Telebirr
277 subscribers
59 photos
2 files
10 links
Download Telegram
Forwarded from telebirr
በአገልግሎቱ ከዚህ ቀደም ደንበኞችን በድምፅና በተወሰኑ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በተናጠል ያስተናግዱ የነበሩ የጥሪ ማዕከሎችን አሰራር ያዘመነና በልዩ ልዩ አማራጮች ማለትም በድምጽ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፣ በኢሜል፣ በድረ-ገጽ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ እንዲሁም ቻትቦትን (Chatbot) በመጠቀም የሚቀርቡ የደንበኞች ጥያቄያዎችን በአንድ ላይ አቀናጅቶ ለደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎች ማቅረብ በማስቻሉ ቀልጣፋና ተደራሽ የደንበኞች አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል፡፡

ድርጅቶች እና ተቋማትም ይህን አገልግሎት ተጠቅመው የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሳለጥ ብሎም የደንበኞቻቸውን ተሞክሮ እና እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ የሚችሉበት ትልቅ እድል በመሆኑ አብራችሁን ለመስራት ፍላጎቱ ያላችሁ ድርጅቶች እና ተቋማት በድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!
ለተጨማሪ መረጃ፡ bit.ly/3gksBRi

#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
Forwarded from telebirr
ኩባንያችን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለጉዳዮች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ለሚያገኟቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር በመጠቀም ለመፈጸም የሚያስችል አሰራር በዛሬው ዕለት ተግባራዊ አደረገ!
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለጉዳዮች በድረ ገጽ www.etrade.gov.et ላይ ለሚያገኟቸው የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ስያሜ እንዲሁም ተያያዥ አገልግሎቶች በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆነው አገልግሎት በማግኘት እና ክፍያቸውን በቴሌብር በመፈጸም ውጣውረዳቸውን ማስቀረት እና ውድ ጊዜያቸውን መቆጠብ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡
ይህ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ በሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ 4.8 ሚሊየን ብር የአገልግሎት ክፍያ ለ38 ሺህ አገልግሎቶች ተፈጽሞበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3TQz7xW
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
Forwarded from telebirr
ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ የሚያዘምን እና የሚያሳልጥ፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ የመረጃ ክምችት እና አጠቃቀም እንዲሁም ተዛማች የክላውድ አገልግሎት ፍላጎት የሚያሟላ የቴሌ ክላውድ አገልግሎትን ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምሯል።

የቴሌክላውድ ኮምፒዩቲንግ አገልግሎቶች በሶስት አማራጮች የቀረበ ሲሆን Infrastructure as a Service (IaaS) መረጃዎቻቸውን ማስቀመጥ፣ መቀመር የሚያስችል የክላውድ መሰረተ ልማት፣ Platform as a Service (PaaS)- የሶፍትዌር አልሚዎች ካሉበት ሆነው ላበለፀጓቸው ሶፍትዌሮች የተሟላ የዳታቤዝ ማኔጅመንት ሲስተም (MySQL DB) የሚያገኙበት እና Software as a Service (SaaS)- በውጭ ምንዛሪ የላይሰንስ ክፍያ ሳይከፍሉ ሶፍትዌሮችን ከቴሌክላውድ በተመጣጣኝ ክፍያ በብር ማግኘት የሚችሉበት አገልግሎቶች ናቸው።

ቴሌክላውድ አገልግሎትን በድረ-ገጻችን https://telecloud.ethiotelecom.et ማግኘት የሚቻል ሲሆን ክፍያውንም ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነው ቴሌብር ካሉበት በመክፈል ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3Wa7eCI
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