✨✨✨🌱🌱🌱✨✨✨🌱🌱🌱✨✨✨🌱🌱🌱
✨✨🌱ኃጢአትህን ኹሉ በዲያብሎስ ላይ አታሳብብ✨✨🌱
በንስሐ ተስፋ ከቆረጥክ ዲያብሎስ ይወድሃል፡፡ ግን እርሱ እንዲረካ አታድርግ፡፡ ለድኅነት ቀንም ሁሌም ዝግጁ ሁን፡፡
እነዚህን ኹሉ የተናገርኩት ዲያብሎስን ከነቀፋ ነፃ ለማውጣት ሳይሆን እናንተን ከስንፍና ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ኃጢአታችንን ኹሉ በእርሱ እንዳናሳብብ በእውነት ይስፈልጋል፤ ለሁሉም ክፋታችን ሰይጣንን ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነም የራሳችንን ቅጣት እንጨምራለን፤ ጉዳዩን ኹሉ ወደ እርሱ ስላስተላለፍንም ይቅርታ አናገኝም - ልክ ሄዋን ይቅርታን እንዳላገኘች ሁሉ፡፡
✨✨🌱
ግን ይህን አናድርግ፡፡ እራሳችንን እንወቅ፡፡ ቁስላችንን እንወቅ። ከዚያም መድኃኒቶቹን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፤ ደዌውን የማያውቅ ሰው፣ ድካሙን አይፈውስምና፡፡
ብዙ ኃጢአት ሠርተናል፤ ይህን በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ሁላችንም ቅጣት ይገባናል፡፡ እኛ ግን ያለ ይቅርታ አይደለንም፣ ከንስሐ አንቀርም፤ አሁንም በአደባባይ ቆመናል፤ በንስሐም ተጋድሎ ውስጥ ነን፡
አርጅተኻል እና በመጨረሻው የሕይወት ደረጃ ላይ ነህ? አሁን እንኳን ከንስሐ እንደወደቅክ አታስብ፡፡ በራስህ መዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ በመስቀል ላይ ነፃ የወጣውን ዘራፊ አስብ፡፡ እርሱ ዘውድ ከተቀዳጀበት ጊዜ የበለጠ ምን አጭር ነገር አለ? ያም ሆኖ ይህ ለእርሱ መዳን በቂ ነበር፡
✨✨🌱
ወጣት ነህ? በወጣትነትህ አትተማመን፣ ከፊትህ ረዥም ጊዜም እንዳለ አታስብ “የእግዚአብሔር ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" (፩ኛ ተሰ. ፭፣፪) ለዚህም ነው ፍጻሜያችንን የማይታይ ያደረገው፣ ተግተን እንድንጸና።
ማንም ኃጢያተኛ ሊያደርግህ አይችልም ይላል አቡነ ቴዎድሮስ - ዲያብሎስም ቢሆን፡፡ ለኃጢአት የመስማማት ወይም የመቃወም ኃይል ያለው በአንተ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
አሁን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ክፋት እንዲሆን የፈቀደ እንደሆነ አልያም በሌላ ምክንያት እንደሆነ እንመርምር።
✨✨🌱
በስንፍና በልቡም ምኞት ወደ ራሱ ኃጢአትን ከሚያስገባ ሰው በቀር፣ ኃጢአት በማንም ላይ ሊጫን አይችልም፡፡ ፈቃደኛ ባልሆነው እና ኃጢአትን በሚቃወመው ሰው ላይ ዲያብሎስ ኃይል የለውምና፡፡
ዲያብሎስ በኢዮብ ላይ ይህን የኃጢአት ክፋት ለመጫን የክፋት ዘዴውን ኹሉ ከተጠቀመ በኋላ ዓለማዊ ንብረቱን ኹሉ ገፍፎት፣ በሞት ሰባቱን ልጆቹን ነጥቆት፣ ከጭንቅላቱ ፀጉር እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ የሚያስፈሩ ቁስሎችን፣ የማያባሩ ስቃዮችን ከሰጠው በኋላ የኃጢአት እድፍ በኢዮብ ላይ እንዲጣበቅ ለማድረግ በከንቱ ሞከረ፤ ኢዮብ በዚህ ኹሉ ጸንቶአልና፤ ከቶ አምላኩን ለመሳደብ ፍቃደኛ አልነበረም።
✨✨🌱
የነፍስ ምግብ
✨ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
✨በፍሉይ ዓለም የተተረጎመ

ክፍል ዐሥራ አምስት
መረጋጋት
የረጋ ሰው ችግሮቹን በረጋ መንፈስ ይፈታል። እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ መረጋጋቱን አያጣም፣ ይልቁንም በምክንያታዊነትና በተመጣጠነ መንገድ ይንቀሳቀሳል። ስለዚህ ባህሪው በአእምሮ ጤናማና ተቀባይነት ያለው ነው፣ ኃይለኛ ግብረመልሶችንም አያስከትልም። ተቃውሞውን በሚገልጽበት ወይም በሚቃወምበት ጊዜ እንኳ ይህንን የሚያደርገው በረጋ መንፈስ፣ በነጥብ ላይ ያተኮረና በሚያምን መንገድ ነው፣ በነርቭ ውጥረት ሳይሆን በሎጂክ ይመራል። በዚህ መንገድ በሁኔታው ውስጥ ጥቅምን ለማግኘት ይሳካለታል እንጂ ከተቃዋሚዎቹ ጋር አይጋጭም። በሌላ በኩል ግን፣ ሌላ ሰው ከተቃወመ በጫጫታ ያደርገዋል፣ በከፍተኛ ድምፅ ሁከት ይፈጥራል። ሌላኛውን ወገን በሻካራ ክሶች ይከሳል፣ ከሰዎችና ከፍላጎቶቻቸው እንዲሁም ከሀሳቦቻቸው ጋር በጣም ባለጌ በሆነ መንገድ ይገናኛል! በዚህ ሁሉ ውስጥ ስህተት መሥራትና ቦታውን ማጣት ለእርሱ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተመልከት ሰላማዊው ሰው ከሥራው ቢለቅ እንኳ ይህንን የሚያደርገው በረጋ መንፈስ ነው። ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር መተባበር እንዳልቻለ ሲገነዘብ፣ ለእነሱ ምንም ዓይነት ችግር ሳይፈጥርና በዙሪያቸው ያለውን ከባቢ አየር ሳይረብሽ በጸጥታ ይወጣል። ነገር ግን የማይረጋጋው ሰው ከሥራ ቢለቅ፣ በመልቀቁ ምክንያት መላውን ዓለም ማወክ ይፈልጋል። እናም ሁከት ካልተፈጠረ ይቆጣና እንዲህ ይላል፦ እኔ እንዴት እለቃለሁ ሁሉ ነገር ግን እንደነበረ ይቀጥላል? እገሌ ወይም እገሌ እኔን ለመደገፍ ለምን አልተቆጡም? ሌሎቹስ ለምን እንደ እኔ አላደረጉም?!" በባሕርይው አማካኝነት፣ የረጋው ሰው ለሌሎች አርአያ ነው። ከእርሱ ሰላማዊነትንና መልካም ባሕርይን ይማራሉ፣ ከችግሮችና ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር እንዴት እንደሚገናኙም ተሞክሮ ያገኛሉ። የሐዋርያውን ቃል ያስታውሳሉ፦ "ከእናንተ ዘንድ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አኗኗሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኝነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኝነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉ።" (ያዕቆብ 3:13-16)። ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሌሎች ስህተቶች ሲናገር እንዲህ ይላል፦ "ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስህተት ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየዋህነት መንፈስ አቅኑት።" (ገላትያ 6:1)።
ይቀጥላል
ዘሴት እልፍ
ሰኔ 6 2018 ዓ/ም
https://t.me/z2e1ms
መረጋጋት
የረጋ ባሕርይና ችግሮችን መፍታት

Telegram
ምክረ ሐሳብ
ይህ መደብ የተባላሸውን አመለካከታችንን የምናስተካክልበትና ትውልድ የምንቀርጽበት ታላቋን ኢትዮጵያ የምንመልስበት ነው
❤3
🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንፀተ ቤታ (ሕንፀታ) በሰላም አደረሳችኹ
ሰኔ ፳፩ (ሕንፀታ ወቅዳሴ ቤታ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን) ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡
ጌታችንም ከእመቤታችን እና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ከሰማየ ሰማያት ወርዶ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ ‹‹እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ፤ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያንን አንፀዋል።
እግዚአብሔር አምላክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፍቅር፥ ረድኤት፥ ጸጋ - የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን! አሜን🙏
🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱

❤2
ሰኔ_24
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊው
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ አራት በዚች ቀን አባ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት ሞተ። ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር።
አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል። እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር።
ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው። ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው። አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው። አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው።
እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሠህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ። ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ።
ሰይጣንም ቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብሉና በመጠጡ በዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽናንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር።
ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእነርሱ ሩቅ ነበረና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ።
ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ። ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ። እግዚአብሔርም ትዕግስቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበ ምኔት ሆነ።
