እውነት አርነት ያወጣል
2.79K subscribers
372 photos
70 videos
37 files
367 links
እውነት አርነት ያወጣል!!!
Download Telegram
እኛ እጅ ገብቷል

በቅርቡ ደግሞ እናንተ ጋር ይደርሳል
ለንባብ በቅቷል

ስታዲየም ያለው መሠረተ ክርስቶስ መጻሕፍት መደብር ይገኛል

ሼር አድርጉልኝ 🙏
ዛሬ ማርያም ለአባ ጊዮርጊስ ጽዋዕ ያጠጣችው ቀን ነው ተብሎ ይታሰባል። ታሪኩ የሚከተለውን ይመስላል፦

ከሰባት ቀናት የሱባዔ ቆይታ በኋላም፤ ‹‹እንደተለመደው በሥዕለ ማርያም ሥር ተደፍተው ሲያለቅሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤልን አስከትላና ጽዋዓ እሳት አስይዛ መጥታ የሕይወት ጽዋዕ አጠጣቻችው፡፡ አባ ጊዮርጊስም የሕይወት ጽዋዕን ከጠጡ በኋላ የሰማይና የምድር ምስጢር ሁሉ ተገለጸላቸው››፡፡ ከዚህም በኋላ ከአርባ በላይ መጻሕፍትን ለመጻፍ ችሏል፡፡

የሕይወት ጽዋዕ›› የተባለውን መጠጥ በተመለከተ ገድሉ ላይ ‹‹የመረጥሁህና የልጄ ወዳጅ ጊዮርጊስ ብላ በስሙ ጠራችው፡፡ ከዕውቀት ወንዝ የመጣና ከጥበብ ምንጭ የተገኘ ከመለኮት ባሕር የተቀዳ ይህን ንጹሕ ጽዋ /እንካ/ ንሣ ጠጣ፡፡ ለስም አጠራርዋ ሰጊድ ይሁንና የዓለም ሁሉ ንግሥት እመቤታችን ያን ጊዜ በቀኝ እጅዋ ሰጠችው፡፡ ሳይጠጣውም ወደ ውስጡ ተመለከተ ይህን ጽዋ የጠጣ አይኰነንም ከሕይወት ባሕር ተቀድቶአልና የሚል መጽሐፍ አገኘ፡፡… ይህም በዮሴፍ ቤት በርሐ ጽዮን ሐዋርያት የጠጡት መንፈሳዊና ሰማያዊ መጠጥ ነው፡፡ በበዓለ ሃምሳ ከጠጡት ያልተለየ ነው፡፡ ይኸውም የሚናገር እሳት፣ የሚያድን እሳት መለኮታዊ እሳት ነው›› የሚል ተጽፎ ይገኛል (የደብረ ባሕርይ ጋስጫ አባ ጊዮርጊስና አቡነ በጸሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም፣ ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ገድለ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል - ግእዝና አማርኛ፤ (ታኅሣሥ 2004) ገጽ 34 - አጽንዖት የግል)፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ‹‹ሐዋርያት የጠጡት መንፈሳዊና ሰማያዊ መጠጥ ነው›› ተብሎ የተጠቀሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለት ላይ ‹‹በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው›› የተባለው ቅዱሱ መንፈስ ነው፡፡ ‹‹ማርያም›› ለአባ ጊዮርጊስ ያጠጣችው መንፈስ ቅዱስን እንደ ሆነ በገጽ 44 ላይ ‹‹እመቤታችን ማርያምም የገለጠችለት የመጻሕፍትን ዕውቀት ብቻ አይደለም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኀይልንም አለበሰችው እንጂ›› ተብሎ የተጻፈውን መመልከት ይቻላል፡፡ በገድሉ ትረካ መሠረት መንፈስ ቅዱስን የምትሰጠው ማርያም ናት ማለት ነው፡፡ በገድለ አባ ጊዮርጊስ እንደተጠቀሰው መንፈስ ቅዱስ ‹‹… ከዕውቀት ወንዝ የመጣና ከጥበብ ምንጭ የተገኘ…››፣ ‹‹… ከሕይወት ባሕር …›› የተቀዳ ሳይሆን ራሱ ዕውቀት ሰጪ፣ ራሱ የጥበብ ባለቤት የሆነና ራሱ የሕይወት ምንጭ የሆነ ቅዱስ መንፈስ ነው፡፡ በፍጡር እየተቀዳና በዕቃ እየተጨለፈ የሚወሰድ ሳይሆን እሱ በዓለሙ ሁሉ የመላ ለሁሉ እንደ ወደደ የሚሠራ ገናና አምላክ ነው፡፡
ከዛሬው ንባቤ ላቅምሳቹ ብዬ ነው

እስኪ ሐሳብ ስጡበት
እኔና እርሱ

ከአንድ ሰው ጋር የነበረኝ ውይይት በአጭሩ

እኔ፤ ስንት አዳኝ ነው ያለው?

