🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞
1.26K subscribers
349 photos
45 videos
23 files
717 links
ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው።
(ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል።
(إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)
Download Telegram
‎⁨من جوامع دعاء النبي .. بطاقة⁩.pdf
591.2 KB
☝️ ይህ በትክክለኛ ሰነድ ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የተገኙ ጥቅል መልእክት ያላቸው (ጀዋሚዕ) ዱዓዎች ስብስብ ነው።

ለሌሎችም ያስተላለፉት!

አላህ በመልካም ከሚተባበሩት ያድርገን!

من جوامع دعاء النبي صلى الله عليه وسلم

✍ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
በዒድ እለት የመልካም ምኞትን መግለጽን በተመለከተ

«የመልእክተኛው ባልደረቦች የዒድ ቀን በሚገናኙበት ወቅት አንዳቸው ለሌኛው "ተቀበለ አላሁ ሚና ወሚንከ" ይባባሉ ነበር።» (ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ ላይ ዘግበውታል አልባኒም ሰነዱ ትክክለኛ ነው ብለዋል)
ትርጉሙም: ‐ "አላህ ከእኛም ከአንተም መልካም ስራችንን ይቀበልን" ማለት ነው።

እንኳን አደረሳችሁ በመባባል የመልካም ምኞትን መግለጽ እና ዱዓእ መደራረግ በሸሪዓ መሰረት ያለው ለመሆኑ ይህ ግልፅ መረጃ ነው።

✍ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
*تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال*

*አላህ መልካም ስራችንን ይቀበልን!*

እንኳን ለዒድ አል‐አድሃ በአል በሰላም አደረሳችሁ።

✍ *ጣሀ አህመድ*


🌐 https://t.me/tahaahmed9
ተክቢራን ማድረግ ከኢስላም ሀይማኖታዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ነው !!

በዒደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰአት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በኢደል-አድሀ ደግሞ ከዙል-ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ ከኢስላም ሀይማኖታዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ነው፡፡
ከዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር-ረዲየላሁ ዓንሁማ- እንደተላለፈው:- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የዒደል-ፊጥር እለት ከቤታቸው ወጥተው እስከመስገጃው ድረስ ተክቢራን ያደርጉ ነበር::" (አል-ሃኪም እና በይሃቂይ ዘግበውታል) አልባኒ ኢርዋእ-አልገሊል ላይ ሰሂህ ብለውታል::
አል ኢማም አነወዊይ እንዲህ ብለዋል:- "በሁለቱ ዒዶች ተክቢራን ማድረግ ለሁሉም የተደወደደ መሆኑን ዑለማዎች የተስማሙበት ጉዳይ ነው::"(ሸርህ ሙስሊም)

✍ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ዒድ á‰ áŒáˆá‹“(ዓርብ) ዕለት ሲውል የዒድ እና የጁመዓ ሰላትን በተመለከተ የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ

የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ በቁጥር  21160 ባወጣው መግለጫ ተከታዮቹን ሀሳቦች ጠቅሷል።
 
¡ áŠ˘áˆ›áˆ™ ሰላተል ጁምዓ እንዲሰገድ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጁምዓ ለመስገድ በቂ ሰዉ ካልተገኘ ዙህርን ያሰግዳል።
¡ áˆ°áˆ‹á‰°áˆ á‹’ዾ á‹¨áˆ°áŒˆá‹° ሰው የጁምዓ ሰላትን ባይገኝ ይፈቀድለታል። ነገር ግን ዙህርን በወቅቱ የመስገድ ግዴታ አለበት ። ዙሁህርን ባለበት ከመስገድ ይልቅ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ጁምዓን ቢሰግድ የተሻለ ነው።
¡ á‹¨á‹’ዾን ሰላት ያልሰገደ ግን ይህ ፍቃድ አይመለከተዉም። ጁምዓን የመስገድ ግዴታ አለበት።
¡ á‰ á‹šáˆ… እለት ጁምዓ በሚሰገድባቸዉ መስጂዶች ሲቀር የዙህር አዛን አይደረግም።

✍ ጣሀ አህመድ (1431 የተፃፈ)

🌐
https://t.me/tahaahmed9
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

(ክፍል–3)

የሶስተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስረኛው የዒድ ቀን ነው።

1⃣ ሚና ሲደርስ ወደ ጀምረተል—ዓቀባ በመሄድ "አላሁ አክበር " እያለ በማከታትል ሰባት ጠጠሮችን ይወረውራል።
2⃣ ሀድይ ወይም የመቃረቢያ መስዋእት ካለው ያርዳል።
3⃣ ፀጉሩን ይላጫል ወይም ያሳጥራል።

