Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹
39.7K subscribers
28.6K photos
195 videos
2.02K files
9.85K links
ሕክምና፣ መረጃ፣ ሥራ ቅጥር፣ የትም/ት ዕድል መረጃዎች ላይ የሚያተኩር ቻነል ነው።
መፍትሔው አለን!
Contact፡ @tenamereja1

📱 0974512131

Facebook: facebook.com/tenamereja
🌿 ለማስታወቂያ- Advert your services
0974512131
@tenamereja1
Download Telegram
#የኮንትራት #ቅጥር #ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱ የክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ባለሙያዎችን በማቺንግ ፈንድ በጀት በኮንትራት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ፡፡

ዝርዝሩን ከማስታወቂያው ይመልከቱ ፡፡
እንደ ሀገር የተነሱ የህክምና ባለሞያዎችን ጥያቄ ወደ ግለሰብ ማውረድ በራሱ በድሬዳዋ ጤና ሴክተር ላይ ተቋማዊ አመኔታ እንዳያሳጣ ነገሮች በጥንቃቄ ቢታዩ

ከሰሞኑን እንደ ሀገር የተነሱ የህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ ዶ/ር ሐብታሙ አለሙ እንደ አንድ የሕክምና ባለሞያ ከየትኛውም ፓለቲካ ውግንና በፀዳ መልኩ ጥያቄውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያስተጋባ ታዝበናል።

በተመሳሳይ ትላንትና ዛሬ ይህ የህክምና ባለሞያ ዶ/ር ሐብታሙ በዲሲፒሊን ችግር ከሚሰራበት ድሬዳዋ ሳቢያን ሆስፒታል ወደ ገጠር አካባቢ እንዲዘዋወር የሚያሳይ ደብዳቤ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ እየታዘብን ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚሰራጩ መልክቶች አጠቃላይ በሚል ደረጃ ዶ/ር ሐብታሙ መሰረታዊ የህክምና ባለሞያዎችን ጥያቄ ስላስተጋባ ወደ ገጠር እንዲዘዋወር በማድረግ የመቀጮ እርምጃ እንደተወሰደበት የሚያሳዩ መልክቶች የያዙ ናቸው።

የእኔ ጥያቄ ቅጣቱ ትክክል ነው አደለም ሳይሆን እውነት ደብዳቤው ላይ የተገለፀውና በዚህ ደረጃ የስብእና ችግር ያለበትን ዶ/ር ሐብታሙ ፈፅሞ ሊመጣልኝ አለመቻሉ ነው።

ቢሆን እንኳን በተገለፀው የዲሲፒሊን ችግር ከቦታው ቢነሳ እንዴት ደብዳቤው ላይ በተገለፀው ባህሪ ሌላ ቦታ ተመድቦ ሊሰራ ይችላል ?

ዶ/ር ሐብታሙ ድሬዳዋ ላይ በብዙ ለሀገር እና ለወገን በሚጠቅሙ መልካም ስራዎች የምናቀው ወጣት የህክምና ባለሞያ ነው። ዶ/ር በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት ላይ ጊዜውን ገንዘቡንና ጉልበቱን እንዲሁም እውቀቱን ለድሬዳዋ ሳይሰስት ሲሰጥ እንደመጣ ከደብዳቤው በተቃራኒ ያለውን ወገናዊ ስብእና ብዙዎች ይመሰክራሉ።

በግሌ ዶ/ር ሐብታሙ ድሬዳዋ ላይ በብዙ መልካም ስራዎቹ አቀዋለው። ከእጅግ መልካም ስራዎቹ አንዱ ድሬዳዋ ከተማ በከፍተኛ የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ውስጥ ወድቃ ከተማዋ በከፍተኛ የህክምና ባለሞያ እጥረት ተጨንቃ በቆዘመችበት ወቅት ዶ/ር ሐብታሙ ገና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ 4ኛ ዓመት የጤና ሳይንስ ተማሪ ነበር። ድሬዳዋ ላይ ስለተከሰተው የችኩንጉንያ ወረርሽኝና በገጠማት የህክምና ባለሞያ እጥረት ምክንያት ነፍሰ ጡር እናቶች ሳይቀር ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉ አወጋውት። በወቅቱ ሀሳቤን በመቀበል ከወንድማችን ዶ/ር ሚካኤል ሸዋል ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ እና ሐረር አለማያ አካባቢ ድሬዳዋ ያስተማረቻቸውን ከ50 በላይ የህክምና ባለሞያዎች አስተባብረው ወደ ድሬዳዋ በማምጣት የበጎ ፍቃድ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

