳን በመሄድ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ሰዎች የዳኑት በማርያም በኩል እንደኾነ የሚናገሩትን ክፍሎች እንመለከታለን፡፡
አዳም
እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን መልካም አድርጎ ከፈጠረ በኋላ ሰውን በመልካሚቱ ስፍራ በገነት ሲያኖረው ከአንዲት ትእዛዝ በቀር ምንም ሸክም አይጠበቅበትም ነበር፡፡ አዳም ግን ያንን አንድ ትአዛዝ ለመጠበቅ ስላልቻለ ከመልካሚቱ ስፍራ ከገነት ወጣ፡፡
አዳም ወደ ገነት ተመልሶ እንዴት ገባ? የሚለውን ጥያቄ ለእንዚራ ስብሐት መጽሐፍ አዘጋጆች ብትጠይቋቸው በሁለት ዓይነት መንገድ ይመልሳሉ፡፡ የመጀመሪያው ቀጣዩን ይመስላል፤
"በመጀመሪያ የገነት በር በሔዋን በደል ምክንያት ተዘጋ፡፡ በመሸ ጊዜም በአንቺ ጽድቅ በአንቺ ተከፈተ፡፡ በሰይጣን ጦር የቆሰለውም የድኅነት መድኀኒትን በአንቺ ተሰጠ፡፡ በኃጢአት የሞተውም በአንቺ ጽድቅ ዳነ" - እንዚራ ስብሐት ገጽ 127፡፡
በዚህ ምንባብ መሠረት በገነት የተዘጋው የገነት በር በማርያም ጽድቅ ተከፈተ፡፡ በመጀመሪያ ሔዋንንና ማርያምን ማነጻጸር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልኾነና በሐዋርያት ዘመን ያልነበረ በኋላ ዘመን ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን አሾልከው ያስገቡት እንግዳ ትምህርት ነው፡፡ የውዳሴ ማርያም አንድምታ እና ተኣምረ ማርያም ይኼ ትምህርት የተጀመረው በሶርያዊው ሊቅ በቅዱስ ኤፍሬም ነው ሲሉ፤ ‹‹የብርሃን እናት›› መጽሐፍ አዘጋጅ ግን በዚህ ሐሳብ አይስማሙም፤ ሰማዕቱ ዮስጦስ ነው የሚለውን እንደሚከተለው ጽፈዋልና፤ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ሔዋንና ማርያምን በማነጻጸር ውድቀታችንን ከመዳናችን ጋር አስተያይቶ የጻፈው ሰማዕቱ ዮስጦስ…›› ነው፡፡ የዚህ ትምህርት ጀማሪ ማንም ይሁን ማን በኋላ ዘመን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ እንጂ ሐዋርያዊ አይደለም፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ነው ያስተማረው፤ ‹‹ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ኾኖአልና። ኹሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ኹሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና›› (1ኛ ቆሮንቶስ 15÷21-22)። ከዚህም የምንረዳው በሴት የመጣ ሞት በሴት ድል ተመታ የሚለው አባባል የሰው ብቻ ትምህርት እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡
ሰዎቻችን ይሄን ምንባብ ትክክል ነው ለማለት የሚያነሡት ሐሳብ ከማርያም መወለዱን ለማሳየት ነው በሚል ነው፡፡ ምንባቡ የሚናገረው ከአንቺ በመወለዱ ሳይኾን ‹‹በአንቺ ጽድቅ በአንቺ ተከፈተ›› ነው፡፡ ይሄም ደግሞ ገነት የተከፈተው በኢየሱስ ሳይኾን በማርያም ጽድቅ ነው የሚለው፡፡ ይሄ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው እንግዳ ትምህርት ነው፡፡
ከዚህም ሌላ ምንባቡ የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹በሰይጣን ጦር የቆሰለውም የድኅነት መድኀኒትን በአንቺ ተሰጠ›› በዚህ ምንባብ ደግሞ የድኅነት መድኀኒት በእርሷ የተሰጠ በማስመሰል ቀርቧል፡፡ አንባቢው ልብ እንዲልልን የምፈልገው መድኀኒቱ ከእርሷ ተወለደ አላለም፡፡ ይልቁንስ እርሷ ራሷ መድኀኒት እንደኾነች በማስመሰል ‹‹በአንቺ›› በማለት ነው የተቀመጠው፡፡
ነገሩ በዚህ ቢያበቃ መልካም ነበር፤ በቀጣይ ደግሞ እንደዚህ ይላል፤ ‹‹በኃጢአት የሞተውም በአንቺ ጽድቅ ዳነ››፡፡ በዚህ ሐሳብ ደግሞ በኃጢአት ምክንያት የሞተውም በእርሷ ጽድቅ እንደሚድን የተገለጸው ማርያም አዳኝ ተደርጋ የተሳለች መኾኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ...
https://t.me/tewoderosdemelash/1047

ከዚህ በፊት በነበረን ጸሑፍ አዳም ወደ ገነት ተመልሶ እንዴት ገባ? የሚለውን የመጀመሪያ ነጥብ ተመልክተን ነበር፡፡ ዛሬም ከዚህ ሐሳብ ሳንርቅ የእንዚራ ስብሐት መጽሐፍ አዘጋጆች የሚከተለውን ጽፈዋል፤ ‹‹የዓለሙ አባት /አዳም/ በአንቺ የተድላ ቦታ ገነትን ወረሰ›› (ገጽ 42-43)፡፡
በዚህ ጽሑፍ መሠረት የሁሉ አባት አዳም በበደለው በደል ምክንያት ከወጣበት ገነት ተመልሶ የገባው በማርያም ነው የሚል ሐሳብ ነው የምናገኘው፡፡ ለዚህ የሚረዳ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንባብ የሌለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የክርስቶስን ሞት ከንቱ የሚያደርግ ሐሳብ ነው፡፡
የክርስቶስን ሞት ከንቱ የሚያደርገው አዳም ይቅርታን ያገኘውና ከእግዚአብር ጋር የታረቀው ጌታ ኢየሱስ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱና በመስቀል ሞት በመሞቱ ምክንያት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደም ሳይፈስ ስርየት እንደሌለ አስረግጦ ይናገራል (ዕብራውያን 9÷22)፡፡ ደሙን ያፈሰሰው ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ብቻ በመሆኑ ስርየት ያገኘው በእርሱ ሞት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አዳም በማርያም ወደ ገነት ገባ የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው ከሰዎች ልብ የወጣ ትምህርት ነው ማለት ነው፡፡
https://t.me/tewoderosdemelash/1049

የራሷን መቀመጫ ያላየችው ዝንጀሮ በሌሎቹ እንደ ተሣለቀችው÷ ከሳሻችንም በቤቱ ያለውን ሳይመለከት ወደ ሰው ቤት ዐይኑን ያማተረው ሰው÷ ‹‹ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ግን ይህን አውግስጢኖሳዊ ወለድ የኾነ ሉተራዊና ካልቪናዊ አስተምህሮ በፍጹም አትቀበልም›› በማለት ራሱን አዋድዶና ወደ ሌላው ጣቱን ጠቍሞ የሚከተለውን ይላል፤
በካልቪን አስተምህሮ መሠረት ሰው ነጻ ፈቃድ ስለሌለውና ውሳኔውና ድርጊቱ ለመዳኑ አንዳችም ሚና ስለሌለው÷ ሕገ ወጥነትንና ሥርዐት አልበኛነትን የማበረታታት ዐቅም ነበረው። ምክንያቱም ሰው መልካምም አደረገ ክፉም አደረገ ውጤቱ ያው አስቀድሞ የተወሰነበ(ለ)ት ከኾነ÷ ለምን ከኀጢአት ጋራ ይጋደላል? ለምን ከክፋት ይርቃል? መልካም ለማድረግስ ለምን ያተጋዋል?
በዚህ በከሳሻችን ጽሑፍ መሠረት÷ የቅድመ ውሳኔን ትምህርት የሚያስተምሩ ሰዎች ሕገ ወጥነትንና ሥርዐት አልበኛነትን የሚያበረታቱ ናቸው። በዚህም የተነሣ ከክፋት ለመራቅና መልካም ለማድረግ የሚበረታታበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም ‹‹መልካምም አደረገ ክፉም አደረገ ውጤቱ ያው አስቀድሞ…›› ተወስኖበታልና ይላል።
ከሳሹ ወደ ሌሎች ጣቱን ጠቍሞ በከሰሰበት በዚህ ክስ÷ ርሱም ኾነ የሚመራው ተቋም የሚከሰሱ መኾናቸውን ዘንግቶታል። ምክንያቱም በመጻሕፍታቸው ከዚህ በታች ያሉትን ሐሳቦች እናገኛለንና፤
ከመጽሐፉ የተወሰደ
🕯💡🕯💡🕯💡🕯
ይሄን መጽሐፍ በማሳተም አግዙን

የዲቦራና የባርቅ መዳኛ
በዘመነ መሳፍንት ከነበሩት መሳፍንት መካከል አንዷ ዲቦራ ነበረች፡፡ በጊዜው የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሣራን እንዲዋጋ መልእክተኞችን ወደ ባርቅ ስትልክ ‹‹አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም›› በማለቱ አብረው ወደ ቃዴስ ሄዱ፡፡
በመጽሐፉ እንደምናነበው ‹‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፤ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ›› በማለት እግዚአብሔር በባርቅ በኩል የሠራውን ሥራ ይነግረናል፡፡
የሕዝቡ ጠላት የነበረው ሲሣራ እንዴት ሞተ ወደሚለው ስንሄድ ደግሞ፤ ‹‹እነሆም፥ ባርቅ ሲሣራን ሲያባርር ኢያዔል ልትገናኘው ወጥታ፦ ና የምትሻውንም ሰው አሳይሃለሁ አለችው። ወደ እርስዋም ገባ፥ እነሆም፥ ሲሣራን ወድቆ ሞቶም አገኘው፥ ካስማውም ከጆሮግንዱ ውስጥ ነበረ። በዚያም ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንገሥ ኢያቢስን በእስራኤል ልጆች ፊት አዋረደ›› በማለት እግዚአብሔር በኢያዔል በኩል ያደረገውን ያሳየናል (መሳፍንት ምዕራፍ 4)፡፡
እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ሕዝቡን ሲጠብቅ ዲቦራንና ባርቅን አብሮ እየጠበቀና እያዳነ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሁለቱንም ሰዎች ማነው ያዳናችሁ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብላቸው መልሳቸው ‹‹እግዚአብሔር››› የሚል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
የድርሳነ ማርያም አዘጋጆች ግን ከዚህ ሐሳብ ጋር አይስማሙም፤ እንደዚህ ጽፈዋልና፡- ‹‹የዲቦራ መዳኛዋ፣ የባርቅ የድኅነቱ መጽናኛም አንቺ ነሽ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 57)፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጆች በዚህ ጽሑፋቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒ መቆማቸው ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም 1) ዲቦራና ባርቅ በነበሩበት ዘመን ማርያም አልነበረችም፤ ስለዚህ ማርያም አዳኝ ሆና ልትጠቀስ የምትችልበት ምክንያት የለም፡፡ 2) የሁለቱ ታላላቅ ሰዎች ታሪክ በሰፈረበት ቦታ ላይ የታሪኩ ባለቤት እግዚአብሔር በግልጽ ሰፍሯል፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ነው፡፡ ታሪኩን ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር ወስደው ለፍጡር ለመስጠት መሞከር የታሪኩን ባለቤት መናቅ ነው፡፡
የኢዮብ መድኀኒት አንቺ ነሽ
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው ከሰፈሩላቸው ሰዎች መካከል የኢዮብን ያኽል በመከራ ውስጥ ያለፈ፡፡ ምንም እንኳ በከባባድ መከራ ውስጥ ቢያልፍም እግዚአብሔርን ሳያሳዝን በጽናት የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡
በኢዮብ ላይ ከደረሱት መከራዎች መካከል በከባድ ቁስል መመታቱ አንዱ ነው፡፡ የቁስሉ ክብደት ምንም ያህል ብርቱ ቢሆንም ኢዮብ ግን በአምላኩ ላይ የነበረው እምነት ብርቱ ስለ ነበር ‹‹እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል›› በማለት መመኪያው አምላኩ ብቻ መሆኑን አሳይቷል (ኢዮብ 13÷16)፡፡
ይሄን ብርቱ አባት የእንዚራ ስብአት መጽሐፍ አዘጋጆች የማርያም ጥገኛ ሊያደርጉት ዳድተዋል፤ ‹‹የቁስል ችግርን መከራን በተቀበለ ጊዜ የኢዮብ የሕይወቱ መድኃኒት አንቺ ነሽ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 197)፡፡
የመጽሐፉ አዘጋጆች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ የላቸውም እንዳይባል ብዙ ባይሆንም የመጽሐፍ ቅዱስን ምንባባት በአግባቡ ያሰፈሩበት ቦታ አለ፡፡ በሚያነሧቸው አንዳንድ ታሪኮች ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የራቀ ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡
ማርያም በኋላ ዘመን የመጣች አይሁዳዊት ሴት ብትሆንም ወደ ኢዮብ ዘመን ወስደው የኢዮብ የሕይወቱ መድኀኒት ነሽ ማለት ዘመን እንኳ ለይተው የማያውቁ ሰዎች መሆናቸውን ያሳያል፡፡
ከዚህም በላይ የታሪኩ ባለቤት ኢዮብ መድኃኒቱ እግዚአብሔር መሆኑን እየመሰከረ ከእርሱ ይልቅ አዋቂ ነን እያሉ ያሉት ሰዎች ማርያም ናት መድኀኒትህ እያሉት መሆኑን ቢያውቅ ምን ይሰማው ይሆን?
ሔኖክ በአንቺ ከሞት ዳነ
ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉ ምክንያት ‹‹አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና›› ተብሎ የተጻፈለት አባት ነው (ዘፍጥረት 5÷21-24)፡፡ መጽሐፉ በግልጽ ምክንያቱን እያስቀመጠ የድርሳነ ማርያም አዘጋጆች ግን ‹‹ሔኖክም በአንቺ ከሰው ልጆች ተሰወረ፡፡ ከሞት እጅም ዳነ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 91)፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ሔኖክ የተወሰደበትን (የመጽሐፉ አዘጋጆች ተሰወረ ያሉት) እና ሞት ያላገኘውም ‹‹አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ…›› ነው በሚል ያስቀመጠ ቢሆንም ከቃለ እግዚአብሔር ተቃራኒ በመቆም ላይ ጎበዝ የሆኑት የድርሳነ ማርያም አዘጋጆች ‹‹በአንቺ›› በማለት በዘመኑ እንኳ ያልነበረችውን ሴት በመካከል ያስገባሉ፡፡ በዚህም ደግሞ ለቃለ እግዚአብሔር ታዛዦች አለመሆናቸውን አሳይተዋል፡፡
ሎጥ በአንቺ ዳነ
ሎጥ ከአብርሃም ተለያይቶ መልካም ወደመሰለው ስፍራ ሄደ፡፡ መርጦት የሄደበት አገር ነዋሪዎች በከፋ በደል ውስጥ በመግባታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩት መላእክት ለሎጥ እንዲህ አሉት፤ ‹‹እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል››፡፡ ይሄን ከመንገራቸው በፊት ግን ‹‹ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው›› የሚል ትእዛዝ አዘውታል፡፡ ይሄም ብቻ ሳይሆን፤
ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት - ዘፍጥረት ምዕራፍ 19፡፡
በዚህ ታሪክ ውስጥ የሎጥን ቤተ ሰቦች ለማዳን እግዚአብሔር ከላካቸው መላእክት ውጪ ማንም የሌለ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡
የድርሳነ ማርያም መጽሐፍ አዘጋጆች ግን የሚከተለውን ጽፈዋል፤ ‹‹ሎጥም ከዲንና ከእሳት ዝናም በአንቺ ዳነ›› (እንዚራ ስብአት ገጽ 82)፡፡ ይሄ ደግሞ ድፍረት የተሞላበት ስሕተት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እንደዚህ ማድረግ ያስፈለገው ማርያምን በሰዎች ልብ ውስጥ አተልቆ ለመሣል ነው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
https://t.me/tewoderosdemelash/1052

እኛ መጽሐፉን እናምናለን ስለዚህም ሐዋርያት አይተው የነገሩንን የኢየሱስን ዕርገት አሜን ብለን ተቀብለናል። ሐዋርያት ስላላዩት ያልነገሩንን የፍጡርን ዕርገት ደግሞ አንቀበልም።
ስሑታኑ በሐዋርያት ስም መነገድ ልማዳቸው ነውና ሐዋርያት ያላዩትን የፍጡር ዕርገት እንዳዩ አድርገው ይዋሻሉ።
እነዚህን ከሚመስሉ ዋሾዎች ልጆቻችሁን ጠብቁ!!!
https://t.me/tewoderosdemelash/1053