እነዚህን ተግባራት በመፈፀሙ የመጀመሪያ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል—አወል) ይከሰትለታል። በመሆኑም ከግብረ—ስጋ ግንኙነት ውጭ በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩ ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
4⃣ ወደ መካ መሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህ ማድረግ፦
ወደ መካ ይሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህን (የሐጅ ጠዎፍን) ያደርጋል። ሙተመቲዕ (በሐጅ ወራት ዑምራን ፈፅሞ በዚያው ጉዞ ሐጅን የሚያደርግ) የሆነና እንዲሁም ሙተመቲዕ ባይሆንም በመጀመሪያ የመግቢያ ጠዎፉን ሲያደርግ አሰከትሎ በሰፋና መርዎ መካከል ሰዕይ ያላደረገ ከነበረ የሐጅን ሰዕይ ያደርጋል።
በዚህ ተግባሩም ሁለተኛ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል አስ–ሳኒ) ይከሰታል። በመሆኑም የግብረ—ስጋ ግንኙነትን ጨምሮ ሌሎቹም በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩበት ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
5⃣ ወደ ሚና በመመለስ አስራ አንደኛውን ሌሊት በዚያ ያድራል።

ይቀጥላል…

ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ… አላህ ያግራልን!

✍️*ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
መብላት፣ መጠጣት እና መልበስ እሰከ የት ድረስ ሊሆን ይገባል?

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– " ብሉ፣ ጠጡ፣ ምፅዋትን ስጡ እንዲሁም ልበሱ ይህን ድርጊታችሁን ድንበር ማለፍ ወይም ኩራት እሰካልተቀላቀለው ድረስ።" (
ሀዲሱን ነሳኢ ዘግበውታል አልባኒም ሀሰን ብለውታል)

ኩራት (መኺላ):– የሚለው ቃል ትርጉም በዚህ አገባቡ ልታይ ማለትን እና በራስ ድርጊትም ይሁን ማንነት መገረምን ያካትታል።

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ጥቂት ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶች

1⃣ኛ. ዒድ መሆኑ ከታወቀበት ሰአት ጀምሮ ወንዶች ከሰላተል ጀመዓ መቅረት ብሎም በረመዳን ሲሰግዱት የነበረውን ዊትር ሰላት ማቋረጥ፤ አንዳንዴም አምልኮዎች በዚህ ያበቃሉ የተባለ ይመስል እርግፍ አድርጎ መተው ይስተዋላል፡፡
2⃣ኛ. የዒዱን ዋዜማ ለሊት በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው ማድረግን በተመለከተ የመጡት ሀዲሶች ከሰነድ አንፃር ደካማዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ለሊቱን በተለያዩ የሚጠቅሙም ይሁን ያማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ማሳለፍ፤ በዚህም የተነሳ የፈጅር ሰላትን አለመስገድ እና ሰላተል-ዒድን እንደ ቀላል በመመልከት ችላ ብሎ መተው::
የዒድ ሰላትን በተመለከተ  "ሰላተል-ዒድ በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው" የሚለው የአቡ ሀኒፋ አቋም ሲሆን ከኢማሙ አሻፊዒይ እና  አህመድም ከተዘገቡት ሁለት የተለያዩ አቋሞች አንዱ የሚጠቁመውም ይህንኑ ነው። ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑ-ተይሚያህ እና ሌሎች ብዙ ዑለማዎችም ይህን አቋም የሚደግፉ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
3⃣ኛ.በአለባበስና መቆነጃጀት ዙሪያ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል ብዙ ወንዶች ፂማቸውን መላጨትና ማሳጠር እንዲሁም ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች እነዲወርድ በማድረግ የሚፈፅሙት ስህተት ይገኝበታ። ሴቶች ደግሞ ሽቶን በመቀባት በመገላለጥ የሚፈፅሙት ስህተት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የመጡት ነብያዊ አስተምህሮቶች በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፡፡
 
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( مَا أَسْفَلَ مِنْ الْكَعْبَيْنِ مِنْ
الْإِزَارِ فَفِي النَّارِ) رواه البخاري (5787)

ከአቡሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከሽርጥ ከቁርጭምጭሚት የወረደዉ የእሳት ነው"  (ቡኻሪና በቁጥር (5787) ዘግበዉታል)
ይህ ሁሉንም የልብስ አይነት እንደሚያካትት ለመግለፅ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ ለሀዲሱ "ከቁርጭምጭሚት የወረደው እሱ የእሳት ነው" የሚል ርዕስ ሰጥተውታል።
በሌላ ሴቶች ከቤት ሲወጡ ምን አይነት ስነ-ስርአት መከተል እንደሚገባቸው በሚጠቁም ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:-"ማንኛዋም ሴት ሽቶን ተቀብታ ወደ መስጂድ የወጣች እንደሆነ እስክትታጠብ ድረስ ሰላቷ ተቀባይነት የለውም፡፡"(ኢብኑ ማጃህ እና አህመድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡)
 
