ትኩስ መረጃ
2.41K subscribers
5.81K photos
350 videos
1 file
4.33K links
Download Telegram
ኢዜማ፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን በንጹሃን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት መንግሥት አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ኃላፊነት የሚወስዱ አካላትን በመለየት "ሕጋዊ የእርምት እርምጃ" እንዲወስድ ጠየቀ።

ፓርቲው፣ "ማንነትን" ወይም "ኃይማኖትን" መሠረት ባደረገ ጥቃት በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑ ዜጎች ለጊዜው "ማንነቱ ባልታወቀ" አካል እንደተገደሉ፣ ቤተክርስቲያን እንደተቃጠለና ከጥቃቱ የሸሹ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተሠደዱ መረዳቱን ገልጧል።

ለዚህ ዐይነቱ "ማንነትን መሠረት" ያደረገ ጥቃት ምንጬ የአገሪቱ ፖለቲካ "በማንነት ላይ የተመሠረተ" መኾኑ ነው ያለው ፓርቲው፣ በማንነት ላይ የተመሠረተው ፖለቲካ መፍትሔ እንዲበጀለት የኹሉም ባለድርሻ አካላት የቤት ሥራ መኾኑን አጽንዖት ሠጥቷል።

ኢዜማ፣ በምስራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ የአካባቢው አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተደጋጋሚ ተፈትነው ወድቀዋል በማለት ተችቷል።

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
👎1🔥1🥰1
ትኩስ መረጃ
Photo
🌍አጫጭር መረጃዎች
 
🇮🇷 ኢራን በአሜሪካ ለተፈጸመባት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ በሚል በኩዌት እና ባህሬን ላይ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከ6 ሀገራት ጋር መከሩ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ከፈረንሳይ፣ ቱርኪ፣ ኳታር፣ ግብፅ፣ ፓኪስታን እና ሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን በኤክስ ገጻቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡
 
 🇰🇼 የኩዌት ወታደራዊ ባለስልጣን የኢራን የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሀገራቸው ላይ ያደረሱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ያቆሰለ እና አለም አቀፍ አየር ማረፊያውን የጎዳ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ሳኡድ አብዱልአዚዝ አል-ኦታይቢ ጥቃቶቹ በአየር ማረፊያዉ ህንፃው ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳት ያደረሱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል ።
 
🇺🇸🇮🇷 የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የኢራን ባሊስቲክ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኩዌት እና ባህሬን ወደሚገኙት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸዉን ተከትሎ እራስን የመከላከል ጥቃት በሚል በሆርሙዝ ባህር ዳርቻ በሚገኘው የኢራን ቄሽም ደሴት ላይ የአጸፋ እርምጃ ማድረሱን አስታወቀ።
 
🇺🇸🇮🇷 የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ባህር አቅራቢያ የሚገኘውን የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በመምታት የኢንጂን ክፍሏን ጎድቷል ሲል አስታወቀ፡፡
 
🇦🇪 ኢራን በኩዌት፣ ባህሬን ላይ ጥቃት ካደረሰች በኋላ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ 'የባህረ ሰላጤው ሀገራት በአንድነት' እንዲቆሙ ጠየቀች።የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት አማካሪ አንዋር ጋርጋሽ በበኩላቸው የኢራን ተደጋጋሚ “ወረራ” በኩዌት እና ባህሬን ላይ ጠንካራ እና የተዋሃደ የባህረ ሰላጤ አቋም ይጠይቃል ብለዋል።

🇮🇷 ኢራን በአሜሪካ ለደረሰባት ጥቃት ኩዌት እና ባህሬን 'ቀጥታ ተጠያቂ ናቸው' አለች።ኢራን የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃቶች የተኩስ ማቆም ስምምነትን እና ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ኮንናዋለች፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኩዌት እና ባህሬን ለጥቃቱ “ቀጥታ እና ግልፅ ሃላፊነት አለባቸው” ሲል ግዛታቸው እና ተቋማቸዉ  ለአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ጥቅም ላይ ውሏል።
 
🇱🇧🇮🇱ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን በጢሮስ የሊባኖስ ሆስፒታል አቅራቢያ የደረሰዉን የእስራኤል ጥቃት አወገዘ፡፡እስራኤል በጢሮስ ደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት ቢያንስ አራት ሰዎችን የገደለ ሲሆን 127 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የእስራኤል ጥቃት "የህክምና ተልእኮውን የመጠበቅ ከባድ ውድቀት" በማለት አውግዘዋል።
 
