አንቀጸ ብርሃን ትምህርት ክፍል
321 subscribers
29 photos
1 video
1 file
81 links
ይህ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ነው
የትምህርት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ የተለያዩ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኑ ሆሳዕና በዓርያም እንበል❗️

የዘንድሮውን የሆሳዕና በዓል የት ለማሳለፍ አስበዋል  ፧ ከቀጠሮ በፊት ቀጠሮ እንስጦት ሆሳዕናን በመርካቶ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃ የዘንድሮው የሆሳዕና በዓል አዘጋጅ የመርካቶ ደ/ኃ/ቅ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት ቤት ነው።

ስለሆነም በዓሉን የተመለከቱ ልዩ ልዩ መርሐግብሮችን ከመጋቢት 19 ጀምሮ ወደ እናንተ እየደረሱ ይገኛል።

በበዓሉ ዋዜማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጥምቀተ ባሕር የሚካሄደውን የማጠቃለያ መርሐግብር ጨምሮ የሆሳዕና አውደ ርዕይ ፣ ዝማሬ ፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ሆሳዕና በአርያም ብለው በዘመሩ ህጻናት ይቀርባሉ።

ኑ ሆሳዕና በአርያም ከህጻናቱ ጋር እንበል።


ንቀጸ ብርሃን ሚዲያን በተለያዩ አማራጮች ይከተሉ
https://www.youtube.com/@anqetseberhanmedia7501

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Anqetseberhansundayschool

የፌስቡክ ፔጅ
http://www.facebook.com/sundayschoolofSR
1
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ ሶስት

ምሥጢረ ቁርባን ፩

በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉዳን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የወላዲተ አምላክ ፍጡነ ረድኤት የሰአሊተ ምህረት የድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወደደንና እስከ ሞት ድረስ ባፈቀረን በጌታችን በኢየሱስ  ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላም እላችሃለው። 
እግዚአብሔር አምላክ ቢፈቅድና ቢረዳን ዛሬ  ምስጢረ ቁርባንን  እንመለከታለን፡፡

ቁርባን፡- የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን በቁሙ መንፈሳዊ አምኅ፣ መሥዋእት፣ መባዕ ለአምላክ የሚቀርብ  የሚሰጥ ገንዘብ ማለት ነው፡፡
ምሥጢረ ቁርባን ማለት ካህኑ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ በጸሎተ ቅዳሴው በባረከው ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት፣ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆንበትና እኛም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ይህንን የክርስቶስ ሥጋና ደም የምቀበልበት ዐቢይ ምሥጢር ነው፡፡

👉የምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ በብሉይ ኪዳን

1. ካህኑ የሰላም ንጉሥ መልከጼዴቅ፣ አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ድል ነስቶ ሲመለስ ይዞ የተቀበለው ወይንና ሕብስት፡፡ ዘፍ 14፡18-20፣ ዕብ 5፡6-10፣ ዕብ7፡3-7፡፡
መልከጸዴቅ ለአብርሃም የሰጠው ኅብስትና ወይን የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ሲሆን መልከጸዴቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡

2. ለእስራኤል በምድረ በዳ የወረደላቸው መና የጌታ ሥጋና ደም ምሳሌ ሲሆን መናው የተገኘበት ደመና ደግሞ ጌታ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነባት የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡ ዘጽ 16፡13፣ ዩሐ 6፡49-51
👉 በብሉይ ኪዳን የሚሰጠው ጥቅም

🌹ድኅነተ ሥጋና መንጻት ይሰጥ ነበር
🌹የሥጋ በረከት ያሰጥ ነበር
🌹ጊዜያዊ እርቅ ያሰጥ ነበር

👉 በብሉይ ኪዳን ቁርባን ያቀረቡ አበው

1.አዳም፡- ባቀረበው ቁርባን ከ5 ቀን ተኩል በኃላ አድንሃለሁ የሚለውን ተስፋ አግኝቷል፡፡ ገላ 4፡3-7

2.ኖኅ፡- ባቀረበው ቁርባን ምድር ሁለተኛ በንፍር ውኃ እንደማትጠፋ የቀስተደመና ምልክት የጸና ቃል ኪዳን ተቀብሏል፡፡ ዘፍ 8፡20-22. ዘፍ 9፡8-17

3. አብርሃም፡- ባቀረበው ቁርባን በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ የሚል ተስፋ አግኝቷል፡፡ ዘፍ 18፡3-18

👉የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት

ቁርባን የተጀመረው ከሰው በደል ወዲህ ነው፡፡ ዘፍ 4፡3-4 ነገር ግን መስዋዕት ኦሪት አልፎ መስዋዕተ ሐዲስ በመተካቱ ድኅነተ ነፍስ የሚያሰጥ ምሥጢረ ቁርባን የተጀመረው በጸሎተ ሐሙስ ምሽት በአልዓዛር ቤት በጌታችን አማካኝነት ነው፡፡ ማቴ 26፡26-29

