💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል ሰባት
ምሥጢረ ሥጋዌ ክፍል ፬
በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛችሁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች እስከሞት ድረስ በታመነ ፍቅር በወደደን ባከበር በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ !!!
✅ ርዕስ * አምላክ ሰው ሆነ ስንል እንዴት ነው ? *
ሰው አምላክ ሆነ ስንል *
• በፍጹም ተዋህዶ ነው፣
• ተዋህዶ ፡- ማለት አንድ መሆን፣ መዋሐድ አለመለያየት ማለት ነው፡፡
• አንድም፡- ተዋህዶ የማይወሰነው፣ የማይዳሰሰው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከአብና ከመንፈስቅዱስ ሳይለይ በማህጸነ ድንግል አድሮ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ መወለዱን ያሳየናል፡፡
• ወንጌላዊው ዩሐንስ ‹‹ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ›› ያለው ይህ ፍጹም ተዋህዶ ነው፡፡ ዩሐ 1፡14
• ቅዱስ ቄርሎስ ስለ ቃልና ሥጋ ተዋህዶ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ቃል ሥጋ ሆነ ሲባል ቃል ተለውጦ ሥጋ ሆነ ማለት አይደለም ሥጋም ተለውጦ መለኮት ሆነ ማለት አይደለም፡፡›› በማይመረመር የተዋህዶ ምሥጢር፣ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፣ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ሆነ እንጂ፡፡
• ይህም ማለት የመለኮት ገንዘብ በተዋህዶ የሥጋ ገንዘብ የሥጋ ገንዘብ በተዋህዶ የቃል ገንዘብ ሆነ ማለት ነው፡፡ ፊተኛና መጨረሻ መባል የሚገባ ቃል ሲሆን ሥጋ ግን በተዋህዶ የቃል ገንዘብ የራሱ አድርጓልና ፈተኛም ኋለኛም ነኝ ሊል በቃ ራዕ 1፡17
• የሥጋ ገንዘብ፡- መራብ፣ መጠማት፣ መድከም ፣መሞት፣ ግዙፍነት፣ ውሱንነት ወዘተ . .
• የቃል ገንዘብ፡- ሁሉን ቻይነት፣ ቀዳማዊነት፣ ዘላለማዊነት፣ ረቂቅነት፣ ፈተኝነት፣ ኋለኝነት፣ ፈጣሪነት ወዘተ . . . .
• እንደ ቤተክርስቲያናችን ት/ት መሰረት በተዋህዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ሆነ፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነዋል፡፡ ይህ ማለት ቀዳማዊነት ያልነበረው ሥጋ ቃልን ተዋህዶ ቀዳማዊ አምላክ ተባለ/ ሐዋ ፡56/ ዘመን የማይቆጠርለት ቃል ደግሞ፣ ሥጋን ተዋህዶ ዘመን ተቆጠረለት፡፡ አንድም፡ ሁለት አካል አንዱ አንዱን ሳያጠፋው ሳይለውጠው ያለመቀላቀል፣ ያለመደራረብ/ በተዐቅቦ/ በመጠባበቅ አንድ መሆን ተዋህዶ ይባላል፡፡
• ተዐቅቦ/መጠባበቅ/ - ማለት በጠቅላላው ትስብእትና መለኮትን ከቱላኤ፤ከውላጤ የሚጠብቅ አነጋገር ነው፡፡ ምሥጢሩም ሙሴ በደብረሲና ሐመልማል ከነበልባል ነበልባል ከሐመልማል ተዋህዶ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው ሐመልማሉ ነበልባሉን ሳያጠፋው አንዳየ መለኮትም ትስብእትን አላጠፋውም ትስብእቱም መለኮቱን አልለወጠውም ማለት ነው ዘፀ 3፡1
• ትስብዕት፡- ማለት አካልንም፣ ባህርይንም አንድ አድርጎ የሚያሳይ አነጋገር ነው እንጂ አካልን ወይም ባህርይን ብቻ የሚያሳይ አነጋገር አይደለም፡፡
• አንድም፡ ተዐቅቦ እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ ተዐቅቦ ነው፡፡ የሥጋ አካሉ ግዙፍ፣ ባህርዩ በውኃ፣ በመሬት፣ በነፋስ በእሳት ያሉ ባህርያት እርጥበት፣ ደረቅነት፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ ነው፡፡ የነፍስ አካሏ ረቂቅ፣ ግብሯ ለባዊነት፣ ነባቢነት ሕያዊነት ነው፡፡
• እነዚህ ሁለቱ ነፍስና ሥጋ ሲዋሀዱ ሥጋ ግዙፍነቱን ለቆ ሳይረቅ፣ ሳይለወጥ፣ ነፍስ ርቀቷን ለቃ ሳትገዝፍ፣ ሳትለወጥ ነው፡፡ እነዚህም አካላቸው ሲዋሃድ ባህርያቸውም እንደዚሁ ተዋህዷል እንጂ ተለይቶ የቀረ አይደለም፡፡
• ነፍስና ሥጋ በተዐቅቦ ተዋህደው የተገኘው አካል አንድ ሰው ቢበል እንጂ ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ሊባል አይችልም፡፡ ረቂቅ መለኮትም ግዙፍ ሥጋን በተዐቅቦ ቢዋሃድ አንድ አካል አንድ ባህርይ ይባላል እንጂ ሁለት አካል ሁለት ባህርይ ሊባል አይችልም፡፡
• የነፍስና የሥጋ አካላቸው ሲዋሐድ ባህርያቸው ከተዋህዶ በአፍዐ/በውጭ/ እንዳልቀረ መለኮትና ትብስእትም አካላቸው ሲዋሐድ ባህሪያቸው አልተዋሃደም ሊባል አይችልም፡፡ ‹‹የማይመረመር የአብ ህሊናው እርሱ ነው፡፡ የአብ ጥበቡ እርሱ ነው፣ የአብ ኃይሉ እርሱ ነው፡፡ ቀኝ እጁ፣ ክንዱ እርሱ ነው፡፡›› /ኢሳ 4፡13 ዩሐ 12፡38፣ ሮሜ 10፡16፣ ሮሜ 11፡32፣ ሃይ.አበው ገጽ 22 ም.2 ቁ 12-13/
• ‹‹የማይመረመር የማይለወጥ ቃል፣ የሚለወጥ ሥጋን ተዋህዶ መለወጥ ይስማማው የነበረ ሥጋን የማይለወጥ አደረገው፡፡ ስለዚህ በተዋሀደው በመዋቲ አዳም ሥጋ ተገለጠ፣ የማይለወጥ ባህርይ ያለው ቃል የሚለወጥ ባህርይ ባለው ሥጋ ሞቶ በፍዳ የተያዙትን በወንጌሉ አዳናቸው፡፡// ዩሐ 1፡14፣ 1ጢሞ 3፡16፣ ፊሊ 2፡6-8/
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ዓለምን ያዳነው መለኮታዊ ባሕርይ የተዋሐደው ሰብአዊ ባህርይ ባለው አካለ ትስብእት በመሆኑ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ ብለን እናምናለን፡፡ ተነሠ ዐረገ መባሉም እንደዚሁ በተዋሕዶ ነው፡፡