 🇺🇸🇮🇱🇮🇷 አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የጀመሩት ጦርነት 96ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ግጭቱ በድጋሚ በባህረ ሰላጤው አካባቢ እየሰፋ ይገኛል፡፡
 
🇮🇱🇱🇧 የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ በምትገኝ ኻልዴህ ውስጥ ተሽከርካሪን መምታቱ ተሰምቷል፡፡ጥቃቱ የተፈፀመው ዋና ከተማውን ከደቡብ ሊባኖስ ጋር በሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና ላይ ሲሆን ከቤይሩት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ ነው። በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸዉ እስካሁን ግልጽ አይደለም፡፡
 
🇮🇷 የኢራን ታኒም የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ኢራናዊዉ የሕግ አውጭ ኢስሜል ኮውሳሪ አሜሪካውያን “ከኃይል እና ከኃይል ቋንቋ በስተቀር ምንም አይረዱም” ሲሉ የኢራን ጦር ኃይሎች አሜሪካን እንዲጋፈጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
👍1🥰1👏1
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ትራምፕን የጦርነት ስልጣን ለመገደብ የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ እንዳይወስዱ የሚያግድ የውሳኔ ሃሳብ በ215 ለ 208 ድምፅ ያጸደቀ ሲሆን፤ አራት የሪፐብሊካን አባላት ከዲሞክራቶች ጋር በመተባበር ያሳለፉት ይህ ውሳኔ በኮንግረሱ እና በዋይት ሃውስ መካከል ያለውን ፍጥጫ እንዲሁም በፓርቲው ውስጥ ያለውን ልዩነት ያሳየ ሆኗል።

የምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መሪ ግሬገሪ ሚክስ ውሳኔውን በትራምፕ ሕገ-ወጥ የኢራን ጦርነት ላይ የተሰነዘረ ጠንካራ ተግሳጽ ሲሉ የገለጹት ቢሆንም፣ የውሳኔ ሃሳቡ አሁንም በሪፐብሊካኖች በሚመራው ሴኔት መጽደቅ ያለበት በመሆኑና ከዚህ ቀደም መሰል ሙከራዎች ሳይሳኩ በመቅረታቸው፣ እርምጃው በየካቲት ወር የተጀመረውንና የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲዘጋ ምክንያት የሆነውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመግታት መቻሉ አጠራጣሪ መሆኑ ተመልክቷል።

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
👍31👏1🎉1
ትኩስ መረጃ
Photo
በአሪ ዞን የሞባይል ስልክ ለመስረቅ ባለንብረቱን ደረቱን በስለት ወግተው የገደሉት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
 
ተከሳሾቹ ባለንብረቱ ላይ አካላዊ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ደረቱን በስለት ወግተው ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል።ተከሳሾቹ አቶ ሀብታም  አውላ እና  ምስጋናው መስፍን የተባሉ ሲሆን ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ስዓት ላይ አርክሻ በተባለ  አካባቢ የወንጀል ድርጊቱን ፈፅመዋል።የግል ተበዳይ የአቶ አበበ በየነ ንብረት የሆነውን ቴክኖ ሞባይል ለመውሰድ ሲታገሉ በኃይል ይዘውት መሬት ላይ በመጣል ሁለተኛ ተከሳሽ እጁን በመጠምዘዝ ስልኩን ወስደዋል። በመቀጠልም  አንደኛ ተከሳሽ በያዘው ጩቤ ሟችን ደረቱ ላይ አንድ ጊዜ ወግቶ ጉዳት ያደረሰበት መሆኑ ተነግሯል ።
 
ይሁን እና ተጎጂው የህክምና እርዳታ ሲደረግለት ቢቆይም  ህይወቱ ማለፉን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት  አቶ የሱፍ አህመድ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ዓ/ህግ የኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1 ሀ እና 671/2ን ጠቅሶ ክስ  አቅርቦባቸዋል።ተከሳሾች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምንም ብለው ክደው ቢከራከሩም ዐቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃ  የወንጀሉን ድርጊት ስለመፈፀማቸው ከበቂ በላይ በሆነ ማሰረጃ  አስረድቷል።
 
ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ  ክሱን የመከላከል መብታቸውን ቢጠብቅላቸውም ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የዐ/ህግን የማሰረጃ ቃል ያላስተባበሉ በመሆናቸው ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ  ባቀረበባቸው ክስ መሰረት  የኢፌዲሪ ወንጀል ህግ  ጥፋተኛ ናቸው ብሏል።በተከሳሾች በኩል የቀረቡ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክኒያቶችን በመቀበል ከመነሻው እርከን ዝቅ በማለት በእርከን 42 ስር ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአሪ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾችን እና መሰሎቻቸውን ያርማል ያስተምራል በማለት  እያንዳንዳቸው በ22 ዓመት ፅኑ እስራት  እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉን አቶ የሱፍ አህመድ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
 
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👍1🤩1
በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት ለምርጫ ገለጸ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (CECOE / ኅብረት ለምርጫ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርቱ፣ በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ ከአንድ እስከ 10 የሚሆኑ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ገለጸ።

እንዲሁም በስምንት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሳይገኝ እና የመራጭነት ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ መፈቀዱንም ኅብረቱ በምርጫ ትዝብት ጊዜያዊ ሪፖርቱ ላይ አስታውቋል።

ኅብረቱ ከታዘባቸው 2,506 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ2,458 ጣቢያዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት የተከለከለ ሰው እንዳልነበር መታዘቡን ጠቅሷል፤ ይሁንና በ46 የድምጽ መስጫ  ጣቢያዎች  ከ1 እስከ 10 ግለሰቦች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸው ተገልጿል።

በሁለት ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸውን የኅብረቱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👎1💩1
አትሌት ይሄይስ ታደለው ከሌላ አትሌት በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉ ተሰማ

የዚህ ግድያ ፈፃሚ የሆነው እና ስሙ በህግ አካላት በኩል በይፋ ያልተገለጸው ሌላኛው አትሌት ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ ወዲያውኑ ከስፍራው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ታውቋል

#ዳጉ_ጆርናል

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👍1🤩1
የአርሲውን ጥቃት ተከትሎ ክልሉ የሰጠው መግለጫ‼️👇
"የአርሲው ጥቃት ምርጫውን ለማደናቀፍ በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው" የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ።
በጥቃቱ ከዚህም በላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህዝቡና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል። አሸባሪው ሸኔ ይህንን ጥቃት ያደረሰው ከታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብሎ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት የነበረ ቢሆንም በህዝቡ አስተዋይነት ከሽፏል ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አዩዘሀበሻ

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
👍2🔥1🤩1
የጠለታ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ‼️👇
የአርሲውን ጥቃት ተከትሎ ከትናንት በስተያ ግንቦት 25 ሪጴ ሎላ የሚባለዉ መጠነኛ ሀይል ተንቀሳቅሶ ነበር።
ጥቃት ወደተፈፀመበት ቦታ ሳይሄዱ በአቅራቢያው በሬ ታርዶለቸዉ ከትናንት ጀምሮ በመብላት ለይ ናቸዉ ብለዋል። ዉድመት ወደ ደረሰበት ቦታ ጠለታ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፣መከላከያ ሰራዊት ወደስፍራው ለመንቀሳቀስ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ወደ ጠለታ የሚወስደው መንገድ በመበላሸቱ ተመልሰው ቅርብ ቦታ እንዲቀመጡ ተደርገዋል ብለዋል።
ከደጋማው ቦታ ገበሬው ለእገዛ መቶ የነበረ ቢሆንም ሪጴዉ መከልከሉን ገልፀውልናል።
ዋንኛው ገበሬው እንዲሁም የአካባቢው ሚሊሻ የተቸገረው ተተኳሽ ነው ብለዋል።
ታጣቂዎቹ ከበርካታ የዞኑ ወረዳ ተውጣጥተው መጥተው ነው ብዛት ሆነው ድንገት ጥቃቱን የከፈቱት ብለዋል።
የአብዛኞቹ ቀብር ተፈፅሟል፣ሁለት ስዎች ያተነሱ አሉ እንደዚሁም አደራሻችዉ የጠፉም ሰዎች አሉ ብለውናል።
ታጣቂዎቹ እስከትናንት ግንቦት 26 መሳሪያዎችን አጥምደው እዛው ጥቃት እየተፈፀመበት አካባቢ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ለሊቱን(ለግንቦት 27 አጥቢያ) ወደ ቆላው መውረዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
(አዩዘሀበሻ)
==================

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
🤩2👍1🔥1
ትኩስ መረጃ
Photo
ኤርትራ ተመረጠች‼️
ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በ85ኛው መደበኛ ስብሰባው ላይ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ ቁልፍ አጀንዳዎችን የተወያየ ሲሆን፣ በስብሰባውም ለድርጅቱ 81ኛ ጠቅላላ ጉባኤ መሪ የሚሆኑትን አካላት መርጧል።

