አንቀጸ ብርሃን ትምህርት ክፍል
321 subscribers
29 photos
1 video
1 file
81 links
ይህ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ነው
የትምህርት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ የተለያዩ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው
Download Telegram
❤️ዮሴፍ ዘአርማትያስ በቀደምት አበው 🌷

#ክፍል ሁለት#

ሀ/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ዮሴፍ ያረፈደ ቢሆንም በእምነት ያለውን ጀግንነት ያሳያል ሐዋርያቱ ፈርተው በሸሹበት ሰአት ዮሴፍ በአደባባይ ተአማኝነቱን አሳየ።

ለ/ ሊቁ አውግስጢኖስ ዘሂፖ

የነቢዩ ኢሳይያስን ትንቢት ያሳየናል ኢሳ 53÷9 ዮሴፍ በዝግታ አምነው ነገር ግን በዓላማ የሚሠሩ አማኞችን ይወክላል ባለጥግነቱን ለክርስቶስ በመጠቀሙ ምድራዊ ሀብት ላላቸው ሰዎች ሁነኛ ምሳሌ ነው።

ሐ/ሊቁ አርጌንስ

በተለይ ምሳላያዊ ምልከታ አለው አዲስ መቃብር ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ያሳያል  ዮሴፍ ደግሞ  የአማኞች ክርስቶስን በክብርና በንጽሕና መቀበልን ይወክላል።

መ/ ሊቁ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ

ታሪካዊ ፋይዳው ላይ ያተኩራል ። ዮሴፍ የክርስቶስ እውነተኛ ሞት  እና እውነተኛ መቀበርን በመመስከር የክርስቶስን ሰውነት ለሚክዱ መናፍቃን  ምስክር ይሆናል።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞ

ዮሴፍ ዘአርማትያስ

ባለጸጋና የሸንጎ አባል
ድብቅ ደቀመዝሙር
ጲላጦስን የጌታን ሥጋ የጠየቀ
ወደ ሮማዊያን ሥልጣን የተጠጋ
ድፍረት +መስዋዕትነት

ኒቆዲሞስ

ፈሪሳዊና መምህር
ድብቁን ምሥጢር ፈላጊ ዮሐ ፫
የመግነዙን ጨርቅ ያመጣ
ታላቅ ሰው
በእምነት ያደገ

ኒቆዲሞስ በሌሊት በመምጣት የዳግም ልደትን ምሥጢር የተማረ ነው ዮሐ 3 ከዚያም ደግሞ ስለክርስቶስ ጥብቅና የቆመ ነው ዮሐ 7 በመጨረሻም ገንዞ የቀበረ መምህር ነው ዮሐ 19÷39

ኒቆዲሞስ እምነቱ በጥቂቱ እያደገ የመጣ ነው የዮሴፍ ግን በአንድ ጊዜ የተገለጠ ነው።

❇️የምንረዳው ነገር ❇️

የተደበቀ እምነት በሥራ ካልተገለጠ ከንቱ ነው ድፍረት ደግሞ በከባድ ችግር ውስጥ መገለጥ የሚችል ነው ሁለቱም ሰዎች ሁለት የተለያዩ ደቀ መዛሙርትነትን ያሳያሉ እነርሱም በማደግ የሚገለጥና በአንድ ተግባር የሚታይ ናቸው

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ❇️
ይቀጥላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://t.me/sraged
2
ዮሴፍ ዘአርማትያስ🍐

ክፍል ሦስት

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ  ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።

ዕለተ ዓርብ


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ

ስለድፍረታቸው
በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።

❇️  ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም

ዮሴፍ ዘአርማትያስ


ግልጽ እምነትን ይወክላል
መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
  አዲስ መቃብር  ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።

ኒቆዲሞስ



መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል

❇️ የጌታ መቀበር

የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል 
አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።

❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል

ማጠቃለያ



እምነት በሥራ እንደ ዮሴፍ የሚገለጥ እንጂ ተሸሸጎ የሚኖር አይደለም በሥራ ለመግለጥ ትጋት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ያለንን መሆኑን ከዮሴፍ እንማራለን በክርስቶስ መከራው ውስጥ በመሳተፍ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችንን መገለጥ አለብን።

የአርማትያሱ ዮሴፍን ከዮሴፍ አረጋዊ ጋር በማመሳሰል አንድ ናቸው የሚሉ አሉ ይህ በፍጹም ስህተት ነው ዮሴፍ አረጋዊ በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደምንመለከተው ያረፈው ጌታችን 25 ዓመት ሲሆነው ነው በዚያ ላይ ሥራው እንጨት ጠራቢ የነበረ ነው ይህ ግን ባለጸጋ የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ ነው።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ የሐዲስ ኪዳን ጻድቅ ሲሆን ከኒቆዲሞስ ጋር ሐምሌ 17 ቀን ይከበራል በወንጌል ከተገለጠው ታሪክ በቀር የሚገለጥ ታሪክ ባይኖርም እንግሊዝ ሄዶ እንዳስተማረና መከራን ተቀብሎ ሰማዕት እንደሆነ በትውፊት ይነገራል


ይቆየን
ስለነበረን ጊዜ የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነና የተወደሰ ይሁን
ከትንሳኤው ረድኤት  በረከት ይክፍለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
http://t.me/sraged
ዮሴፍ ዘአርማትያስ🍐

ክፍል ሦስት

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ  ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።

ዕለተ ዓርብ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ

ስለድፍረታቸው
በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።

❇️  ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም

ዮሴፍ ዘአርማትያስ

ግልጽ እምነትን ይወክላል
መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
  አዲስ መቃብር  ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።

ኒቆዲሞስ


መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል

❇️ የጌታ መቀበር

የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል 
አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።

❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል

ማጠቃለያ


እምነት በሥራ እንደ ዮሴፍ የሚገለጥ እንጂ ተሸሸጎ የሚኖር አይደለም በሥራ ለመግለጥ ትጋት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ያለንን መሆኑን ከዮሴፍ እንማራለን በክርስቶስ መከራው ውስጥ በመሳተፍ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችንን መገለጥ አለብን።

የአርማትያሱ ዮሴፍን ከዮሴፍ አረጋዊ ጋር በማመሳሰል አንድ ናቸው የሚሉ አሉ ይህ በፍጹም ስህተት ነው ዮሴፍ አረጋዊ በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደምንመለከተው ያረፈው ጌታችን 25 ዓመት ሲሆነው ነው በዚያ ላይ ሥራው እንጨት ጠራቢ የነበረ ነው ይህ ግን ባለጸጋ የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ ነው።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ የሐዲስ ኪዳን ጻድቅ ሲሆን ከኒቆዲሞስ ጋር ሐምሌ 17 ቀን ይከበራል በወንጌል ከተገለጠው ታሪክ በቀር የሚገለጥ ታሪክ ባይኖርም እንግሊዝ ሄዶ እንዳስተማረና መከራን ተቀብሎ ሰማዕት እንደሆነ በትውፊት ይነገራል


ይቆየን
ስለነበረን ጊዜ የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነና የተወደሰ ይሁን
ከትንሳኤው ረድኤት  በረከት ይክፍለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
http://t.me/sraged
2
የኤማሁስ መንገደኞች

በትንሣኤ እሁድ ከኢየሩሳለም ወደ ኤማሁስ  ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ይሄዱ ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም የሄዱት የቂጣን በዓል ሊያከብሩ ነበር፡፡ 

እነዚኽ ሰዎች ሉቃስና ቀለዮጳ ናቸው። የሚላኑ አምብሮስ ሲናገር የሁለቱ ተጓዦች ስም አማኦን እና ቀለዮጳ ይባላል ይላል Ammanon and Cleophas. 

በምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ትውፊት ቀለዮጳ የራሱ የሉቃስ ስም ነው። ስሙን ደብቆ ነው ይላሉ። ማርቆስ በጌታ ስቅለት ቀን ሊይዙት ሲሉ ልብሱን ጥሎ መሮጡን ስሙን ደብቆ የራሱን ታሩስ “አንድ ሰው” በሚል ጽፏል። ማር.14:51

ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከሚሄዱት ከሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ተገናኘ “እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር። ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር” ሉቃ.24:13
ቅዱስ ቄርሎስ ዘአሌክሳደርያ “ሁለቱ ስለክርስቶስ ይነጋገሩ ነበር። ዳግም በሕይወት እንደማይኖርና በመሞቱ ሐዘንተኛ ሆነው” እነዚኽ ሁለቱ ከሰባ አርድእት መካከል ነበሩ። ከቀለዮጳ ጋር የነበረው ስምዖን ነው ጴጥሮስ ወይም ቀነናዊ ያይደለው ይለናል። (cyril of Alexandria) በሉቃስ ወንጌል  ትርጓሜ። 

ሐዘንተኞች ሆነው ስለ ክርስቶስ እየተወያዩ ይሄዱ ነበር፡፡ አብሯቸው መሆኑን አላወቁም በዚያ ሦስተኛ ሰው ሆኖ አብሯቸው መጓዝ ጀመረ። ይኽ ሰው ኢየሱስ ነበር። ከትንሣኤ በኋላ አካሉ ተለውጧልና ማን መኾኑን አላወቁም። የተገለጠላቸው እንደማንኛውም ሰው ስለነበር አላወቁትም። 
“ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር” ጌታን አላወቁትም ነገር ግን ሊወያዩ ፈቃደኛ ነበሩ ። ዐይናቸውን ይሳወረው አለማመናቸው ነበር። እርሱን እንዳያውቁት ያደረገውም አውቆ ነው። በውስጣቸው ያለውን ጥያቄና ጥርጣሬ እንዲያወጡ እንዲናገሩ ፈልጎም ነው። በመቀጠል በብሉይ ኩዳን መጽሐፍት ጥርጣሬያቸውን ፈወሰ። 

እንግዳው እንዲህ አላቸው “እርሱም፦ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው” ያሳዘናቸው ኢየሱስን ማጣታቸው ነበር፡፡ የጌታም ጥያቄ አስደነቃቸው፡፡ 

“ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው ” “እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው” ውይይታቸውን  ወደ እውነቱ መለሳቸው። ሁለቱም የሆነውን ሁሉ ተረኩለት።

“እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው፡፡ ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፦ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር። ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።” 

ትልቅ ተስፋ ቢኖራቸውም አልትፈጸመላቸውም፡፡ እስራኤልን ያድናል ብለውም ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ እስራኤልን ከሮም ነጻ የሚያወጣ ነበር የመሰላቸው። እንደ ፓለቲካ መሪ ቆጠሩት። አሕዛብንም እንደሚያድን ግን አልተረዱም፡፡ የመስቀል ሞኝነት ታየባቸው። 
 እነዚኽ መንገደኞች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ በቃልና በሥራው ብርቱ ነቢይ” አድርገው ነው የሚያምኑት። ከዚያ በላይ ማየት አልቻሉም። ታላቅ ሰው፣ አስተዋይ ሰው ወይም መልካም ሰው እንደሆነ ብቻ አወቁት። 

ስለ ትንሣኤው በሴቶችና በሌሎች የተነገረውን በፍጹም አላመኑም፡፡ ስለዚህ እንዲህ አላቸው “እርሱም፦ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው። ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።” ሉቃ.24:25

በሕማማቱ ምክንያት ሰዎች ከኃጢአተኝነታቸው ወደ እግዚአብሔር ወዳጅነት ክብር እንዲሚነሡ አረጋገጠላቸው፡፡ ያለ መስቀል ክብር የለምና። ሁሉም ነገር የተፈጸመው ሳይታሰብ ሳይሆን በትንቢት በተነገረው መሠረት ነው። መጻሕፍት ስለመሲሁ የተናገሩትን ቢያውቁ ኖሮ በመስቀል ያምኑ ነበር፡፡

ኤማሁስ ሲደርሱ አልፎ የሚሄድ መሰላቸው ከነርሱ ጋር እንዲሆን ለመኑት፡፡ “ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው” ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከነርሱ ጋር እንዲሆን ለመኑት “እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ” እንግዳ ሆኖ ገባና እንደ አስተናጋጅ ሠራ፡፡ ሁሌም ቢሆን እንደ አገልጋይ ይሠራል። 

“ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።” ባርኮ መቁረሱ የመጨራሻውን እራት አስታወሳቸው፡፡ ምስጢራዊውን እንጀራ ከተቀበሉ በኋላ አይናቸው ተከፈተ አወቁት፡፡ በጸሎተ ሐሙስ እንዳደረገው። በጌታ ትንሣኤ ተሳትፎ ያላቸው (ከሥጋውና ደሙ የተካፈሉ) ዓይናቸውን ይከፍታል። ራሱን የገለጠው በቁርባን ነው። 

ከእነርሱ ተሰወረ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “እርስ በርሳቸውም፦ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ” ልባቸውና አእምሯቸው ተነካ። ትልቅ እውነት ብዙ ጊዜ የሚገለጠው ባልታወቀ አኳኋን ነው፡፡ በተራ የመንገድ ጉዞ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ በተከበረ ሕይወቱ መስቀልና ክብር በአንድ ጊዜ ታዩ፡፡ ስለ ትምህርቱ ሳይሆን ስለ ሕማማቱና ስለ መነሣቱ አስታወሳቸው። “የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ” 2.ጢሞ.2:15

 
ሰዎቹ የመጡበትን  ጉዳይ ትተው ከኤማሁስ በዚያው ሰዓት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ “በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም፦ ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው” ተሰብሰበው ለነበሩት ተረኩላቸው፡፡ “እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው” ሉቃ.24:35
 


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ አራት

ምሥጢረ ቁርባን ፪

በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉዳን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የአቁራርተ መአት ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወደደንና ባፈቀረን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላም እላችኋለው።

👉 ቀሳውስት ኅብስቱን በጻሕል ፣ ወይኑን በጽዋ አድርገው የሚያቀርቡት ቁርባን ወደ አማናዊ የክርስቶስ ሥጋ ወደሙ የሚለወጠው መቼ ነው ? 
ኅብስቱ ሥጋ አምላክ ፣ ወይኑም ደመ አምላክ የሚለወጠው ቄሱ ፣ "
  አእኲተ ፣ባረከ ፤ወቀደሰ " ብሎ በባረከው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ኅብስቱን ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ወይኑንም ደመ ወልደ እግዚአብሔር አድርጎ ይለውጠዋል ፤ በዚህ ጊዜ ፍጹም ሥጋ አምላክ ፣ ደመ አምላክ ይሆናል።

ቅዱስ ቁርባኑን ከመቀበላችን በፊት ምን ማድረግ ይገባናል?

1. ጸሎተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ካህን በጻሕል ፣ወይኑን በጽዋ ዕ አድርጎ እየባረከ ፣ ጸሎተ ቅዳሴውን ሲያደርስበት ፣ ኅብስቱ ተለውጦ የወልደ እግዚአብሔር ደም እንደሚሆን ከልብ ማመን ይገባል።

2. በሐሳብ ፣በቃል ፣በተግባር የፈጸሙትን ኃጢአት ለንስሀ አባት መንገር ይገባል።

3. የሰሩትን ኃጢአት ተናዝዞ ፣ከንስሀ አባት የሚሰጠውን ቀኖና ማለትም ጾም ፣ጸሎት ፣ስግደት ፣ምጽዋትና ሌላም ይህንን የመሰለውን ሁሉ ተቀብሎ መፈጸም ይገባል።

4. ከማንኛውም ኃጢአት መራቅ ያስፈልጋል።

5.ከመቀበላችን በፊት አስራ ስምንት ሰአት መጾም ያስፈልጋል።

6. ገላን መታጠብና ንጹህ መሆን ፤ ከተቻለ ለቁርባን የሚሆን ልብስ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ። ካልተቻለ ግን ያለንን ልብስ ማጠብና መቀበል ያስፈልጋል።

7. በአስራ ስምንት ሰአታት ውስጥ ደም ከፈሰሰ መቀበል አያስፈልግም። በዝንየትም ከተመታን መቀበል የለበትም።
8.  በሶስት ቀን ውስጥ ከሩካቤ ሥጋ መራቅ ያስፈልጋል።
9. ሴትም ብትሆን በወርኃ ትካት ጊዜ መቀበል የለባትም።

ከተቀበሉ በኋላ መደረግ  ያለባቸው ነገሮች 

1. እጅን ወይም ገላን በውሃ አለመታጠብ
2. ምግብን ለብቻ መብላትና ማስተረፍ የለብንም።

3. ከተቀበልን በኋላ ማየ ማቊረርት እስከምንጠጣ  አፍን በመሐረብ መያዝ አለብን ።

4. ብዙ ርቀት አለመጓዝ
5. ላብን የሚያወጣ ሥራን አለመስራት
6. ስግደት አለመስገድ
7. የቆረብንበትን ልብስ አለማውለቅ ፣ ነጠላችንን እስከ አስራ ሁለት ሰአት አለማውለቅ፣ ምራቅን አለመትፋት የመሳሰሉት ናቸው።

👉 የቅርባን አቀባበል ቅደም ተከተል

1. ጳጳሳት
2. ቆሞሳት
3. የቅዳሴው ልዑካን
4. ሕጻናት
5. አረጋውያን
6. ወራዙት ተባእት
7. ወራዙት አንስት
8. ንዑሰ ክርስቲያን ናቸው።

ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

ይቆየን..........