عن أبي هريرة قال: قال صلى الله عليه وسلم : "صِنفانِ مِن أهلِ النارِ لم أرَهما..... ونِساءٌ كاسياتٌ عارياتٌ مميلاتٌ مائلاتٌ، رؤوسُهُنَّ كأسنِمَةِ البُخْتِ المائلةِ لا يَدْخُلْنَ الجنةَ ولا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وإن رِيحَهَا لَيوجَدُ مِن مَسيرةِ كذا وكذا". رواه مسلم(2128)
 
ሙስሊም አቡ ሁረይራን ዋቢ አድርገው ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:-   "ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች በእኔ (ዘመን) አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ)" አሉና፤ የመጀመሪያዎቹ ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው ካብራሩ በኋላ "ሌለኞቹ ሴቶች ናቸው፤ ለብሰው ያልለበሱ አካሄዳቸው እና እንቅስቃሴያቸው ወደርካሽ አላማ ያዘነበለ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ናቸው:: እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም" አሉ::

ክፍል 2 ይቀጥላል.…

✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶች

ክፍል 2

4⃣ኛ. ባዕድ በሆኑ ወንዶችና ሴቶች መካከል መቀላቀል፤ አልፎም መጨባበጥና መሳሳም፡፡ ይህ ሸሪዓው ክፉኛ የኮነነው ተግባር ነው፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ከእለታት አንድ ቀን ከመስጂድ በመውጣት ላይ ሳሉ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመንገድ ላይ ተቀላቅለው ተመለከቱ ይህንን ክስተት በማስመልከትም "ከወንዶች ወደ ኋላ ሁኑ፤ የመንገዱንም መሀከል ይዛችሁ ልትጓዙ አይገባም" አሉ፡፡ ይህንን ሀዲስ የዘገበው ሰሃቢይ "ከዚህ በኋላ ሴቶች በጣም ወደ ዳር ከመውጣታቸው ልብሳቸው በአጥር ይያዝ ነበር፡፡" በማለት ይናገራል፡፡(አቡዳውድ  ሱነናቸው ላይ ሲዘግቡት አልባኒ ሀሰን የሚል ደረጃ ሰጥተውታል) ይህ ሀዲስ ሸሪዓ በጥቅሉ ወደ ሀራም የሚያደርሱ ነገሮችን የከለከለ መሆኑን ከሚያሳዩ መረጃዎች አንዱ ነው፡፡
    በሌላ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰለም በርሳቸው ላይ ይሁን) "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም" ማለታቸው ሰፍሯል፡፡ ሀዲሱ አንድ ሰው ምንም እንኳ የተቀደሰ አላማና ንፁህ ልቦና ነው የያዝኩት ቢልም ባዕድ ሴቶችን ከመጨበጥ ሊቆጠብ እንደሚገባ የሚያመለክት ነው፡፡
5⃣ኛ. እንደ ሙዚቃ እና መሰል የተከለከሉ ነገሮችን ከማድመጥ፣ ፊልሞችን በመመልከት ጊዜን ከማጥፋት መቆጠብ ያስፈልጋል:: እንዲሁም  ሌሎችንም ሀራም የሆኑ ተግባራትን በሙሉ መጠንቀቅ ይገባል::
6⃣ኛ. በዒድም ይሁን በሌላ ጊዜ በኢስላም ማባከን እጅጉን የተኮነነ ተግባር ቢሆንም በዒድ እለት በአንዳንዶች ዘንድ ከሚታዩት ስህተቶች መካከል ምግብና መጠጥን ማባከን ነውና ልንርቀው ይገባል::    
ኢስላም በራሱ የተሟላ ነው!
  እንደሚታወቀው ሀይማኖታችን ኢስላም ምሉዕ ነው፡፡ ስለሆነም ለሁሉም የአምልኮ ዘርፎች እንዲሁም የህይወት መስኮች  ደንቦችን ደንግጓል ስርዐቶችንም አስቀምጧል፡፡ ሕግጋቶቹ ፍትሀዊ እና ሚዛናዊ ስርዐቶቹም ለሁሉም ቦታ እና ዘመን የሚበጁ ናቸው፡፡ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል:-
{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا} المائدة 3

