FIDEL POST NEWS
20.3K subscribers
9.85K photos
970 videos
209 files
749 links
Fast news about Ethiopia
Download Telegram
በአዲስ አበባ የተሰረቁ እቃዎችን ይከማችባቸዋል በተባሉ ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ 69 ተጠርጣሪዎች፣ 1 ሺህ 232 የሞባይል ስልኮች፣ 87 ላፕቶፖችና ሌሎች በርካታ እቃዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ በላከው መግለጫ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተለያዩ የተሰረቁ እቃዎችን የሚቀበሉ ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ መያዙን አስታውቋል

በጥናት ላይ ተመስርቶ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተሰረቁ ንብረቶች ተገኝተዋል

በአዲስ አበባ ፖሊስ ልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አለማየሁ አያልቄ፤ የተሰረቁት ንብረቶቹ የተያዙት በተጠና መልኩ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን ገልጸዋል።

በአራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ የካ፣ አዲስ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች እቃዎቹ ከነ ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች በ82 ቤቶች በተደረገ ብርበራ 1 ሺህ 232 የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ 87 ላፕቶፕ ኮምፒተሮች ተይዘዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት ኬብሎች፣ 232 የመኪና ስፖኪዮ፣ 3 ቴሌቪዥን፣ 6 ፕሌስቴሽን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አንድ ወታደራዊ ሬዲዮ እና ሌሎች በርካታ የተለያዩ የመኪና እቃዎች መያዛቸውን ተናግረዋል።

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ 69 ተጠርጣሪዎችና ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስለመዋላቸውም ተናግረዋል።

ፖሊስ በከተማዋ የሚፈፀሙትን የቅሚያ፣ የስርቆትና ሌሎች ወንጀሎች ለመከላከል የጀመረውን ጥረትና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ረዳት ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ንብረት የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች ቀርበው ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው መውሰድ የሚችሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ማኅበራት የመምህራን ደመመዝ ካልተጨመረና የደረጃ እድገት ማሻሻያ ካልተደረገ በመስከረም ሥራ ማቆም አድማ እንጠራለን በማለት ለመንግሥት በላኩት ይፋዊ ደብዳቤ ማስጠንቀቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ማኅበራቱ መንግሥት ለጥያቄያቸው ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቶ በምንወስደው ርምጃ ለሚፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ አንሆንም ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ትምህርት ሚንስቴር ጉዳዩን እያጠናሁት ነው ብሏል። መንግሥት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን በቅርቡ ባደረገው የደመወዝ ማሻሻያ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ወርሃዊ ደመወዝ ከዩኒቨርስቲ አስተማሪ ደመወዝ ይበልጣል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ በፍልስጤም ጋዛ ሰርጥ ከእስራል የተተኮሰው ሮኬት ሲፈነዳ ። ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ።
የሮማኒያ ሴቶች በሀገራቸው ያሉት የዩክሬን ሴቶች" ባሎቻንን እያማገጡ አስቸገሩ ። ከሀገራችን ይውጡ " በማለት ግድግዳ ላይ ወረቀት እየለጠፉ ነው

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘው ፅሁፍ እንዲህ ይላል;

"ክብር የሌላቸው ስደተኛ ሴቶች! ወደዚህ አይመጡም። ከባሎቻችን ዝሙት መስራት ገንዘቦቻቸውንም መምጠጥ አቁሙ ።🙊ከሮማኒያ ውጡ። ወደ ዩክሬን ተመለሱ። ወደ ግንባር ሂዱ እና የዩክሬን ወታደሮችን ጠንካራ መንፈስ እንዲኖራቸው አድርጉ"🦸♂️።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማምሻውን ከፍልስጤም ጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬት እየተተኮሰ መሆኑን ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ሰውን ለመርዳት የማይታክት ሰው! !! ታዬ ወርቁ

መድረክ ሲመራ የተዋጣለት ሰው ነው ። ከሚያገኘው ገንዘብ ለተቸገሩት ይረዳል። ከወዳጆቹና ከበጎ ፍቃደኞች ገንዘብ እያሰባሰበ የተቸገረን ይረዳል ።የታመመን ያሳክማል
።ስራ ላጡት ስራ ይፈልጋል። እንዲሁ በነፃ ! !! ሰውን በመርዳት ልቡ ሐሴት የምታደርግ ሰው !! አይደክመውም ለአንዱ የተገኘውን እርዳታ ሰጥቶ ለሌላው ደግሞ ነገ ይሯሯጣል። ሰው ሰው የሚሸት መልካም ሰው! !
ድርቤ ወልተጂ በፖላንድ ዳይመንድ ሊግ የ1500 ውድድር የቦታውን ክብረወሰን በመሥበር አሸንፋለች፡፡የኦሪጎን ሻምፒዮና የርቀቱ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ጉዳፍ ፀጋይ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳልያ በ3ኛነት አጠናቀቀች
*******************

በኮሎምቢያ ካሊ ላለፉት 6 ቀናት በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያ ሶስተኛ ደረጃን አጠናቅቃለች፡፡

የአትሌቲክስ ቡድኑ በቆይታው በ6 ወርቅ፣ በ5 ብር እና 1 የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎችን በማምጣት ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን እና ጃማይካን ተከትላ በ3ኛነት ፣ከአፍሪካ ደግሞ በ1ኛነት እንድታጠናቅቅ አስችሏል፡፡

በሻምፒዮናው 19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ማሰለፉን ያስተወቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፣የተገኘው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከተሳተፈችበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር የተገኘው ውጤት እጅግ የሚያኮራ መሆኑንም ፌደሬሽኑ ገልጿል።

ኬንያ 3 ወርቅን ጨምሮ በአጠቃላይ በ10 ሜዳልያ ኢትዮጵያን ተከትላ ከዓለም 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡


አሜሪካ በቀዳሚነት የጨረሰችው 7 የወርቅ፣4 የብርና 4 የነሀስ በድምሩ በ15 ሜዳልያ ሲሆን፣ጃማይካ ደግሞ በ6 ወርቅ፣7 ብር እና 3 ነሃስ በድምሩ በ16 ሜዳልያ በ2ኛነት አጠናቃለች፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦኬዥን ካፌና ሬስቶራንት የሕፃናት ልብ ህሙማን የሕክምና ማእከልን ለመርዳት በወዳጅነት አደባባይ የሚገኘው ቅርንጫፉ ውስጥ የልጆች የፒዛ መስራት ትርኢት እያካሔደ ይገኛል።

ልጆች እየተዝናኑ ፒዛ እየሰሩ የእድሜ እኩዮቻቸውን ይረዳሉ።

የልብ ስፔሻሊስት ሀኪሞችም በቦታው ተገኝተው ገለፃ እየሰጡ ነው። ከ 7ሺሕ ሕፃናት በላይ የልብ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ እየጠበቁ ይገኛሉ።

በኦኬዥን ካፌ የተዘጋጀው ይሕ የፒዛ መስራት ትርኢት ሙሉ ገቢው ለልብ ሕሙማን ሕፃናት ማእከል የሚውል ነው። ትርኢቱ ሁሐተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን ፤ መጪው እሁድ ድረስ የሚቀጥል ነው።

ካፌው ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን እያዝናኑ ሌሎችን የሚረዱበትን ኘሮግራም ላይ አሁንም በመመዝገብ እንዲሳተፉ ጥሪውን አቅርቧል።
Ethio mass link https://play.google.com/store/apps/details?id=ethio.mass.link
Android Application for various job seekers and creative Ethiopians as well as those looking for professionals. Download it from your phone and try it.
ለተለያዩ ተመራቂዎች: ስራ ፈላጊዎችና የፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ፕሮፌሽናል ባለሞያዎችን ለሚፈልጉ የተዘጋጀ Android Application ነው።በስልኮ ከሊንኩ ተጭነው አውርደው ይሞክሩት።
Check out "Ethio Mass Link"
https://play.google.com/store/apps/details?id=ethio.mass.link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኩባ. በማታንዛስ በኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ በሱፐር ታንከር ቤዝ ዘይት ማከማቻ ፋሲሊቲ ላይ ትናንት ምሽት በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ 67 ሰዎች ቆስለዋል፣ 17 የእሳት አደጋ ተከላካዮችም ጠፍተዋል ተብሏል።
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ844 ኪሎ ግራም በላይ የዝሆን ጥርስ ተይዟል ተባለ

በ2014 በጀት ዓመት ከ844 ኪሎ ግራም የሚልቅ የዝሆን ጥርስ በሕገወጦች ሲዘዋወር መያዙን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው ከ57 ኪሎ ግራም በላይ የከርከሮ ጥርስ፣ ከ79 ኪሎ ግራም የሚልቅ የጉማሬ ጥርስ እና ከአምስት ኪሎ ግራም የበለጠ የአውራሪስ ቀንድ ከሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ተይዟል።
የአጋች ታጋች ድራማ በኬንያ ሰማይ
~~//~~

በጎረቤት ኬንያ ባለቤትነቱ የሲቲዝን ቲቪ የሆነ ድሮን የካሳራኒ ስታዲየም ላይ ሲያንዣብብ በነበረ ንስር መታገቱን ኬንያ ማክስ ኒውስ ዘግቧል።

በሰማይ ላይ በሚያንዣብብ ንስር ያልታሰበ እገታ ድሮኑ ላይ ስለፈፀመበት የሲቲዝን ቲቪ የቀጥታ ስርጭት እንደተቋረጠ የዜና ወኪሉ አስታውቋል።

የአጋች ታጋች ድራማዊ ትዕይንቱን ተከትሎ ፖሊስ በተደጋጋሚ ወደ ሰማይ ቢተኩስም እንዳልተሳካለት በዘገባው ተገልጿል።

ንስሩ ድሮኑን እገታ ሲፈፅም የሚያሳየው የፎቶ ምስል ቅዳሜ እለት በበርካታ ኬንያውያን በማህበራዊ ገፃቸው በስፋት ተቀባብለውታል።

ነገሩ ወዲህ ነው!

እውነታውን አረጋጋጭ ግን በኬንያ ማክስ ኒውስ የተለቀቀው ሪፖርት የሃሰት መረጃ መሆኑን አረጋግጧል።

ንስር አዚሚዮ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ራይላ ኦዲንጋ በካሳራኒ ስታዲየም ያደረጉትን የመጨረሻ ሰልፍ እንዳቋረጠ የሚወጡ ዘገባዎች የሃሰት መረጃ ናቸው ~ ብሏል።

በኬንያውያን ዘንድ በሰፊው የተሰራጨው ምስል በ2016 የተቀረፀ እንጂ፤ ቅዳሜ ዕለት በካሳራኒ ስታዲየም አልነበረም።

ፋክት አረጋጋጭ በተጨማሪም የራይላ ዝግጅት የሲቲዝን ቲቪ ዘገባ ቅዳሜ እለት ሙሉ በሙሉ እንዳልተቋረጠ አረጋግጧል።

ፎቶግራፉ የተነሳው በመጋቢት 2016 በፎቶግራፍ አንሺ ኮይን ቫን ዌል ሲሆን የሰለጠነ ንስር ከ~Guard From Above በተሰኘ ኔዘርላንድስ ኩባንያ ባደረገው የፖሊስ ልምምድ ላይ የተነሳ ፎቶ መሆኑን አረጋግጧል።
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን !

በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦

• መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

• ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው።

• የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ ጠይቀዋል።

• በመንግስት የተደረገው የደረጃ ማሻሻያ ረጅም ጊዜ በዩንቨርሲቲ ያስተማሩ መምህራንን ልምድ ያላገናዘበ በመሆኑና በመምህራን መካከል በቀጣይ ፍትሀዊ የደምወዝ ልዩነት እንዲኖር ስለማያስችል የደረጃ ማሻሻየው የመምህራንን ልምድ እና ማዕረግ ያገናዘበ እንዲሆን ጠይቀዋል።

• የረዳት ፕሮፌሰር የአካዳሚክ ማዕረግ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የ3ኛ ዲግሪ መደረጉን በተመለከተ ያለን ቅሬታ አላቸው።

• የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑ ላይ አቤቱታ አላቸው።

• የቺፍ ቴክኒካል ረዳት II የትምህርት ደረጃን ፒ ኤችዲ ዲግሪ መሆኑም ላይ አቤቱታ አላቸው።

ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጣቸው እያሉ የሚገኙት መምህራኑ ይህ ካልሆነ እስከ ስራ የማቆም አድማ መምታት ድረስ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

👉 ትምህርት ሚኒስቴር ለሪፖርተር ፥ " ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ላይ ለውጦች ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ባለፈ የምንለው ነገር የለም። የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ አይደለም የሲቪል ሰርቪስ ጉዳይም ነው "

ያንብቡ : telegra.ph/ETH-08-07-2

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ሰኞ መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላቹ! !!