በቀጣይ ክፍል መስዋዕተ ሐዲስና አማናዊ መስዋዕት በሚል ርዕስ እንመለሳለን።

ይቀጥላል.........

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://t.me/sraged
🌾ዕርገተ ክርስቶስ🌾

“እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው” ሐዋ. 1÷9

+ዕርገት ማለት ወደላይ ከፍ ከፍ ማለት ሲሆን የመሬትን የስበት ኃይል የሚያሸንፍ ከፍታ ነው፡፡ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ያረገው የመሬት የስበት ኃይልሳይገድበው ነው፡፡ የክርስቶስ ዕርገት ቀድሞ በትንቢት የተነገረ፤ በሚያምኑት ዘንድ በናፍቆት ሲጠበቅ የቆየ እና በራሱ በጌታችን የተሰበከ ነው፡፡

+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ፴፫ ዓመታት ከሦስት ወራት በምድር ኖሯል፡፡ በ፴ ዓመቱ ተጠመቀ ለ፫ ዓመታት አስተማረ፣ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ ቤዛ ሆነልን፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታንተለይቶ ተነሣ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ተገለጠላቸው፡፡

+ዛሬም ጌታችን ኢየሱስ ከዕርገቱ በፊት ከተነሣ በኋላ ስላስተማራቸው ትምህርቶች፣ ደቀመዛሙርቱን ስላዘዛቸው ትዕዛዝ እናያለን፡፡

+ጌታችን ከተነሣ በኋላ ባሉት ፵ ቀናት በተለያዩ ጊዜያት ለደቀመዛሙርቱ ተገልጾ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ያስተምራቸው ነበር፡፡ ስለክርስቶስ የተነገረውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢት ከዚያ በፊት አላስተዋሉም ነበር፡፡

+ጌታችንም ስለ እርሱ የተጻፉትን ተረጎመላቸው፣ አዕምሮቸውንም ከፈተላቸው መጻሕፍትንም አስተዋሉ፤ እምነታቸውን አጸናላቸው፡፡ ስለ ትንሣኤው የነበራቸውን ጥርጣሬም ከልቦናቸው አጸዳላቸው፡፡

+የሚከተሉትን ትዕዛዛት እና ኃላፊነቶችም ሰጣቸው፡-
"ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡
(ማር ፲፮ ፥ ፲፭)

"ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፡፡
(የሐዋ ፩ ፥ ፭)

"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ… አስተምሯቸው፡፡
(ማቴ. ፳፰ ፥ ፲፱ – ፳)

"እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፡፡
(የሐዋ.ሥ ፩ ፥ ፰)

+በወንጌል ለመስበክ እና በስሙ ለማጥመቅ ወደ ዓለም ሲወጡ፣ እንደሚገረፉ ወደ ነገሥታት የፍርድ አደባባይም እንደሚያወጧቸው ነገሯቸዋል፡፡

+እስከመጨረሻም የጸና ግን ይድናል በማለትእስከ ዓለም ፍጻሜ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆንና መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ኃይልን እንደ ሚያገኙምቃል ገብቶላቸዋል፡፡

+ከሙታን በተነሣ በ፵ ኛው ቀን ደቀመዛሙርቱን ወደ ደብረዘይት ወሰዳቸውና ባረካቸው፡፡ ተሰብስበው ትምህርቱን እየሰሙም ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለ፡፡ ወደ ሰማይም ዐረገ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረው፡፡

+ደቀመዛሙርቱ ክርስቶስ ወደ ዐረገበት ቀና ብለው እየተመለከቱ ሳለ ሁለት መላዕክት ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው “ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይሄ ከናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሏቸው፡፡

+ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ በተነሣ በአርባኛው ቀን በድል ዐረገ፡፡ ወደ ሰማይ እያረገ ሲሄድ እንዳዩት ደግሞ በዓለም ላይ ሊፈርድ ይመጣል፡፡ ማረጉን አምነን ዳግም መምጣቱን እንናፍቅ፡፡�

+ደቀመዛሙርቱም ጌታ ካረገበት ከደብረ ዘይት እግዚአብሔርን እያከበሩ ተመለሱ፡፡ እንደታዘዙት መንፈስ ቅዱስን እስኪቀበሉም በኢየሩሳሌም ቆዩ ፡፡

+እኛም በኢየሩሳሌም በተመሰለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎትና በአገልግሎት በመትጋት ልንቆይ ይገባል ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏🏼
👍2🙏1
በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡

በዚያም ዕለት  በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!
👍1
ክፍል ዐሥራ አንድ
መረጋጋት

2.የነርቭ መረጋጋት

ቁጣቸው የረጋ ሰዎች አሉ፣ ሌሎች ደግሞ ቁጣቸው የሚቀጣጠል ነው። የረጋ ቁጣ ያለው ሰው በፍጥነት አይበሳጭም፣ ምናልባትም በጣም በዝግታ ነው። እሱ ልክ እንደማይናወጥ ተራራ ነው፣ ወይም ደግሞ በማዕበል ቢመቱ እንኳ ሳይነቃነቁ በቦታቸው በጸጥታ እንደሚቆሙትና በዙሪያቸው ባለው መታወክ እንደማይገረሙት በኑቢያ አባይ ላይ የተጋለጡት ስድስቱ ታላላቅ ዓለቶች ነው።

ነገር ግን ነርቮቹ ስስ የሆኑ ሰው በቀላሉ ይቆጣል፣ ምናልባትም በጣም በትንሽ ምክንያት ወይም ያለምንም ምክንያት፣ በውስጣዊ ጥርጣሬውና በምናቡ ብቻ ይጮኻል፣ ይደነፋል።

ነርቭ የረጋው ሰው ጠንካራ ሰው ነው፤ ምክንያቱም ውጫዊ ሁኔታዎች ሊያስቆጡት አይችሉም፣ ይልቁንም ጠንካራ ነርቮቹ ሊቋቋሟቸው ይችላሉ። በዚህ የውስጥ ጥንካሬውም የሰዎችን ክብርና አድናቆት ያተርፋል።

የሚደነፋውና የሚጮኸው ግን፣ ምንም ያህል ቢቆጣና ሁከት ቢፈጥር፣ ቢሳደብና ቢዝት፣ ሌሎችንም የሚያስፈራ ቢመስልም፣ የኃላፊነት ክብር አያገኝም። መነሳሳቱ የቁጣውን ድክመት ወይም የባህሪውን ድክመት ያሳያል።

ማንም ሰው ይህንን ደካማ ሰው የመሳቂያ ወይም የመጫወቻ ሊያደርገው ቢፈልግ ይችላል። ለምሳሌ ነርቭ ደካማ የሆነ መምህር ቢኖር፣ የተማሪን ስህተት ወይም ሁከት መሸከም አይችልም፤ ስለዚህ ማንኛውም ተማሪ ለክፍል ጓደኛው፣ "ይህ መምህር ሲበሳጭ ማየት ትፈልጋለህ?" ሊለው ይችላል። ለተማሪዎቹ በጭራሽ አያስፈራም። እሱ ዝም ብሎ አስቂኝ ሆኖ ይታያል። ስለዚህ ተማሪው መምህሩን እንደሚያስቆጣው የሚያውቀውን ነገር ያደርጋል፣ ከዚያም ቁጭ ብሎ ይመለከታል!