‹‹ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ከሀይማኖት በኩልም ለእናንተም ኢስላምን ወደደኩ...›› (አልማኢዳ፡ 3)
ከዚህም በመነሳት መጨመርንም ይሁን መቀነስን አይቀበልም እንዲሁም ከሌሎች መኮረጅንም ሆነ መመሳሰልን ይከለክላል፡፡
ይህንን እዉነታ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን) በነዚህ ሁለት ነብያዊ አስተምህሮቶች ይገልፁታል፡፡

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من ŘŁŘ­ŘŻŘŤ في أمرنا هذا ما ليس منه فهو عد ) رواه البخاري (2697)  ومسلم (1718)

"በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ ) رواه أبو داود (4031)

"ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡" (አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
ስለሆነም ዒዳችንን ስናከብርም ይሁን ማንኛውንም አይነት ዒባዳ ስንፈጽም ከጭማሪ (ቢደዓ) እራሳችንን ልናርቅ እንዲሁም በማነኛውም የህይወታችን ክፍሎች ከሌሎች ጋር መመሳሰልን ትተን ሙሉ የሆነውን ሸሪዓን በማወቅ ወደ ተግባር ልንለውጥ ይገባል::

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال.
 
አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!!

✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*


🌐
https://t.me/tahaahmed9
ከዙል–ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "አያሙ አት‐ተሽሪቅ (ከዙል‐ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት) የመብላት፣ የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናት ናቸው።" (
ሙስሊም ዘግበውታል)

መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ሐዲስ በነዚህ ቀናት የምንፈፅማቸውን ዋነኛ ነገሮች ጠቁመውናል። ትኩረት ልናድረግበት እና ልንተዋወስበት የሚገባው ትልቁ ነገር አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ) እንዲሁም እርሱ በእኛ ላይ የዋለውን ውለታ በማስታወስ ማመስገን ነው። ይህን የሚታደሉ ጥቂቶች ናቸው።

አላህ እርሱን ለማስታውስ፣ ለማመስገን እና አሳምሮ ለማመለክ ይርዳን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

(ክፍል–4/ የመጨረሻው ክፍል)

የአራተኛው እለት ተግባር

እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ አንደኛው ቀን ነው።

1️⃣ በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል። የመጀመሪያው ከዚያም መካከለኛው ከዚያም ጀምረተል–ዓቀባ ላይ እያንዳንዱ ጉድጓድ ላይ ሰባት ሰባት ጠጠሮችን በማከታትል እና እያንዳነዱን ጠጠር በሚወረውርበት ጊዜ "አላሁ አክበር " በማለት ይሆናል። ጠጠር የመወርወር ተግባሩ የሚሆነው ጸሐይ ከአናት ከተዘነበለች በኋላ ነው። ከዚያ በፊት መወርወሩ አይፈቀድም።
ከመጀመሪያው እና መካከለኛው የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓድ በኋላ ዱዓእ ለማድረግ መቆም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
2️⃣ አስራ ሁለተኛውን ለሊት ሚና ውስጥ ያድራል።

የአምስተኛው እለት ተግባር


እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሁለተኛው ቀን ነው።

1️⃣ በአራተኛው እለት እንዳደረገው ሁሉ በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
2️⃣ ተቻኩሎ በአስራ ሁለተኛው ቀን ከሚና መውጣት ከፈለገ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይወጣል ወይም እስከ አስራ ሶስተኛው ቀን መዘግየት ከፈለገ በዚያው ያድራል።

የስድስተኛው እለት ተግባር


እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሶስተኛው ቀን ነው።
የዚህ እለት ተግባር ሚና ላይ የዘገዩትን ሰዎች ብቻ ነው የሚመለከተው።

1️⃣ ከዚህ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት በፈፀመው መሰረት በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
2️⃣ ከዚያ በኋላ ሚናን ለቆ ይወጣል።
የመጨረሻው ስራ ጠዋፈል—ወዳዕ (የመሰናበቻ ጠዎፍ) ይሆናል። እርሱም ወደ ሀገሩ ሊመለስ ሲል የሚያደርገው ነው።

ተፈፀመ

አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ታላቅ ብስራት ለወላጆች...

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር ልዩ የክረምት ኮርስ በተመላላሽ እና በርቀት ለሁሉም ፆታ በተመቻቸ መልኩ ያዘጋጀ መሆኑን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።

🖍 ዕድሜያቸው ከ10 - 12 ለሆኑ ልጆች፣
🖍 ከ13- 14 ለሞላቸው ታዳጊዎች፣ እንዲሁም
🖍 15 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወጣቶች፣

✔️ እምነታቸውን ከምንጩ የሚያውቁበት
✔️ የኢባዳን አፈፃፀም የሚማሩበት
✔️ ኢስላማዊ ተርቢያ የሚቀስሙበት
✔️ መልካም አርአያዎቻቸውን የሚተዋወቁበት
✔️ጌታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁበት
ታላቅ ኮርስ...

