ተዋህዶ ሃይማናኖቴ
172 subscribers
715 photos
129 videos
21 files
329 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ "እግዚአብሔር ልጆቹን ወደ ጽድቅ ተራራ ጠራቸው ፤ ሰብስቦም ስለ አምላክነቱም አስተማራቸው"፡፡ ወዶ እና ፈቅዶ እዚህ ቻናል ተሰብስበን እድንማማር የረዳን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነና የተከበረ ይሁን ለዘለዓለሙ #አሜን፡፡
Download Telegram
መሪ ደብረታቦር ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን
#መስከረም_21

#ብዙኃን_ማርያም

በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤

#ጉባዔ_ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አር*ዮስ የሚባል መና*ፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህ*ደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አር*ዮስ ክህ*ደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአር*ዮስ ክህ*ደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮ*ስን አው*ግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡

(#ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረገጽ)
@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
@tewahdowochnen
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
Audio
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሀሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
……
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
በአሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
…..አዝ…..
ገብተሻል ላትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆነሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንቺ ነው የጠፋው ተገኝቶ
….አዝ….
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሐረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራንዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
….አዝ…..
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ የሀዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
…አዝ…..
ከሀገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዞአችን
በአደርንበት አድርሽ በሄድንበት ሂጂ
ለፃድቃን አይደለም ለኃጢያን አማልጂ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
"ልቦናዬ ያውጣ" አዲስ ዝማሬ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ (Official Video)
ልቦናዬ ያውጣ

ልቦናዬ ያውጣ ውዳሴ ለክብርሽ
ሰላም ለኪ ድንግል ፀጋን የሞላብሽ
የእግዚአብሔር ከተማ የመለኮት ሃገር
ስላንቺ የሚነገር አለን ድንቅ ነገር/2/
አዝ-----
የነቢያት ድንግል የአበው ምሳሌ
እናቴ እልሻለሁ ቢበዛም በደሌ
ከቅዱሳን ሁሉ ያንቺ ክብር ይበልጣል
አምላክን ልጄ ነው ማንስ ብሎት ያውቃል
አዝ-----
ሄዋን ባትታዘዝ ለእግዚአብሔር ቃል
ሞትና መርገሙ ወደ ዓለም ገብቷል
የመላኩን ብስራት በእምነት ብትሰሚ
ሞገስን ተቀበልሽ በቀኙ እንድትቆሚ
አዝ-----
ፍቅርሽ ጉልበት አለው ባህሩን ያሻግራል
ልመናሽ ፅኑ ነው ግዳጅ ይፈፅማል
ስለዚህ ድንግል ሆይ እንወድሻለን
ስምሽን ለልጅ ልጅ እንዘክራለን
አዝ-----
ቀድሞም አልነበረም ወደፊትም አይኖር
ከፍጥረታት ሁሉ በሰማይ በምድር
ከእግዚአብሔር በታች ዛሬም ተሞሽራ
ድንግል ትታያለች ከከበሩት ከብራ


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሊቀ ገ/ዮሀንስ ገ/ፃዲቅ
ድል አለ በስምህ|@Z_TEWODROS TELEGRAM CHANNEL |
እንኳን አደረሳቹ !

ድል አለ በስምህ

ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ሰልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ሰልህ


አዝ ====

ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ሰምህ ነው

አዝ ====

በእልልታ ቢፈርሰ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው/2/

አዝ ======

ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ


አዝ=====

የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግሰ
ሆነኸ ነው ክብርና

ዘማሪ ገ/ዮሀንስ ገ/ፃዲቅ
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥

•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
❤️ •✥• @tewahdowochnen •✥•
Audio
የማይሸረሸር አለቴ
የማይናጋ መሰረቴ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሞገሴ
አንተህ ነህ የጽድቅ ልብሴ

ቀራንዮ ላይ የቆመ
በፍቅር የተተለመ
ከፊቴ ተነሰነሰ
ደምህ ሕይወቴን ወረስ

እፎይ ልበል ልዘምር
ሁነኸኛል ጌታ ክብር

የሲና ምድር ኅብስቴ
የተከተልከኝ አለቴ
መርገሜን ሰብሮ አለፈ
ሰላምህ ውስጤ ጎረፈ

የማትደፈር ክልሌ
የድል አርማዬ አክሊሌ
ዓለምን ማሸነፊያዬ
አንተ ነህ ክንዴ ጌታዬ

ማዳፎችህን አይቼ
በዕንባ ረጠቡ ጉንጮቼ
ትዝታዬ ነው ዘወትር
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
በዙርያችን ካሉ |@Z_TEWODROS
#በዙሪያችን_ካሉ

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከጸኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
#አዝ
ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች ንግስት መባልን
በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙምስክር
የቅድስትአርሴማ እጹብነው የሷ ክብር/2/
#አዝ
እግዚአብሔር ጽናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅጽሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለአለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች /2/
#አዝ
ይኸው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለጻት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አረጋት
አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር/2/
#አዝ

እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ /2/

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖
ዘማሪት ሲ/ር ሊዲያ #እናቴ ቅድስት አርሴማ
@Z_TEWODROS ON TELEGRAM
✞ እናቴ ቅድስት አርሴማ

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣውኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ


ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

አዝ----------

ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር የታጨሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለውኝ በሂወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
በአንቺ አፍሮ የሄደ ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

•✥•🍁 @tewahdowochnen 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
​​ሥደትሽን ሣስብ

ሥደትሽን ሣስብ ስለ አንቺ ልገፋ
ለካስ ሥደት አለ ቀን በሰው ሢከፋ
ወስዶ ሣያስቀርሽ ወንዝ እና ጅረቱ
ምሣሌ ሆነሻል ድንግል ለፍጥረቱ /፩/

/አዝማጅ/።።።

እንዳልቅበዘበዝ ሁኚ ከአጠገቤ
ድንግል ሆይ ሥራሽን መዝግቦታል ልቤ
በምሕረት ይለፈኝ በፍጹም ይቅርታ
እሺ ባይው ልጅሽ የታቀፍሽው ጌታ

/አዝማች/።።።

ሡላማጢስ ብሎ ሶለሞን ጠራሽ
የሠላም መገኛው አንቺ ስለሆንሽ
እንበረከካለሁ እሠግዳለሁ ለአንቺ
ጠላት እንዳይጥለኝ ጉልበቴን አበርቺ

/አዝማች/።።።

የኮቲባ ቁጣ ዛቻ እና ክፋቷ
አስተናግዳዋለች ምድር አፏን ከፍታ
በአንቺ ላይ ያመጹት በቁጣው ጠፍተዋል
ከጥቅልሉ መዝገብ ከእርሱ ተሽረዋል

/አዝማች/።።።

ለተጠሙት ነፍሳት ያጠጣቸው ጌታ
ከጀርባሽ ላይ ሆኖ በዱር ተንገላታ
የግብጽን ጣዖታት በግርማው መታቸው
ኢየሱስ ክርስቶስ የአለቆች ጌታቸው

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ስደትሽን ሳስብ |@Z_TEWODROS
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @tewahdowochnen •✥•💚
💛 •✥• @tewahdowochnen •✥•💛
💖 •✥• @tewahdowochnen •✥• 💖