FIDEL POST NEWS
19K subscribers
17.6K photos
2.71K videos
390 files
1.27K links
Fast news about Ethiopia
Download Telegram
ለፍርድ ቤት ምንም ንብረት የለኝም በማለት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ አቅርበዋል የተባሉት አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በአንድ ወር ከ15 ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ነው።

አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በቀላል እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸው መሆናቸውንና በቀበሌ ቤት እንደሚኖሩ በመግለጽ ለፍርድ ቤቱ በቃለ-መሐላ አረጋግጠው አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ ሰተዋል ተብለው ነው፡፡

ይሁንና ስለግለሰቡ ሀብትና ንብረት አጣርቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው የአዳማ ከተማ አስተዳደር ግለሰቡ በስማቸው የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ያላቸው መሆኑን እና በመጠጥ ችርቻሮ ንግድ ስራ ላይም ተሰማርተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ አረጋግጧል።

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 481 እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 452 መሰረት የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳያስፈለግ ግለሰቡ ጥፋተኛ በተባሉበት የወንጀል ህግ አንቀፅ ለሌሎችም ግለሰቦች ያስተምራል በማለት በነሀሴ 27 ቀን 2014 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ አቶ ኃይለማርያም ወዳጆን በ1 ወር 15 ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
የ“ኢንሳ” ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ ተቋሙን እንዲመሩ ተሾሙ

ካለፈው ህዳር ወር 2014 ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ሰለሞን ሶካ፤ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሾሙ። አቶ ሰለሞን የመሪነት ቦታውን የተረከቡት “ኢንሳ”ን ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ የመሩትን ዶ/ር ሹመቴ ግዛውን በመተካት ነው።

አቶ ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነ መሾማቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቢያረጋግጡም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል። ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በሶፍት ዌር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ሰለሞን፤ በ“ኢንሳ” ከሶፍት ዌር መሐንዲስነት እስከ ቡድን መሪነት ባሉት ቦታዎች አገልግለዋል።

ኃላፊነታቸውን ለአቶ ሰለሞን ያስረከቡት ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከጥር 2012 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት መርተውታል። ዶ/ር ሹመቴ ወደ ኢንሳ ከመምጣታቸው በፊት ለስምንት ወራት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ዶ/ር ሹመቴ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትም ነበሩ።

ethiopiainsider
24 የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ የቡድኑ ተዋጊዎች ተደመሰሱ
********

የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ እስካሁን ባለው ሂደት 24 የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ የሽብር ቡድኑ ተዋጊዎች መደምሰሳቸውን ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

ድሽቃን ጨምሮ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ነው የተገለጸው።

የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና የጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል መሃመድ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ከሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት ያደረገው ሙከራ በፀጥታ ኃይሉና በሕዝቡ የተቀናጀ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።

ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሹ የውጭ ጠላቶች የውስጥ ባንዳዎችን በመቅጠር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
" ... አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው " - የሶማሌ ክልል ፕ/ት ሙስጠፌ ሙሁመድ

በቅርቡ በሶማሊያና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ጥቃት ፈፅሞ የነበረው የአልሸባብ ቡድን 800 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን 100 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ በተረጋገጠ ትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

የአልሸባብ ጥቃት በሽንፈት መጠናቀቁን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ እና እንዳይዳፈር የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው በወንዶች 3ሺ ሜትር በመልኬነህ አዘዘ 2ኛዋን ወርቅ አገኘች

************
ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው በኮሎምቢያው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 3ሺ ሜትር የፍፃሜ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በርቀቱ 7፡44.06 በሆነ ጊዜ 1ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ለአገሩ ያመጣው አትሌት መልኬነህ አዘዘ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ወክሎ አብሮት የተሰለፈው ድርባ ግርማ ደግሞ ውድድሩን 4ኛ በመውጣት ጨርሷል፡፡ ኬንያዊያን 2ኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ለርቀቱ የተዘጋጀውን የብርና ነሐስ ሜዳሊያ ወስደዋል፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ያገኘችው የሜዳሊያ ብዛት በ2 ወርቅ ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ በአጠቃላይ በ6 ሜዳሊያ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን ከኬንያ በመቀጠል 4ኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደስተኝነት እንበለው?