ከዚህ በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ በአቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር አረጋውያኑንም ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት አላቸው እርሱም መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መልካም አደረጉብህ በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ።
በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህ በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጕድጓዶችን ሁሉ ሞላ። አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም እግዚአብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን አላቸው።
በአንዲትም ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋራ ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ አላቸው አባ ሙሴም አባቴ ሆይ ምናልባት እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና ብሎ መለሰ።
ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ አላቸው እነርሱም አባታችን አንተስ አትሸሽምን አሉት እርሱም በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለሚለው የእግዚአብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ አላቸው።
ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስለ አልፈለጉ ከእርሱ ጋራ ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መልአክ አየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም በአየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።
ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርስቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው የንስሐን ኃይሏን ተመልከቱ። ሥጋውም በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

❤5
ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት
አባታችን አብርሃም እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ድንኳን ሠርቶ እንግዶች እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ ይኖር ነበር፡፡ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን፣ ርኅራኄውን፣ ትሕትናውን አይቶ ሊፈትነው አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ የተጎዳ ሰው መስሎ፣ ራሱን ፈንክቶ፣ ከጎዳና ላይ ቆሞ አብርሃም ቤት ለሚመጡ እንግዶች “ወዴት ትሄዳላችሁ? እያለ ይጠይቃቸው ጀመር፡፡ እነርሱም ወደ አብርሃም ቤት እንደሚሄዱ በገለጹለት ጊዜ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደተወ፣ ልብሱን ገፎ እንደመለሰው ነገራቸው፡፡ እንግዶቹም እውነት መስሏቸው እያዘኑ ይመለሱ ነበር፡፡ በዚህ የተሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት መምጣት ቀረ፡፡ አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔር ያለ እንግዳ አይበላምና ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡
በሦስተኛው ቀንም ይህን ደግነቱ እግዚአብሔር ተመልክቶ በኦሪት ዘፍጥረት ፲፰፥፩-፲፱ ተጽፎ እንደምናገኘው አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በሦስት ሰዎች አምሳል በመምሬ አድባር ዛፍ ተገለጡለት፡፡ አብርሃምም ከድንኳን ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሰገደና “አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈው” አለ፡፡ እነርሱም “ስለ ደከመን አዝለህ ውሰደን” አሉት፡፡ አንዱን አዝሎ ከገባ በኋላ በአምላካዊ ግብር ሁለቱም ገብተው ተገኙ፡፡ አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ሣራ ፈጥኖ ገባና “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት፡፡ አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፤ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ፡፡ እርጎና ማር፣ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
