ተዋህዶ ሃይማናኖቴ
172 subscribers
715 photos
129 videos
21 files
329 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ "እግዚአብሔር ልጆቹን ወደ ጽድቅ ተራራ ጠራቸው ፤ ሰብስቦም ስለ አምላክነቱም አስተማራቸው"፡፡ ወዶ እና ፈቅዶ እዚህ ቻናል ተሰብስበን እድንማማር የረዳን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነና የተከበረ ይሁን ለዘለዓለሙ #አሜን፡፡
Download Telegram
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
|አዲስ ጌታ የለም @Z_TEWODROS
መሠረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽረዋም መስቀል ላይ የሞተው
ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘለዓለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም /2/

#አዝ
የእንግዳው ትምርት የጠላት እንክርዳድ
በመህሩ ጊዜ ይለያል ሲታጨድ
ጌታ ጌታ ያለው እንዲሁ በብልጠት
 አይወርስም ፈጽሞ የሰማዩን እርስት /2/

#አዝ
እራስ ለሆነላት ሆናለች አካሉ
ትታዘዘዋለች ዘወትር ለቃሉ
የፊት መጨማደድ ሳያገኛት ድካም
ታምና ትኖራለች እስኪመጣ ዳግም /2/

#አዝ
 የሰማዕታቱ ደም የከፈሉት ዋጋ
 የመላእክቱ ዜማ የሰማዩ ፀጋ
 የሐዋርያት ስብከት የነቢያት ትንቢት
ይገኛልበውስጧ በፀጋው ግምጃ ቤት/2/

#አዝ .
ጎዳናውን ጥሰን ብንጓዝ በሀሰት
ለአንደበታችን አውጀን ሐርነት
አይዘጋም ደጇ አይጠፋም መብራቷ
እየሱስ ነው ክብሯ ጌጥና ውበቷ /2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowocnen •✥• 💖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#ምሬሃለው በለኝ |@Z_TEWODROS
#ምሬሃለው_በለኝ

ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም/2/
መሃሪው መድሃኒዓለም
ይቅር ባይ እንዳንተ የለም

#አዝ
በሃጢአት ድንኳኖች ይብቃ መቀመጤ
የቀናውን መንፈስ አድሰው በውስጤ
የምህረት አይኖችህ ይዩኝ በይቅርታ
ስለ ድንግል ማርያም እስራቴን ፍታ /2/

#አዝ
 ቸል በማለቴ የደምህን ዋጋ
 ተመልሼ ገባሁ ከጥፋት መንጋጋ
 ሰላሜ ደፍርሶ ተቅበዝባዥ ሆኛለሁ
 ስለ እናትህ ብለህ ማረኝ እልሃለሁ
 ስለ ድንግል ማርያም ማረኝ እልሃለሁ

#አዝ
በከንቱ መሻቴ ሥጋ ነፍሴን ቀብሮ
አቅም አጥቻለሁ አጥንቴ ተሰብሮ
ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንድታደርገኝ
ስለ ድንግል ማርያም ከሃጢአቴ አጠበኝ
ስለ ድንግል ማርያም ምሬሃለሁ በለኝ

#አዝ
ከንፈሮቼን ከፍተህ ልቁም ለምስጋና
አንተን የጋረደኝ ጣሪያ ይነሳና
አልብሰኝ ፅድቅህን ይቅር መራቆቴ
ስለ ድንግል ማርያም መልሰኝ ከቤቴ /2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖

https://www.youtube.com/channel/UCGjlTux6hKInAcxn5RvwT7A
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#ደም ግባት አልባ |@Z_TEWODROS
ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ
ጀርባው በጅራፍ ስለ እኔ ደማ
የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ
ክብር  አለበሰኝ እርሱ ተገፎ /2/


#አዝ
በሐሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ
ክፋዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ
ለእኔ ግን ሆኗል መውጫ መንገዴ /2/
ታስረሃል ስለ እኔ እየሱስ መድህኔ /2/

#አዝ
ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፋ
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፋ
 በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ
 እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ /2/
 ታርደሃል  ስለ እኔ እየሱስ መድህኔ /2/

#አዝ
ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑ
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ
እጅ እግሩን ሚስማር ሲቸነክረው
የሞትን እሾህ ከእኔ ነቀለው
ተዋጋህ ስለ እኔ እየሱስ መድህኔ /2/