👉የምሥጢረ ቁርባን አገልግሎት/ጥቅም/

1. በምሥጢረ ቁርባን የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን፡፡ ዮሐ 6፡54
ቅርንጫፍ ከግንዱ እስካልተለየ ድረስ ሕይወት እንዲኖረው ሁሉ ከርስቲያኖችም የወይን ግንድ ከሆነው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አለመለየታችንን ፣ በሕይወት መኖራችንን፣ ለኃጢአት አለመሞታችንን እናረጋግጣለን፡፡ ዩሐ 6፡54

2. በዕለተ ዓርብ ጌታችን በጎልጎታ በመልዕልተ መስቀል ላይ የቆረሰውን ቅዱስ ሥጋና የፈሰሰውን ክቡር ደም እንቀበላለን፡፡

3.በመንፈሳዊ ዕውቀት የምናድግበትና በፀጋው የምንበለጽግበትን የሕይወት ምግብ እናገኛለን፡፡

4. ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን በሕይወታችን ውስጥ ይኖራል፡፡ ዮሐ 6፡35

👉ቅዱስ ቁርባን በስንዴና በወይን የሆነበት ምክንያት

ከአዝርእት ሁሉ ለጌታ ይሆን ዘንድ ስንዴ ከፍራፍሬ ደግሞ ወይን መሆኑ ምክንያት ነበረው
1. ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ፣ መልኬጸዴቅ በወይን በስንዴ ያመሰግን ነበር፡፡ ዘፍ14፡18፣ ዕብ 7፡1-3፣ ይህም የሥጋ ወደሙ/ቁርባን/ ምሳሌ ነው፡፡

2. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፣ ‹‹ በልቤ ደስታን ጨመርኩ ከስንዴ ፍሬ ከወይን ከዘይትም በዛ›› መዝ 4፡7
ምሥጢር ስላለው ነው፡ ይኸውም ስንዴ ስብ ሥጋን ይመስላል፣ ወይን ደግሞ ትኩስ ደምን ይመስላል፡፡ ስለዚህ በሚመስል ነገር መስጠቱ ነው፡፡

👉 ቅዱስ ቁርባን በመብልና በመጠጥ የሆነበት ምክንያት ለምንድን ነው ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውና ደሙን በወርቅ በብር ሳይሆነ በመብልና በመጠጥ ያደረገበት ምክንያት
መብልና መጠጥ ከሰውነት ጋር ይዋሐዳሉ ወርቅና ብር ግን አይዋሐዱም ስለዚህ በሰውነት እንዲዋሐደን ለማስረዳት ነው
ተርቦ ሳለ ሰው ወርቅና ብር ከሚሰጠው ለርሃቡ ምግብ ለጥማቱ መጠጥ የሰጠውን እንደሚወድ እወዳችኋለሁ ትወዱኛላችሁ ሲለን ሥጋውና ደሙን በመብልና በመጠጥ አደረገው፡፡

ማጠቃለያ፦

ቅዱስ ቁርባን መታሰቢያ ወይም ምሳሌ ሳይሆን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም ነው፡፡ ማቴ 26፡26-29፣ ዮሐ 6፡51፣ በ1ኛ ቆሮ 11፡23-24
ይህንን ለመታሰቢዬ አድርጉት ሲል መከራዬን ሕመሜን ቤዛነቴን እያሰባችሁ አምናችሁ ሥጋዬንና ደሜን ተቀበሉ ማለቱ ነው
ቅዱስ ቁርባን እንደ ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ ተቀብለን የምንተወው ሳይሆን በተደጋጋሚ የምንቀበለው ምሥጢር ነው፡፡
በኃጢአት ሆነው ሥጋ ወደሙን መቀበል አይገባም፣ ከተቀበልን ግን ዕዳ ይሆንብናል፡፡ 1ኛ ቆሮ 11፡27
ሥጋ ወደሙ በዕድሜ ፣ በጾታ ሳይወሰን ለማንኛውም ክርስቲያን የተፈቀደ ነው፡፡ 1ኛ ጴጥ 3፡18
ቀሳውስት በቅዳሴ ጊዜ የሚያቀርቡት ኅብስት አማናዊ የክርስቶስ ሥጋ ወይኑም አማናዊ የክርስቶስ ደም ነው፡፡

ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ ስም ከምድር እስከ አርያም ከናጌብ እስከ አድማስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የተመሰገነ ይሁን !!! አሜን !!!
ይቆየን !!!

ወስ ብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን !!!

ይቀጥላል......
ይህንን ያውቃሉ
13ቱ ሕማማተ መስቀል
7ቱ የመስቀሉ ቃላት
7ቱ ተዐምራት
5ቱ ችንካሮች
5ቱ ኃዘናት

13ቱ --ሕማማተ_መስቀል

1ኛ. ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. በገመድ መሳብ)
3ኛ.በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ፡በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. በጥፊ መመታት)
7ኛ. ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. መስቀል መሸከም)
11ኛ. በችንካር መቸንከር)
12ኛ. በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ፣መራራ ሐሞትንመጠጣት)

ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት

1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ
23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ
23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)

ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች

1. ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
4. ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

አምስቱ ኃዘናት

1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35
2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48
3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1
4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡
ዮሐ 19:17-22
5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42

http://t.me/sraged
1
❤️💜❤️💜🍏🍏

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

👉የጌታችን ትንሳኤ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታንን በቃል አስተምሮናል፡፡ ማቴ 20፡19፣ ሉቃ 18፡31-33፣ ማቴ 27፡62-64 በቃል ብቻ አይደለም ሞቶ መነሣት ትንሣኤን በተግባር በመፈጸም አሳይቶናል ዮሐ 20፡1፣ ማቴ 28፡1፣ ሉቃ 24፡1 ማር 16፡1 ጌታችን ዓርብ በ9 ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በሥልጣኑ ለየ፡፡ ዮሐ 19፡30 11 ሰዓት ሲሆን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀል አውርደው በአይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፍነው ማንም ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ የመቃብሩንም ደጃፍ በታላቅ ድንጋይ ዘጉት ማቴ 27፡57፡61 ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በለየ ጊዜ ሦስት መዐልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፡፡ በነፍሱም ደግሞ ወደ ሲኦል በመውረድ ለነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው ነጻም አወጣቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህን ሲገለጽ ‹‹በሥጋ ሞተ በመንፍስ ግን ህያው ሆነ እርሱም ደግሞ ሄዶ በወህኒ ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ሰበከላቸው›› 1 ጴጥ 3፡18 በማለት ተናግሯል፡፡ ከተዋህዶ በኋላ መለኮትና ትስብእት ለቅጽበተ ዓይን መለያየት የለባቸውምና ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር በመውረድ ሥጋን ሙስና መቃብር ማለት ፈርሶ በስብሶ እንዳይቀር ሲያደርገው በነፍስ ወደ ሲዖል በመውረድ ነፍሳትን ከዲያብሎስ ማርኮ ነፃ አውጥቷል፡፡

👉የትንሣኤ አማናዊነት

የጌታችን ከሞት መነሣት ለክርስትናው ሃይማኖት ወሳኝ ነው፡፡ ትንሣኤ ዓለምን የለወጠ ምሥጢር ነው፡፡ ትንሣኤው ኃይል ነው፡፡ ጌታ ከሞት ባይነሳ ኖሮ ክርስትና ያለፈ ታሪክ ብቻ በሆነ ነበር፡፡ ስለዚህ በትንሣኤው እውነተኝነት ወይም አማናዊነት ማመን በእምነት ውስጥ የማዕዘን ደንጊያ ነው፡፡ በጥንት ዘመን የነበሩ ሁለት ክርስቲያኖች ሲገናኙ‹‹ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ --- እውነት ተነሣ›› በማለት ነበር ሰላምታ የሚለዋወጡት ወይም ደግሞ ‹‹ማራናታ›› በሚል ቃል ሰላምታ የሚመጣው ማለት ነው፡፡ ‹‹ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ … በእውነት ተነሣ›› የሚለው የክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሰላምታ ልውውጥ በብዙ ሐገሮች እስከዛሬ ቀጥሎአል፡፡
እንግዲህ እነዚህ ሰላምታዎች ክርስቲያኖች በክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊነት ያላቸውን ጽኑ እምነት የሚያሳይ ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊ ባይሆን ምን ያህል ከንቱ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲገልጽ ‹‹ ክርስቶስ ከሙታን እንዴት የለም ይላሉ? ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሳማ፣ ክርስቶስ ካልተነሳ እንግዲህስ ስብከታችን ከንቱ ነው፡፡ እምነታችሁም ደግሞ  ከንቱ ናት… በዚህች ህይወት /በምድራዊ ህይወት/ ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን›› በማለት ያለ ክርስቶስ ትንሣኤ በክርስትና ያለው ሁሉ ከንቱ እንደሚሆን ገልጧል፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፡12-29
ዮሐ 20፡6-7 የተልባ እግር ልብሱና በራሱ ላይ የነበረው ጥምጣም ተለያይተው መቀመጣቸው ለጌታ ትንሳኤ አስረጂ ናቸው፡፡ በአይሁድ አባባል የጌታ ሥጋ ተሰርቆ ከሆነ ሰራቂው እንዴት ከፈኑን ከሰውነቱ ማለያየት ቻለ ዓላማውስ ምንድን ነው ጠባቆችስ በጥበቃ ላይ ሳለ እንዴት ከፈኑን ከሰውነቱ ለይቶ ማስቀረት ቻለ
ለዚህ ነው በቁጥር 8 ላይ ‹‹በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደመቃብር የመጣው ሌላው ደቀመዝሙር(ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው) ደግሞ ገባ አየም፣ አመነም›› የተባለው ምክንያቱም ደቀመዝሙሩ የተመለከተው ጌታ ሲነሣ አይደለም ይልቁንም ከፈኑን እንጂ ይህ ደግሞ ለመነሣቱ ማስረጃ ስለሚሆን አየም አመነም፡፡ ምንም እንኳን የክርስቶስ ከሞት መነሣት በብዙ መንገዶች የተረጋገጠ ቢሆንም አይሁድ ግን ያደረጋቸውን ተአምራቶች እንዳሳበሉ/እንደካዱ/ ሁሉ ትንሣኤውን ክደዋል፡፡ ማቴ 27፡63-66፣ 28፡11-15፣ 16-21 ፣ 17፡22-23፣ ሉቃ 24፡23-27፣ 24፡46፣ 24፡7፣

ይቆየን !!!

በቀጣይ ‹‹የአይሁድ ክህደት በትንሣኤውም ላይ›› በሚል ርዕስ እንመለሳለን!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!
https://t.me/sraged
በስመ አብ ወውልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!


የአይሁድ ክህደት በጌታ ትንሳኤ

አይሁድ ከመጀመሪያውም የጌታን መምጣት ያልተቀበሉ ናቸው ምክንያቱም የጠበቁት እንደነ ንጉስ ዳዊት ነግሶ በጦርነት ከሮም ነጻ የሚያጣቸው መሲህ ይጠብቁ ስለነበር ነው ። እስራኤላዊያን ከጌታ ልደት አስራ አምስት ዓመት  ቀድሞ በሮም ቀኝ ግዛት ስር ነበሩ። እስራኤላዊያን ጌታን እንደማይቀበሉ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ አስቀድሞ ተናግሯል ። ኢሳ 1፥2

ከጽንሰቱ እስከ ትንሳኤ ድረስ ጌታን ተቃውመዋል ።  ሊቀ ካህናቱ ሀናና ቀያፋ የጌታን መነሳት ሲሰሙ በመደናገጥ በከተማው የሐሰትን ወሬ አስወርተዋል ። የጌታን ሥጋ ሰርቀውታል ብለው አስነገሩ ይጠብቁ የነበሩትንም ወታደሮች በሐሰት እንዲመሰክሩ አድርገዋል። ወታደሮቹም አንዱ ጴጥሮስ ወሰደው ሌላው ዮሐንስ ወሰደው ሌላው ከሐዋርያት አንዱ ወስደው አራተኛው ደግሞ ዮሴፍና ኒቆድሞስ ወሰዱት ብለው ተለያይተው በጲላጦስ ፊት መስክረዋል። በመሰረቱ የጌታን ሥጋ ሲወስዱ ታድያ ለምን የተገዘበትን መግነዝ መተው ለምን አስፈለጋቸው ። መግደላዊት ማርያምም ጌታን በአትክልት  ስፍራ  አግኝታ የጠየቀችውም ይህንን የሐሰት ምስክርነት ይዛ ጌታዬን ወሰደውታል ወዴት እንዳለ ታውቀዋለህ? ወስደኸው ከሆነ ? ብላ ለመጠየቅ አብቅቷታል ።

ሰማዕቱ ቅዱስ ጲላጦስም የጌታን መግነዝ አምጥቶ ለዮሴፍና ኒቆድሞስ  አሳየው እነርሱም የገነዙበት እርሱ መሆኑን ነገሩት ። እርሱም ወስዶ እውራንን አበራበት ፤ ድውይን ፈውሰበት ፤ ጎባጣን አዳነበት ። ሙትን አስነሳበት ። ይህን ሁሉ ተመልክተው ግን ሊያምኑ አልቻሉም ይባስ ብለው የቤተልሔሙን ንጉስ ሄሮሥስ አሳምነው ከራሳቸው ጎን አደረጉ ። የጌታን ሥጋ የደበቁበትን ጉድጓድ አገኘን ብለው የሀሰት ፈጠራ በመፍጠር ለጲላጦስ ነገሩት ። የልባቸውን ክፋት የክህደታቸው ጥግ የጭካኔያቸውን ደረጃ ተመልክቶ በማዘን ፍላጎታቸውን ይፈጽም ዘንድ ወድ ጉድጓዱ በመሄድ መግነዙን በሥጋው ላይ ቢያደርግ ሙቱ ተነሳ ። የሚደንቀው ነገር ግን ከሙት የተነሳው ፈያታዊ ዘየማን ጥጦስ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ መሆኑ ነው ። ተነስቶም በጌታችን ኃይል መነሳቱን መስክሯል ። በከተማውም በመዞር የጌታን ትንሳኤ መስክሯል ። አይሁዳውያን ግን ከዓለት የጠጠረ ልባቸውን ከፈርኦን ይልቅ አደንድነው የጌታን መነሳት አንቀበልም ብለው ከሄሮድስ ጋር ተመሳጥረው ፈያታዊ ዘየማንን አንገቱ እንዲሰየፍ በማድረግ ሰማዕት እንዲሆን አድርገውታል ። ጲላጦስ ለሮሙ ቄሳር አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትን ተቀብሏል። ይህን ሁሉ ነገር እያዩ ሊያምኑ ያልቻሉት አይሁዳዊያን ለምን ይሆን ቢባል በምድራዊ ሀሳብ ስለተጓዙ ነው። እውነትም ጌታን አይተው ትንሳኤውን ተመልክተው ያላመኑት አይሁዳውያን ከንቱዎች ናቸው ። ጌታ እንዳለ ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው እውነት ነው።  የሐዋርያትን አይን አይን አድርገን አየነው ፥ የሐዋርያትን እጅ እጅ አድርገን ዳሰስነው ስለዚህ አማን ውእቱ ተንስአ እሙታን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን እናምናለን እንመሰክራለን።

ይቆየን.........

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!
https://t.me/sraged
🍎🍎🍎🍎ዮሴፍ ዘአርማቲያስ🍏🍏🍏🍏

በሐዲስ ኪዳን በጌታችን ሞት ጊዜ ሆኖ በጀግንነት እና በሥራው ትብብር ምልክት ሆኖ ይቀርባል 

ሀብታምና የተከበረ ሰው ነው ማቴ 27÷57
የአይሁድ ሸንጎ( ሲንሃይድረይም) አባል ነበር በዚህም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሽሽግ ደቀ መዝሙር ነበር ዮሐ 19÷38  ይህም በሥልጣኑ የተነሳ ፍራቻ ስለ ነበረበት ነው
አርማቲያ ከተባለች በናዝሬት ውስጥ የምትገኝ ትንሽ መንደር የተገኘ ሰው ነው

🍊🍏 በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቀበር ላይ የነበረው ሚና 🍊🍏

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በመስቀል ላይ ነፍሱን በገዛ ሥልጣኑ ሲለያት ዮሴፍ ዘአርማትያስ ጴንጤናዊ ጲላጦስ ዘንድ በመሄድ የክርስቶስ ሥጋ እንዲሰጠው ለመነው ጲላጦስ ከፈቀደለት በኋላ ሥጋውን ከኒቆዲሞስ ጋር በመሆን ከመስቀል አውርዶ በሐዲስ መግነዝ ገነዙት ውስጥም ለራሱ ባሠራው አዲስ መቃብር ቀበረው ማቴ 27÷60 ይህም የነቢዩን ኢሳይያስን ትንቢት የፈጸመ ነው ኢሳ 53÷9 "ከባለጠጋችም ጋር በሞቱ ...."

🍐 መንፈሳዊ ጠቀሜታው🍏

ድፍረትን ያሳያል ሌሎች በፈሩበት ሰአት በአደባባይ በሕዝቡና በሊቀ ካህናቱ ፊት ራሱን አቅርቦ በግልጥ የክርስቶስን ሥጋ ጠየቀ
እምነትና ፍቅርን ይገልጣል ካለው ቦታ አኳያ ያለውን ተጽዕኖ ሳይፈራ እምነትን ፍቅሩን ገለጠ
ለመቀበሩና ለመነሳቱ እውነተኛና ቁልፍ ምስክር ለመሆን በቃ

🍐ቅዱስ ትውፊት🍊

በትውፊት እንደተገለጠው ሐዋርያዊ ተልዕኮን ይፈጽም ዘንድ የወጣ ነበር በምዕራብ ቤተ ክርስቲያን እንግሊዝና አካባቢው እንዳስተማረ ይናገራሉ።

ይቀጥላል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://t.me/sraged
❤️ዮሴፍ ዘአርማትያስ በቀደምት አበው 🌷

#ክፍል ሁለት#

ሀ/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ዮሴፍ ያረፈደ ቢሆንም በእምነት ያለውን ጀግንነት ያሳያል ሐዋርያቱ ፈርተው በሸሹበት ሰአት ዮሴፍ በአደባባይ ተአማኝነቱን አሳየ።

ለ/ ሊቁ አውግስጢኖስ ዘሂፖ

የነቢዩ ኢሳይያስን ትንቢት ያሳየናል ኢሳ 53÷9 ዮሴፍ በዝግታ አምነው ነገር ግን በዓላማ የሚሠሩ አማኞችን ይወክላል ባለጥግነቱን ለክርስቶስ በመጠቀሙ ምድራዊ ሀብት ላላቸው ሰዎች ሁነኛ ምሳሌ ነው።

ሐ/ሊቁ አርጌንስ

በተለይ ምሳላያዊ ምልከታ አለው አዲስ መቃብር ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ያሳያል  ዮሴፍ ደግሞ  የአማኞች ክርስቶስን በክብርና በንጽሕና መቀበልን ይወክላል።

መ/ ሊቁ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ

ታሪካዊ ፋይዳው ላይ ያተኩራል ። ዮሴፍ የክርስቶስ እውነተኛ ሞት  እና እውነተኛ መቀበርን በመመስከር የክርስቶስን ሰውነት ለሚክዱ መናፍቃን  ምስክር ይሆናል።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞ

ዮሴፍ ዘአርማትያስ

ባለጸጋና የሸንጎ አባል
ድብቅ ደቀመዝሙር
ጲላጦስን የጌታን ሥጋ የጠየቀ
ወደ ሮማዊያን ሥልጣን የተጠጋ
ድፍረት +መስዋዕትነት

ኒቆዲሞስ

ፈሪሳዊና መምህር
ድብቁን ምሥጢር ፈላጊ ዮሐ ፫
የመግነዙን ጨርቅ ያመጣ
ታላቅ ሰው
በእምነት ያደገ

ኒቆዲሞስ በሌሊት በመምጣት የዳግም ልደትን ምሥጢር የተማረ ነው ዮሐ 3 ከዚያም ደግሞ ስለክርስቶስ ጥብቅና የቆመ ነው ዮሐ 7 በመጨረሻም ገንዞ የቀበረ መምህር ነው ዮሐ 19÷39

ኒቆዲሞስ እምነቱ በጥቂቱ እያደገ የመጣ ነው የዮሴፍ ግን በአንድ ጊዜ የተገለጠ ነው።

❇️የምንረዳው ነገር ❇️

የተደበቀ እምነት በሥራ ካልተገለጠ ከንቱ ነው ድፍረት ደግሞ በከባድ ችግር ውስጥ መገለጥ የሚችል ነው ሁለቱም ሰዎች ሁለት የተለያዩ ደቀ መዛሙርትነትን ያሳያሉ እነርሱም በማደግ የሚገለጥና በአንድ ተግባር የሚታይ ናቸው

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ❇️
ይቀጥላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://t.me/sraged
2
ዮሴፍ ዘአርማትያስ🍐

ክፍል ሦስት

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ  ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።

ዕለተ ዓርብ


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ

ስለድፍረታቸው
በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።

❇️  ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም

ዮሴፍ ዘአርማትያስ


ግልጽ እምነትን ይወክላል
መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
  አዲስ መቃብር  ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።

ኒቆዲሞስ



መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል

❇️ የጌታ መቀበር

የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል 
አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።

❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል

ማጠቃለያ



እምነት በሥራ እንደ ዮሴፍ የሚገለጥ እንጂ ተሸሸጎ የሚኖር አይደለም በሥራ ለመግለጥ ትጋት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ያለንን መሆኑን ከዮሴፍ እንማራለን በክርስቶስ መከራው ውስጥ በመሳተፍ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችንን መገለጥ አለብን።

የአርማትያሱ ዮሴፍን ከዮሴፍ አረጋዊ ጋር በማመሳሰል አንድ ናቸው የሚሉ አሉ ይህ በፍጹም ስህተት ነው ዮሴፍ አረጋዊ በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደምንመለከተው ያረፈው ጌታችን 25 ዓመት ሲሆነው ነው በዚያ ላይ ሥራው እንጨት ጠራቢ የነበረ ነው ይህ ግን ባለጸጋ የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ ነው።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ የሐዲስ ኪዳን ጻድቅ ሲሆን ከኒቆዲሞስ ጋር ሐምሌ 17 ቀን ይከበራል በወንጌል ከተገለጠው ታሪክ በቀር የሚገለጥ ታሪክ ባይኖርም እንግሊዝ ሄዶ እንዳስተማረና መከራን ተቀብሎ ሰማዕት እንደሆነ በትውፊት ይነገራል


ይቆየን
ስለነበረን ጊዜ የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነና የተወደሰ ይሁን
ከትንሳኤው ረድኤት  በረከት ይክፍለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
http://t.me/sraged
ዮሴፍ ዘአርማትያስ🍐

ክፍል ሦስት

ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ  ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።

ዕለተ ዓርብ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ

ስለድፍረታቸው
በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።

❇️  ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም

ዮሴፍ ዘአርማትያስ

ግልጽ እምነትን ይወክላል
መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
  አዲስ መቃብር  ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።

ኒቆዲሞስ


መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል

❇️ የጌታ መቀበር

የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል 
አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።

❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል

ማጠቃለያ


እምነት በሥራ እንደ ዮሴፍ የሚገለጥ እንጂ ተሸሸጎ የሚኖር አይደለም በሥራ ለመግለጥ ትጋት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ያለንን መሆኑን ከዮሴፍ እንማራለን በክርስቶስ መከራው ውስጥ በመሳተፍ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችንን መገለጥ አለብን።

የአርማትያሱ ዮሴፍን ከዮሴፍ አረጋዊ ጋር በማመሳሰል አንድ ናቸው የሚሉ አሉ ይህ በፍጹም ስህተት ነው ዮሴፍ አረጋዊ በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደምንመለከተው ያረፈው ጌታችን 25 ዓመት ሲሆነው ነው በዚያ ላይ ሥራው እንጨት ጠራቢ የነበረ ነው ይህ ግን ባለጸጋ የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ ነው።

ዮሴፍ ዘአርማትያስ የሐዲስ ኪዳን ጻድቅ ሲሆን ከኒቆዲሞስ ጋር ሐምሌ 17 ቀን ይከበራል በወንጌል ከተገለጠው ታሪክ በቀር የሚገለጥ ታሪክ ባይኖርም እንግሊዝ ሄዶ እንዳስተማረና መከራን ተቀብሎ ሰማዕት እንደሆነ በትውፊት ይነገራል


ይቆየን
ስለነበረን ጊዜ የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነና የተወደሰ ይሁን
ከትንሳኤው ረድኤት  በረከት ይክፍለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
http://t.me/sraged
2
የኤማሁስ መንገደኞች

በትንሣኤ እሁድ ከኢየሩሳለም ወደ ኤማሁስ  ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ይሄዱ ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም የሄዱት የቂጣን በዓል ሊያከብሩ ነበር፡፡ 

እነዚኽ ሰዎች ሉቃስና ቀለዮጳ ናቸው። የሚላኑ አምብሮስ ሲናገር የሁለቱ ተጓዦች ስም አማኦን እና ቀለዮጳ ይባላል ይላል Ammanon and Cleophas. 

በምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ትውፊት ቀለዮጳ የራሱ የሉቃስ ስም ነው። ስሙን ደብቆ ነው ይላሉ። ማርቆስ በጌታ ስቅለት ቀን ሊይዙት ሲሉ ልብሱን ጥሎ መሮጡን ስሙን ደብቆ የራሱን ታሩስ “አንድ ሰው” በሚል ጽፏል። ማር.14:51

ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከሚሄዱት ከሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ተገናኘ “እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር። ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር” ሉቃ.24:13
ቅዱስ ቄርሎስ ዘአሌክሳደርያ “ሁለቱ ስለክርስቶስ ይነጋገሩ ነበር። ዳግም በሕይወት እንደማይኖርና በመሞቱ ሐዘንተኛ ሆነው” እነዚኽ ሁለቱ ከሰባ አርድእት መካከል ነበሩ። ከቀለዮጳ ጋር የነበረው ስምዖን ነው ጴጥሮስ ወይም ቀነናዊ ያይደለው ይለናል። (cyril of Alexandria) በሉቃስ ወንጌል  ትርጓሜ። 

ሐዘንተኞች ሆነው ስለ ክርስቶስ እየተወያዩ ይሄዱ ነበር፡፡ አብሯቸው መሆኑን አላወቁም በዚያ ሦስተኛ ሰው ሆኖ አብሯቸው መጓዝ ጀመረ። ይኽ ሰው ኢየሱስ ነበር። ከትንሣኤ በኋላ አካሉ ተለውጧልና ማን መኾኑን አላወቁም። የተገለጠላቸው እንደማንኛውም ሰው ስለነበር አላወቁትም። 
“ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር” ጌታን አላወቁትም ነገር ግን ሊወያዩ ፈቃደኛ ነበሩ ። ዐይናቸውን ይሳወረው አለማመናቸው ነበር። እርሱን እንዳያውቁት ያደረገውም አውቆ ነው። በውስጣቸው ያለውን ጥያቄና ጥርጣሬ እንዲያወጡ እንዲናገሩ ፈልጎም ነው። በመቀጠል በብሉይ ኩዳን መጽሐፍት ጥርጣሬያቸውን ፈወሰ። 

እንግዳው እንዲህ አላቸው “እርሱም፦ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው” ያሳዘናቸው ኢየሱስን ማጣታቸው ነበር፡፡ የጌታም ጥያቄ አስደነቃቸው፡፡ 

“ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው ” “እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው” ውይይታቸውን  ወደ እውነቱ መለሳቸው። ሁለቱም የሆነውን ሁሉ ተረኩለት።

“እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው፡፡ ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፦ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር። ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።” 

ትልቅ ተስፋ ቢኖራቸውም አልትፈጸመላቸውም፡፡ እስራኤልን ያድናል ብለውም ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ እስራኤልን ከሮም ነጻ የሚያወጣ ነበር የመሰላቸው። እንደ ፓለቲካ መሪ ቆጠሩት። አሕዛብንም እንደሚያድን ግን አልተረዱም፡፡ የመስቀል ሞኝነት ታየባቸው። 
 እነዚኽ መንገደኞች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ በቃልና በሥራው ብርቱ ነቢይ” አድርገው ነው የሚያምኑት። ከዚያ በላይ ማየት አልቻሉም። ታላቅ ሰው፣ አስተዋይ ሰው ወይም መልካም ሰው እንደሆነ ብቻ አወቁት። 

ስለ ትንሣኤው በሴቶችና በሌሎች የተነገረውን በፍጹም አላመኑም፡፡ ስለዚህ እንዲህ አላቸው “እርሱም፦ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው። ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።” ሉቃ.24:25

በሕማማቱ ምክንያት ሰዎች ከኃጢአተኝነታቸው ወደ እግዚአብሔር ወዳጅነት ክብር እንዲሚነሡ አረጋገጠላቸው፡፡ ያለ መስቀል ክብር የለምና። ሁሉም ነገር የተፈጸመው ሳይታሰብ ሳይሆን በትንቢት በተነገረው መሠረት ነው። መጻሕፍት ስለመሲሁ የተናገሩትን ቢያውቁ ኖሮ በመስቀል ያምኑ ነበር፡፡

ኤማሁስ ሲደርሱ አልፎ የሚሄድ መሰላቸው ከነርሱ ጋር እንዲሆን ለመኑት፡፡ “ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው” ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከነርሱ ጋር እንዲሆን ለመኑት “እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ” እንግዳ ሆኖ ገባና እንደ አስተናጋጅ ሠራ፡፡ ሁሌም ቢሆን እንደ አገልጋይ ይሠራል። 

“ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።” ባርኮ መቁረሱ የመጨራሻውን እራት አስታወሳቸው፡፡ ምስጢራዊውን እንጀራ ከተቀበሉ በኋላ አይናቸው ተከፈተ አወቁት፡፡ በጸሎተ ሐሙስ እንዳደረገው። በጌታ ትንሣኤ ተሳትፎ ያላቸው (ከሥጋውና ደሙ የተካፈሉ) ዓይናቸውን ይከፍታል። ራሱን የገለጠው በቁርባን ነው። 

ከእነርሱ ተሰወረ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “እርስ በርሳቸውም፦ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ” ልባቸውና አእምሯቸው ተነካ። ትልቅ እውነት ብዙ ጊዜ የሚገለጠው ባልታወቀ አኳኋን ነው፡፡ በተራ የመንገድ ጉዞ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ በተከበረ ሕይወቱ መስቀልና ክብር በአንድ ጊዜ ታዩ፡፡ ስለ ትምህርቱ ሳይሆን ስለ ሕማማቱና ስለ መነሣቱ አስታወሳቸው። “የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ” 2.ጢሞ.2:15

 
ሰዎቹ የመጡበትን  ጉዳይ ትተው ከኤማሁስ በዚያው ሰዓት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ “በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም፦ ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው” ተሰብሰበው ለነበሩት ተረኩላቸው፡፡ “እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው” ሉቃ.24:35
 


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ አራት

ምሥጢረ ቁርባን ፪

በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉዳን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የአቁራርተ መአት ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወደደንና ባፈቀረን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላም እላችኋለው።

👉 ቀሳውስት ኅብስቱን በጻሕል ፣ ወይኑን በጽዋ አድርገው የሚያቀርቡት ቁርባን ወደ አማናዊ የክርስቶስ ሥጋ ወደሙ የሚለወጠው መቼ ነው ? 
ኅብስቱ ሥጋ አምላክ ፣ ወይኑም ደመ አምላክ የሚለወጠው ቄሱ ፣ "
  አእኲተ ፣ባረከ ፤ወቀደሰ " ብሎ በባረከው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ኅብስቱን ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ወይኑንም ደመ ወልደ እግዚአብሔር አድርጎ ይለውጠዋል ፤ በዚህ ጊዜ ፍጹም ሥጋ አምላክ ፣ ደመ አምላክ ይሆናል።

ቅዱስ ቁርባኑን ከመቀበላችን በፊት ምን ማድረግ ይገባናል?

1. ጸሎተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ካህን በጻሕል ፣ወይኑን በጽዋ ዕ አድርጎ እየባረከ ፣ ጸሎተ ቅዳሴውን ሲያደርስበት ፣ ኅብስቱ ተለውጦ የወልደ እግዚአብሔር ደም እንደሚሆን ከልብ ማመን ይገባል።

2. በሐሳብ ፣በቃል ፣በተግባር የፈጸሙትን ኃጢአት ለንስሀ አባት መንገር ይገባል።

3. የሰሩትን ኃጢአት ተናዝዞ ፣ከንስሀ አባት የሚሰጠውን ቀኖና ማለትም ጾም ፣ጸሎት ፣ስግደት ፣ምጽዋትና ሌላም ይህንን የመሰለውን ሁሉ ተቀብሎ መፈጸም ይገባል።

4. ከማንኛውም ኃጢአት መራቅ ያስፈልጋል።

5.ከመቀበላችን በፊት አስራ ስምንት ሰአት መጾም ያስፈልጋል።

6. ገላን መታጠብና ንጹህ መሆን ፤ ከተቻለ ለቁርባን የሚሆን ልብስ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ። ካልተቻለ ግን ያለንን ልብስ ማጠብና መቀበል ያስፈልጋል።

7. በአስራ ስምንት ሰአታት ውስጥ ደም ከፈሰሰ መቀበል አያስፈልግም። በዝንየትም ከተመታን መቀበል የለበትም።
8.  በሶስት ቀን ውስጥ ከሩካቤ ሥጋ መራቅ ያስፈልጋል።
9. ሴትም ብትሆን በወርኃ ትካት ጊዜ መቀበል የለባትም።

ከተቀበሉ በኋላ መደረግ  ያለባቸው ነገሮች 

1. እጅን ወይም ገላን በውሃ አለመታጠብ
2. ምግብን ለብቻ መብላትና ማስተረፍ የለብንም።

3. ከተቀበልን በኋላ ማየ ማቊረርት እስከምንጠጣ  አፍን በመሐረብ መያዝ አለብን ።

4. ብዙ ርቀት አለመጓዝ
5. ላብን የሚያወጣ ሥራን አለመስራት
6. ስግደት አለመስገድ
7. የቆረብንበትን ልብስ አለማውለቅ ፣ ነጠላችንን እስከ አስራ ሁለት ሰአት አለማውለቅ፣ ምራቅን አለመትፋት የመሳሰሉት ናቸው።

👉 የቅርባን አቀባበል ቅደም ተከተል

1. ጳጳሳት
2. ቆሞሳት
3. የቅዳሴው ልዑካን
4. ሕጻናት
5. አረጋውያን
6. ወራዙት ተባእት
7. ወራዙት አንስት
8. ንዑሰ ክርስቲያን ናቸው።

ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

ይቆየን..........

በቀጣይ ክፍል መስዋዕተ ሐዲስና አማናዊ መስዋዕት በሚል ርዕስ እንመለሳለን።

ይቀጥላል.........

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://t.me/sraged