እሱ፤ አንድ ብቻ እሱም ጌታችን ነው

እኔ፤ ማርያምስ መድኃኒት ተብላ ተጠርታ የለ? እሷስ አታድንም?

እሱ፤ የመድኃኒት እናት ስለሆነች ነው መድኃኒቱን የወለደችው እሷ ስለሆነች መድኃኒት እንላታለን

እኔ፤ መቼ ነው የወለደችው?

እሱ፤ (ይሄን አታውቅም? ከሚል ሳቅ ወይም ስላቅ በኋላ) ከዛሬ 2000 ዓመት በፊት

እኔ፤ ዛሬ ማርያም መድኃኒት ናት?

እሱ፤ አዎ ናት

እኔ፤ ለምን? አንድ አዳኝ ነው ያለው ብለኸኝ ነበርኮ

እሱ፤ ነገርኩህኮ መድኃኒቱን ስለወለደች ነው መድኃኒት የምትባለው አልኩህ አይገባህምንዴ?

እኔ፤ እሱ ገብቶኛል ስለወለደችው መድኃኒት የተባለችበት ምክንያት ነው ያልገባኝ እሱን ልታስረዳኝ ትችላለህ?

እሱ፤ ቆይ እኔ ልጠይቅህ ጌታችንን የወለደው ማነው?

እኔ፤ ማርያም

እሱ፤ በቃሃ ለዚህ ነው መድኃኒት የምትባለው

🤔😳🤔😳🤔😳🤔

እኔ ግራ ገባኝ የገባቹ አስረዱኝ አልገባኝም
የዚህ መጽሐፍ ዐላማ መምህራን ዐደራቸው ለቃለ እግዚአብሔርና ለቃሉ ባለቤት ለእግዚአብሔር በመኾኑ፣ ለሚያስተምሩት ትምህርት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየትና ማሳሰብ ነው። ሕዝበ ክርስቲያኑ ጽሑፋችንን ቢያነብብና ስብከታችንን ቢሰማ፣ እኛን ፈልጎ ሳይኾን፣ እግዚአብሔርን ናፍቆ በመኾኑ ከቅዱሱ ቃል ሳንርቅ ታላቁን እግዚአብሔርን ብቻ ማሳየት ይኖርብናል። ስለ ኾነም አገልጋዮችን ‹‹ከተጻፈው አትለፍ›› ማለት ይገባል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ

በቅርብ ቀን
በጣም በቅርቡ
እኛ እጅ ገብቷል

በቅርቡ ደግሞ እናንተ ጋር ይደርሳል
በቅርብ ስርጭት ይጀምራል
በቅርብ ቀን
ለ2017 ዓ.ም. ሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት፣ በነገረ መለኮት ዘርፍ ለመጨረሻው ዙር ዕጩ ኾነው የቀረቡት የመጻሕፍት ዝርዝር በምስሉ ላይ የተመለከቱት ናቸው። በመኾኑም፣ ርስዎ ያነበቡትንና ዕውቅና ይገባዋል የሚሉትን አንድ መጽሐፍ፣ ዕጩ ከተደረገበት ዘርፍ ለመምረጥ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦


https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/
እግዚአብሔርን ማስረሳት

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አንድ የመመሪያ መጽሐፍ አለው፡፡ እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ይባላል፡፡ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ በኩል የመጽሐፉ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ ሊያሳውቀን የወደደውን ሁሉ እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ በመሆኑም ክርስቲያኖች ከዚህ መጽሐፍ አልፈው በራሳቸው መንገድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን መቀጠል አይችሉም፡፡
በዚህ መንገድ ውስጥ ከሄዱት መካከል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንዱ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ‹‹እንዚራ ስብሐት›› በተሰኘው መጽሐፉ በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያን ባስገባው ጽሑፉ እግዚአብሔርን ትተን በፍጡር እንድንታመን የሚያደርግ መልእክት አስተላልፏል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በሚኖሩን ተከታታይ ጽሑፎች ‹‹በርግጥም እግዚአብሔር ምን ይሠራልናል?›› የሚል ጥያቄ የሚያጭሩ ሐሳቦችን ከመጽሐፉ ውስጥ እናሳያለን፡፡

ይቅርታን የምታጎናጽፈዋ ማርያም

የቅዱሳንንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ሐሳብ በተደጋጋሚ ሲነገር ሰምተናል፡፡ እሱም፤ ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡን ናቸው፣ እነሱ ይቅርታ የሚያሰጡ እንጂ በራሳቸው ይቅርታ የሚያደርጉ ናቸው ብለን አናምንም የሚል ነው፡፡ በዚህ ሐሳብ ውስጥ ከሚቀርቡት አንዱ ማርያም ናት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በዚህ ሐሳብ የሚስማማ አይመስልም ምክንያቱም ከዚህ በታች በቀረበው ጽሑፉ በኩል ማርያም በራስዋ ይቅርታ የምታደርግ ናት የሚል ሐሳብ አቅርቧል፡፡