የነርቭ መረጋጋት በሁለት ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው፦ በአካላዊ እና በሥነ-ልቦናዊ ሁኔታ። ነርቮች እንዲደክሙ የሚያደርጉ ብዙ አካላዊ ምክንያቶች አሉ ነገር ግን አሁን በሁሉም ውስጥ አንገባም። እዚህ ላይ የሰዎችን ነርቭ፣ አልፎ ተርፎም ምርጥ የተባሉ ሰዎችን ጭምር በተደጋጋሚ ወደሚያደክም አካላዊ ምክንያት ትኩረታችንን እናዞራለን፣ እሱም ድካም ነው። ሰውነት በድካምና በውጥረት ከዛለ፣ ነርቮች ምንም ነገር መሸከም የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ።

በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እራስዎን ካገኙ የእኔ ምክር፣ ከማንም ጋር፣ በተለይም ጥብቅ አመለካከት ካላቸውና በቀላሉ ሊያምኑ ከማይችሉ ሰዎች ጋር ወደ ረጅም ውይይት ወይም ሰፊ ክርክር እንዳይገቡ ነው። በእንደዚህ ዓይነት የድካም ስሜት ውስጥ ሆኖ አስፈላጊ ጉዳዮችን መወሰን ወይም ችግሮችን መፍታት ተገቢ አይደለም። ሲደክሙዎት ወደ ክርክር እንዳይገቡ ተጠንቀቁ፣ ቁጣዎን ሊያጡ ይችላሉና።

የድካም ሁኔታ እንቅልፍን፣ ወይም ቢያንስ እረፍትና መዝናናትን ይፈልጋል። የሚወዷቸው ሰዎች የእርስዎን የድካም ሁኔታ ሊገነዘቡ ይገባል፣ እናም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ወደ ውይይት ወይም ችግሮችን ለመፍታት ሊጎትቱዎት አይገባም።

ለነርቭ መረጋጋት ከሚረዱ መንገዶች አንዱ የደስታና የደስተኝነት መንፈስ ነው። ደስተኝነት በሰውነት ውስጥ ነርቮችን የሚያረጋጋ የመዝናናት ሁኔታን ይፈጥራል። በደስተኝነት መንፈስ የሚታወቁት ሁሉ የረጋ ነርቭ አላቸው፣ በቀላሉም አይቆጡም። ትንኮሳን በሚያስቅ ቀልድ ሊመልሱት ይችላሉ፣ ይህም ሊያስቆጣቸው የሚሞክረውን ሰው ጭምር እንዲስቅ ያደርገዋል፣ በዚህም ጉዳዩ ይረግባል።

አስተሳሰባቸው ጠባብ የሆኑና ጥብቅ የሆኑ፣ ሳቅ ኃጢአት እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ነርቮቻቸው ብዙ ጊዜ የተወጠሩ ሆነው ያገኟቸዋል። የሰዎችን ባህሪ የሚቀበሉበት ጥብቅ ጭካኔ ብዙ ጊዜ ከባቢ አየር እርጋታውን እንዲያጣና ሁኔታው እንዲባባስ ያደርገዋል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ ለመረጋጋት አስተዋፅኦ ስለሚያደርጉ ሁኔታዎች ስንነጋገር ወደዚህ ነጥብ ለመመለስ ተስፋ አደርጋለሁ። ነገር ግን መረጋጋት ከሌላቸው ነርቮች ስለሚመጣው ጉዳት ለመነጋገር በቀጥታ እንቀጥል።

ነርቮቹ በቀላሉ የሚቀሰቀሱበት ሰው በዚህ ምክንያት እራሱን ይጎዳል፣ ሌሎችንም ይጎዳል። እራሱን በአእምሮ ህመም፣ በልብ ህመም እና በከፍተኛ የደም ግፊት፣ እንዲሁም ከመጠን በላይ በመቆጣቱና በቁጣ ፍንዳታው በሚመጡ የተለያዩ የስነ-ልቦና እክሎች ይጎዳል። ነርቮቹን ለተወሰነ ጊዜ ለማረጋጋት ማስታገሻዎችንና የእንቅልፍ ክኒኖችን ለመውሰድ ሊገደድ ይችላል፣ ከዚያም ውጥረቱ በውስጣዊ ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶችና በውጫዊ ትንኮሳዎች እንደገና ይመለሳል፣ እሱም እንደገና ወደ ማስታገሻዎች ይመለሳል! ነርቮቹ ልክ እንደ ላስቲክ ይሆናሉ፣ እሱም በተደጋጋሚ በመሳብና በመላላት የመለጠጥ አቅሙን ያጣልና ይበላሻል።

እንዲህ ዓይነቱ ሰው በነርቭ በሽታዎች በሚመጡ ችግሮች አዙሪት ውስጥ ይገባል። ሕክምናው ምልክቶቹን ለማከም ቢሞክርም፣ ከሁሉ በላይ አስፈላጊው ነገር ከነርቭ ችግሮች በስተጀርባ ያሉትን ምክንያቶች ማከም ነው፣ በመጀመሪያም ሰውየውን መረጋጋት እንዳለበት ማሳመን ነው። የረጉ ነፍሳት በነርቭ ህመም አይሰቃዩም፣ ማስታገሻዎችም አያስፈልጓቸውም ምክንያቱም በተፈጥሯቸው ሰላማዊ ናቸው።

ነርቮቹን መቆጣጠርና ማረጋጋት የሚችል ሰው ቃላቱንም መቆጣጠርና ስህተት እንዳይሠራ ማድረግ ይችላል። እንዲሁ ባህሪውን መቆጣጠርና እራሱን ማዘዝ ይችላል፣ በዚህም በሚሳተፍባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ከመሸነፍ ይልቅ ያሸንፋል።

እነዚህ ሁሉ ነገሮች ጤናማ መንፈሳዊ አመለካከትንና ግለሰቡ በመረጋጋት ባህሪውን፣ መብቱንና ክብሩን መጠበቅ እንደሚችል የውስጥ እምነትን ይፈልጋሉ። የነርቭ ፍንዳታዎች ግልጽ ስህተት መሆናቸውን ማወቅ አለበት። ይህ በሌሎች ሰዎች ፊት ግልጽ የሆነ ድክመት ነው፣ ይህም የሚመለከተው አካል ችግሮቹን በምክንያትና በሎጂክ በረጋ መንፈስ መፍታት እንደማይችልና በዚህም ወደ ነርቭ ፍንዳታዎች እንደሚመራ ጮክ ብሎ ያውጃል። ነርቮቹ የሚቀጣጠሉበት ሰው ክፉ ነገር እንዳሸነፈውና እሱን መቋቋም እንዳልቻለ አመልካች ነው፣ ለዚህም ነው የተቀጣጠለው፤ ሐዋርያው ግን እንዲህ ይላል፦ "ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።" (ሮሜ 12:21)።

የሚቆጣ ነርቭ ያለው ሰው ምንም የመቋቋም አቅም የሌለውና በውስጡ የፈረሰ ሰው ነው፤ የረጋ ነርቭ ያለው ሰው ግን ጠንካራና ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ሰው ነው።

3. የምላስ(የአንደበት) ፀጥታ

ይቀጥላል

ግንቦት 28 2018 ዓ/ም
https://t.me/z2e1ms
1
ክፍል ዐሥራ ሁለት

መረጋጋት



የልሳን (የአንደበት) ዝምታ


በሰላማዊ መንገድ የሚናገር ሰው በሁሉም ዘንድ የተወደደ ነው፤ የማይረጋጋ አንደበት ግን ባለቤቱን ለብዙ ስህተቶች ይዳርገዋል። የማይረጋጋ አንደበት በርካታ ውጫዊ ምልክቶች አሉት፣ ከእነሱም መካከል፦

1. ለፍላፊ (ተናጋሪ) አንደበት፦

ንግግሩን በጭራሽ የማያቆም አንደበት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን፦ «በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት አይታጣም» ይላል (ምሳሌ 10:19)። ይህ አንደበት ከአቅሙና ከዕውቀቱ በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ ጭምር በማንኛውም ርዕስ ላይ ያለማቋረጥ ይናገራል። ዝም ማለት አይችልም። በከንፈሮቹና በጥርሶቹ መካከል እራሱን መግታት አይችልም። መውጣትና መናገር አለበት፣ በጣም ረቂቅ በሆኑ የሳይንስና የፖለቲካ ነጥቦች ላይ እንኳ በጭራሽ ሊያቆም አይችልም ዋናው ነገር መናገሩ ብቻ ነው፣ ስለ ሌሎች ሰዎች ጉዳይ፣ ስለ ምሥጢራቸውና ስለ ግል ሕይወታቸው ጭምር ይናገራል። ይህ የማይረጋጋ አንደበት ነው፤ በመረበሹም ምክንያት ባለቤቱ ሊቆጣጠረው ወይም ሊገራው አይችልም። ሐዋርያው ያዕቆብ፦ «ልሳኑን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የዚህ ሰው አምልኮ ከንቱ ነው» ይላል (ያዕ 1:26)። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው አንደበቱን ሊገታ ይገባል እንጂ ያለ ገደብ ከአንዱ ርዕስ ወደ ሌላው እንዲንከራተት በነፃነት ሊተወው አይገባም። ይህንን ማድረግ ካልተቻለው ግን፦ «አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ» እያለ ይጸልይ (መዝ 141:3)።

2. ከማይረጋጋ አንደበት የሚወጣ ስለታም፣ ከፍ ያለና ጮክ ያለ ድምፅ፦

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔርና በነቢዩ ኤልያስ መካከል በነበረው ውይይት የረጋ ንግግር ምሳሌ ይሰጠናል፦ «ታላቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮችን ሰነጠቀ ዓለቶችንም በእግዚአብሔር ፊት ሰበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ከነፋሱም በኋላ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ... ከምድርም መንቀጥቀጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ ቀጭን የዝምታ ድምፅ ሆነ... ድምፅም ወደ እርሱ መጥቶ፦ ኤልያስ ሆይ፥ በዚህ ምን ታደርጋለህ? አለው» (1 ነገ 19:11-13)፤ ይህ ለእርሱ የተናገረው የእግዚአብሔር ድምፅ ነበር። የረጋ ሰው እንደሚያልፍ ነፋስ በጸጥተኛ ድምፅ ይናገራል፣ የማይረጋጋ ሰው ግን እንደ ኃይለኛ ውሽንፍር ባለ ድምፅ ይናገራል።
በስብከት ጊዜ እንኳ በከፍተኛና በስለታም ድምፅ የሚሰብኩና ምዕመናንን በጭካኔ የሚገሥጹ ሰበካውያን አሉ። «የመድረኩን ምሰሶዎች ያናውጡ» እና አድማጮቻቸውን በመቀመጫቸው ጠርዝ ላይ ያስቀምጡ ስለነበሩት የቀድሞ የሕዝብ ተናጋሪዎች የተባለው በእነሱ ላይ ይሠራል። እንዲህ ዓይነቱ የሰበካ ዘዴ መንፈሳዊ ተፅዕኖ ከማምጣት ይልቅ ሕዝቡን ያውካል። መንፈሳዊው ሰባኪ ግን ምዕመናንን የሚያምንደው በረጋ መንፈሳዊ ትምህርትና በእርሱና በእነሱ ውስጥ ባለው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፤ በሰውነት ሕዋሳት መነቃቃት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ውጤታማነት በእግዚአብሔር ፍቅር ያቀጣጥላቸዋል። ብዙ ሰዎች እራሱ በጣም በተደሰተ ሰባኪ በስብከቱ ወቅት ይነካሉ። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይህ ተፅዕኖ ይጠፋባቸዋል። በሌላ በኩል ግን የረጋ መንፈሳዊ ማሳመን በነፍስ ውስጥ የበለጠ ዘላቂና የላቀ ተፅዕኖ አለው።
ምንም እንኳ ሰዎች እንዲሰሙ አንዳንድ ጊዜ በሕዝብ መካከል ጮክ ያለ ድምፅ መጠቀም ቢያስፈልግም፣ በግል ውይይቶች ውስጥ ግን ይህንን መጠቀም በፍጹም አያስፈልግም የረጋ ሰው ከሌሎች ጋር ሲነጋገር ድምፁን ከፍ አያደርግም። ከአድማጩ ፍላጎት በላይ የሆነ ድምፅ አይጠቀምም። ስለዚህ በውይይቶቹ ውስጥ ምንም ዓይነት ጫጫታ የለም። አንዳንድ ሰዎች ውይይት ሲያደርጉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ንግግር ሲያቋርጡ፣ የሚሰሙት ሰዎች የሚጣሉ የሚመስላቸው ጊዜ የለምን? አዎን፣ በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ይጮኻሉ፣ በሹክሹክታ ሲያወሩም ይንጫጫሉ። በፍጥነት ይናገራሉ፣ ድምፃቸውም የጫጫታ ነው።

3. የሰላም እጥረት ካለበት ድምፅ ውጫዊ ምልክቶች መካከል አሳማሚና ሻካራ ቃላትን የመጠቀም ዝንባሌም አንዱ ነው፦

ለምሳሌ ንግግሩ ሻካራና ከባድ የሆነ፣ ቃላቶቹ መራራ፣ አሳማሚ፣ ነቃፊ፣ ነካሽና አጥፊ የሆኑ ሰው ሊኖር ይችላል። ቃላቶቹ ከአፉ የሚወጡት ልክ ከሮኬት እንደሚተኮስ ጥይት ነው። ያንኑ አመለካከትና ሀሳብ በረጋ ቃላት መግለጽ ይችል ነበር።

4. የአንደበት ጭምትነት ከሆኑት ገጽታዎች አንዱ በውይይት ውስጥ መረጋጋት ነው፦

የረጋ ሰው በጸጥታ ይወያያል፣ በዚህም መንገድ ሌሎችን ያሸንፋል። ቅዱስ ዲዲሞስ ዕውሩ ፈላስፎችንና አረማውያንን ያለ ምንም ጥቃት እጅግ በጣም በትሕትና ይከራከራቸው እንደነበረው ማለት ነው። የእርሱ ዘዴ እነሱን ማሸነፍ እንጂ መርገጥ ወይም ማሳፈር አልነበረም።
የማይረጋጋው ተናጋሪ ግን ውይይቱን ወደ ጠብ ወይም ክርክር ይለውጠዋል፣ በዚህም ውይይቱ ይሞቃል፣ ከባቢ አየሩም ይወጠራል፣ እጅግም ይበከላል። በእርሱ አቀራረብ ውስጥ ለመዝለልና ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጁነትን፣ እና አመለካከቱን ሙሉ በሙሉ ሳይሰማ ለመመለስ ጠንካራ ዝንባሌን ታገኛለህ። ከእርስዎ ጋር የሚወያየው እርስዎን ለመረዳት ወይም ከእርስዎ ጋር ወደ እውነት ለመድረስ ሳይሆን በራሱ ክርክሮች እርስዎን ለማስደንገጥና እርስዎን ለማሸነፍ፣ የእርስዎን አመለካከቶች ለመስበርና ድክመትዎን ለማጋለጥ ነው። በውይይቱ ወቅት እርስዎንና የእርስዎን አመለካከት ማሾፍና የመሳቂያ ማድረግ እንዳለበት ይሰማዋል፣ ልክ እርስዎ ጠላት እንደሆኑና እሱ መበቀል እንደሚፈልግ።
በሌላ በኩል ግን በረጋ መንፈስ የሚወያይ ሰው በውይይቱ ወቅት እርስዎን እንደ ጓደኛ ያሸንፍዎታል። ሙሉ በሙሉ በረጋ መንፈስ፣ በነጥብ ላይ ያተኮረ ንግግር ያደርጋል፣ እርስዎ ሲናገሩ አያቋርጥም ወይም የግል ጥቃት አይሰነዝርም፣ እርስዎ በጣም ከተደሰቱ ደግሞ ያረጋጋዎታል። እንደተሸነፉ ሳይሰማዎት በእርሱ አመለካከት ላይ እንዲስማሙ ሊያሳምንዎት ይችላል። የእርሱ መረጋጋት ተቃዋሚዎች እንደሆናችሁ በምንም መንገድ እንዲሰማችሁ አያደርግም፣ ይልቁንም አብራችሁ ወደ እውነት ለመድረስ የምትጥሩ ሁለት ጓደኛሞች እንደሆናችሁ እንጂ። ከዚህ በተቃራኒ ግን በውይይቱ ወቅት ዓይኖቹ የሚቀሉ፣ ድምፁ ከፍ የሚልና በንዴትና በባለጌነት ተቃውሞዎችን እያነሳ የሚበሳጭ በጣም የተወጠረ ተናጋሪ አለ። ስድብን የሚያመለክቱ ቃላትን እንኳ ሊጠቀም ይችላል።
የማይረጉ ሰዎች በሚወያዩበት ጊዜ ሁል ጊዜ እርስ በርሳቸው ይቋረጣሉ። በውይይቱ ውስጥ አምስት ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ አራቱ በአንድ ጊዜ ይናገራሉ፣ አንዱ ብቻ ጫጫታውን ይሰማል። ከእነሱ መካከል አንዳቸውም የሌላውን ለመስማት ዝግጁ አይደሉም። ሁሉም እርስ በርሳቸው ይቋረጣሉ፣ ነገር ግን መቶ የረጉ ሰዎች ውይይት ቢያደርጉ ኖሮ በጥብቅ ሥርዓት ይከናወን ነበር፣ የውጭ ድምፅ አይሰማም ነበር።
ብዙ ሀሳቦች እርስ በርሳቸው ቢታገሉም፣ እውነት ግን አንዲት ብቻ ናት። ሆኖም እያንዳንዱ ሰው እውነት የራሱ የግል አመለካከት እንደሆነ ያስባል። መረጋጋት ካለ፣ አመለካከታቸው ምንም ያህል የተለያየ ቢሆንም፣ በፍቅር በተሞላ ውይይት ከሰዎች ጋር በአንድነት መምጣት ይችላሉ።