ለመመዝገብ፤
፨ ለወንዶች ከሰኔ 17- 28 ባሉት ቀናት 18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዋና ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመምጣት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፤

፨ ለሴቶች ደግሞ ከሰኔ 17- 23  18 ባለው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር በቤቴልና ፉሪ ቅርጫፎች መመዝገብ

📌 ለበለጠ መረጃ 
 ለወንዶች፤ በስልክ ቁጥር
0912617007
0912023190
0912617005

 ለሴቶች፤
18 ኢብኑመስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ለመማር
0904366666

ለቤቴል ቅርጫፍ 
0911105653
0911375952
0913840323

ለፉሪ ቅርጫፍ 
0911479151
0912058590
0926948459   ይደውሉ፤

የምዝገባ ቀንና ሰዓት፤
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ 2:30-9:30 በአካል በመገኘት ይመዝገቡ፤

ልጆቻችሁ በእውቀት ብርሀን ከፍ ይበሉ!




__
🕌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@merkezuna
🔊 ዓሹራ እና የፊርዓውን ፍፃሜ

በ2002 በጃሊያ አዳራሽ ከቀረበ ትምህርት የተቀነጨበ

🎙 ጣሀ አህመድ

Http://goo.gl/ndDKMW

👍🏻 ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ
Http://telegram.me/nesihastudio

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ከዓሹራእ ቀን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቁም ነገሮች

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- "የዓሹራእ ቀንን መጾም ያለፈውን አመት ወንጀል ያሳብሳል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ::" (ሙስሊም ዘግበውታል)
🟢 የዓሹራእ ቀን ከሙሐረም ወር አስረኛው ቀን ነው:: በዚህ እለት ነበር አላህ ነብዩ ሙሳ እና ህዝባቸውን ከፊርዓውን ያዳናቸው::
🟢 የዓሹራእን ቀን መጾም የተወደደ ስለመሆኑ ዑለማዎች ስምምነት ኢጅማዕ ያላቸው መሆኑን ነወዊ እና ኢብኑ-ሐጀር እንዲሁም ሌሎችም ዘግበዋል::
🟢 የረመዳን ወርን መጾም ግዴታ ከመሆኑ በፊት ይህን ቀን መጾም ግዴታ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ግዴታነቱ ተሽሮ በፍላጎት የሚጾም የሱና ጾም ሆኗል::
🟢 በአራቱም መዝሀብ ዑለማዎች አቋም መሰረት ከዓሹራእ ቀን በተጨማሪ ዘጠነኛውንም ቀን መጾምም ይወደዳል:: ይህም መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ይህንን ቀን እንደሚያክብሩት በሰሙ ግዜ እንዲህ በማለታቸው ነው:- "በአላህ ፍቃድ እስከ ሚቀጥለው አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን አብረን እንጾማለን::" (ሙስሊም ዘግበውታል)
🟢 ከዓሹራእ ቀን ጾም ጋር በተያያዘ ዑለማዎች የተለያዩ መረጃዎችን በመመርኮዝ በዚህ መልኩ ቢሆን የተሻለ ነው ሲሉ የሚሰነዝሮቸው ሀሳቦች አሏቸው ከነዛም መካከል የተወሰኑትን ለመጠቆም ያህል:-
1⃣ ዘጠነኛውን ቀን ከአስረኛው ቀን ጋር መጾም አስረኛውን ቀን ብቻ ከመጾም የተሻለ ነው:: ከላይ ያሳለፍነው "በአላህ ፍቃድ እስከ ሚቀጥለው አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን አብረን እንጾማለን::" የሚለው ሀዲስ ይህንን ሀሳብ ያጠናክራል::

ይቀጥላል…

🌐
https://t.me/tahaahmed9
ከዓሹራእ ቀን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቁም ነገሮች

(ክፍል ሁለት)