አንድ አካል አንድ ባሕርይ የምንለው ይህ አካል ይህ ባሕርይ በመለኮትና በትስብእት ተዋሕዶ አንድ የሆነ ነው እንጂ የመለኮት ብቻ ወይም ምሉእ፣ ስፉሕ፣ ረቂቅ፣ ሲሆን የማይታይ ፣ በእጅ የማይዳሰስ፣ የሚቆረስ ሥጋ የሚፈስ ደም የሌለው ስለሆነ በቅዱስ ሥጋው በክቡር ደሙ ዓለም አዳነ ማለት አይቻልም፡፡ *በወንጌላዊው በቅዱስ ዩሐንስ ቃል ሥጋ ኮነ ያለው መቅረቱ መታበሉ ነው፡፡ * የትስብእት ብቻ ነው እንዳይባልም የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ የዕሩቅ ብእሲ ደም እንኳንስ ዓለምን ሊያድን ለራሱም አዳኝ የሚያስፈልገው ነው፡፡ ስለዚህ ተዋህዶ ሁለት ነገሮች እንደመሆናቸው ይገለጻል እንጂ አንድ ብቻ የማይነገር ስለሆነ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ግልጽና የግድ ነው፡፡
በቀጣይ ክፍላችን ከተዋህዶ በኋለ ሁለትነት የለም በሚል ርዕስ ተመልሰን እንማማራለን !! ይቆየን !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
ይቆየን !!! ይቀጥላል .... .
http://t.me/sraged

Telegram
አንቀጸ ብርሃን ትምህርት ክፍል
ይህ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ነው
የትምህርት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ የተለያዩ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው

❤3
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል ስምንት
ምሥጢረ ሥጋዌ ክፍል ፭
በክ ርስቶስ ክርስቲያን የተባላችሁ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የእናታችን የአማላጃችን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወ ደደንና ባፈቀረን እስከ ሞት ድረስ በደረሰልን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላምታዬን አቀርባለው።
✝ ሁለትነት ከተዋዕዶ በኋላ
ባለፈው ተዋዕዶን በስፋት ለማየት ሞክረናል። እኛ ኦርቶዶክስ ተዋዕዶ ከኦርቶዶክስ መለክያዊያንና ከካቶሊክ ቤተ እምነት የምንለየው ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ከሁለት አካል አንድ አካል ብለን በማመናችን ነው። ከተዋዕዶ ሁለትነት የለም ። አንድ አካል አንድ ባህርይ የሚለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት።
👉1ዮሐ 1፥1 " ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን ፥በዐይኖቻችን ያየነውን ፥የተመለከትነውንም ፥ እጆቻችንም የዳሰሱትን እንነግራችዋለን።"
በተዋዕዶ ካልሆነ በስተቀር ቅድመ አለም የነበረውን ማን ሊዳስስ ይችላል?
👉ሐዋ 20፥28 " በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን..." እግዚአብሔር ደም የለው ታዲያ በማን ደም ነው የዋጃት ቢሉ በተዋዕዶ በነሳው ሥጋ ነው። ኢየሱስ በገዛ ደሙ አላለም ምክንያቱም ሰው ሲሆን የተሰጠው ስም ነውና እግዚአብሔር አለ እንጂ ይህም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ያሳያል ።
👉ማር 14፥61" የብሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን ? ኢየሱስም አዎን ፥እኔ ነኝ የሰውን ልጅ በኃይል ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው" ቀያፋ የጠየቀው ማንን ነው ? ክርስቶስን አይደል በማን አካል እመጣለው አለ? በማንም በመለኮት እንዳትሉ መለኮት አይያዝ አይታሰር በሥጋ እንዳትሉ የባህርይ ልጅ ነኝ በሐሰት አይመሰክር። ተ ዋዕዶ ነው እንጂ
👉 ራዕ 2፥8 " ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻ እንዲህ ይላል...." ቅደመ ዓለም የነበረ ድኅረ ዓለም የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው ለሰው አይቻለውም ። ግን መሞት የሰው ባህርይ ነው። ህያው መሆን ደግሞ የአምላክ ነው። ታዲያ የተነገረው ለማን ነው? ለሥጋ ወይስ ለመለኮት ለተዋዕዶ ነው እንጂ።
👉 ፊል 2፥6 " በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ እግዚአብሔርነትን እንደመቀማት አልቆጠረውም ፥የባሪያውን መልክ ይዞ መጣ እንጂ" አየህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥርት ባለ ቃል አዋዕዶ አምላክ ስለሆነ በእግዚአብሔር መልክ ነበር አለ፡፡
👉 ሮሜ 5፥10 " ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን...." በመስቀል ላይ የተሰቀለው ወልደ አብ ወልደ ማ
ርያም መሆኑን መሰከረ ። የተሰቀለው ስጋዊ ባህርይ ቢሆን ኖሮ በልጁ ሞት ባላለ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ አንድ አካል አንድ ባህርይ መሆን ተናገረ እንጂ ። በመስቀል የተ ሰቀለው ወልደ ማርያም ነው ቢሉ ሥጋ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ ማለት አይችልም በሉ። መለኮት ነው ቢሉ መለኮት ተጠማው ማለት አይችልም በሉ። ታዲያ የተሰቀለው አንሥ ክርስቶስ ሆኖ ሳለ እንዴት ሁለት አካል ነው ማለት ይቻላል ?
