እውነት አርነት ያወጣል
2.79K subscribers
374 photos
70 videos
37 files
367 links
እውነት አርነት ያወጣል!!!
Download Telegram
ከዛሬው ንባቤ ላቅምሳቹ ብዬ ነው

እስኪ ሐሳብ ስጡበት
እኔና እርሱ

ከአንድ ሰው ጋር የነበረኝ ውይይት በአጭሩ

እኔ፤ ስንት አዳኝ ነው ያለው?

እሱ፤ አንድ ብቻ እሱም ጌታችን ነው

እኔ፤ ማርያምስ መድኃኒት ተብላ ተጠርታ የለ? እሷስ አታድንም?

እሱ፤ የመድኃኒት እናት ስለሆነች ነው መድኃኒቱን የወለደችው እሷ ስለሆነች መድኃኒት እንላታለን

እኔ፤ መቼ ነው የወለደችው?

እሱ፤ (ይሄን አታውቅም? ከሚል ሳቅ ወይም ስላቅ በኋላ) ከዛሬ 2000 ዓመት በፊት

እኔ፤ ዛሬ ማርያም መድኃኒት ናት?

እሱ፤ አዎ ናት

እኔ፤ ለምን? አንድ አዳኝ ነው ያለው ብለኸኝ ነበርኮ

እሱ፤ ነገርኩህኮ መድኃኒቱን ስለወለደች ነው መድኃኒት የምትባለው አልኩህ አይገባህምንዴ?

እኔ፤ እሱ ገብቶኛል ስለወለደችው መድኃኒት የተባለችበት ምክንያት ነው ያልገባኝ እሱን ልታስረዳኝ ትችላለህ?

እሱ፤ ቆይ እኔ ልጠይቅህ ጌታችንን የወለደው ማነው?

እኔ፤ ማርያም

እሱ፤ በቃሃ ለዚህ ነው መድኃኒት የምትባለው

🤔😳🤔😳🤔😳🤔

እኔ ግራ ገባኝ የገባቹ አስረዱኝ አልገባኝም
የዚህ መጽሐፍ ዐላማ መምህራን ዐደራቸው ለቃለ እግዚአብሔርና ለቃሉ ባለቤት ለእግዚአብሔር በመኾኑ፣ ለሚያስተምሩት ትምህርት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየትና ማሳሰብ ነው። ሕዝበ ክርስቲያኑ ጽሑፋችንን ቢያነብብና ስብከታችንን ቢሰማ፣ እኛን ፈልጎ ሳይኾን፣ እግዚአብሔርን ናፍቆ በመኾኑ ከቅዱሱ ቃል ሳንርቅ ታላቁን እግዚአብሔርን ብቻ ማሳየት ይኖርብናል። ስለ ኾነም አገልጋዮችን ‹‹ከተጻፈው አትለፍ›› ማለት ይገባል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ

በቅርብ ቀን
በጣም በቅርቡ
እኛ እጅ ገብቷል

በቅርቡ ደግሞ እናንተ ጋር ይደርሳል
በቅርብ ስርጭት ይጀምራል
በቅርብ ቀን
ለ2017 ዓ.ም. ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት፣ በነገረ መለኮት ዘርፍ ለመጨረሻው ዙር ዕጩ ኾነው የቀረቡት የመጻሕፍት ዝርዝር በምስሉ ላይ የተመለከቱት ናቸው። በመኾኑም፣ ርስዎ ያነበቡትንና ዕውቅና ይገባዋል የሚሉትን አንድ መጽሐፍ፣ ዕጩ ከተደረገበት ዘርፍ ለመምረጥ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦


https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/
እግዚአብሔርን ማስረሳት

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አንድ የመመሪያ መጽሐፍ አለው፡፡ እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ይባላል፡፡ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ በኩል የመጽሐፉ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ ሊያሳውቀን የወደደውን ሁሉ እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ በመሆኑም ክርስቲያኖች ከዚህ መጽሐፍ አልፈው በራሳቸው መንገድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን መቀጠል አይችሉም፡፡
በዚህ መንገድ ውስጥ ከሄዱት መካከል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንዱ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ‹‹እንዚራ ስብሐት›› በተሰኘው መጽሐፉ በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያን ባስገባው ጽሑፉ እግዚአብሔርን ትተን በፍጡር እንድንታመን የሚያደርግ መልእክት አስተላልፏል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በሚኖሩን ተከታታይ ጽሑፎች ‹‹በርግጥም እግዚአብሔር ምን ይሠራልናል?›› የሚል ጥያቄ የሚያጭሩ ሐሳቦችን ከመጽሐፉ ውስጥ እናሳያለን፡፡

