የስታፍ አንድነት እና የስልጠና ጊዜ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!
የ2018 ዓ.ም የክልል እና የአካባቢ አስተባባሪዎች (Regional & Area Coordinators) ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ በስኬት ተካሂዷል። በነበረን ቆይታ፦
የቃል ጥናት፡ "ተልዕኳዊ ህይወት እና ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ)
ስልታዊ አቅጣጫ፡ በቀጣይ አገልግሎት ትኩረቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶች
ሕብረትና ጸሎት፡ አብሮ ጌታን ማምለክ እና የልምድ ልውውጥ ነበረን።
ቀጣይ ርምጃ፦ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በሁሉም ክልላዊ ቢሮዎቻችን ለሚካሄደው የተማሪ መሪዎች ጉባኤ (Student Leaders Summit) በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
@suethio
#ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

❤24🔥2🥰2
🎓 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በሙሉ፡ በጸሎታችን ውስጥ አላችሁ! 🙏
የፈተናው ጊዜ ደርሷል! ለዚህ ወሳኝ ጊዜ በርትታችሁ እንዳጠናችሁ እና በደንብ እንደተዘጋጃችሁ እናውቃለን። አሁን በልበ ሙሉነት ወደ ፈተናው ክፍል ገብታችሁ ያጠናችሁትን የምታሳዩበት እና ውጤቱን ደግሞ ለእግዚአብሔር አደራ የምትሰጡበት ሰዓት ነው።
የፈተና ወረቀቱን ከመግለጣችሁ በፊት በጸሎት ጀምሩ፤ የእግዚአብሔር ሰላም አእምሯችሁን እንዲያረጋጋው ጋብዙ። ፈተናውን ስትሰሩ ጥያቄዎችን በጥንቃቄ አንብቡ፣ ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ፣ እንዲሁም ያላችሁን አቅም ሁሉ አውጥታችሁ ስሩ። ከሁሉ በላይ ደግሞ የወደፊት እጣ ፈንታችሁ ያለው በፈተና ውጤት ላይ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር እጅ መሆኑን አምናችሁ በእርሱ ታመኑ።
"ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።" — ምሳሌ 16፥3
ከቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ቤተሰብ በሙሉ ለስኬታችሁ፣ ለተረጋጋ አእምሮ እና ለሙሉ ሰላም አጥብቀን እንጸልያለን። በእምነት ተራመዱ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው!
#SU
#የቃለ_እግዚአብሔር_አንባቢዎች_ማህበር
#መከተል
#መታነፅ
#ማገልገል

❤16🙏9👍8🥰2