👉 ማቴ 3፥17 " በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ " አብ የመሰከረለት ለመለኮት ነው እንዴ አይደለም ለሚጠመቀው ሥግው ቃል እንጂ ።
👉 ዮሐ 15፥24 " አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል..." አይሁድ ያዩት ሥጋውን እንጂ መለኮቱን አይደለም በተዋዕዶ ስለሆነ እንጂ ።
👉 ዮሐ 10፥30 " እኔና አብ አንድ ነን።" ሥጋ ከአብ ጋር አንድ መቼ ሆነ? መለኮት እሱ እንዳትሉ የተናገረው ሥግው ቃል ነው ስለዚህ በተዋዕዶ ነው ። ዘፍ 3፥22 " አዳም ክፉና ደጉን ያውቅ ዘንድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ያለውም ለዚሁ ነው፡፡
👉 ዮሐ 9 ሙሉ ልምሻ የነበረውን ሰው ምራቅን እንትፍ ብሎ ጭቃን አብኩቶ አይንን ሰርቶለታል ። መለኮት ምራቅ አለው ጭቃን ያቦካል አያቦካም በእርምሞ በቃሉ የፈጠረ ነውና፡፡ ሥጋ ምንም በሌለበት ግንባር ላይ አይንን ይሰራል ?አይሰራም ግብሩ አይደለምና ።ታዲያ ይህን ተአምር ማን አደረገ ? በተዋዕዶም ነው እንጂ ።
👉 ሐዋ 1፥9 "ይህን እየነገራቸው ከፍ ከፍ አለ....." ሲያርግም በተዋዕዶ ነው ። ሥጋውን ከመቃብር ትቶታል ለሚሉ እስቲ አንድ ጥያቄ እንጠይቃቸው መለኮት ከፍ ከፍ እያለ የሚያርገው ቦታ ገድቦት ነው ? አይደለም በተዋዕዶ ስለሆነ ፥የተዋዕደውን ሥጋ አለመተውን ሲያመላክት ነው፡፡
👉 ሐዋ 7፥ 56 " ሰማይ ተከፈተ ፥የሰውን ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለው " ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታን በቀኙ ቆሞ አየሁት ያለው በመለኮት አይደለም በተዋዕዶ ነው እንጂ ። በዙፋኑ የተቀመጠውም በተዋዕዶ ነው ። መዝ 109 ላይ እንደተናገረው " ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካስረግጥልህ በቀኝ ተቀመጥ አለው ።"
👉 ራዕ 1፥7 "...የወጉትም ሁሉ ያዩታል...." ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣም በተዋዕዶ ነው። ከፍርድ በኋላም በዙፋኑ ለዘላለም የሚቀመጠውም በተዋዕዶ ነው።
ከተዋዕዶ በኋላ ሁለትነት የለም ። ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ብለን እናምናለን ፡፡ እንዲህ እናምናለን እንዲህ እንታመናለን።
ይቆየን............
ምሥጢረ ሥጋዌ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከሁሉም ምሥጢራት በኋላ እንመለከታለን ። ባህር በጭልፋ እንደመጨለፍ ያህል ምሥጢረ ሥጋዌ አየን እንጂ አላለቀም እናንተው አንብቡ አባቶችንም ጠይቁ ። ባለማወቅ መዳን የለም በማወቅም መዳን የለምና።
ወስ ብሐት ለእግዚአ ብሔር

❤4👏2
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል ዘጠኝ
ምሥጢረ ጥምቀት ፩
በክርስቶስ ክርስቲያን የተባላችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ.. አሜን የአምላካችን ስም ከምድር እስከ አርአያም ድረስ የተመሰገነ ይሁን አሜን !!!