ይቅርታን የምታጎናጽፈዋ ማርያም

የቅዱሳንንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ሐሳብ በተደጋጋሚ ሲነገር ሰምተናል፡፡ እሱም፤ ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡን ናቸው፣ እነሱ ይቅርታ የሚያሰጡ እንጂ በራሳቸው ይቅርታ የሚያደርጉ ናቸው ብለን አናምንም የሚል ነው፡፡ በዚህ ሐሳብ ውስጥ ከሚቀርቡት አንዱ ማርያም ናት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በዚህ ሐሳብ የሚስማማ አይመስልም ምክንያቱም ከዚህ በታች በቀረበው ጽሑፉ በኩል ማርያም በራስዋ ይቅርታ የምታደርግ ናት የሚል ሐሳብ አቅርቧል፡፡

‹‹ምሳሌ የሌለሽ ንግሥት ሆይ ዛሬም ልመናን በማብዛት እማጸንሻለሁ፡፡ መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽም ዘመኑን ሁሉ ይከተለኝ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 9)፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ላይ ሦስት ችግሮችን የምናገኝ ቢሆንም ‹‹እማጸንሻለሁ›› የሚለውን በሌላ ጽሑፍ የምንመለከተው በመሆኑ ሁለቱን ችግሮች ብቻ ከዚህ በታች አሳያለሁ፤

1. ‹‹ምሳሌ የሌለሽ››፤ የመጽሐፉ አዘጋጅ አባ ጊዮርጊስ መጽሐፍ ቅዱስን የተማረ ነው ተብሎ የሚታመን በመሆኑ በቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ ምሳሌ የሌለው ተብሎ የተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን አይረሳም ተብሎ ተስፋ ይደረጋል፡፡ ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም›› ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳይያስ 46÷9)፡፡ በዚህም ምክንያት ታላቁ ነቢይ ኤርምያስ ‹‹አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው›› ይላል፡፡ በርግጥም እንደርሱ ያለ ማንም የለም (ኤርምያስ 10÷6)፡፡

ከዚህ አልፎ ለሚመጣ ሰው ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?... እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ›› ተብሎ ተጽፏልና እርሱን እንዲያነብ ይመከራል (ኢሳይያስ 40÷18፡ 25)፡፡ በዚህም ደግሞ አባ ጊዮርጊስ የተሳሳተ ጽሑፍ የጻፈ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ለማርያም በዚህ ልክ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በታች በሆነ ሁኔታ ምሳሌ የሌላት ተብሎ ስላልተጻፈ ጸሐፊው የልቡን መሻት ነውና የጻፈው፡፡

2. ‹‹መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽ››፤ ቀደም ሲል እንደተባለው ማርያም ወደ እግዚአብሔር የምታደርስ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር የምታስታርቅ ናት የሚል እምነት እንዳላቸው በአንደበት ይነግሩናል፡፡ ይሄ ግን ውሸት ነው፡፡ ምክንያቱም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት መካከል የሆነው አባ ጊዮርጊስ ማርያም የራሷ የኾነ ይቅርታ እንዳላት (ይቅርታሽ ነውና የሚለው) በመጻፍ በዚህ ይቅርታዋን እንደምታጎናጽፍ ሊያሳይ እየሞከረ ነው፡፡

ይሄ የአባ ጊዮርጊስ ጽሑፍ አሁን አሁን በውሸት ከሚናገሩት ንግግር ጋር ብቻ ሳይሆን ከታላቁ መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋርም አይስማማም፡፡ ምክንያቱም ቅዱሱ መጽሐፍ ይቅርታን የምናገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያስተምራል፡፡ ‹‹አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?›› የሚል ጥያቄ ይጠይቅና ራሱ መልሱን ሲሰጥ ‹‹ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና›› ይላል (መዝሙር 130÷3-4)፡፡ በርግጥም ከእርሱ ውጪ ይቅርታ ሊያደርግ የሚችል አካል የለም፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው›› የሚል ምክር ካቀረበ በኋላ ‹‹ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ›› በማለት ያበረታታል (ኢሳይያስ 55÷7)፡፡ ኢሳይያስ ይቅርታው የእግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ይቅርታውም›› በማለት የጻፈ ሲኾን የእንዚራ ስብአት መጽሐፍ አዘጋጅ ደግሞ ‹‹ይቅርታሽ›› በማለት ይቅርታን ለፍጡር ሲሰጥ ይታያል፡፡

ወገኖቼ ይቅርታን ያገኘነው እንዲሁ በጸሎት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ ዋጋ ተከፍሎልን፣ ደም ፈሶልን ነው፡፡ ይኼን የይቅርታን መንገድ ደግሞ ጌታችን እንዲህ ብሎ ነግሮናል፤ ‹‹ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው›› (ማቴዎስ 26÷28)፡፡ ስለዚህ በሌላ አካል ይቅርታ ይገኛል እያሉ ዓይንህን ወደ ፍጡራን እንድታማትር የሚያደርጉህን ሰዎች አትስማቸው፡፡፡፡
እናንትዬ የእኔ ወዳጆች