ዶ/ር ሐብታሙ በህክምና ዘርፍ ተመርቆ ድሬዳዋ ከመጣ ማግስት በግሉ ሲሰራ ከምናቃቸው በጎ አድራጎቶች በዘለለ ላለፉት 8 አመት ላሳልያን በጎ አድራጎት ማህበርን ከጓደኞቹ ጋር በማቋቋም ለተከታታይ አመታት ህፃናት ተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁስ በሟሟላት ወደ ትምህርት ቤት ይልካሉ። ድሬዳዋ ላይ በየአመቱ ጎበዝ መምህራኖችን ድጋፍ እያፈላለጉ የአመቱ ምርጥ መምህር በማለት ይሸልማሉ። እሱ የመሰረተው ላሳልያን በጎ አድራጎት ማህበር በኮቪድ ወቅት የተጫወተውን መልካም ተግባር በድሬዳዋ ጤና ቢሮ የተመሰከረለት ነው። በተጨማሪ የድሬዳዋን ማህበረሰብ በማስተባበር በየስድስት ወሩ ደም ይለግሳሉ። ዶ/ር ሐብታሙ ሳቢያን ሆስፒታል መስራት ከጀመረ ወዲህ የሆስፒታሉን መልካም ገፅታ ከመገንባት ጀምሮ ነዋሪው የጤና መድን እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እታዘባለው።

ይህ ለአመታት ያልተቋረጠ፣ በስራና በስራ ብቻ የተመዘነ መልካም ወገናዊ ስብእና ያለውን ሰው የድሬዳዋ ጤና ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ላይ ያለውን ዶ/ር ሐብታሙ ፈፅሞ ሊገልፅልኝ አልቻለም።

ታዲያ እንዲህ ያሉ ሀገርን በተግባር የሚወዱ ወጣት የሕክምና ባለሞያዎችን ወደ ራስ በማቅረብ የበለጠ ሀገር እና ወገናቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ የተፈጠሩ ችግሮችን ተቀራርቦ በውይይት መፍታት ቢቻል እመክራለው።

Dr. Habtamu Alemu  ከቃል በላይ ለሆነህ አገልግሎትህ ድሬዳዋ ታመሰግንሀለች !

በቃሉ ምስጋናው (በቃል ድሬ)

@tenamereja
Call_for_Applications_Biomanufacturing_Fellowship_Programme_Final.pdf
2.4 MB
🌍 Apply NOW to Africa CDC's Biomanufacturing Fellowship Programme!

Launched under the Platform for Harmonized African Health Products Manufacturing (hashtag#PHAHM), this programme supports a bold continental vision to scale up local production of vaccines, diagnostics, and therapeutics—essential for building resilient health systems and reducing Africa’s reliance on external supply.
#AFRICACDC
@TENAMEREJA
Forwarded from Medical Info Ad
CPD
#ከታላቅ ቅናሽ ጋር #የሞያ_ፈቃድ_ለማሳደስ_CPD_ይመዝገቡ   (CPD_አሁን_ይመዝገቡ)

  አስደሳች ዜና #የሙያ ፍቃዳችሁን ላላሳደሳችሁ የጤና  ባለሙያዎች በሙሉ

CPD Online ይሰልጥኑ አሁን ይደውሉ ይመዝግቡ   ወይንም  በቴሌግራም ይመዝገቡ
                 Telegram :- @infocpd
                  Call :- +251974059645
                     