በዚህም መሰረት የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኤርትራ የከፍተኛ አባል ሀገራትን ድምጽ በማግኘት ከጠቅላላ ጉባኤው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዷ ሆናለች።

ኤርትራ ከተመረጡ ሌሎች 16 አገራት ጋር በመሆን የጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ አባላትን (ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ) በመቀላቀል የጠቅላላ ጉባኤውን ቢሮ በጋራ ትመራለች።

በተጨማሪም ከእሷ ጋር እንደ አፍጋኒስታን፣ ፊንላንድ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ፓራጓይ እና ዚምባብዌ ያሉ ሀገራትም በምክትል ፕሬዝዳንትነት መመረጣቸውን ለመረዳት ተችሏል

በተመሳሳይ ዕለት በምስጢር በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት፣ የወቅቱ የባንግላዲሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካሊሉር ራህማን የ81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል

ሚስተር ራህማን 99 ድምጽ በማግኘት የተመረጡ ሲሆን፣ ተፎካካሪያቸውን የቆጵሮሱን አንድሪያስ ካኩሪስን በ91 ድምጽ አሸንፈዋል። በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሥራቸውን በይፋ የሚረከቡት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ካሊሉር ራህማን ከአሸናፊነታቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ወቅት ከባድ የፋይናንስ ቀውስ እና ዓለም አቀፍ የእምነት ማጣት ጉድለት እየገጠመው መሆኑን ጠቅሰው፣ አባል ሀገራቱ ድርጅቱ መለወጥና የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በተግባር ማሳየት እንዳለባቸውና በየብስ የሚደረገውን እያንዳንዱን አስተዋጽኦ ውጤታማ በማድረግ የጠፋውን እምነት መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👍1🤩1
ትኩስ መረጃ
Photo
አዲስ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል-ህወሓት‼️
ሕወሃት አዲስ አውዳሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ። ህውሃት ከፊታችን አውዳሚ ጦርነት እየመጣ ይገኛል አስወግዱ ሲል ለአለማቀፍ ማህብረሰብ ባሰራጨው ደብዳቤ፣ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል።
በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ድርጅቱ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም "ሊቀረፍ የማይችልና አውዳሚ ጦርነትን ለመከላከል የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ" በሚል ርዕስ ለዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች እና ለዓለም አቀፍ አጋሮች ባሰራጨው የዲፕሎማሲያዊ ማስታወሻ ሀገሪቱ ወደ አዲስ የትጥቅ ግጭት እያመራች መሆኑን አስጠንቅቋል።
እንደ ሕወሃት መግለጫ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የውይይት እና የስምምነት መንፈስ እየጠፋ በመምጣቱ በእርሱ ፋንታ "የአንድ ወገን ውሳኔ፣ ማስገደድ እና ወታደራዊ የኃይል እርምጃ" ፖሊሲዎች እየነገሱ መጥተዋል ብሏል። ይህ አካሄድ መቀጠሉ ደግሞ ዳግም የትጥቅ ግጭት መከሰቱ የማይቀሬ እንዲሆን እያደረገው ነው ብሏል።
ይህ ሊቀሰቀስ የሚችለው ጦርነት በኢትዮጵያ ድንበር ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር የጠቆመው መግለጫው በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀጣናዊ ውጥረት እና ለጎረቤት ሀገራት የሚታየውን የጠብ አጫሪነት ዝንባሌ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ግጭቱ አጠቃላይ ቀጣናውን ሊያናጋና ሰብዓዊ ቀውሱን ሊያባብስ እንደሚችል አመልክቷል። የፌዴራል መንግሥቱ "ግትር አቋም" ይዟል ሲል የወቀሰው ሕወሃት፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ግን አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።

ከሰሞኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትግራይ ወጣቶች ወደ ወታደራዊ የስልጠና ካምፖች መግባታቸውን ሪፖርቶች በተሰሙበት በዚህ ወቅት የወጣው መግለጫ ጨምሮም "ማንኛውም ማህበረሰብ ሊሸከመው የሚችለው የጽናት ገደብ አለው" በሚል በትግራይ ላይ ያለው ጫና መጥበቁን የገለጸው ድርጅቱ፣ ቢሆንም ግን ብቸኛው አማራጭ መንገድ የፖለቲካ ውይይት መሆኑን በጽኑ እንደሚያምን አስታውቋል።
በመጨረሻም ሕወሃት የችግሩን ስር የሰደዱ መንስኤዎች ለመፍታት እንዲቻል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመራና የሚደገፍ ታማኝ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመርና ለዚህም ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው ገልጿል።
===================