እግዚአብሔር አምላክ ቢፈቅድና ቢረዳን ዛሬ ምስጢረ ጥምቀትን እንመለከታለን፡፡
✅ ምሥጢረ ጥምቀት ✅
•ጥምቀት ‹‹አጥመቀ/አጠመቀ›› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን መነከር፣ መጥለቅ፣ መደፈቅ፣ በውኃ ውስጥ በስመ ሥላሴ መዘፈቅ ማለት ነው፡፡
•ጥምቀት የሥላሴ ልጅነት የሚሰጥበትና የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት ሚስጢር ነው፡፡
የጥምቀት አስፈላጊት/ ጥቅም/
•በጥምቀት እንድናለን፣ ማር 16፡16‹‹ በጥምቀት ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ እንወለዳን፡፡ የመጀመሪያው ሥጋዊ ልደት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በጥምቀት የሚገኘው መንፈሳዊ ልደት ነው፡፡ ዩሐ 3፡3፣ ቲቶ 3፡5፣ ኤፌ 5፡26
•በጥምቀት የኃጢአት ስርየት ይገኛል፡፡ የሐዋ 2፡38፣ 1ኛ ቆሮ 6፡11
•በጥምቀት ከክርስቶት ጋር አብረን እንሞታለን፣ ከእርሱም ጋር እንነሳለን፡፡ ሮሜ 6፡8፣ ሮሜ 6፡3-4
•በጥምቀት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን፡፡ ገላ 3፡27
•በጥምቀት የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡፡ ቆላ 2፡11-13
የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን
•ኖኅና ቤተሰቡ በመርከብ ከጥፋት ውኃ መዳናቸው የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ 8፡18፣ 1ኛ ጴጥ 3፡20-21
•የእስራኤል ባሕረ ኤርትራን ማቋረጥ የጥምቀት ምሳሌ ነውው፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2
•ግዝረት የእግዚአብሔር ህዝብ መለያ ምልክት ነበር፡፡ ዘፍ 17፡14፣ዩሐ3፡3-6፣
•ግዝረት ሊመጣ ላለው ለጥምቀት ምሳሌ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ቆላ 2፡10-11
✅ የጥምቀት አመሰራረት ✅
የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ጌታችን መድኃኒቻችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ጥምቀትን የመሠረተው በተግባ በማሳየት፣ በቃል(በትምህርት)፣ በማዘዝ ነው፡፡ ማቴ3፡13-27፣ ማር 1፡9-11፣ ሉቃ 3፡21-22፣ ዩሐ 1፡31-34
የክርስቶስ ጥምቀት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተጠመቀ
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዩሐንስ እጅ በባህረ ዮርዳኖስ የተጠመቀው እንደ አይሁድ ሥርዓት ለመንጻት፣ እንደ ዩሐንስ ጥምቀት ከእስር ኃጢአት ለመንጻት አይደለም፡፡
•ለአብነት ፣ እርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ለማለት አርአያ ለመሆን ዩሐ13፡12-19
•በብሉይ ኪዳንም ተሰውሮ የነበረውን አንድነትና ሦስትነት ለመግለጥ ማቴ 3፡16-17
•ጠላት ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡፡ ቆላ 2፡14-15
•የእኛን ጥምቀት ለመባረክና ለመቀደስ
✅ ጌታችን ለምን በ30 ዘመኑ ተጠመቀ ✅
•በኦሪት ሕግ መሰረት ለክህነት አገልግሎት መመረጥ የሚቻለው በ30 ዘመን እንደነበር ሁሉ እርሱም የሊቀካህናቱን ተግባር ፣ የመምህርነቱን ሥራ፣ የአዳኝነቱን ሥራ በ30 ዘመኑ በጥምቀት ጀመረ፡፡ ዘኅ4፡23፣ ዘኅ 4፡1-3፣46-48
•አዳም በ30 ዘመን አግኝቶት የነበረውን በኋላም ያጣውን ልጅነት ሊመልስለት
•ሥልጣነ ክህነት/ ቅስና/ በ30 ዘመን ጀምሮ መቀበል እንዳለባቸው ለማጽናት
✅ ጌታችን ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ ✅
•አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ መዝ 113፡3-7
•የተመሰለውን ምሳሌ አማናዊ/እውነተኛ/ ለማድረግ፡፡ ይኸውም አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን ድል አድርጎ ዮርዳኖስን ተሻግሮ መልከጼዴቅን አግኝቶ ኅብስት አኮቴትና ጽዋና በረከት ማግኘቱ፣ ማቴ 14፡17፣ ዕብ 7፡1-10
•እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምድረ ርስት ለመግባታቸው ፡፡ ኢያሱ 3፡14-17፣ ኢያሱ 4፡15-18
•ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ማረጉ 2ኛ ነገ 2፡8-14
•ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከለምጹ መፈወሱን ፡፡ 2ኛ ነገ 5፡14
•ኢዮብ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከደዌ መዳኑን፡፡
•በዮርዳኖስ የተጣለው የዕዳ ደብዳቤያችንን ይቀድልን ዘንድ ቆላ 2፡14
የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራተ የበኩራት ልጆች የሰማነውን ያነበብነውን በልቦናችን ላይ በእውነት ይፃፍልን፡፡ በቀጣይ ክፍል * ጌታችን ለምን በውኃ ተጠመቀ * በሚል ርእስ እንመለሳለን ።
ላስተማረን ለመከረን ለአባቶቻችን አምላክ ምስጋና ይግባው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቀጥላል........

❤2
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስር
ምሥጢረ ጥምቀት ፪
በክርስቶስ ክርስትያን የተባላችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ.. አሜን የአምላካችን ስም ከምድር እስከ አርአያም ድረስ የተባረከ ይሁን አሜን !!!
ጌታችን ለምን በውኃ ተጠመቀ?
ጌታችን የሁሉ ፈጣሪ ሲሆን በማር፣ በወተት ወይም በሌላ ፈሳሽ ሳይጠቀም በውኃ የተጠመቀበት ምክንያት ነበረው፡፡ ምክንያቶቹም
ሰዎች ውኃ ለመዓት እንጂ ለምህረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምህረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ፣
ውኃ በሁሉም ቦታ ለሁሉ ሰው ይገኛል፣ ጥምቀትም ለመላው የሰው ዘር የተሰጠ ነው፡
ውኃ በአትክልት ላይ ቢያፈሱት ያለመልማል፣ እናንተም በውኃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋና ነፍስን ታገኛላችሁ ሲል
ውኃ እድፍን ያነጻል፣ በውኃ ስንጠመቅ የነፍስን ንጽሕና እንደምናገኝ ለማጠየቅ ነው
ውኃ መልክን ያሳያል፣ እንዲሁም በጥምቀት የሥላሴን ምሥጢር በዓይነ ሕሊናችን እናያለን ሲል
ውኃ እሳት ያጠፋል፣ እናንተም ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል
ውኃ የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ዘፍ.2፣ ዩሐ 1፡14፣ መዝ 1፡3
በነብዩ ሕዝቅኤል የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ
የክርስትያኖች ጥምቀት
ሰው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም እንደተባለ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እምነታችንን ለማጽናት ከሥላሴ ልጅነት ለማግኘት ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስቅዱስ በጥምቀት እንወለዳለን፡፡ ዩሐ 3፡5፣ ማቴ 28፡28-19
ጥምቀት የሚፈጸመው በቅድሚያ ቤተክርስቲያን በከበረ/በተጸለየበት/ ውኃ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስቅዱስ ስም አጥማቂው በተገኘበት ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር በመነከር ነው፡፡ ሮሜ 8፡12፣ በአጠቃላይ ለጥምቅት አስፈላጊ ነገሮች ከዚህ በታች የተቀመጡት ናቸው፡፡
የተጠማቂው ሀይማኖት ፡፡ ማር 16፡16፣ የሐዋ 2፡34፣ ሐዋ 8፡37
አጥማቂው ካህን፣ ማጥመት የሚገባቸው ካህናት ብቻ ናቸው፡፡ ማቴ 28፡19
በውኃ መጠመቅ፡፡ ዩሐ 3፡5፣ የሐዋ 8፡38፣ ኤፌ 5፡26፣ ሕዝ 36፡25
በሥላሴ ስም መጠመቅ ማቴ 28፡19
ጥምቀት አንዲት ናት
ጥምቀት በወራጅ ውኃ ብትፈጸም፣ በፈሳሽ ውኃ ብትፈጸም፣ በገንዳ ውኃ ብትፈጸም፣ በሊቀጳጳስ ፣ በኤጴስ ቆጶስ፣ በቄስ እጅ ብትደረግ አንዲት ናት፡፡ ኤፌ 4፡5 ጥምቅት የማይደገም አንድ ብቻ የሆነበት ምክንያት አለው
ከሥጋዌ ወላጆቻችን በሥጋ የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ከመንፈሳዊ አባታችን የምንወለደደው መንፈሳዊ ልደታችንም አንድ ጊዜ ብቻ ስለሆነና ሰለማይደገም፡፡ ዩሐ 3፡6-8
የጥምቀት ምሳሌ የሆነው ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚፈጸም ጥምቀትም አንድ ጊዜ ብቻ ይፈጸማል፡፡ ቆላ 2፡11-13
ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንሆንበት ምስጢር በመሆኑ ጌታም የሞተውና የተነሳው አንድ ጊዜ ብቻ ነውና፡፡ ቆላ2፡12፣ ሮሜ 6፡3-4
ማጠቃለያ፡- ጥምቀት ሰው በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስቅዱስ ስም በውኃ ሦስተ ጊዜ ጠልቆ ዳግመኛ ተወልዶ የቤተክርስቲያን ወገን ለመሆን የሚችልበት ምሥጢር ነው፡፡ ማቴ 28፡19 ወደ ቤተክርስቲያንና መንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ ዩሐ3፡6 ጥምቀት አትደገምም፣ አትከለስም፡፡ ኤፌ 4፡5
የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራተ የበኩራት ልጆች የሰማነውን ያነበብነውን በልቦናችን ላይ በእውነት ይፃፍልን፡፡

👇👇👇✍✍✍✝✝✝🍏🍏
በስመ አብ ወውልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ አንድ
ምሥጢረ ጥምቀት ፫
በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች የቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ቅዱሳን ወዳጆች በወደደንና ባፈቀረን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላም እላችኋለው ።
ባለፈው ክፍላችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላሳ ዘመኑ በባህረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ጥምቀትን እንደመሰረተ ተመልክተናል ። ዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድና ቸርነት የሕጻናት ጥምቀትን እንመለከታለን።
👉👉 የሕጻናት ጥምቀት
የእኛ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናት በ40ና በ80 ቀን ታጠምቃለች ። ምክንያቱም ኩፋ 4፥9 " ከተፈጠረባት ምድር ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኋላ ይገዛትም ይጠብቃትም ዘንድ ገነት አስገባነው፥ ሚስቱንም በሰማንያ ቀን አስገባናት ። " ይላል ። አዳምና ሔዋን ከመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ልጅነትን ተቀብለው በመላእክት ታጅበው በ40ና 80 ቀን ገነት እንደገቡ ዛሬም ወንድ ልጅ በተወለደ በ40 ቀኑ ፥ሴት በተወለደች በ80 ቀኗ የሥላሴ ልጅነት ያገኙ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ታጠምቃለች ።
👉 በብሉይ የጥምቀት አምሳል የሆነችውን ግዝረትን ስንመለከት ይፈጸም የነበረው በሕጻንነት ነው። በተወልዱ በ8ኛው ቀን ይገረዙ ዘንድ እግዚአብሔር ለአብርሃም አዞታል።ይህም ሕዝብን ከአሕዛብ ሲለይ እንደቆየ ሁሉ ዛሬም ጥምቀት አማኙን ከኢ -አማኙ ትለያለች። ዘፍ 17፥1-5 ያልተገረዙትም በአዋቂነታቸው ይገረዛሉ አብርሃም ሲገረዝ የ99 ዓመት እስማኤል ሲገረዝ የ13 ዓመት እንደነበሩ ሁሉ በሕጻንነት ያልተጠመቁትን ንዑሰ ክርስቲያን አላጠምቅም አትልም ሶስት አመት ትምህርተ ሃይማኖትን አስተምራ ሲያምንና እምነቱን ሲመሰክር ታጠምቀዋለች። ይህም የንዑሰ ክርስቲያን ጥምቀት ይባላል።ቆላ 2፥11-12 " የሥጋንም ሰውነት በመግፈፍ በክርስቶስ መገረዝ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ የተገረዛችሁ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበራችሁ። " ብሎ አረጋግጦልናል ።
👉 በዘሌ 12፥1-8 ላይ እስራኤላዊያን በመንፈሰ ረድኤት የእግዚአብሔር በረከት እንዲያ ድርባቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸው እንዲረጋገጥ ወንድ ልጅ በተወለደ በ40 ቀኑ ሴት ልጅ በተወለደች በ80 ቀኗ ወላጆቻቸው የመንጻት ወራታቸው ሲፈጸም መስዋዕት ለማቅረብ ይዘዋቸው ወደ ቤተ መቅደስ እንዲሄዱ ታዘዋል ። ካህናቱም ባርከዋቸው ስምቸውን መዝገበው የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸውን አ ገንዝበው ይሰዷቸው ነበር። እንድዚሁም ቤተ ክርስቲያን ሕጻናቱን በ40ና 80 ቀን አጥምቃ የእግዚአብሔር ወገን ታደርጋለች። ይህ ደግሞ ያልተሻረ ሕግ ነው ጌታም ሲያስተምር እኔ ሕግና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ላጸና እንጂ ማቴ 5፥17 ስለዚህ ይህን ሕግ የሥላሴ ልጅነት በማሰጠት አጽንቶታል ።
👉 1ቆሮ 10፥1-2 " ወንድሞች ሆይ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለው አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባህር መካከል ተሻገሩ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባህር ተጠመቁ " ታዲያ እዚህ ጋር የተጠመቁት አዋቂዎች ብቻ ናቸው አይደለም ሕጻናትም ጭምር እንጂ።