መብላታቸውም አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በሰው አምሳል ስለ ተገለጡና ለአብርሃምም የበሉ መስለው ስለታዩት ተመግበዋል ተባለ እንጂ ለሥላሴ መብል መጠጥ የሚስማማቸው ሆኖ አይደለም፡፡ ሥላሴ ምግብ በሉ ማለት ቅቤ ከእሳት ገብቶ አልቀለጠም እንደ ማለት ነው፡፡ ከዚያም የታረደው ጥጃ ተነሥቶ “ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ” ብሎ አምላክን አመስግኗል፡፡
ሊሄዱም ሲሉ ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ቃል “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅ ታገኛለች” አለ፡፡ ለጊዜው ስለ ልጁ ይስሐቅ ሲሆን ፍጻሜው ግን እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ሲነግረው ነው፡፡ ይህ ታሪክ የተፈጸመው ከ፳፻-፲፰፻፶ (2000-1850) ዓ.ዓ. አካባቢ ነው፡፡ ከዚህ ብዙ ትምህርት እንማራለን፡፡ ለምሳሌ ያህልም የሚከተሉትን እንጠቅሳለን፡፡
ሀ. የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት
አንድነቱና ሦስትነቱ እንዴት ነው? ቢሉ በዘፍጥረት ፲፰፥፪-፭ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል መመልከት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ “ዓይኑንም ባነሣ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳን ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ እንዲህም አለ፤ “አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈው፤ ውኃ ላምጣላችሁ እግራችሁንም ታጠቡ” የሚለው ኃይለ ቃል ሦስትነቱ “ሦስት ሰዎች… ሊቀበላቸው፣ ወደ እነርሱ” የሚሉት ሐረጋት ሦስተነቱን ሲገልጽ “በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ” የሚለው ዓረፍተ ነገር ደግሞ አንድነቱን ይገልጻል፡፡ እንዲሁም ሦስት መስፈሪያ የሦስትነት፣ እንጎቻው (ዳቦ) አንድ መሆኑ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡
ለ. እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅ እንደሚወልድ ያበሠረበት ቀን ነው፡፡
አባታችን ጻድቁ አብርሃም እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ አበ ብዙኀን (የብዙዎች አባት) እንደሚሆን ቢነግረውም ልጅ ግን አልነበረውም፡፡ በዚህ እንግዳ ተቀባይነቱና መልካም ሥራው እግዚአብሔር በእንግድነቱ ከቤቱ በገባ ጊዜ በእርጅናው ልጅ እንደሚወልድ (ልጅ እንደሚሰጠው) አበሠረው፡፡
እግዚአብሔር እንደ አብርሃም ቅን ልቡና ያላቸውና ለጋሾች ለሆኑ፣ ምጽዋት መስጠትና እንግዳ መቀበል የዘወትር ልማዳቸው አድርገው በሚኖሩ ሰዎች ቤት እንደሚገኝ እንዲሁም ሲገባም የተዘጋ ማኅፀን እንደሚከፍት፣ ቤትንም በበረከት እንደሚሞላ እንዲሁም የተሠወረ ምሥጢር እንደሚገልጽ እንረዳለን፡፡
ሐ. የአብርሃም ድንኳን
አባቶቻችን ሊቃውንት እንደተረጎሙልን የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ በአብርሃም ድንኳን አላፊ አግዳሚ ያርፍበት፣ ይመገብበት እንደነበር ሁሉ እመቤታችን የነፍስም የሥጋም መድኃኒት፣ የዘለዓለም ማረፊያ፣ እውነተኛ መብልና መጠጥ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷ ናትና በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በአብርሃም ድንኳን እንደገቡ፣ በስድስተኛው ወርም ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እመቤታችን ተልኳልና፡፡ (ሉቃ.፩፥፳፮)
በሐምሌ ሰባት (፯) ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት ተገኝቶ እንደባረከው ቅን ልቡና ያላቸውን፣ ለጋሾች ለሆኑ፣ ምጽዋትን ለሚያቀርቡ፣ እንግዳ መቀበል የዘወትር ልማዳቸው ላደረጉ ሰዎች በቤታቸው ይገባል፡፡ የተዘጋውንም ማኅፀን እንደከፈተ ቤቱንም እንደባረከ አይተናል፡፡ ዛሬም እኛም ለተራቡ በማብላት፣ ለተጠሙ በማጠጣት፣ ለታረዙ በማልበስ፣ በመመጽወትና በመሳሰለው ተግባር መኖር፣ በቀና አስተሳሰብ መጓዝ እንዳለብን መጽሐፍ ይነግረናል፡፡
የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ቸርነታቸውና ምሕረታቸው አይለየን፤ አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!!!