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👍1🤔1
ትኩስ መረጃ
Photo
ኢትዮጵያና አይ ኤም ኤፍ (አይኤምኤፍ) የ468 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደረሱ‼️

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተራዘመው የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አምስተኛ ግምገማ ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሙሉ በሙሉ ሲጸድቅ፣ ኢትዮጵያ የ468 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ያደርጋታል።

ይህም ሀገሪቱ በ4 ዓመታት ውስጥ ከምታገኘው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ እስካሁን የተለቀቀላትን የገንዘብ መጠን ወደ 2.65 ቢሊዮን ዶላር ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ ስምምነቱ ሊደረስ የተቻለው ከአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የድርጅቱ ልዑክ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባደረገው የሁለት ሳምንታት ጉብኝትና ተከታታይ የሥራ ውይይቶች ማጠናቀቂያ ላይ ነው።

በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለጫ ላይ እንደተመለከተው ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከቀጠናዊ ቀውሶች ጋር ተያይዞ የመጣውን ትልቅ ውጫዊ ጫና በመቋቋም ረገድ ከፍተኛ ጥንካሬ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ፣ ዓለም አቀፋዊ አለመረጋጋትና የሸቀጦች ዋጋ መዋዠቅ አሁንም እያደገ በመምጣቱ በኢኮኖሚው የወደፊት ጉዞ ላይ የሚታዩት ስጋቶች መጨመራቸውን አይ ኤም ኤፍ አስጠንቅቋል


ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
👍21👏1
ትኩስ መረጃ
Photo
ወደኋላ አስር አመት‼️
ማንኛውም ደረሰኝ ሳይቆርጥ የተገበያየ አካል በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርሰው የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቁ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ለ10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳቡን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ ነው፡፡

ዛሬ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ የግብር አስተዳደር አዋጅ በተለይ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚደረግ ግብይት ላይ ከፍ ያለ ቅጣትን የሚያስከትሉ አንቀፆችን የያዘ ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ህጋዊ ደረሰኝ ያልሰጠ እንደሆነ በእያንዳንዱ ባልሰጠው ደረሰኝ ልክ 100 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በገንዘብ ይቀጣል ይላል የማሻሽያ አዋጁ ማብራሪያ፡፡

በተጨማሪ ይሄንኑ አስተዳደራዊ ቅጣት በዓመት ሁለት ጊዜ የተቀጣ እንደሆነ እና ሆን ብሎ ድርጊቱን መፈፀሙን ከቀጠለ ድርጊቱ እንደ ወንጀል ጥፋት ተቀጥሮ በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑም ተብራርቷል፡፡

በተጠቀሰው ድርጊት የድርጅት ስራ አስኪያጅ በግል በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው በወንጀሉ ተግባር ተባባሪ ከሆነ ወይንም ደረሰኝ ያለመስጠትን መከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት ያልዘረጋ ከሆነ እንዲሆንም ተደንግጓል፡፡

በሌላ በኩል አንድ ግብር ከፋይ ግብር ከከፈለ በኋላ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ በማንኛው ጊዜ እንደገና ሂሳቡ ተመርምሮ ወይም በኦዲት ተጨማሪ ግብር ሊጠየቅ ይችላል ይላል የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፡፡

ይህም በ10 ዓመት የተገደበው በኢትዮጵያ የንግድ ህግና የሂሳብ አያያዝ ህጎች መሰረት የሂሳብ ሰነዶች ተጠብቀው መቆየት ያለባቸው ለ10 ዓመታት ብቻ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ሌላው የታክስ አስተዳደር አዋጁ ማሻሻያ የያዘው አዲስ ነገር በታክስ ባለስልጣኑ እና በታክስ ከፋዩ መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት መፍቻ ዘዴን ይመለከታል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ህግ ግብር ከፋዮች የተጣለባቸውን ግብር ተገቢ አይደለም ብለው ባመኑ ጊዜ መፍትሄ ፍለጋ በታክስ አስተዳደሩ ስር ለተቋቋመ የቅሬታ ሰሚ ፣ ለግብር ይግባኝ ኮሚሽን እና የህግ ትርጉምን በተመለከተ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች እንዲመለከቱት የሚያስችል ስርዓት ነበር፡፡