#አዝ
 እርቃኑን ሆኖ ፈተለው ልብሴን
 እንዲሁ ወዶኝ ጠጣው ቆምጣጤዬን
በምህረቱ ጠል ነፍሴን አርክቶ
 አለመለመኝ እርሱ ተጠምቶ    ተጠማህ ስለ እኔ እየሱስ መድህኔ /2/


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen
•✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen
•✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen
•✥• 💖
ፍልሰታ የሕፃናት ደስታ
ዝማሬ ዳዊት
#ፍልሰታ_የሕፃናት_ደስታ

የፍቅር የሰላም የደስታ ፆማችን
ከጌታችን እናት በረከት ማግኛችን
ፍልሰታ መታለች እጅግ ደስ ይበለን
ለቅዳሴ እንሂድ ልጆች ተሰብስበን

ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ

ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ
ከመቤታችን እጅ ሰበኗን አግኝቶ
የተደሰተባት የበረከት ፆም ወቅት
ፍልሰታ መታለች እንሂድ ለፀሎት
#አዝ
መንፈሳዊ ቅናት ሐዋርያት ቀንተው
እነሱም ለማየት ትንሣኤዋን ሽተው
በህብረት በመሆን ጠይቀው በእምነት
ትንሣኤዋን አዩ በፆምና ፀሎት
#አዝ
ሁል ግዜ በዓመት የምንናፍቃት
በፍቅር ምንፆማት ለማግኘት በረከት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንማርባት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንቁረብባት

ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ

💚 @tewahdowochnen 💚
💛 @tewahdowochnen 💛
❤️ @tewahdowochnen ❤️
#ኢትዮጵያዊው ጻድቅ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/
#አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
#አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሐይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
#አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ
ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
#አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስኮ ቆመህ በአንድ እግርህ
የመተ ሎሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጀ

ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
       ★ @tewahdowochnen
ሐዋርያው መነኩሴ
አኮቴት ዘማኅሌት
#ሐዋርያው መነኩሴ

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡት ሥላሴ
ዋስ ጠበቃ ሆኗል ተክልዬ ለነፍሴ

ዳሞት ይናገረው ያንተን ሐዋርያነት 
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት 
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት 
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መላእክት /2/ 
#አዝ
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሃይናኖት 
ከሰው ልጅ ልቡና ይወጣል አጋንንት 
የቅዳሴው እጣን ሲወጣ ከዋሻው 
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/ 
#አዝ
የኢትዮጵያን ምድር አረስከው በመስቀል 
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል 
ትናንት የዘራኸው ዛሬም ለእኛ ሆንዋል 
አምላከ ተክለ አብ ብለን ተምረናል
#አዝ
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ በማጠንህ 
ቅዱስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን 
ጸሎት ትሩፋትህ ትኅትና ስግደትህ 
ጾምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሠህ/2/ 
#አዝ
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው 
ሞቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው 
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ 
ስድስት ክንፉ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ /2/ 

ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
       ★ @tewahdowochnen
ገድሉ ታምራቱ
አኮቴት ዘማኅሌት
#ገድሉ ተአምራቱ

ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
#አዝ ------------------
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
#አዝ ---------------------
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
#አዝ -----------
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው ተክልዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
#አዝ -----------------
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ

ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
       ★ @tewahdowochnen
ነይ ነይ ድንግል ሆይ
ቀሲስ ዘበነ ለማ
ነይ ነይ

ነይ ነይ ማርያም ነይ ነይ
ድንግል ሆይ ነይ ነይ
ያን የእሳት ባሕር ከቶ እንዳላይ

#አዝ
በሐመረ ኖኅ የተመሰልሽው
በአሮን በትር የተመሰልሽው
የምስራቋ በር/2/ ቶሎ ድረሺ

#አዝ
ዓለም ከብዶብኝ ተጨንቄአለሁ
ሀዘን በዝቶብኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
እረ ነይ ድንግል ሆይ/2/ እጠራሻለሁ

#አዝ
ሚስጥሬን ገልፀሽ ለሕርያቆስ
ፈጥነሽ ያማለድሽ ለቤተዶኪማስ
ነይልኝ ድንግል ሆይ/2/ ልቤ ይፈወስ

#አዝ
ድንግል ቀርባለች ጩኸቴን ሰምታ
የኃጢአቴ ገመድ እስሬ ተፈታ
አከብራታለሁ/2/ ልጇ በልልታ

#አዝ
ውበቱ አንቺ ነሽ ሲሎንዲስ
ነይ ብሎ የሚጠራሽ ሱላማጢስ
አትቅሪ ድንግል ሆይ/2/ ደጅሽን ልሳለም✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