👉 ዮሐ 3፥5 "ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም " ታዲያ እነዚህ ሕጻናት ሳይጠመቁ ሰላሳ አመት ሳይሞላቸው ቢሞቱ አይድኑም ? ማን ልጠየቅ ነው ታዲያ ? እነሱ ወይስ ቤተሰብ ? ስለዚህ መዳን በራሳችን ሥራና እምነት እንጂ በሌላ አይደለም ። ያልተጠመቀ ደግሞ አይድንም ስለዚህ በሕጻንነት መጠመቅ አለባቸው ። መንግስተ ሰማይ የአዋቂዎች ብቻ አይደለችም ፡፡
👉 እግዚአብሔር ሕጻናቱን ከጸጋው አያርቃቸውም ። ነቢዩ ኤርሚያስ ከማኅጸን መርጧል ።መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ከማኅጸን ቀድሷል ። ኤር 1፥4-5 ; ሉቃ 1፥42-45 ። " ሕጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው የእግዚአብሔር መንግስት እንድዚህ ላሉት ናትና። ማቴ 19፥13-15; ማር 10፥ 14-16; ሉቃ 18፥ 15-17 ታዲያ እኛ ምን ቤት ነን እነሱን ከበረከቱ የምንከለክላቸው ።
👉 ቅዱሳን ሐዋርያት እን ደታዘዙት አስተምረው ሲያጠምቁ ቤተሰቡን በሙሉ ነው ያጠመቁት ከእነዚህም ውስጥ ሕጻናት ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የመቶ አለቃውን ቆርኔሌዎስ እስከ ቤተሰቡ አጥምቆታል። ሐዋ 10፥44-48 ሊድያም ከነቤተሰቧ ሐዋ 16፥15 የእስር ቤቱም ዘበኛ እስከነቤተሰቡ 1ቆሮ 1፥16 ። ታዲያ ከጌታ እግር ስር የተማሩት ሐዋርያት ተሳሳቱ እንበል ? አልተሳሳቱም ሁሉንም በአብ በውልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቁ እንጂ።
👉 ማር 16፥16 " ያመነ የተጠመቀ ይድናል " ይላል ስለዚህ ሕጻናትን ሳያምኑ ታጠምቃላችሁ ይላሉ ። የመጽሐፍን ቃል ባለማወቅ የተነሳ ትስታላችሁና እንዳለው ብዙዎች በገዛ ፍቃዳቸው እየተረጎሙ ከእውነተኛው መንገድ ፈቅ ብለዋል፡፡ ይህ ቃል የተነገረው ለንዑሰ ክርስቲያን መሆኑ ከላይ መመልከት በቂ ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት ሲያዛቸው ሂዱ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ስበኩ ስብከታችሁን ተቀብሎ ላመነ አጥምቁ ብሏቸዋል ። ይህም ለአዋቂዎች የተነገረ ነው ። ቤተ ክርስቲያናችን ለሕጻናትም ቢሆን ሥርአትን ሰርታለች ። ክርስትና አባትና እናት አሰናድታ ሕጻናቱ ከተጠመቁ በኋላ እንዲያስተምራቸው ገስጽሠው እንዲያሳድጓቸው ስርአትን ሰርታለች ። ኃላፊነታቸውን ባይወጡ ፍርዱ በእነሱ ላይ ይሆናል ፡፡
ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቀጥላል......

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ ሁለት
ምሥጢረ ጥምቀት ፬
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉዳን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኙ የአቁራሪተ መአት ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወደደንና ባፈቀረን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላምታዬን እየቀረብኩ ወደ ጽሑፌ እገባለው ።
✍ የጥምቀት አስፈላጊነት
1. ድኅነትን ያስገኛል ፦ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል። "
2. ዳግም መወለድን ያጎናጽፋል። " እውነት እውነት እላለሁ ሰው ከውሀና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት አይገባም ።" ቲቶ 3፥5; ኤፌ 5፥26
3. የኃጢአት ሥርየት ይገኛል።
ሐዋ 22፥16 "ተነሳና ስሙን እየጠራ ተጠመቅ ፥ከኃጢአትም ታጠብ " ይላል እንዲሁም አናንያ ለቅዱስ ጳውሎስ ይሄንኑን ብሎታል ።ሐዋ 9፥15-16 ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ብሏል " ከእናንተ አንዳንዶች እንዲህ ነበራችሁ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥቧችኋል ፥ ተቀድሳችኋል ፥ ጸድቃችኋል ፡፡ " 1ቆሮ 6፥11 ቅዱሳን ሐዋርያት በበዓለ ኃምሳ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሕዝቡን ሰብኳል ከዚያም ምን እናድርግ ሲሉት " ንስሀ ግቡ ኃጥአታችሁ ይሰተሰርይ ዘንድ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ " ሐዋ 2፥ 37-38 ሠለሰቱ ምእትም በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ብለዋል።
4. በጥምቀት አዲስ ህይወት ይገኛል ። "እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር እንደተነሳ እንዲሁ እኛም በአዲስ ህይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን " ሮሜ 6፥4
5. ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆናለን ። "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችሁታል። " ገላ 3፥27
6. የቤተ ክርስቲያን አባል እንሆናለን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የጥምቀት ምሳሌ በቡሉይ ኪዳን
1. ግዝረት ፦ ሕዝብን ከአሕዛብ እንደሚለይ ሁሉ ጥምቀትም ያመኑትን ካላመኑት ትለያለችና ።ዘፍ17፥4 ; ቆላ 2፥ 10-12
2. እስራኤላዊያን ባህረ ኤርትራን መሻገር ፦ ባህረ ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስት እንደገቡ እኛም በጥምቀቱ አምነን ብንጠመቅ መንግስተ ሰማያትን መውረሳችንን ያመላክታል። 1ቆሮ 10፥1-12
3. ንህማን በዮርዳኖስ ባህር መጠመቅ ፦ ተጠምቆ ከለምጹ እንደዳነ በጥምቀት የኃጢአት ሥርየት ይገኛልና ።2ነገ 5፥ 8-14
4. ሕ ዝበ እስራኤላዊያን ባህረ ዮርዳኖስ ተሻግረው ምድረ ርስት መግባታቸው በጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባታችን ያመላክታል።
@ ...በውሀ አጠብኩሽ ከደምሽም አጠራሁሽ በዘይትም ቀባሁሽ ...ሕዝ 16፥9 @
ምሥጢረ ጥምቀት ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል ፡፡ በምሥጢረ ጥምቀት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከምሥጢራቶች በኋላ እንመለከታለን ። ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ ስም የተመሰገነ ይሁን ፡፡
ይቆየን......