ይህን ለማድረግ ግን ግብር ከፋዮች ቅድሚያ የተወሰነባቸውን ግብር ከ50 እስከ 75 በመቶ መክፈልም ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ያም ሆኖ መፍትሄ ለማግኘት ረዥም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በማብራሪያው ተጠቅሷል፡፡

በተሻሻለውና በረቂቅ ደረጃ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቀረበው የታክስ አስተዳደር አዋጅ የተጠቀሰው አሰራር እንዳለ ሆኖ በአጭር ጊዜ አለመግባባቶችን ለመፍታት ያግዛል የተባለ የገለልተኛ አስማሚን አሰራር ስራ ላይ ያውላል ተብለዋል፡፡

ይህም አዲስ “የመስማማት ሥርዓት” በሚል አዋጁ እንዲዘረጋ በሚፈቅደው ገለልተኛ አስማሚ ግብር ከፋዩን እና ግብር ሰብሳቢውን በሚስጥራዊነት መርህዎች ጭምር የሚያስማማበት ሥርዓት ነው ተብሏል፡፡
#ሸገር ኤፍኤም

ግንቦት 27 2018 - ሀሙስ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይከታተሉ
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
1👍1👏1
ትኩስ መረጃ
Photo
በወልመራ ወረዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በድብቅ ታጥቆ በገባው የጦር መሳሪያ ባለቤቱን እና የችሎቱን ዳኛ ተኩሶ በመግደሉ በቁጥጥር ዋለ።

በሆለታ ከተማ በሚገኘው የወልመራ ወረዳ የመጀመርያ ፍርድ ቤት የቤተሠብ ክርክር ችሎት ላይ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረ ግለሠብ በእለቱ በችሎቱ ተገኝተው ውሣኔውን ስታነብ የነበረችውን ዳኛ ና በሕግ ስትከራከር የነበረችውን ባለቤቱን ደብቆ ይዞት በገባው ሽጉጥ መግደሉን ፖሊስ አስታውቋል።

የሆለታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ፀጋዬ ቶልቻ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት፣ ግንቦት 27 ቀን ረፋድ ላይ በወረዳው ፍርድ ቤት የግራ ቀኝ ክርክር ተደርጎበት የሠነበተው የባልና ሚስት ክርክር ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሣኔ ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

በሆለታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ባልና ሚስት ለወራት በይገባኛል የንብረት ክርክር  ሲከራከሩ ቆይተው የመጨረሻ የፍርድ ውሣኔ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ በድብቅ ሽጉጥ በመታጠቅ ወደ ፍርድ ቤቱ ችሎት በመግባት የመጨረሻው የችሎት ውሣኔ ሲሰማ አቅዶና ተዘጋጅቶ ይዞት በገባው ሕገወጥ የጦር መሣርያ የሕግ ባለቤቱ ላይ እና የችሎቱ ዳኛ ወይዘሮ ወርቄ ፈካንሣ ላይ ተኩሶ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል።

ግለሠቡ የፍርድ ውሣኔውን በንቃት ሲከታተል ቆይቶ በመጨረሻው ውሣኔ ተከትሎ ተዘጋጅቶ በድብቅ በያዘው  ሽጉጥ ባለቤቱን ቅድምያ በመምታት በመቀጠል ደግሞ ውሣኔውን ባነበበችው ዳኛ ችሎት ላይ ተኩሶ መግደሉን ገልፀዋል።ይሕ አሣዛኝ ድርጊት የተከሠተው በፍታሕቤር ክርክር ችሎት ላይ የሚታየው የፍተሻ ክፍተት ሲሆን ፍርድ ቤቶች የራሣቸው የጥበቃ ሰራተኞች በፈጠሩት ክፍተት ነው።

በአሁኑ ሠዓት ፖሊስ በፍርድ ቤቱ የተመደቡ  የጥበቃ አካላትና ችሎት አስከባሪ ፖሊሶችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ያለ ሲሆን በድርጊቱ ፖሊስና የሕግ ባለሞያዎች ዘንድ ትልቅ ሐዘኔታ የፈጠረ ቢሆንም በአስቸኳይ የወንጀል ድርጊቱ ተጣርቶ ለፍትሕ አካላት እንደሚቀርብና የፍትሕ ውሣኔው ለሕብረተሠብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልፀዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል