ማያዬ ሚዲያ
130 subscribers
851 photos
50 videos
53 files
874 links
ጥበብ ደግሞ በንግግር ይገለፃል፣በቃላት ተውቦ ለጆሮ ተመጥኖ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ንግግር በግጥም፣በወግ፣በታሪክ…ሊገለፅ ይችላል፡፡
Download Telegram
#National_Exam_Result

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70,544 ወይም 12.8% የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 88 ትምህርት ቤቶች 100% ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁ ሲሆን፣ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ። ጥዋት እና ማታ ብቻ ለመታየት የሚወጡ የመንግድ ዳር ስካቫተሮች፣ ተው የሚል አካል ባለመኖሩ ውድ የሰው ህይወት አሳጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደገለጸው፣ አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