*** ማሳሰቢያ  ተመሳሳይ ስለሚኖር  የ እኛ  በጣም ቅናሹ ኪሰዎን የሚያጎድ የ እኛ ነው !!
         (Benefit  packages)
15 CEU =400 BIRR
30 CEU=600  BIRR
45 CEU=800 BIRR
60 CEU=1000 BIRR
           
Online CPD TRAINING (All Health Department )

ባሉበት ቦታ ሆነው ስልጠናውን ይውሰዱ ፡ ሰርትፌኬትዎን ባሉበት ቦታ ይቀበሉ
             
               ከ ሌሎች ልዩነታችን
👌 1ኛ  ልዩ የሚያደርገን እውቅና ያለን

    በጤና ሚንስቴር ብቸኛ እና እውቅና ያለው  የ CPD ስልጠናዎች የሚቀርቡበበት  ዌብሳይት እንደሆን ያውቃሉ።

        All department (ሁሉም ድፓርትመንት)
1. GP    
2. HO  
3. Ansthetsia 
4. Nurse
5. Midwifry  
6.Pharmacy 
7. Labratory
8, others health professional

      Registration - Ongoing
ስልጠናውን በተመቾት ጊዜ ይውሰዱ፤ የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ።

👌 2ኛ ልዩ የሚደርገን በታማኝነት ድጋፍ ምክር መስጠት
  ሁሌም ምዝገባ ሁሌም ስልጠና አለ
ለስልጠና ብለዉ ጊዜ ገንዘብዎን  አያባክኑ።ባሉበት  ሆነው የሚፈልጉትን  CEU ነጥቦች እንዲያሟሉ እናግዛለን

    ለበለጠ መረጃ እና ቲክኒካል ድጋፍ

            ባሉበት ሆነው  አሁን ይደውሉ
*** 👉 ትክክለኛው ስልክ ቁጥር ይሄ ብቻ ነው!!
📱 +251974059645

እና በ ቴሌግራም  ያናግሩን
  👉 @Infocpd

ቲሌግራም ግሩፕ ለመቀላቀል
👉https://t.me/infocpdonlinetraining
Forwarded from Agmasu
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Basic Step and one minute workflow to get automatic Proforma at www.newtonmedical.et


CBC | Chemistry | Ultrasound | OR Light | OR Table | Suction Machine


📞0975989927
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
“ በሙያው ጠቅላላ ሀኪም ነው ቤተሰብ ለመጠየቅ እየሄደ ነው በጥይት ተመትቶ የተገደለው ” - የሟች ጓደኛ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መራቢቴ ወረዳ በእናት ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሀኪሙ “በተተኮሰበት ጥይት” መገደሉን የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ዶክተር ገብረሚካኤል ወልደ መላክ ተገደለ የተባለው ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ በመኪና እየተጓዘ መራቢቴ አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡን የሟች ጓደኛ፣ “ ቤተሰብ ለመጠየቅ እየሄደ ባለበት ነው በጥይት ተመትቶ የተገደለው። ትላንት ጠዋት 3 ሰዓት ነው የተገደለው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌሎች የቅርብ ሰዎቹ በበኩላቸው፣ “ እናት ሆስፒታል ነበር ተቀጥሮ የሚሰራው። መንገድ ላይ መኪና ውስጥ ሆኖ ነው የተተኮሰበት ሰው ሲደርስ ሞቶ ነው ተገኘ ” ብለዋል።