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!
ቀጣይ.....#ምሥጢረ ቁርባን#

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኑ ሆሳዕና በዓርያም እንበል❗️
የዘንድሮውን የሆሳዕና በዓል የት ለማሳለፍ አስበዋል ፧ ከቀጠሮ በፊት ቀጠሮ እንስጦት ሆሳዕናን በመርካቶ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃ የዘንድሮው የሆሳዕና በዓል አዘጋጅ የመርካቶ ደ/ኃ/ቅ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት ቤት ነው።
ስለሆነም በዓሉን የተመለከቱ ልዩ ልዩ መርሐግብሮችን ከመጋቢት 19 ጀምሮ ወደ እናንተ እየደረሱ ይገኛል።
በበዓሉ ዋዜማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጥምቀተ ባሕር የሚካሄደውን የማጠቃለያ መርሐግብር ጨምሮ የሆሳዕና አውደ ርዕይ ፣ ዝማሬ ፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ሆሳዕና በአርያም ብለው በዘመሩ ህጻናት ይቀርባሉ።
ኑ ሆሳዕና በአርያም ከህጻናቱ ጋር እንበል።
አንቀጸ ብርሃን ሚዲያን በተለያዩ አማራጮች ይከተሉ
https://www.youtube.com/@anqetseberhanmedia7501
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Anqetseberhansundayschool
የፌስቡክ ፔጅ
http://www.facebook.com/sundayschoolofSR

❤1
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
ክፍል አስራ ሶስት
ምሥጢረ ቁርባን ፩
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉዳን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰኛችሁ የወላዲተ አምላክ ፍጡነ ረድኤት የሰአሊተ ምህረት የድንግል ማርያም የአስራት የበኩራት ልጆች በወደደንና እስከ ሞት ድረስ ባፈቀረን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰላም ሰላም እላችሃለው።
እግዚአብሔር አምላክ ቢፈቅድና ቢረዳን ዛሬ ምስጢረ ቁርባንን እንመለከታለን፡፡
✍ ቁርባን፡- የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን በቁሙ መንፈሳዊ አምኅ፣ መሥዋእት፣ መባዕ ለአምላክ የሚቀርብ የሚሰጥ ገንዘብ ማለት ነው፡፡
✍ ምሥጢረ ቁርባን ማለት ካህኑ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ በጸሎተ ቅዳሴው በባረከው ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት፣ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆንበትና እኛም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ይህንን የክርስቶስ ሥጋና ደም የምቀበልበት ዐቢይ ምሥጢር ነው፡፡
👉የምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ በብሉይ ኪዳን
☘ 1. ካህኑ የሰላም ንጉሥ መልከጼዴቅ፣ አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ድል ነስቶ ሲመለስ ይዞ የተቀበለው ወይንና ሕብስት፡፡ ዘፍ 14፡18-20፣ ዕብ 5፡6-10፣ ዕብ7፡3-7፡፡
መልከጸዴቅ ለአብርሃም የሰጠው ኅብስትና ወይን የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ሲሆን መልከጸዴቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡
☘ 2. ለእስራኤል በምድረ በዳ የወረደላቸው መና የጌታ ሥጋና ደም ምሳሌ ሲሆን መናው የተገኘበት ደመና ደግሞ ጌታ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነባት የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡ ዘጽ 16፡13፣ ዩሐ 6፡49-51
👉 በብሉይ ኪዳን የሚሰጠው ጥቅም
🌹ድኅነተ ሥጋና መንጻት ይሰጥ ነበር
🌹የሥጋ በረከት ያሰጥ ነበር
🌹ጊዜያዊ እርቅ ያሰጥ ነበር
👉 በብሉይ ኪዳን ቁርባን ያቀረቡ አበው
1.አዳም፡- ባቀረበው ቁርባን ከ5 ቀን ተኩል በኃላ አድንሃለሁ የሚለውን ተስፋ አግኝቷል፡፡ ገላ 4፡3-7
2.ኖኅ፡- ባቀረበው ቁርባን ምድር ሁለተኛ በንፍር ውኃ እንደማትጠፋ የቀስተደመና ምልክት የጸና ቃል ኪዳን ተቀብሏል፡፡ ዘፍ 8፡20-22. ዘፍ 9፡8-17
3. አብርሃም፡- ባቀረበው ቁርባን በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ የሚል ተስፋ አግኝቷል፡፡ ዘፍ 18፡3-18
👉የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት
ቁርባን የተጀመረው ከሰው በደል ወዲህ ነው፡፡ ዘፍ 4፡3-4 ነገር ግን መስዋዕት ኦሪት አልፎ መስዋዕተ ሐዲስ በመተካቱ ድኅነተ ነፍስ የሚያሰጥ ምሥጢረ ቁርባን የተጀመረው በጸሎተ ሐሙስ ምሽት በአልዓዛር ቤት በጌታችን አማካኝነት ነው፡፡ ማቴ 26፡26-29
👉የምሥጢረ ቁርባን አገልግሎት/ጥቅም/
1. በምሥጢረ ቁርባን የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን፡፡ ዮሐ 6፡54
ቅርንጫፍ ከግንዱ እስካልተለየ ድረስ ሕይወት እንዲኖረው ሁሉ ከርስቲያኖችም የወይን ግንድ ከሆነው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አለመለየታችንን ፣ በሕይወት መኖራችንን፣ ለኃጢአት አለመሞታችንን እናረጋግጣለን፡፡ ዩሐ 6፡54
2. በዕለተ ዓርብ ጌታችን በጎልጎታ በመልዕልተ መስቀል ላይ የቆረሰውን ቅዱስ ሥጋና የፈሰሰውን ክቡር ደም እንቀበላለን፡፡