2⃣ ከአስረኛው ቀን ጋር አስራ አንደኛውን ቀን መጾም ይህ ከአይሁዶች ጋር ላለመመሳሰል ሲባል የተሻለ ነው:: ይህንን ሀሳብ ከዓሹራእ ቀን በፊት ወይም በኋላ መጾምን በተመለከተ የተዘገበውን ደካማ ሀዲስ መሰረት በማድረግ ሳይሆን ከላይ ያሳለፍነው እና መሰል አይሁዶችን መቃረንን የሚያመላክቱ ሀዲሶችን ሀሳብ እንዲሁም በዚህ ወር ጾምን ማብዛት የተወደደ መሆኑን መሰረት በማድረግ ነው::
3⃣ አስረኛውን ቀን ብቻ መጾምን በተመለከተ ከላይ በመጀመሪያ የጠቅስነውን ሀዲስ መረጃ በማድረግ አብዛኞቹ ዑለማዎች የዓሹራእን ቀን ብቻ መጾም አይጠላም ብለዋል::
🔴 የዓሹራን ቀን በተመለከተ ከመጾም ውጪ በዚህ ቀን የተለየ የሚደረግ ማንኛውም አምልኳዊም ሆነ ሌላ የተለየ ተግባር በመልእክተኛው ሱና ውስጥ ምንም አይነት መሰረት የሌለው መሆኑን እና በዚህ ቀን በተለየ መልኩ እንዲህ ማድረግ ይወደዳል እንዲህ ማድረግ ይገባል በሚል የሚወሩ የተለያዩ ነገሮች ትክክለኛ መሰረት ያላቸው ሀዲሶችን የተመረኮዙ አለመሆናቸውን አውቆ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በትክክለኛ እና ጠንካራ ሀዲስ ላይ የተመሰረተውን ጾም በመጾም ወደ አላህ እንዲቃረብ ዑለማዎች በአንክሮ ይመክራሉ።

በመጨረሻም ማንኛውም ነገ አላህ ፊት ቀርቤ ስራዬን እመረመራለሁ ስለዚህ መልካም ስራን ሰርቼ ከጌታዬ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ የሚል ሰው የሚሰራውን ስራ ለአላህ ብቻ አጥርቶ በኢኽላስ ሊሰራ እንዲሁም የአላህ እና የመልእክተኛው ትእዛዝ ካለበት ተግባር ውጪ ሌላን ስራ ከመስራት ሊርቅ ይገባል::
ሁላችንም ልብ ብለን የእነዚህን ሁለት ሀዲሶች መልእክት እንድናስተንትን እጋብዛለሁ: –
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-"በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ ሰው ስራው ተመላሽ ነው፡፡" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላው ሀዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-"ማንኛውም ስራ የሰራ በዚያ ስራ ላይ የእኛ ትእዛዝ ከሌለበት ስራው ተመላሽ ነው፡፡" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

አላህ መልካም ሰራን ከሚሰሩት እና ከሚቀበላቸው ያድርገን!

✍ ጣሀ አህመድ (ሙሐረም 1442 የተፃፈ)

🌐
https://t.me/tahaahmed9
የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ

የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም በዒባዳ ያሳልፉታል።

ሺዓዎች ግን ስለ ዓሹራ ቀን ሲያስቡ ሚታወሳቸው የታላቁ ሰሀቢይ የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ልጅ ሁሰይን የተገደሉበት ቀን መሆኑ ብቻ ነው። ሺዓዎች በዚህ ቀን ሀዘናቸውን ለመግለፅ እራሳቸውን የሚጎዱ ብዙ ነገሮችን በስፋት ይፈፅማሉ። ጭንቅላትንና ሌሎች አካሎቻቸውን በስለት መብጣትና ማድማት (ተጥቢር)፣ ፊታቸውን መደብደብ (ለጥም፣) እራስን በሰንሰለት መግረፍና ማንገላታት፣ በእንብርክክ መሄድ፣ ብዙዎችም ዘንድ ጥቁር መልበስና የለቅሶ ሙሾ ማውረድ ብሎም በራስ ላይ ኩነኔን መጥራት የተለመዱ የአሹራ ትእይንቶቻቸው ናቸው።

በእጅጉ ይገርማል፤
ለኛ ለአህሉሱና ደስታን ሲያላብሰን፣ ተስፋን አሰንቆ ድልን ሲያበስረን፤ ለወንጀላችን ማርታን ለማግኘት ሩጫ ውስጥ ሲከተን፤

ለሺአዎች ግና፤
የሀዘን የዋይታ፣ የውድቀት የሽንፈት ማስታወሻ፣ የተስፋ ማጨለሚያ ነው!!

ሁሰይን የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ በኢስላማዊ እውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ሰሀቦች አንዱ ኗቸው።


ቀረውን ከተከታዩ ሊንክ ያንብቡ
http://clearfaith.blogspot.com/2015/10/blog-post.html?m=1
Audio
📌 ስለ ምርጫ …

🔗ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ustazilyas/1579

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ @ustazilyas
እውን ሙዚቃና ዘፈን በኢስላም አልተከለከለምን?