በዚህች ሊንክ ገብታችሁ ይሄን መጽሐፍ በመምረጥ የበለጠ እንድትጋ እንድታበረታቱኝ እጠይቃለሁ



https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/
የዛሬ ገጠመኜን እንካችሁ

በዘርዐ ያዕቆብ ላይ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ እጄ እንደገባ ጉዞዬ ወደ ቤት ነበርና ባስ ውስጥ ገባሁ። ባሱ ባዶ ስለነበር ለንባብ የሚመች መቀመጫ መርጬ መጽሐፉን ጀመርኩ። ዘግይቶ በመምጣት አጠገቤ የተቀመጠው ሰው አብሮኝ እያነበበ እንደ ነበረ ግን አላወኩም ነበር።

ጎረቤቴ የመጽሐፉን ርዕስና አዘጋጅ ጠየቀኝ፤ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ሲገጥመኝ የመጽሐፋን የፊት ሽፋን ማሳየትን እመርጣለሁ። ምክንያቱም ወሬ ተጀምሮ ንባቤ እንዳይቋረጥብኝ ነበር። ሰውየው ግን በጥሩ ሞራልና ጎላ ባለ ድምጽ ወሬ ጀመረ። ወደ ንባቤ እንደማልመለስ ሲገባኝ መጽሐፉን ከድኜ ለወሬ ተመቻቸሁ።

ከጎረቤቴ ረዘም ያለ ንግግር ጸሐፊ መሆኑ ገባኝና ጠየኩ። አዎ ጽፌያለሁ ብሎ የመጽሐፉን ሽፋን በስልኩ አሳየኝና እሱ ግን ሁለት መጻሕፍት እንደሚወድ ነገረኝ።

የመጀመሪያ የጠቀሰልኝ "ወልታ ጽድቅ" የተሰኘውን መጽሐፍ ነው። መጽሐፉን በጣም እያደናነቀ በዚህ ጉዳይ ሁነኛ መጽሐፍ መሆኑን እንደቀበል ደጋግሞ ነገረኝ። የወዳጄን የዲያቆን አግዛቸውን መጽሐፍ ሽፋን ከፌስ ቡክ በማውጣት ይሄን መጽሐፍ አንብበኸዋል? አልኩት። የመጽሐፉን ሽፋን በጥንቃቄ ተመልክቶ የት እንደሚያገኘው ሲጠይቀኝ ፊቱ ላይ መጓጓት ይታይበታል። የመጽሐፉን ይዘት ስነግረው ቀደም ሲል ሲያደንቀው የነበረውን መጽሐፍ ደግሞም አላነሣውም።

ወደ ሁለተኛው መጽሐፍ የገባው በእኔ ጠያቂነት ነበር። "ሁለት መጻሕፍት እንደምትወድ ነግረኸኝ ነበር፤ ሁለተኛው ማነው?"። እሱም "መድሎተ ጽድቅ ነው" ብሎ እንደስሙ ነው በማለት ደጋግሞ ሲያወራ የስሙን ትርጉም ጠየኩት። ጎረቤቴም "የእውነት ሚዛን" አለኝ። "እኔ ግን አልስማማም ምክንያቱም ጸሐፊው ሐሰተኛ ክስ ያቀርባልና" አልኩት።

ጎረቤቴም ቆፎጠን ባለ ድምጽ "በፍጹም" አለኝ። እኔም "እንግዲያውስ መጽሐፉን አላነበብከውም" አልኩት። ጎረቤቴም መልሶ "እሺ ያነበብከውን ሐሰተኛ ክስ ንገረኝ" አለኝ።

"የመጀመሪያውን ቅጽ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመጀመሪያውን ንዑስ ርዕስ መመልከቱ ብቻ ጸሐፊው ሐሰተኛ ከሳሽ መሆኑን ለመረዳት ያግዛል። ገና ሲጀምር በውሸት ዓይኑን የከፈተ ጸሐፊ በቀጣይ እውነት ይናገራል ብሎ ማለት ይከብዳል። ይሄም ሐሳብ በዚህ ጽሑፍ ላይ ተገልጿል" በማለት በቅርቡ ለንባብ የሚበቃውን የ"መዛኙ ሲመዘን ቅጽ ፪"ን ሽፋን በማሳየት የመጽሐፉን ሐሳቡ ነገርኩት።

ቅድም የነበረው ወኔ ጠፍቶ ቀዝቀዝ በማለት ቤቱ እንደገባ የነገርኩትን ክፍል እንደሚመለከተው ቃል ገባልኝ። አያይዞም አንተ ያልከው ሐሳብ በመጽሐፉ ላይ ከተገኘ የመጽሐፉ አዘጋጅ ቀጣፊ ነው ማለት ነው" አለኝ። በሚገባ ቀጣፊ እንጂ ብዬው እጄ ላይ ወደያዝኩትና ለዚህ ውይይት መነሻ ወደሆነን መጽሐፍ ተመልሶ ጠየቀኝ። እኔም መጽሐፉ ገና አሁን እጄ እንደገባና እንዳላነበብኩት ነግሬው ስለራሱ መጽሐፍ (የእሱ መጽሐፍ ከዘመን ቆጠራ ጋር የተያያዘ ሐሳብ ያለው ነው) ሲወራኝ መውረጃችን ደረሶ ተሰነባበትን።