5. ስለ ውይይት ያልነውን ስለ ተግሣጽም (ስለ ወቀሳም) ማለት እንችላለን፦
1
የጸጥታ ወቀሳ ወደ ሰላም ይመራል፣ ጮክ ያለው ግን ክፍፍሉንና ክርክሩን ያባብሳል። ጌታ ኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ጴጥሮስን የገሠጸበት ውብ ምሳሌ አለን። እርሱ፦ «አንተ ከዳተኛ ና፣ አንተ ገረድ የፈራህ፣ የማውቀውም የለም ብለህ የማልህና የረገምክ። ሁሉም ቢክዱህ እኔ አልክድህም ብለህ ከዚህ በፊት የገባኸኝ ቃል ኪዳን ይህ ነውን?» አላለውም።
ጌታ ኢየሱስ አንዲትም አሳማሚ ቃል አልተናገረውም፣ ዝም ብሎ በረጋ መንፈስ፦ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?» አለው። እርሱም፦ «አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ» አለው። እርሱም፦ «ግልገሎቼን አሰማራ» አለው። ደግሞ ሁለተኛ ጊዜ፦ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?» ... «በጎቼን ጠብቅ» ... «በጎቼን አሰማራ» አለው (ዮሐ 21:15-17)። ጥያቄውንም ጴጥሮስ እስኪረዳው ድረስ ሦስት ጊዜ ደገመው። ተግሣጹ ውጤት ነበረው፣ የጴጥሮስ ልብ ሳይቆስል ፍቅር ተመሠረተ
6. አንደበት የረጋ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም የሚያረጋጋ መሆን አለበት፦

ለሚያረጋጋ ንግግር እንደ ምሳሌ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል አለን፦ «የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች» (ምሳሌ 15:1)። ሌላው ምሳሌ የንሥሐ አባትን ነፍስ የሚያረጋጋ፣ የልብ ሰላም የሚሰጥ፣ በኃጢአቱ ምክንያት የመጣበትን የልብ አለመረጋጋት የሚያስወግድ የሚያጽናና የንሥሐ አባት ነው። ከዚህ በተቃራኒ ግን ተንሥሐተኛው ሰላሙን እንዳጣ፣ በተስፋ መቁረጥ እንደተሸነፈና መጥፋቱ እንደማይቀር እየተሰማው እንዲሄድ የሚያደርግ የንሥሐ አባት አለ።
የረጋ ሰው መረጋጋት ወደ ሌሎች ይፈሳል፣ ከተጨነቁም ያረጋጋቸዋል። የማይረጋጋው ሰው ግን በረጋ መንፈስ ያሉትን እንኳ በሁከቱ ይበክላቸዋል፣ ያናውጣቸዋልም።

https://t.me/z2e1ms
ግንቦት 29 2018 ዓ/ም

ለሌሎች እናጋራ
ክፍል ዐሥራ ሦስት
መረጋጋት


የፊት ገጽታ መረጋጋት


ጥቂት ሰዎች የፊታቸውን ገጽታ መቆጣጠር ይችላሉ። በአብዛኛው የፊት ገጽታ የልብን ሁኔታ ይገልጣል፣ ሰውየው ቢወደውም ባይወደውም። ልቡ ከተጨነቀ፣ ግራ መጋባቱ በፊቱ ገጽታ ላይ ይታያል። ከተቆጣ፣ ከተበሳጨ፣ ከተጸየፈ ወይም ከፈራ፣ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች በፊቱ ገጽታ ላይ ወይም በዓይኖቹ አመለካከት ላይ ይታያሉ፣ በሃሳብ ተበታትኖ በህልም ዓለም ውስጥ ቢሆን እንኳ፣ የፊቱ ገጽታ ይገልጠዋል። የሰው የፊት ገጽታ በውስጡ ስላለው ነገር ያለፍላጎቱ የሚሰጠው የእምነት ቃል ነው መረበሹን ሊክድ ይችላል፣ ነገር ግን የፊቱ ገጽታ በክህደቱ ውስጥ እውነት እየተናገረ እንዳልሆነ ያሳያል። አንዳንድ ጊዜ ሰው መረጋጋቱን ያጣል፣ እናም ሰዎች ምክንያቱን ሲጠይቁት ይክዳል። ነገር ግን የድምፁ ቃና፣ የእጆቹ እንቅስቃሴ፣ የዓይኖቹ አመለካከት፣ ምናልባትም የከንፈሮቹ እንቅስቃሴና የፊቱ ቀለም ሁሉ በውስጡ ስላለው ነገር ምንም ጥርጥር በማይተው መልኩ ይናገራሉ። ልብ ምስጢሩን የሚሸሽግ የተቆለፈ የቅምጥ ቤት ይመስላችሁ! እሱ ብዙ ጊዜ በፊቱ ገጽታ አማካኝነት በግልጽ ይገለጣልና በግልጽ ይወጣል። የሰው ዓይን በአብዛኛው የውስጥ ስሜቱ የሚታይበት እና ሀሳቡም ጭምር ሊነበብበት የሚችል መስታወት ነው። ማንኛውም አስተዋይ ሰው ማየት ይችላል፤ ለዚህም ነው አንዳንድ ሰዎች አብረዋቸው ከሚቀመጡት ሰዎች ጋር ሲሆኑ በዓይኖቻቸው ውስጥ ያለውን ስሜት ወይም መነካካት እንዳያዩባቸው ጥቁር መነጽር የሚያደርጉት። የረጋ ልብ ያለው ሰው ዘና ያለ፣ ብሩህ የፊት ገጽታ አለው። ከእርሱ ጋር መቀመጥና ፊቱን መመልከት፣ ከልቡ ፈስሶ የፊቱ ገጽታ የሚሸፍነውን ያንን ድንቅ መረጋጋት ማስተንተን ትወዳለህ። ስለሆነም፣ ከመነኮሳት አንዱ ቅዱስ አባ እንጦንስን፦ "አባት ሆይ፥ የእርስዎን ፊት ማየት ብቻ ይበቃኛል" ማለቱ በጭራሽ አያስደንቅም፤ ምክንያቱም በቅዱሱ ፊት ላይ ልቡን የሞላውን የውስጥ ሰላም ማየት ይችል ነበርና፣ ንጽህናንና መለኮታዊነትንም ሁሉ በዚያ አየ። ነገር ግን የማይረጋጋ ልብ ያለው ሰው የፊት ገጽታው የተወጠረ ነው። በቁጣ ወይም በስሜት ውስጥ ሲሆኑ፣ እንዲሁም በሐዘን ወይም በጭንቀት ውስጥ ሲሆኑ የውስጥ ሰላምና መረጋጋት ስለሚያጣቸው የፊት ገጽታቸው ዘና የማይሉ ሰዎች አሉ። ይህ ሁሉ በፊታቸው ገጽታ ላይ ይታያል። ሁኔታቸው የፊታቸው ገጽታ በጣም የሚያስጨንቅ ከመሆኑ የተነሳ ለረጅም ጊዜ ልታያቸው የማትችልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል። አገላለጻቸው የተወጠረ ስለሆነ፣ ለሚመለከቷቸው ሰዎች መረጋጋት አስተዋፅኦ አያደርጉም። ስለዚህ በፊቱ ገጽታ ላይ ቁጥጥር ሊኖረውና ሊያረጋጋው ያስፈልጋል። ለሰውየው ከሁሉ የሚበጀው ልቡን ማረጋጋት ነው፣ ከዚያም የፊቱ ገጽታ በራሱ ጊዜ ወዲያውኑ ይረጋጋል።