✍🏻 ሙሀመድ ሀሰን ማሜ (ጥር 2003)
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌼»‌‌✽‌┉┉┄┄

አንደሚታወቀው ኢስላም ሰፊና ጥልቅ አስተምህሮቶች፤ ረቂቅና ጥልቅ መመሪያዎችና ድንጋጌዎች አሉት፡፡ ሁሉንም የህይወት ዘርፎች  ዳሷል።  ሳያስተምረን ያለፈው የህይወት ጉዳይ የለም። በተለያየ መልክና ዘዴ እያንዳንዱን የህይወት ክፍል በመዳሰስም ወደር የሌለው ሃይማኖት ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንንም እውነታ የማንኛውም አማኝ ልቦናና ህሊና ያውቀዋል፡፡

ሆኖም በኢስላም ድንጋጌ እና መመሪያ ላይ በየጊዜው እና በየወቅቱ የተለያዩ ብዥታዎችና ውዥንብሮችን የሚፈጥሩ ሰዎች አልጠፉም፣ ነበሩም፣ አሉም፣ ይኖራሉም፡፡ በየጊዜው ብቅ ጥልቅ ከሚሉ በርካታ ውዥንብሮች መካከል የሙዚቃን ብይን የተመለከተው ይጠቀሳል። የራሳቸውን ግንዛቤ ለማስተላለፍ ሲፈልጉ፤ ኢስላም ስለዘፈንም ይሁን ስለሙዚቃ ክልክልነት የተናገረው ነገር የለም፡፡ ክልክል ለመሆኑ የቀረቡ መረጃዎችንም የወደቁና ተቀባይነት የሌላቸው እንደሆኑ፤ ሲጠኑ በሁለት እግር መቆም የማይችሉ  እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ የሚነዙት ብዥታ ተራ አሉባልታ እንደሆነ በእዚህ መልዕክቴ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ በተለይም ሰሞኑን አቶ ሀሰን ታጁ በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ የጣዕም ልኬት የሙዚቃ ዝግጅት ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ይህ አይነቱን አመለካከት በስፋት ስላብራራ አጠር ያለ ምላሽ አዘጋጅቻለው። አላህ ስራችንን ሁሉ በኢኽላስ የተፈፀመ እንዲያደርገውነ እለምነዋለሁ።  እግዛንም ከእርሱ ብቻ እጠይቃለሁ፡፡

ዘፈንና ሙዚቃ በኢስላም የተከለከለ መሆኑን በተለያዩ ኢስላማዊ መረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
1ኛ- ከቁርአን                  2ኛ- ከሐዲስ
3ኛ- ከሰሃቦች                  4ኛ- ከታቢዒዮች
5ኛ- ከአራቱ መዝሃቦች     6ኛ - ከኢጅማዑ አሰለፍ


1ኛ- ከቁርአን
በሱረቱል ሉቅማን ቁጥር 6
وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ [٣١:٦]

“ከሰዎች ያለ እውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን (ለህወል ሀዲስ) የሚገዛ አለ፤ እነዚያ እነሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡”

በእዚህ አንቀፅ ውስጥ “ለህወል ሀዲስ” (አታላይ ወሬ) ተብሎ የተሰየመውና ቅጣቱም አወራጅ ተብሎ የተዛተበት ምን ይሆን? መልሱን ከሰሃቦች ማግኘት ይቻላል፡፡

ሀ. አብድላህ አብኑ መስዑድ

(ስለቁርአን ጥልቅ እውቀት ባላቸው ስመጥር ሰሃባ አንዱ ነው፡፡) ስለ “ለህወል ሀዲስ” (አታላይ ወሬ) ሲጠየቅ ሶስት ጊዜ በመማል “ዘፈን ነው ዘፈን ነው ዘፈን ነው” በማለት መመለሱን ኢብኑ አቡ ሸይባ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ አልሃኪም፣ አልበይሀቂ እና ኢብልጀውዚ ዘግበውታል፡፡

ለ. አብደላህ ኢብኑ ዐባስ

(የዑማው አዋቂና በቁርአን ማብራሪያ ላቅ ያለ እውቀት ያለውና ረሱልም “አላህ ሆይ ሃይማኖቱን አስገንዝበው የቁርአንንም ማብራሪያ አሳውቀው፡፡” ብለው ዱዓእ ያደረጉለት ስመ ጥር ሰሃባ ነው፡፡) ስለ (ለህወል ሀዲስ) “ዘፈንና መሰሎቹ ናቸው” ማለቱን ኢብኑ አቡ ሸይባ፣ (ቡኻሪ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ አልበይሀቂ፣ እና ኢብኑ ጀውዚ ዘግበውታል፡፡)