ሥርዓተ ማኅሌት ዘ ሐምሌ ገብርኤል
#ስቡህ_ከተባለ_በኃላ
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።
መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡
ዚቅ
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።
ወረብ
"ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።
ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።
ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእሳት አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።
ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።
ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡
ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/
መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡
ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡
ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ኢይኩን ሕፀተ /፪/
ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/
መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡
መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።
ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።
ወረብe
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/
ምልጣን፦
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ
አመላለስ:
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/
ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አሃዛ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ፤ አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡
አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/
ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/

⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜🌺💫🌺
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💐💐 ሐምሌ ፳፫ (23) 💐💐
👇
🍂 ለንጊኖስ ሐራዊ 🍂
👉. ለንጊኖስ ከዮናናውያን ወገን ነው። በጲላጦስ ግዛት ወቅት ከሮማ ወታደሮች አንዱ ነበር። በባሕርዩ ከሰው ጋራ በነገር መቀላቀል አይወድም ነበር። በዚህ ምክንያት በጌታ ሞት አልገባም ብሎ ሸሽቶ በዱር ተደብቆ ዋለ። ወደ ማታ ‘እንደምን ሆነ?’ ብሎ ቢጠይቅ፦ ‘እሱማ ሞተ’ አሉት። ከሞተማ አይሁድና ሮማውያን በሞቱ ያልገባውን እንደ ንጉሥ ጠላት አድርገው ያዩት ስለነበር ከእነርሱ ላለመውጣት ፈልጎ በዱሪ ፈረስ ወደ ቀራንዮ ተራራ ገስግሶ ወጣና የሮማ ወታደሮች የሁለቱን ሽፍቶች ጭን ሲሰብሩ እርሱ ደግሞ ከሞተ አልጎዳም በማለት ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው። ያን ጊዜ ከጎኑ ጥሩ ውኃና ትኩስ ደም የ‹ለ›ን ፊደል መስሎ ወረደ። (ዮሐ. 19 ፥ 34)
👉. ለንጊኖስ አንድ ዐይና ሰው ነበር። ደሙ ተፈንጥቆ ቢነካው ዐይኑ በራ። እርሱም፡- “ዐያችሁ የክርስቶስን ቸርነት! የጠላትን ዐይን ያጠፉታል እንጂ ያበሩታልን?!” ብሎ በዕለተ ዓርብ የተደረጉ ተአምራትን መመርመር ጀመረ። በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን ሲሰማ እውነቱን እንዲያስረዳው ወደ ጌታ አጥብቆ ጸለየ። ጌታም ቅዱስ ጴጥሮስን ልኮለት ወንጌልን በሚገባ ተምሮ በስሙ መስበክ ጀመረ። በኢየሩሳሌም የአይሁድና የሮማውያን ተቃውሞ ስላስቸገረው ወደ ታናሿ እስያ ወርዶ በቀጰዶቅያ ወንጌልን ሰበከ። ብዙዎችንም ወደ ክርስትና ሃይማኖት መለሰ። ከዚህ በኋላ ወንጌልን በማስተማሩ ተከስሶ በቀጰዶቅያ ከተማ አንገቱን ተመትቶ በሰማዕትነት ዐረፈ።