የሙያ አጋሮቹ፣ “ ሕይወት የሚያድን ሀኪም ለዚያውም በጥይት እንዴት ሕይወቱ ባጭር እንዲቀጭ ይፈረድበታል ? እኛም ከፍተኛ ስጋት አለብን ” ሲሉ ሀዘነንና ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን እንዳልታወቀ፣ የቀብር ሥርዓቱ የሚፈጸመው ዛሬ እንደሆነ ተመልክቷል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ፣ ዶክተር ገብረ ሚካኤል በ2015 ዓ/ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀና ገና ወጣት ሀኪም ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
እጣ ፈንታዬ ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያ እውነተኛ እጣ ፈንታችን ምን ይሁን?ይህንን ጥያቄ ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲመልስልን በአክብሮት እጠይቃለሁ ።
ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ ?
ዶ/ር ባንቴ እባላለሁ የህጻናት ህክምና ረዚደንት ነኝ ። በጠቅላላ ሐኪምነት ከ6 ዓመት በላይ አገልግያለሁ። አሁን ደግሞ በኢ/ያ ውስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በአንዱ የህጻናት ህክምና ረዚደንት ነኝ
በህክምናው አለም የገጠመኝን እና ያለንበትን እውነተኛ ሁኔታ በቅንነት ለሚረዳው የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀው ዘንድ ለማጋራት ወደድሁና በትግስት እንድታነቧት እጋብዛለሁ ።
እኔም እንደ አብዛው የሀገራችን የጤና ባለሙያ በገጠር አካባቢ ያለች በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ በምትገኝ ትንሽዬ የገጠር ቀበሌ ተወልጄ ያደኩኝ ሲሆን ከ1_4 ክፍል አንድ ት/ቤት ገባሁና በጥሩ ውጤት double ጭምር በማለፍ ከአጠናቀቅሁ በሗላ ወደሚቀጥለው 5_8ኛ ት/ት ቤት ተምሬ ሳጠናቅቅ high school እና preparatory ደግሞ ልየው አስረስ ዘዉዴ በሚባል እንቁ ተወላጅ በአሰሩልን ት/ት ቤት 4 አመት ተምሬ አጠናቀቅሁኝ ።11ኛ እና 12ኛ ክፍል ከት/ት ቤት ጎበዝ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ በመሆን የበትረ ጻድቅ ካሳ ሀገር በቀል ስኮላርሽፕ ተጠቃሚ ነበርኩኝ (በወር100 ብር እየተከፈለኝ ለ2ዓመት ተማርኩ)
በመቀጠልም እውነት መስሎኝ ህክምና እንቁ ሙያ ነው ቤተሰብ ህዝብ ይረዳበታል የተቸገረን ይረዳበታል ራስንም ያኖሩበታል ብዬ ወደ አንዱ የኢ/ያ ዩኒቨርስቲ ገባሁና አየሁት አይ ህክምና አይ ስቃይ ያየሽ ብቻ ይመስክር።ምንም አይነት እረፍት የሌለው በጋሪ የማይሔድ መጽሐፍ ለመጨረስ ሌት ከቀን ስንወጣ ስንወርድ የሚገባው(ባ ላልቶ) ስናሳዝነው ሌላው ደግሞ ሙድ ሲይዝ አንዳንዱ ደግሞ አበዱ ሲለን መቸም አለቀ::ያ 7 አመት ስቃይ መከራ እንግልት ሰቆቃ አለቀና አሁን እንደሰው ልንኖር ነው ብለን ተመረቅን (በተግባር ተረገምን ለዚያውም በጽኑ)
ከዚህም በመቀጠል በጠቅላላ ሐኪም ሙያ ሳገለግል ቤተሰብ መሰረትኩና የልጅ አባት መሆን መጣ ። የጠቅላላ ሐኪም ደመወዝ 9056,ስፔሻሊስት 11,000 አካባቢ መሆኑን ስረዳ ስፔሻሊቲ መማርን ተውኩት ሰረዝኩት ም/ም ይህንን ሁሉ ስቃይ አይቸ ተምሬ ቤተሰቤን የማላስተዳድርና መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ካልቻልኩ ለምን እማራለሁ ??የሚል ውሳኔ ወሰንኩ ።በነገራችን ላይ በአሁኑ ሰዓት አንድ ስፔሻሊስት ሐኪም የሚቀጠረው 12,765ብር ሲሆን የሚደርሰው ደግሞ 8903 ብር ነው ት/ት ሲጀምር የሚፈርመው cost sharing ደግሞ ከ500,000_700,000ብር ነው ይህ ማለት ይህንን ብር ለመክፈል ከደመወዙ አምስት ሳንቲም ሳይነካ ቢያጠራቅም እዳውን ለመክፈል ከ7 አመት ያላነሰ ይፈጅበታል ነገር ግን የእለት ፋላጎቱን እየተጠቀመ ከሆነ ግን ግዴታውን እስኪጨርስ ድረስ ይማቅቃታል እንጅ መቼም ከፍሎ አይጨርስም።