https://t.me/z2e1ms
ግንቦት 30 2018 ዓ/ም

ለሌሌች እናጋራ
ክፍል ዐሥራ አራት
መረጋጋት


የሰውነትና የሕዋሳት ጸጥታ


ሰውነታቸው የማይረጋ፣ በአንድ ቦታ ሊቀመጡ የማይችሉ ሰዎች አሉ። መውጣትና መግባት፣ መነሳትና መቀመጥ፣ መሄድና መምጣት ይፈልጋሉ። በቤት ውስጥ እንኳ ለረጅም ጊዜ አይረጉም፣ ጉብኝቶች፣ ሽርሽሮች፣ ለሰውነት መዝናኛዎችና ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ መኖር አለበት። እነዚህ ሰዎች ተለዋዋጭ፣ የማይረጋጋ ሰውነት ያላቸው ናቸው። ይህ እራሳቸውን ለሰውነት ጸጥታ ከሚያስገዙት መነኮሳት ተቃራኒ ነው። ባህታዊው መነኩሴ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ሳይወጣ ወይም ሳይንቀሳቀስ በበዓቱ ውስጥ ለቀናት ወይም ለሳምንታት ሊቆይ ይችላል፣ ቢንቀሳቀስም ጠቃሚ ለሆነ ነገር ነው። ይህ የሰውነት ጸጥታ ያላቸው ሰዎችና ያለ ምንም ምክንያት በሚንቀሳቀሱት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የማይረጋጋው ሰው በአንድ ቦታ ብቻውን ቢቀመጥ እንኳ፣ ሰውነቱ ያለማቋረጥ ሲንቀሳቀስ ታገኘዋለህ። ከማንኛውም ሰው ጋር ቢነጋገር እጆቹ፣ እግሮቹና ራሱም ሲንቀሳቀሱ ታገኛለህ። ሲናገር በእጁ ሊጠቁም ወይም ጣቱን ሊያነሳ፣ ወይም እጆቹን ያለማቋረጥ ወዲያና ወዲህ ሊያደርግ ይችላል። ሁለት ሰዎች ውይይት ሲያደርጉ እጆቻቸውን ብታይ ሁል ጊዜ ሲንቀሳቀሱ ልታገኛቸው ትችላለህ። ይህ ወታደሩ ሲናገር ጸጥ ብሎ መቆም ካለበት፣ እጁን ካንቀሳቀሰም "ጸጥ በል!" ከሚባለው ከውትድርና ሕይወት ፍጹም ተቃራኒ ነው። አንዳንድ ጊዜ የውስጥ ስሜትን ለመግለጽ ትንሽ እንቅስቃሴ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የማያቋርጥ፣ የማይረጋጋ እንቅስቃሴ መሆን የለበትም። የብዙ ሰዎች እንቅስቃሴ መረጋጋት ማጣትን ያሳያል! እንዲህ ዓይነቱ ሰው ቢገባ ወይም ቢወጣ, በሩን በመክፈትና በመዝጋት ብቻ ጫጫታና ሁከት ይፈጥራል። ቢራመድ፣ በጫጫታ ይራመዳል። ቢጠጣ፣ ሲጎነጭ ድምፅ ይሰማል። በሻይ ኩባያ ውስጥ ስኳር ለማሟሟት ቢፈልግ እንኳ፣ ልክ ደወል የሚደውል ይመስላል። በእንቅስቃሴው ውስጥ ምንም ዓይነት ጸጥታ የለም፣ የረጋው ሰው ግን በቦታው በጸጥታ ይቆያል፣ ምንም ዓይነት ድምፅም አያሰማም። በተረጋጋ ሀገር ውስጥ የተቃውሞ ሰልፎች እራሳቸው የረጉ ሆነው ታገኛቸዋለህ! በእኛ መዝገበ ቃላት መሠረት ግን፣ ሰልፍ ማለት እዚህም እዚያም ጫጫታና ሁከት ማለት ነው፦ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ሲጮኹና መፈክሮችን ሲያሰሙ፣ እጆቻቸውን እያወዛወዙ ሁሉንም ነገርና ሰውን ሁሉ ልክ እንደ አብዮት ሲያውኩ ይታያሉ። በተረጋጋ ሀገር ውስጥ ግን ሰልፈኞች ይወጣሉ፣ ፍላጎቶቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን በያዙ ባነሮች አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ሀሳባቸውንም በጸጥታ ተሸክመው ከአንዱ ጎዳና ወደ ሌላው ይንቀሳቀሳሉ። የሕዋሳት መረጋጋት ከሰውነት መረጋጋት ጋር አብሮ ይሄዳል። የሕዋሳት መረጋጋት ባለቤቱ በረጋ መንፈስ እንዲያስብ ይረዳዋል። የማየት፣ የመስማትና የማሽተት ተለዋዋጭ ሕዋሳት ሀሳቦችን ይወልዳሉ፣ ሀሳቦች ደግሞ በልብ ስሜት ላይ ተፅዕኖ አላቸው። ስለዚህ አንድ ሰው በስብሰባ ላይ ተቀምጦ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ዓይኖቹ ይህኛው ወይም ያኛው ምን እያደረገ እንደሆነ ለማየት እዚህና እዚያ ይቅበዘበዛሉ። ሰው በሚያየውና በሚሰማው ነገር መነካቱ በጣም ቀላል ነው። እንዲያውም በማዕድ ላይ ተቀምጦ እንኳ ሌላው ሰው ምን እንደሚበላና እንዴት እንደሚበላ ለማየት ዓይኖቹ ሊዞሩ ይችላሉ፣ ከዚህም ሙሉ የሀሳብ ሰንሰለት ይከተላል። በዚህ ምክንያት የገዳም አባቶች እንዲህ አሉ። "ወደ ወንድምህ በዓት ከገባህ፥ በውስጡ ያለውን ነገር አትመልከት። በማዕድም ከተቀመጥክ ዓይኖችህ ከፊትህ ያለውን ነገር ብቻ ይመልከቱ።" የሕዋሳት ስለ ሌሎች ምስጢር ማወቅ መፈለግ የሕዋሳት ምንዝርና ይባላል። ጆሮ የመስማት መብት የሌለውን ነገር ለመስማት ቢሞክር፣ የገዳም አባቶች የጆሮ ምንዝርና ይሉታል፣ ይህም ጆሮው የረጋ አለመሆኑን ያሳያል። እንዲሁም ማየት የሌለበትን ነገር ለማየት የሚሞክር ዓይን የማይረጋጋ ሕዋስ ነው፣ ሥራውም ልክ እንደ ሰይጣን ሥራ ሆኗል፦ "በምድር ላይ መመላለስ በእርስዋም ወዲህና ወዲያ ማለት" (ኢዮብ 2:2)። ተለዋዋጭ፣ የማይረጉ ሕዋሳት ለነርቭ መነሳሳት መሠረት ናቸው። ይህ በተለይ አስደሳች ዜና ለመፈለግ ለሚዞረው ጆሮ፣ ሳቢ የሆነ እይታን ለሚፈልገው ዓይን እና "ምን አዲስ ወሬ አለ?" ብሎ በተደጋጋሚ ለሚጠይቀው አፍ እውነት ነው። ይህንን በማድረግ፣ ሕዋሳቱ ለግለሰቡ ልብ፣ ጆሮና ሀሳብ የሚያድክመውንና የአእምሮ ሰላሙን የሚያሳጣውን ነገር ያመጣሉ። የሚገርመው ነገር ሕዋሳቱ በጸሎት ጊዜ እንኳ ሊረጉ አይችሉም!