ሐ. አብደላህ ኢብኑ ዑመር (የመዲና ሙፍቲና የፊቂህ ምሁር ) ለሕወል ሀዲስን በማስመልከት “እርሱም ዘፈን ነው” በማለት አብራርቶታል፡፡

መ. ጃቢር ኢብኑ አብደላህ  (ከኢብኑ ዑመር ቀጥሎ የመዲና ሰዎች ፊቂህ እንዲሁም ሙፍቲ የነበረው) “ዘፈንና ማድመጡ ነው” ማለቱን ኢብኑ ጀሪር ዘግበዋል፡፡

ታዲያ ከእነዚህ ታላላቅና ስመጥር ሰሃቦች ይህን አንቀፅ በተመለከተ (ዘፈን) መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የሰሃቦች ማብራሪያ ማስረጃ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንም ማብራሪያ የተቃረነ አንድም ሰሃባ የለም፡፡

ሰሃቦችም እንዲህ ብለው እንደተረጐሙት ሁሉ ታቢዒዮችም በተመሳሳይ መልኩ አብራርተውታል፡፡ እንደሚከተለውም ዝርዝራቸውን እጠቅሳለሁ፡፡

1.ሙጃሂድ ኢብኑ ጃቢር
2. ዒክሪማህ        
3. መክሁል       
4.ኢብራሂም አል ነኸዒ                          
5. ዐጣእ         
6.ሰዒድ ኢብኑ ጁበይ   
7.አል ሐሰን አል በስሪ                                   
8.ቀታዳህ ኢብኑ ደዓማ                                
9.መይሙን ኢብኑ ሚህራን                                      
1ዐ. ሀቢብ ኢብኑ አቢሳቢት                                                       11. ዐምር ኢብኑ ሹዓይብ                        
12. áŠ á‰Ľá‹ąáˆáˆ˜áˆŠáŠ­ ኢብኑ ጁረይጅ                                                      13. ሰኢድ ኢብኑልሙሰይብ ናቸዉ፡፡

ሱረቱ ነጅም ቁጥር 59 – 61

أَفَمِنْ هَٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ [ŮĽŮŁ:ŮĽŮŠ]وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُونَ [ŮĽŮŁ:ŮŚŮ ]وَأَنتُمْ سَامِدُونَ [ŮĽŮŁ:ŮŚŮĄ]  

“በዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?! ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡”

ይህንም አንቀፅ በማስመልከት ዘንጊዎች ተብሎ የተተረጐመው ቃል በአረብኛው “ሳሚዱን” የሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙን በተመለከተ የየመን ቋንቋ እንደሆ በመጥቀስ “ዘፈን” እንደሆነ አብደላህ ኢብኑ ዐባስ ፣ ሙጃሂድ፣ ዒክሪማና አደሃክ ተናግረዋል፡፡
ሱረቱል ኢስራእ ቁጥር 64

وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ وَأَجْلِبْ عَلَيْهِم بِخَيْلِكَ وَرَجِلِكَ وَشَارِكْهُمْ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ

“ከእነሱ ያቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል በእነሱም ላይ በፈረሶኞችህም ለልብ በገንዘቦቻቸውም፣ በልጆቻቸውም ተጋራቸው፡፡”

ሙጃሂድ ኢብኑ ጃብር (የአብደላህ ኢብኑ ዓባስ ታላቅ ተማሪ) የኢብሊስ ድምፅ ምንነት ሲገልፁ እንዲህ ነበር ያሉት፡፡ “እርሱም ጊና (ዘፈን)፣ ሙዚቃ መሳሪያ፣ ላግጣና  ከንቱ ነገር ነው፡፡”

አድሃክም የዘፋኝ (የሙዚቃ መሳሪያ) ድምፅ ነው” ብለዋል

ኢብኑል ቀይምም እንዲህ በማለት ስለዘፈን ሁኔታ ይገልፃሉ :- “ዘፈን ከታላላቅ የሰይጣን ድምፃችና ነፍስን የሚያስበረግግበት፣ የሚረብሽበት እና ሰላም የሚነሰት ለመሆኑ አያጠራጥርም የቁርአን ወደሚረጋጋበት፣ ሰላም የሚያገኝበትና ወደጌታዋ እንድትመለስ የሚያደርገውን ተቃራኒ ነው፡፡”


👉 ቀሪውን ክፍል በሚከተለው ሊንክ ያንብቡ
https://nesiha.com/%e1%8a%a5%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%88%99%e1%8b%9a%e1%89%83%e1%8a%93-%e1%8b%98%e1%8d%88%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%88%b5%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%88%e1%8a%a8/


┄┄┉┉✽‌»‌‌🌼»‌‌✽‌┉┉┄┄


© ተንቢሀት @tenbihat