👉. ራሱንም ከቀጰዶቅያ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዷት። አይሁድም ባዩአት ጊዜ ደስ አላቸው። ከዚያም ከኢየሩሳሌም ውጪ በአንዲት ኮረብታ ቀበሯት። ከብዙ ጊዜያት በኋላ በሀገረ ቀጰዶቅያ በስብከቱ ያመነች አንዲት ሴት ነበረች። አንገቱ ከተሰየፈበት ቦታ ቁማ ታለቅስ ነበር። በዚህ ሁኔታ እያለች በእግዚአብሔር ፈቃድ ዐይኗን ታወረች። ዐይኗን እንደሚገልጥላት አስባ ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም ልጇን መሪ አድርጋ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። በዚያም እንዳለች ልጇ ሞተና በኀዘኗ ላይ ኀዘን ተጨመረባት። ስለዚህ ምርር ብላ አልቅሳ ተኛች። በተኛችበትም ቦታ በሕልም ለንጊኖስን ከልጇ ጋራ ዐየችው። ዕገሌ ወደሚባል ቦታ ሂደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ ይላታል። እርሷም ቦታውን ጠይቃ ትደርስና ብታስቈፍር ጥሩ የሽቱ መዐዛ ወጣ። ከዚያም ወደራሱ ሲደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿ በሩላት። በዚህ ድንቅ ተአምር እግዚአብሔርን አመስግና ከልጇ ሥጋ ጋራ ወደ ቀጰዶቅያ በመውሰድ በታላቅ ክብር አስቀመጠችው። ይህም የሆነበት ዕለት ኅዳር 5 ቀን ሲሆን የዕረፍቱ መታሰቢያ ሐምሌ 23 ቀን ነው።
🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱
ሰላም ለለንጊኖስ ዘሒሩተ አምላክ ቀጸበቶ፣
ለጴጥሮስ ረድእ ከመ ይትወከፍ ትምህርቶ፣
ከመ ኢየሐሰብ ቦቱ ዘኲናተ እዱ ርግዘቶ፣
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ፣
ምሕረቶ እሴብሕ ወዓዲ ትዕግሥቶ፡፡
እንዲል ዐርኬ
🤲🏾 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በቅዱስ ለንጊኖስ ጸሎትና ምልጃ ይማረን፤ 🤲🏾
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💐💐 ምንጭ፡-
🍂 መጽሐፈ ስንክሳር፣
🍂 መድበለ ታሪክ፦ መ/ር ዐይነ ኵሉ ያየህ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን።
🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺
⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜🌺💫🌺⚜🌺

❤1
የአሮን በትር (በትረ አሮን)
የተነሣው ውዝግብ፡ ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን በእግዚአብሔር ላይ አምፀው ከተቀጡ በኋላ፣ ሕዝቡ በሙሴና በአሮን ላይ ማንጎራጎር ጀመሩ። "የክህነትንና የአመራርን ሥልጣን ለአሮንና ለሙሴ ወገን ብቻ ለምን ተሰጠ?" የሚል ጥያቄ ተነሣ።
የእግዚአብሔር ፈተናና ምስክርነት፡ እግዚአብሔር ውዝግቡን ለመጨረስ ሙሴን እንዲኽ አዘዘው፦ ከ12ቱ የእስራኤል ነገድ አለቆች ዘንድ አንድ አንድ በትር (በጠቅላላው 12 በትሮች) ተቀብለህ የስማቸውን ስም ጻፍባቸው። የሌዊንም ነገድ በትር በአሮን ስም ጻፍ። በትሮቹንም በምስክሩ ድንኳን (በደብተራ ኦሪት) በጽላቱ ፊት አኖራቸው። "እኔ የመረጥኩት ሰው በትሩ ታበቅላለች" አለ።
በነገው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ፣ የሌዊ ወገን የሆነችው የአሮን በትር አብባ፣ ለምልማ፣ አበቧም አፍርቶ የበሰለ ለውዝ አፍርታ አገኛት (ዘኍ. 17:8)። ይኽ ተአምር የአሮንና የሌዋውያን ክህነት በእግዚአብሔር የተመረጠ መሆኑን አስመስክሯል። በትሪቱም ለትውልድ ምልክት እንድትሆን በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንድትቀመጥ ተደረገች።
ምሥጢርና ምሳሌነት (Typology)
የአሮን በትር ተአምራዊ ባሕርይ ለበርካታ አዲስ ኪዳናዊ ምሥጢራት ምሳሌ ነው፦
ሀ. የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ
ይኽ የአሮን በትር ዋናውና ታላቁ ምሳሌነቱ ለእመቤታችን ነው።
ያለ ዘር ማፍራት (ድንግልና)፡ የአሮን በትር የደረቀች እንጨት ነበረች፤ ውኃ ሳትጠጣ፣ አፈር ሳትተከል፣ ዘር ሳይዘራባትና የተፈጥሮ ሕግን በሚቃረን መልኩ አብባ አፍርታለች። እመቤታችንም እንዲሁ በግብረ ብእሲ (በወንድ ዘር) ሳይሆን፣ ያለ ዘር በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን በማኅፀኗ ይዛ መውለዷን ያመላክታል።
የፍሬው ምሳሌ (ክርስቶስ)፡ ከደረቋ በትር የተገኘው የበሰለ ፍሬ (ለውዝ) የዓለም መድኃኔዓለም የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው።
በሃይማኖተ አበውና በቅዳሴ ማርያም ላይ "የአሮን በትር ያለ ተከልና ያለ ውኃ እንዳበበች፤ እንዲሁ እመቤታችን ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስን ወለደች" እየተባለ ይዘመራል።
ለ. የክርስቶስ ትንሣኤ ምሳሌ
የደረቀች እንጨት ወደ ሕይወት ተመልሳ ማበቧና ማፍራቷ፣ ሞቶ የተቀበረውና በሦስተኛው ቀን በሥልጣኑ የተነሳው የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው ምሳሌ ተደርጋ ትተረጎማለች። ሞት ተሸንፎ ሕይወት መገኘቱን ታሳያለች።
ሐ. የእውነተኛ ክህነትና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ
አሮን በበትሩ መለምለም የተመረጠ ካህን መሆኑ እንደታወቀ ሁሉ፣ ክርስቶስም የሐዲስ ኪዳን ዘለዓለማዊ ሊቀ ካህናት መሆኑን ታሳያለች።
እንዲሁም ፍሬ የማያፈሩ የነበሩት አሕዛብ በክርስቶስ በማመናቸው ምክንያት ሕይወት አግኝተው ፍሬያማ መሆናቸውንና የቤተ ክርስቲያንን አባል መሆናቸውን ታመላክታለች።
በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና በሥርዓተ አምልኮ ያለው ቦታ
በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት፡ በዕብራውያን 9:4 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ምስክሩ ድንኳን ሲጽፍ፣ "በውስጧም መና ያለባት የወርቅ መሶብ፣ ያበበችውም የአሮን በትር፣ የቃል ኪዳኑም ጽላቶች ነበሩ" በማለት በትሪቱ የቃል ኪዳኑ ታቦት አካል ሆና ትጠበቅ እንደነበር ይገልጻል።
በሃይማኖታዊ ድርሰቶች (ለምሳሌ፡ የሐሙስ ውዳሴ ማርያም)፡ "እናትነትሽን የሚመስለው የትኛው ነው? የአሮን በትር ያለ ተከል አበበች አፈረችም፤ እንዲሁም እመቤታችን ሆይ ያለ ወንድ ዘር አምላክን ወለድሽልን..." በሚል ምስጋና በሰፊው ትጠቀሳለች።
"እናትነትሽን የሚመስለው የትኛው ነው? የአሮን በትር ያለ ተከል አበበች አፈረችም፤ እንዲሁም እመቤታችን ሆይ ያለ ወንድ ዘር አምላክን ወለድሽልን..." በሚል ምስጋና በሰፊው ትጠቀሳለች።በአጠቃላይ የአሮን በትር በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን መራጭነትና ታላቅ ተአምር ያሳየች፣ በአዲስ ኪዳን ደግሞ የድንግል ማርያምን ድንቅ ድንግልናና የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን (ተዋሕዶ) በትንቢታዊ ምሳሌነት ያስረገጠች ታላቅ ምልክት ናት።
ንዋይ ካሳሁን

በዓለ ደብረ ታቦር
" ነቢዩ ዳዊት ከተራሮች ከፍ ከፍ ባደረጋት
በኪሩቤል አምሳል በመሰላት
በሩቅ ሰማይ ጥግ በደብረ ታቦር
የቃል ኪዳን ራስ ክርስቶስ በተገለጠባት ጊዜ
እነሆ ጴጥሮስ በመካከሏ
ማደሪያ ይሠራ ዘንድ ተመኘ "
ነግሥ ዘደብረ ታቦር
በዓለ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት መካከል አንዱ ነው ምን አድርጎበታል ቢሉ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት ገልጾበታል ታቦር የተራራ ስም ነው ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚያስተምረው ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር በዚህም ዕለት ዘጠኙን ከእግሩ ደብር ትቶ ሶስቱ ጴጥሮስን ዮሐንሰንና ያዕቆብን አስከትሎ ከርእሰ ደብር ወጣ በዚያም
" በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ ።እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው ። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንስራ አለ ።እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እነሆም ፥ ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።”ማቴ 16፣1-5
በዚህ በዓል በተዋሕዶ የከበረ፣ አምላክ ሲሆን በፈቃዱ የሰውን ባሕርይ ያለመለወጥ የተዋሐደ ጌታ መለኮታዊ ክብሩ፣ የተዋሕዶው ፍጹምነት ይነገርበታል፣ የነቢያትና የሐዋርያት ምስክርነት ይተረጎምበታል፡፡ በባሕላዊ ገጽታው ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለሆነ ‹‹ቡሄ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበት ዕለት ስለሆነ ‹‹የብርሃን በዓል›› ይባላል፡፡
የደብረ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ያህል ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ አስቀድሞ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ ተናግሮ ነበር (መዝ. 88፥12)፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ብርሀነ መለኮቱን በመግለጡ ተራሮችም የፈጣሪያቸውን ተዓምራት በማየታቸው የነቢያት ትንቢት ተፈጽሟል፡፡
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር የገለጠው ከተስእሎተ ቂሣርያ በ6ኛው ቀን (ነሐሴ 13 ቀን) ነው፡፡
♦ ተራራ የወንጌል ምሳሌ ናት፡፡ ተራራ ሲወጡት ያስቸግራል፤ ከወጡት በኋላ ግን ከታች ያለውን ሁሉ ሲያሳይ ደስ ይላል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ታስቸግራለች፡፡ ከተማሯት በኋላ ግን ጽድቅንና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡
♦ ተራራ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ ተራራን በብዙ ጻዕር እንዲወጡት መንግስተ ሰማያትንም በብዙ መከራ ያገኟታልና፡፡ (ሐዋ.14፡22)
♦ ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታልና፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ (ክርስቶስ) በሰማይ ነውና፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል (ፊልጵ. 3፥20)፡፡ በዚህም መነሻነት ጌታችን በልዩ ልዩ ኅብረ አምሳል ለደቀመዛሙርቱ ነገረ ተዋሕዶውን አስረዳቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱም ዛሬ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እንደምታምነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ ሲሆን ሰው መሆኑን አመኑ፣ መሰከሩ፡፡
፨ መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ
ሦስቱ ሐዋርያት በተራራው ሳሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሲጸልይ ሳለ መልኩ በፊታቸው ተለወጠ፡፡ ይህም የመለኮቱን ብርሃን ሲገልጥ ነው እንጂ ውላጤ/መለወጥ አይደለም፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዳለ /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ መገለጥ እንጂ መለወጥ የለም፡፡ ሦስት ክንድ ከስንዝር አካል ምሉዕ ብርሃን ሆኗል፡፡ ይህም አበቦች ከአዕጹቃቸው እንዲፈነዱ ያለ መገለጥ ነው፡፡ ፊቱም እንደ ፀሐይ ብሩህ ሆነ፡፡ ልብሱም እንደ በረድ ጸዓዳ ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ነገረ ተዋሕዶን እንዲረዱ የተደረገ መገለጥ ነው፡፡ ሰውነቱን አልካዱም፣ አምላክነቱን ግን ተጠራጥረው ነበርና አምላክነቱን ከሰውነቱ አዋሕዶ ነገረ ተዋሕዶን ገለጠላቸው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ማቴዎስ፣ በወርኃ ነሐሴ በዕለተ እሑድ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል፡፡
፨ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው
መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴና ኤልያስ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሲነጋገሩ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንደታዩአቸው ይነግረናል እንጅ የተነጋገሩትን ዝርዝር አላስቀመጠልንም (ማቴ. 17፡3)። ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት በትውፊት የከበሩ ናቸውና ከቅዱሳን ሐዋርያት በቃል የተማሩትን የሙሴና የኤልያስ ምስክርነት አቆይተውልናል ከሞተ ብዙ ዘመን የሆነውን ሙሴን ከመቃብር አስነስቶ ቀጥሎም በእሳት ሠረገላ ያረገውንና በብሔረ ሕያዋን የሚኖረውን ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት እርሱ የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከመቃብር ተነሥቶ “እኔ ባህር ብከፍልም፤ ጠላት ብገድልም፤ ደመና ብጋርድም፤ መና ባወርድም እንደ እስራኤልን ከክፋታቸው መልሼ ማዳን ያልተቻለኝ ደካማ ነኝ፤ የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ይሉሃል? የሙሴ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ብሎ ስለጌታችን አምላክነት ምስክርነት ሰጥቷል፡፡
በአጠቃላይ በወንጌሉ ያመንንና በስሙ የተጠመቅን ክርስቲያኖች የደብረ ታቦርን በዓል ስናከብር ቅዱስ ጴጥሮስ “ለእኛ በዚህ መኖር መልካም ነው” እንዳለው በደብረ ታቦር በምትመሰለው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነን የቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ሥርዓት አክብረን፣ በምግባር በትሩፋት አጊጠን ሊሆን ይገባል።
መልካም በዓል

https://forms.gle/Cmfxier6xPsNcPS88
ኦንላይን መንፈሳዊ የቀዳማይ ትምህርት መማር ለምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ በአካል መማር ላልቻሉትም እናጋራቸው

Google Docs
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት በትምህርትና ሥልጠና ዋና ክፍል
የርቀትና ተልዕኮ ንዑስ ክፍል የኦንላይን ተማሪዎች መመዝጋቢያ ቅጽ
❤1