‹‹ምሳሌ የሌለሽ ንግሥት ሆይ ዛሬም ልመናን በማብዛት እማጸንሻለሁ፡፡ መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽም ዘመኑን ሁሉ ይከተለኝ›› (እንዚራ ስብሐት ገጽ 9)፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ ላይ ሦስት ችግሮችን የምናገኝ ቢሆንም ‹‹እማጸንሻለሁ›› የሚለውን በሌላ ጽሑፍ የምንመለከተው በመሆኑ ሁለቱን ችግሮች ብቻ ከዚህ በታች አሳያለሁ፤

1. ‹‹ምሳሌ የሌለሽ››፤ የመጽሐፉ አዘጋጅ አባ ጊዮርጊስ መጽሐፍ ቅዱስን የተማረ ነው ተብሎ የሚታመን በመሆኑ በቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ ምሳሌ የሌለው ተብሎ የተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን አይረሳም ተብሎ ተስፋ ይደረጋል፡፡ ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም›› ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳይያስ 46÷9)፡፡ በዚህም ምክንያት ታላቁ ነቢይ ኤርምያስ ‹‹አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው›› ይላል፡፡ በርግጥም እንደርሱ ያለ ማንም የለም (ኤርምያስ 10÷6)፡፡

ከዚህ አልፎ ለሚመጣ ሰው ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?... እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ›› ተብሎ ተጽፏልና እርሱን እንዲያነብ ይመከራል (ኢሳይያስ 40÷18፡ 25)፡፡ በዚህም ደግሞ አባ ጊዮርጊስ የተሳሳተ ጽሑፍ የጻፈ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ለማርያም በዚህ ልክ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በታች በሆነ ሁኔታ ምሳሌ የሌላት ተብሎ ስላልተጻፈ ጸሐፊው የልቡን መሻት ነውና የጻፈው፡፡

2. ‹‹መፍራትን ይቅርታን አጎናጽፊኝ፡፡… ይቅርታሽ››፤ ቀደም ሲል እንደተባለው ማርያም ወደ እግዚአብሔር የምታደርስ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር የምታስታርቅ ናት የሚል እምነት እንዳላቸው በአንደበት ይነግሩናል፡፡ ይሄ ግን ውሸት ነው፡፡ ምክንያቱም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት መካከል የሆነው አባ ጊዮርጊስ ማርያም የራሷ የኾነ ይቅርታ እንዳላት (ይቅርታሽ ነውና የሚለው) በመጻፍ በዚህ ይቅርታዋን እንደምታጎናጽፍ ሊያሳይ እየሞከረ ነው፡፡

ይሄ የአባ ጊዮርጊስ ጽሑፍ አሁን አሁን በውሸት ከሚናገሩት ንግግር ጋር ብቻ ሳይሆን ከታላቁ መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋርም አይስማማም፡፡ ምክንያቱም ቅዱሱ መጽሐፍ ይቅርታን የምናገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያስተምራል፡፡ ‹‹አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?›› የሚል ጥያቄ ይጠይቅና ራሱ መልሱን ሲሰጥ ‹‹ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና›› ይላል (መዝሙር 130÷3-4)፡፡ በርግጥም ከእርሱ ውጪ ይቅርታ ሊያደርግ የሚችል አካል የለም፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው›› የሚል ምክር ካቀረበ በኋላ ‹‹ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ›› በማለት ያበረታታል (ኢሳይያስ 55÷7)፡፡ ኢሳይያስ ይቅርታው የእግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ይቅርታውም›› በማለት የጻፈ ሲኾን የእንዚራ ስብአት መጽሐፍ አዘጋጅ ደግሞ ‹‹ይቅርታሽ›› በማለት ይቅርታን ለፍጡር ሲሰጥ ይታያል፡፡

ወገኖቼ ይቅርታን ያገኘነው እንዲሁ በጸሎት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ ዋጋ ተከፍሎልን፣ ደም ፈሶልን ነው፡፡ ይኼን የይቅርታን መንገድ ደግሞ ጌታችን እንዲህ ብሎ ነግሮናል፤ ‹‹ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው›› (ማቴዎስ 26÷28)፡፡ ስለዚህ በሌላ አካል ይቅርታ ይገኛል እያሉ ዓይንህን ወደ ፍጡራን እንድታማትር የሚያደርጉህን ሰዎች አትስማቸው፡፡፡፡