ዓይን እዚህና እዚያ እያየ ይዞራል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነትም ያቋርጣል፤ እንዲሁም ጆሮ በጸሎት ጊዜ ሊሰማው ለሚችለው ነገር ስሜታዊ ሊሆን ይችላል፣ ይህም ሀሳብን ይበትናል። ይህ ሁሉ የሆነው ሕዋሳቱ የማይረጉ በመሆናቸውና ከማይረጋጋ ሰውነት እንዲሁም ከማይረጋጋ ሀሳብ በመምጣታቸው ነው። ሆኖም፣ ሕዋሳቱ የሰውነት ብቸኛ ችግር ላይሆኑ ይችላሉ። የሰውነት አለመረጋጋት ከምኞቱ የተነሳ ሊመጣ ይችላል። የሰውነት ሁከት ለምግብ ካለው አካላዊ ፍላጎት ወይም ከሥጋ ምኞት የተነሳ ሊመጣ ይችላል, በዚህም መረጋጋቱን ያጣልና የምኞቱን እርካታ ለመፈለግ ከቦታ ወደ ቦታ ይንከራተታል። በአጻጻፋቸው ውስጥ አባቶች እነዚህን ዓይነቶች ምኞቶች የሥጋ ሕማማት ወይም ሕመም ብለው ይጠሯቸዋል፤ ምክንያቱም ሰውነት በኃጢአት ምክንያት ይሰቃያል፣ አይረጋጋምም። የሰውነት አለመረጋጋት ከጤና ምክንያቶች የተነሳም ሊሆን ይችላል።

ይቀጥላል

ዘሴት እልፍ
ሰኔ 4 2018 ዓ/ም
https://t.me/z2e1ms
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

🌱ኃጢአትህን ኹሉ በዲያብሎስ ላይ አታሳብብ🌱

በንስሐ ተስፋ ከቆረጥክ ዲያብሎስ ይወድሃል፡፡ ግን እርሱ እንዲረካ አታድርግ፡፡ ለድኅነት ቀንም ሁሌም ዝግጁ ሁን፡፡

እነዚህን ኹሉ የተናገርኩት ዲያብሎስን ከነቀፋ ነፃ ለማውጣት ሳይሆን እናንተን ከስንፍና ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ኃጢአታችንን ኹሉ በእርሱ እንዳናሳብብ በእውነት ይስፈልጋል፤ ለሁሉም ክፋታችን ሰይጣንን ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነም የራሳችንን ቅጣት እንጨምራለን፤ ጉዳዩን ኹሉ ወደ እርሱ ስላስተላለፍንም ይቅርታ አናገኝም - ልክ ሄዋን ይቅርታን እንዳላገኘች ሁሉ፡፡

🌱
ግን ይህን አናድርግ፡፡ እራሳችንን እንወቅ፡፡ ቁስላችንን እንወቅ። ከዚያም መድኃኒቶቹን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፤ ደዌውን የማያውቅ ሰው፣ ድካሙን አይፈውስምና፡፡

ብዙ ኃጢአት ሠርተናል፤ ይህን በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ሁላችንም ቅጣት ይገባናል፡፡ እኛ ግን ያለ ይቅርታ አይደለንም፣ ከንስሐ አንቀርም፤ አሁንም በአደባባይ ቆመናል፤ በንስሐም ተጋድሎ ውስጥ ነን፡

አርጅተኻል እና በመጨረሻው የሕይወት ደረጃ ላይ ነህ? አሁን እንኳን ከንስሐ እንደወደቅክ አታስብ፡፡ በራስህ መዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ በመስቀል ላይ ነፃ የወጣውን ዘራፊ አስብ፡፡ እርሱ ዘውድ ከተቀዳጀበት ጊዜ የበለጠ ምን አጭር ነገር አለ? ያም ሆኖ ይህ ለእርሱ መዳን በቂ ነበር፡

🌱
ወጣት ነህ? በወጣትነትህ አትተማመን፣ ከፊትህ ረዥም ጊዜም እንዳለ አታስብ “የእግዚአብሔር ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" (፩ኛ ተሰ. ፭፣፪) ለዚህም ነው ፍጻሜያችንን የማይታይ ያደረገው፣ ተግተን እንድንጸና።

ማንም ኃጢያተኛ ሊያደርግህ አይችልም ይላል አቡነ ቴዎድሮስ - ዲያብሎስም ቢሆን፡፡ ለኃጢአት የመስማማት ወይም የመቃወም ኃይል ያለው በአንተ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

አሁን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ክፋት እንዲሆን የፈቀደ እንደሆነ አልያም በሌላ ምክንያት እንደሆነ እንመርምር።

🌱
በስንፍና በልቡም ምኞት ወደ ራሱ ኃጢአትን ከሚያስገባ ሰው በቀር፣ ኃጢአት በማንም ላይ ሊጫን አይችልም፡፡ ፈቃደኛ ባልሆነው እና ኃጢአትን በሚቃወመው ሰው ላይ ዲያብሎስ ኃይል የለውምና፡፡

ዲያብሎስ በኢዮብ ላይ ይህን የኃጢአት ክፋት ለመጫን የክፋት ዘዴውን ኹሉ ከተጠቀመ በኋላ ዓለማዊ ንብረቱን ኹሉ ገፍፎት፣ በሞት ሰባቱን ልጆቹን ነጥቆት፣ ከጭንቅላቱ ፀጉር እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ የሚያስፈሩ ቁስሎችን፣ የማያባሩ ስቃዮችን ከሰጠው በኋላ የኃጢአት እድፍ በኢዮብ ላይ እንዲጣበቅ ለማድረግ በከንቱ ሞከረ፤ ኢዮብ በዚህ ኹሉ ጸንቶአልና፤ ከቶ አምላኩን ለመሳደብ ፍቃደኛ አልነበረም።

🌱
የነፍስ ምግብ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
በፍሉይ ዓለም የተተረጎመ

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ክፍል ዐሥራ አምስት
መረጋጋት


የረጋ ባሕርይና ችግሮችን መፍታት


የረጋ ሰው ችግሮቹን በረጋ መንፈስ ይፈታል። እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ መረጋጋቱን አያጣም፣ ይልቁንም በምክንያታዊነትና በተመጣጠነ መንገድ ይንቀሳቀሳል። ስለዚህ ባህሪው በአእምሮ ጤናማና ተቀባይነት ያለው ነው፣ ኃይለኛ ግብረመልሶችንም አያስከትልም። ተቃውሞውን በሚገልጽበት ወይም በሚቃወምበት ጊዜ እንኳ ይህንን የሚያደርገው በረጋ መንፈስ፣ በነጥብ ላይ ያተኮረና በሚያምን መንገድ ነው፣ በነርቭ ውጥረት ሳይሆን በሎጂክ ይመራል። በዚህ መንገድ በሁኔታው ውስጥ ጥቅምን ለማግኘት ይሳካለታል እንጂ ከተቃዋሚዎቹ ጋር አይጋጭም። በሌላ በኩል ግን፣ ሌላ ሰው ከተቃወመ በጫጫታ ያደርገዋል፣ በከፍተኛ ድምፅ ሁከት ይፈጥራል። ሌላኛውን ወገን በሻካራ ክሶች ይከሳል፣ ከሰዎችና ከፍላጎቶቻቸው እንዲሁም ከሀሳቦቻቸው ጋር በጣም ባለጌ በሆነ መንገድ ይገናኛል! በዚህ ሁሉ ውስጥ ስህተት መሥራትና ቦታውን ማጣት ለእርሱ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተመልከት  ሰላማዊው ሰው ከሥራው ቢለቅ እንኳ ይህንን የሚያደርገው በረጋ መንፈስ ነው። ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር መተባበር እንዳልቻለ ሲገነዘብ፣ ለእነሱ ምንም ዓይነት ችግር ሳይፈጥርና በዙሪያቸው ያለውን ከባቢ አየር ሳይረብሽ በጸጥታ ይወጣል። ነገር ግን የማይረጋጋው ሰው ከሥራ ቢለቅ፣ በመልቀቁ ምክንያት መላውን ዓለም ማወክ ይፈልጋል። እናም ሁከት ካልተፈጠረ ይቆጣና እንዲህ ይላል፦ እኔ እንዴት እለቃለሁ ሁሉ ነገር ግን እንደነበረ ይቀጥላል? እገሌ ወይም እገሌ እኔን ለመደገፍ ለምን አልተቆጡም? ሌሎቹስ ለምን እንደ እኔ አላደረጉም?!" በባሕርይው አማካኝነት፣ የረጋው ሰው ለሌሎች አርአያ ነው። ከእርሱ ሰላማዊነትንና መልካም ባሕርይን ይማራሉ፣ ከችግሮችና ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር እንዴት እንደሚገናኙም ተሞክሮ ያገኛሉ። የሐዋርያውን ቃል ያስታውሳሉ፦ "ከእናንተ ዘንድ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አኗኗሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኝነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኝነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉ።" (ያዕቆብ 3:13-16)። ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሌሎች ስህተቶች ሲናገር እንዲህ ይላል፦ "ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስህተት ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየዋህነት መንፈስ አቅኑት።" (ገላትያ 6:1)።

ይቀጥላል
ዘሴት እልፍ
ሰኔ 6 2018 ዓ/ም
https://t.me/z2e1ms
3