መልካም ቅዳሜ ይሁንላቹ
በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል ያለው "የመተማመን እጦት" ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው ድርድር "ዋና እንቅፋት" እንደሆነ የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔተ ቬበር ተናገሩ።

ልዩ ልዑኳ ከኢትዮጵያ መልስ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በትግራይ ክልል የተቋረጡ አገልግሎቶችን ማስጀመር ለድርድሩ መንገድ እንደሚጠርግ እምነታቸውን ገልጸዋል። ወደ አዲስ አበባ እና ወደ መቐለ አቅንተው ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የተነጋገሩት አኔተ ቬበር "አንዱ ከሌላው ጋር በቅን ልቦና እየተደራደሩ ለመሆናቸው የበለጠ መተማመኛ እንደሚፈልጉ ሁለቱም ግልጽ አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች ዝግጁነታቸውን ከማሳወቅ ባሻገር ወደ ድርድሩ እንዲመጡ የሚያስፈልገውን መተማመን [የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ] ፕሬዝደንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ያጠናክራሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ለድርድሩ "መንግሥት ተጨማሪ ቅድመ-ሁኔታዎች እንደሌሉት አረጋግጧል" ያሉት ልዩ መልዕክተኛዋ "ከመንግሥት በኩል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር ምልክት ከሰጠ ወይም ካስጀመረ ህወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በመቐለ ጉብኝታችን ተረድቻለሁ" ሲሉ አስረድተዋል።(DW)
Facebook Fellowship Program 2023 | Fully Funded |


1) A $42,000 annual stipend to cover living and
conference travel costs
2) ) A paid visit to Facebook headquarters for the annual
Fellowship Summit
3) Various opportunities to engage with Facebook
researchers

For more info, visit https://scholarshipscorner.website/facebook-fellowship-program/

Deadline: September 20, 2022.
University of Alberta Scholarships Without IELTS 2022-23 (Fully Funded)


Scholarships offered by Alberta University for Bachelors Masters and PhD students.

Detail: https://tinyurl.com/yc5xct2u

No need of IELTS for program.
Canadian Government will cover all the expenses

Deadline: 15 December 2022
“ምዕራባዊያን በእርዳታ ስም እጃችንን ለመጠምዘዝ ከሞከሩ ኡጋንዳ ያለ እርዳታም እንደምትኖር እናሳያለን” ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪቪ፤ እርዳታ ከምዕራባዊያን ከመጣልን እንቀበላለን፤ በእርዳታ ስም እጃችንን ለመጠምዘዝ ከሞከሩ ግን ኡጋንዳ ያለ እርዳታም እንደምትኖር እናሳያለን ማለታቸው” ተሰምቷል።

ለኡጋንዳ “ማንም ምን ማድረግ እንዳለብን ሊነግረን አይችልም” ሲሉም ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ተናግረዋል።

በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ "ካምፓላን መጎብኘት ከፈለጉ በራችን ክፍት ነው፣ ሁሌም እንኳን ደህና መጣሽ ብለን እንቀበላታለን" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ነገር ግን ምን ማድረግ እንዳለብን ወደ መናገር ከገቡ ግን "ማንም ምን ማድረግ እንዳለብን ሊነግረን አይችልም" እላታለሁ ብለዋል።
አል አይን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሶስት ወራት ያላያትን አሳዳጊውን ሊቀበል የተገኘው ውሻ ፍቅሩን የገለፀበት ያስቀናል ! !

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ
ጀነራል ባጫ ደበሌ ይፋዊ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዘዳንት አሁሩ ኬንያታ አቀረቡ!

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ጀ/ል ባጫ ደበሌ ይፋዊ የሹመት ደብዳቤያቸው ለሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ኡሁሩ ኬንያታ አቅርበዋል።

በትላንትናው እለት በናይሮቢ ስቴት ሃውስ በተካሄደው ስነስርአት ላይ ከኢትዮጵያ በተጨማሪየአሜሪካ፣የጀርመንና የሱዳን አምባሳደር ሆነው የተመደቡ አዳዲስ አምበሳደራትም የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት አምባሳደሩ በኬንያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራና ሁለገብ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን የሹመት ደብዳቤውን የተቀበሉት ፕሬዝዳንት ኡሁሩም ሀገራቱ ያላቸውን ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኬንያ መንግስት እና ህዝብ ፍላጎት መሆኑን መጠቆማቸውን ከኬንያ ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
******

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፤ ውሳኔዎቹም የሚከተሉት ናቸው፥

1. ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣንን አደረጃጅት፣ ስልጣንና ተግባራትን ለመወሰን በቀረበው ደንብ ላይ ሲሆን የፌዴራል መንግስት የአስፈላሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 3263/2014 የነዳጅና ኢነርጂ ጉዳዮችን የሚመራ ተቋም በአዲስ መልክ ያቋቋመ መሆኑን ተከትሎ ባለስልጣኑ ሴክተሩን በብቃት መምራት የሚያስችል ስልጣንና ተግባር እንዲኖረው የሚያስቸል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲወል ወሰኗል፡፡

2. በመቀጠል ምከር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የብሔራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው። ቀደም ሲል የነበረውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት አገራችን በጀመረቸው አጠቃላይ አገራዊ የሪፎርም አጀንዳ ማዕቀፍ ውስጥ የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎችን ተሳትፎ በማስፋት የክፍያ ስርአቱን ውጤታማነት፣ አስተማማኝነትና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት፣ ገበያው አበክሮ የሚፈልጋቸውንና በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉትን ለውጦች፣ ዕድገቶችና መሻሻሎች ታሳቢ ባደረገ መልኩ የክፍያ ስርዓታችንን ማዘመን ይቻል ዘንድ የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይፀድቅ ዘንድ ወደ ህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

3. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግስት ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ፕሮጀክት እንዲሁም ከዓለዎ አቀፉ የልማት ማህበር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ በተፈቀዱ ብድሮች ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው። ከጣሊያን መንግሥት የተገኘው ብድር 10 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የተገኘው ብድር ደግሞ 46ዐ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ ምክር ቤቱም ብድሮቹ ከ1 ፐርሰንት ያነሰ ወለድ የሚከፈልባቸው፥ እስከ 12 ዓመታት የሚደርስ የችሮታ ጊዜ ያላቸው እና በ38 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ መሆናቸውን ይህም ከአገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ይፀድቁ ዘንድ ረቂቅ አዋጆቹ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወሰኗል፡፡
ዛሬ ለፊደል ፖስት ከደረሱ መልዕክቶች መሀል;
ዛሬ ወደ ፖስታ ቤት ጎራ አልኩና ለ2015 የኪራይ ልከፍል ስል ገና ፖስታ ቁጥሬን ስነግራት 1200 ብር አለችኝ። ለምን ስላት ደንግጬ የ2014 አመት 600ብር የ2015ዓ.ም. 600ብር አለችኝ "
እንዴ የ2014 የሚከፈለውን በ2013ሐምሌ እንደከፈልኩና በሲስተም ፕሪንት አርገው እንደሰጡኝ አስታውሳለሁ።
የገባኝ ያው የ2014 በ2013 ያስከፈሉበትን ደረሰኝ ይጡልታል ተብሎ ይሆናል ብዬ ሳስብ የ2014 600 የከፈልክበትን ደረሰኝ ይዘህ ና አለችኝ።
አሁን ግን በዲጂታል ዘመን ለግል ፖስታ ሳጥን ከ85 ብር 600 መቶ ብር ዋጋ መቀየር አይከብድም።
አምናበ2013 ለ2014 የከፈልኩበትን ደረሰኝ እየፈለኩ ነው እላችኋለሁ ።
ዛሬ ቅዳሜ በመሆኑም ኃላፊ ለማናገር አልተመቸኝም።