ስለዚህ ከጠቅላላ ሐኪም ሙያ በተጨማሪ በትርፍ ሰዓቴ ቤተሰቤን የማስተዳድርበት ጎን ለጎን ስራ ለመስራት ወሰንኩ ነገር ግን ምን ልሰራ እችላለሁ የሚለውን ኢኮኖሚስት ጭምር አማከርኩኝና የተለያዩ ዘርፎችን አሰብኩ።
ከዶሮ እርባታ ጀምሮ የተለያዩ ብዙ መነሻ ገንዘብ የማይጠይቁትን ሞከርኩኝ በነገራችን ላይ የመጀመሪያው ዶሮ አርቢ ሐኪም እኔ ነኝ ይመስለኛል ።
እርሱም አላዋጣም ሌላ ጠንከር ያለ ቢዝነስም አሰብኩ business plan ሳይቀር አሰራሁ ነገር ግን መነሻ ብሩ ከየት ይምጣ ?እንኳን በመቶ ሺዎች ይቅርና ደመወዝ እንደገባ ከሳምንት በሗላ አንድ ሺ የሞላም አይገኝም ስለዚህ ምን ላድርግ? ብድር ከሰው ነውን ? እርሱም አልሆነም ብድር ከባንክ ነውን ? ምኔን አስይዤ እበደራለሁ?ከቤተሰብ ነውን?በዚህ ሰዓት ቤተሰብ እንኳን ያስተማረበትን ውለታ የሚያገኝበት እንጂ እንደገና እርዳታ የሚጠየቅበት አልነበረም ሆኖም ግን የገጠር ድሀ ማህበረሰብ ከየት ሊያመጣ ይችላል።የመጨረሻ አማራጭ በጋራ አዋጥተን አስር ሆነን 350,000 ብር የሚደርስ እቁብ ገባን ያ እቁብም ሊደርሰን አልቻለም ለመግዛትም አልተገኘም ። የጀመርነው ቢዝነስም መንቀሳቀሻው ሲቀር ኪሳራ ሲሆን ዘጋነው ።
ስለዚህ 6 ዓመት አየሁትና አማራጭ ሳጣ ቢያንሰ ረዚደንሲ እየተማርኩኝ ልቆይ ይሆን ብዬ እንደገና ሀሳቤን ቀየርኩኝ።
ይህንንም ያሰብኩት ስፔሻሊስት ስሆን ኑሮየን ያሻሽልልኛል ብዬ አይደለም በተሻለ ሙያ ደረጃ ህዝብ አገለግላለሁ ብዬም አይደለም መጀመሪያ ራስን መያዝ ያስፈልጋልና።12,765ብር ምን ሊያደርግ እንደሚችል ፍርዱን ለእናንተ ልተወው።በጠቅላላ ሐኪም ሁሌ ፋታ በሌለበት ስራ በዚህ ቤተሰብ በማይመራ ክፍያ እጣ ፈንታዬ ምን ይሆናል? ብዬ ሳስብ ተጨነቅሁ ተወዛገብኩ በመጨረሻም ቢያንስ ት/ት እየተማርኩኝ ልቆይ ይሆን ብዬ እየተወዛገብኩና ግራ እየተጋባሁ እውነት ለመናገር ምንም ሳላነብ ተፈተንኩኝ ።ሆኖም ሁለቱንም ፈተና አለፍኩኝና ጭንቀትና ውዝግቡ አሁንም ጨመረብኝ ም/ም ቤተሰቤን ትቼ ነው ወይስ ይዤ የምሔደው?ቤተሰብ ተይዞ በዚህ ኑሮ ውድነት ትልቅ ከተማ ላይማ ከባድ ነው ደመወዝ ለቤት ኪራይ ብቻ ሆና ትቀራለች። ስለዚህ ዘንድሮ ይለፈኝና ቀጣይ ልማር ይሆን አልኩኝ ተጨነኩኝ ሆኖም ይህንን ጭንቀት የሚያውቅ የቅርብ ቤተሰብ እድልህን አታሳልፍ ቤተሰብን እኛም አለን የምትችለውን ከአንተ የምትተርፈውን ታግዘናለህ ሲለኝ መግደርደርም ሆነ ማቅማማት አልፈለኩም እና ለመማር ወስኜ ዩኒቨርስቲ ገባሁ።
ስገባ እዚያም እንደገና አዲስ ችግር ሆነ የዶርም ውድነት በአጠቃላይ የኑሮ ውድነት የሚገዙ በጣም ብዙ ጥቃቅን ነገሮችን ስንል አልሆነም ስለዚህ አንድ ጓደኛዬ ጋር ለምን አንድ ዶርም በጋራ አንይዝም ብለን ተነጋገርንና በጋራ ይዘን መኖር ጀምረናል።ያም ሆኖ የምንኖረውን ኑሮ እኛ እና እግዚአብሔር ብቻ እናውቀዋለን ።
በነገራችን ላይ የምጽፈው ጥቂት ጥቂቱን የሚነገረውን እና ቢያወሩት የሞራት ጉዳት በከፋ ሁኔታ የማያመጣውን ብቻ መሆኑን ያዙልኝ።
ይህ ብቻ አይደለም የጤና ባለሙያው በሙያው ተጋላጭነት ምክንያት ለብዙ በሽታ ተጠቂ ነው ።ይህንንም በሀገራችን በተለያየ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት
Read More