@tewahdowochnen
አልረሳውም ያንን እለት
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#አልረሳውም_ያንን_ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/

ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
#አዝ
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ
ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
#አዝ
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
#አዝ
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ

#ሼር
💚 @tewahdowochnen💚
💛 @tewahdowochnen💛
❤️ @tewahdowochnen ❤️
ዘማሪ በሱፍቃድ እንዳልካቸው
#መስቀል አበባ |@Z_TEWODROS
🌼​​✞መስቀል አበባ

መስቀል አበባ - - ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ - - ውብ አበባ(፪)

መስቀል አበባ - - ተቀብሮ ሲኖር
አደይ አበባ - - ሥነ ሥቅለቱ
መስቀል አበባ - - ዕሌኒ አገኘች
አደይ አበባ - - ደገኛይቱ
#አዝ
መስቀል አበባ - - ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ - - አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ - - ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ - - መስቀል ካለበት
#አዝ
መስቀል አበባ - - ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ - - ሸለቆው ዱሩ
መስቀል አበባ - - አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ - - ላንተ መሰከሩ

ዘማሪ
በሱፍቃድ እንዳልካቸው

"እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ
ነውና በማስተዋል ዘምሩ።"
መዝ ፵፮፥፯

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
" ምክንያት ስላለኝ ነው..."
@ort_mezmurr በቴሌግራም
#ምክንያት_ስላለኝ_ነው

ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ የምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ(፪)
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ

አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እንዳቀረቀረ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ
#አዝ
ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ
#አዝ
ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋም ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ አልፎለት ገዳዩ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ

#ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን
💾 4.3 MB MP3
#share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
💚 @tewahdowochnen 💚
💛 @tewahdowochnen 💛
❤️ @tewahdowochnen ❤️
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
እናታችን ጽዮን
ዝማሬ ዳዊት
#እናታችን_ጽዮን

እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና
መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና
ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን
የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሽን
የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን
በአስራትም በአደራም ለአንቺ ተሰጠን
#አዝ
የኤልጣቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ
የኃጢአታችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ
ምሥራችን ደስታን ይዘሽልን መጣሽ
ማርያም ስንልሽ ደረስሽልን ፈጥነሽ
#አዝ
ውለታሽ ብዙ ነው ለልብ የማይጠፋ
ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ
በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ
የሰማይ የምድሩም ማንም አልጨከነ
#አዝ
በትራችን አንቺ ነሽ የምትደግፊን
ባሕረ እሳትን የምታሳልፊን
ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማኀደረ መለኮት
ሁልጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽዕት

💚 @tewahdowochnen 💚
💛 @tewahdowochnen 💛
❤️ @tewahdowochnen ❤️
" ምክንያት ስላለኝ ነው..."
@ort_mezmurr በቴሌግራም
#ምክንያት_ስላለኝ_ነው

ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ የምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ(፪)
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ

አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እንዳቀረቀረ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ
#አዝ
ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ
#አዝ
ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋም ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ አልፎለት ገዳዩ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ

#ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን

@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
ደጉ መልዓከ ገብርኤል
|@Z_TEWODROS
#ሃያል_ነህ_አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት
#አዝ
በዱራ ሜዳ ላይ - ገብርኤል
ጣኦት ተዘጋጅቶ - ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ - ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ - ገብርኤል
ሲድራቅ እና ሚሳቅ አብደናጎ ፀኑ፤
ጣኦቱን እረግጠው በእግዚያብሄር አመኑ
#አዝ
ተቆጣ ንጉሱ - ገብርኤል
በሶስቱ ህፃናት - ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ - ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት - ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ወረደ መላኩ፤
ከሞት አዳናቸው በሳት ሳይነኩ።
#አዝ
ከእቶኑ ስር ሆነው - ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ - ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው - ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ - ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር፤
አዩ መኩአንንቱ የእግዚአብሄርን ክብር።
#አዝ
ናቡከደነፆር - ገብርኤል
እጁን ባፉ ጫነ - ገብርኤል
ሰለስቱ ደቂቅን - ገብርኤል
ከእሳት ስለአዳነ - ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከ መላኩን፤
ሊአመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
ገብርኤል በሰማይ
|@Z_TEWODROS
ገብርኤል በሰማይ

ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር/2/
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር/2/


ትፀንሺ ሲልክ በከበረ ዜና
ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እንዲፅናና
ከገብርኤል ሰምተው መላዕክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ
ብፅሂት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን ልዑል አብነት አድርገን

/ አዝ =======

ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማህፀንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አገኘነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡት ጋር ብፅሂት ብለናል

/አዝ =======

ከተፈጥሮ በላይ ፅንስን ያዘለለ
የእሳት ምሰሶ ባንቺ ተተከለ
የእግዚአብሔር ሀገሩ የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን
ብፅይት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን

/ አዝ =======

ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዪት
ሰዉና መላዕክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግርግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግማዊት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ
እጅ እንነሳለን ሁነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነው እና


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
ፍልሰታ
@Z_TEWODROS
#ፍልሰታ_የሕፃናት_ደስታ

የፍቅር የሰላም የደስታ ፆማችን
ከጌታችን እናት በረከት ማግኛችን
ፍልሰታ መታለች እጅግ ደስ ይበለን
ለቅዳሴ እንሂድ ልጆች ተሰብስበን

ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ

ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ
ከመቤታችን እጅ ሰበኗን አግኝቶ
የተደሰተባት የበረከት ፆም ወቅት
ፍልሰታ መታለች እንሂድ ለፀሎት
#አዝ
መንፈሳዊ ቅናት ሐዋርያት ቀንተው
እነሱም ለማየት ትንሣኤዋን ሽተው
በህብረት በመሆን ጠይቀው በእምነት
ትንሣኤዋን አዩ በፆምና ፀሎት
#አዝ
ሁል ግዜ በዓመት የምንናፍቃት
በፍቅር ምንፆማት ለማግኘት በረከት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንማርባት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንቁረብባት

ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
Tabor Abera | ምርትነሽ ጥላሁን | Mirtnesh Tilahun (ደብረ ታቦር)
ታቦር አበራ
#ታቦር_አበራ

ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
#አዝ
ሙሴም የቀደመው ሰዉ ኤልያስ ኃይለኛው
ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው
እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል
በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል
#አዝ
ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን
ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቸሃለሁ አሁን
የሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ
አርሙኒየም ደስ አለው ስሳራን ስለመታ
#አዝ
እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ
መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ
የዳዊት ልጆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ
ብልኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ
#አዝ
ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው
ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው
ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው
ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው
#አዝ
የረዳኸው ይናገራል ያሰበከው በሕይወቱ
አቤነዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ
በደስታየም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ
ከነጋር አልቅሰሃ አሳዝኖህ ሀዘኔ

•✥•🍁 @tewahdowochnen 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
በዙርያችን ካሉ |@Z_TEWODROS
#በዙሪያችን_ካሉ

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከጸኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
#አዝ
ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች ንግስት መባልን
በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙምስክር
የቅድስትአርሴማ እጹብነው የሷ ክብር/2/
#አዝ
እግዚአብሔር ጽናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅጽሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለአለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች /2/
#አዝ
ይኸው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለጻት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አረጋት
አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር/2/
#አዝ

እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ /2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
ዘማሪት ሲ/ር ሊዲያ #እናቴ ቅድስት አርሴማ
@Z_TEWODROS ON TELEGRAM
✞ እናቴ ቅድስት አርሴማ

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣውኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ


ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

አዝ----------

ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር የታጨሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለውኝ በሂወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
በአንቺ አፍሮ የሄደ ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

•✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
በዙርያችን ካሉ |@Z_TEWODROS
#በዙሪያችን_ካሉ

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከጸኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
#አዝ
ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች ንግስት መባልን
በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙምስክር
የቅድስትአርሴማ እጹብነው የሷ ክብር/2/
#አዝ
እግዚአብሔር ጽናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅጽሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለአለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች /2/
#አዝ
ይኸው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለጻት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አረጋት
አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር/2/
#አዝ

እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ /2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
✞ እናት አለኝ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#እናት_አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
#አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

@tewahdowochnen
@tewahdowochnen