@tenamereja
አንድ ባለሙያ በሦስት ሺፍት (ፈረቃ) 36 ሰዓት ይሠራል። በቂ ክፍያ ግን እየተከፈለን አይደለም። የኑሮ ውድነቱ በጣም እየጨመረ ነው፣ አንድ የህክምና ዶክተር የተጣራ ደመወዙ 9,000 ብር ነው፣ አንድ ስፔሺያሊስት 11300 የወር ደመወዝ ይከፈለዋል፤ ስለዚህ ደመወዙ በቂ አይደለም! - DW
@tenamereja
«ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየታየ ነው» ጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና የጤና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ጉዳዩን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው እየተመለከተው እንደሆነ ገልጠዋል፡፡ የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች ለጥያቄዎች ትክክለኛና እውቅና እንደሚሰጡ ያመለከቱት ዶ/ር ተገኔ፤ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዳዮች እየታዩ እንደሆነና፤ ጥያቄዎቹ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚፈቱ እንደሚሆኑም አስረድተዋል። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የሥራ ፈጠራ የሚበረታታበት፣ የትምህርት እድሎች የሚመቻቹበት፣ ዝውውርና የደረጃ እድገት የሚታዩ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩንም ሚኒስትሯ በቅርበት እንደሚከታተሉት አብራርተዋል፡፡

በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የጤና አገልግሎት አዋጅ 1363/17 መሠረት የጤና ባለሙያውና ሠራተኛው በሥራ አጋጣሚ ለሚደርስበት ህመምና የጤና ችግር ተጋላጭነት ነፃና ቅድሚያ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የአፈፃፀም መመሪያዎችና ደንቦች እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጭምር እየታዬ በመሆኑ የጤና ባለሙየዎች ጥያቄያቸውን ሥርዓት ባለው ሁኔታ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዶ/ር ተገኔ፣ ባለሙያዎቹ ሲመረቁ የገቡትን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ለህሙማን የሙያ ስነምግባር በተከተለ መንገድ አገልግሎት ይሰጣሉ የሚል እምነት እንዳላቸው እንጂ ለጥያቄዎቻቸው ትኩረት ተሰጥቶ ባለበት ሁኔታ ባለሙያዎቹ ሥራ ያቆማሉ የሚል ግንዛቤ እንደሌላቸው ነው ዶ/ር ተገኔ የተናገሩት፡፡

@tenamereja