3.በመንፈሳዊ ዕውቀት የምናድግበትና በፀጋው የምንበለጽግበትን የሕይወት ምግብ እናገኛለን፡፡
4. ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን በሕይወታችን ውስጥ ይኖራል፡፡ ዮሐ 6፡35
👉ቅዱስ ቁርባን በስንዴና በወይን የሆነበት ምክንያት
ከአዝርእት ሁሉ ለጌታ ይሆን ዘንድ ስንዴ ከፍራፍሬ ደግሞ ወይን መሆኑ ምክንያት ነበረው
1. ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ፣ መልኬጸዴቅ በወይን በስንዴ ያመሰግን ነበር፡፡ ዘፍ14፡18፣ ዕብ 7፡1-3፣ ይህም የሥጋ ወደሙ/ቁርባን/ ምሳሌ ነው፡፡
2. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፣ ‹‹ በልቤ ደስታን ጨመርኩ ከስንዴ ፍሬ ከወይን ከዘይትም በዛ›› መዝ 4፡7
ምሥጢር ስላለው ነው፡ ይኸውም ስንዴ ስብ ሥጋን ይመስላል፣ ወይን ደግሞ ትኩስ ደምን ይመስላል፡፡ ስለዚህ በሚመስል ነገር መስጠቱ ነው፡፡
👉 ቅዱስ ቁርባን በመብልና በመጠጥ የሆነበት ምክንያት ለምንድን ነው ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውና ደሙን በወርቅ በብር ሳይሆነ በመብልና በመጠጥ ያደረገበት ምክንያት
መብልና መጠጥ ከሰውነት ጋር ይዋሐዳሉ ወርቅና ብር ግን አይዋሐዱም ስለዚህ በሰውነት እንዲዋሐደን ለማስረዳት ነው
ተርቦ ሳለ ሰው ወርቅና ብር ከሚሰጠው ለርሃቡ ምግብ ለጥማቱ መጠጥ የሰጠውን እንደሚወድ እወዳችኋለሁ ትወዱኛላችሁ ሲለን ሥጋውና ደሙን በመብልና በመጠጥ አደረገው፡፡
✍ማጠቃለያ፦
ቅዱስ ቁርባን መታሰቢያ ወይም ምሳሌ ሳይሆን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም ነው፡፡ ማቴ 26፡26-29፣ ዮሐ 6፡51፣ በ1ኛ ቆሮ 11፡23-24
ይህንን ለመታሰቢዬ አድርጉት ሲል መከራዬን ሕመሜን ቤዛነቴን እያሰባችሁ አምናችሁ ሥጋዬንና ደሜን ተቀበሉ ማለቱ ነው
ቅዱስ ቁርባን እንደ ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ ተቀብለን የምንተወው ሳይሆን በተደጋጋሚ የምንቀበለው ምሥጢር ነው፡፡
በኃጢአት ሆነው ሥጋ ወደሙን መቀበል አይገባም፣ ከተቀበልን ግን ዕዳ ይሆንብናል፡፡ 1ኛ ቆሮ 11፡27
ሥጋ ወደሙ በዕድሜ ፣ በጾታ ሳይወሰን ለማንኛውም ክርስቲያን የተፈቀደ ነው፡፡ 1ኛ ጴጥ 3፡18
ቀሳውስት በቅዳሴ ጊዜ የሚያቀርቡት ኅብስት አማናዊ የክርስቶስ ሥጋ ወይኑም አማናዊ የክርስቶስ ደም ነው፡፡
ያስተማረን የመከረን የአባቶቻችን አምላክ ስም ከምድር እስከ አርያም ከናጌብ እስከ አድማስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የተመሰገነ ይሁን !!! አሜን !!!
ይቆየን !!!
ወስ ብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን !!!

ይህንን♦♦ ያውቃሉ
✍13ቱ ሕማማተ መስቀል
✍7ቱ የመስቀሉ ቃላት
✍7ቱ ተዐምራት
✍5ቱ ችንካሮች
✍5ቱ ኃዘናት
13ቱ --ሕማማተ_መስቀል
1ኛ. ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. በገመድ መሳብ)
3ኛ.በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ፡በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. በጥፊ መመታት)
7ኛ. ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. መስቀል መሸከም)
11ኛ. በችንካር መቸንከር)
12ኛ. በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ፣መራራ ሐሞትንመጠጣት)
ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ
23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ
23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
ሰባቱ ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች
1. ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
4. ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
አምስቱ ኃዘናት
1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35
2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48
3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1
4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡
ዮሐ 19:17-22
5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42
http://t.me/sraged
✍13ቱ ሕማማተ መስቀል
✍7ቱ የመስቀሉ ቃላት
✍7ቱ ተዐምራት
✍5ቱ ችንካሮች
✍5ቱ ኃዘናት
13ቱ --ሕማማተ_መስቀል
1ኛ. ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. በገመድ መሳብ)
3ኛ.በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ፡በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. በጥፊ መመታት)
7ኛ. ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. መስቀል መሸከም)
11ኛ. በችንካር መቸንከር)
12ኛ. በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ፣መራራ ሐሞትንመጠጣት)
ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ
23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ
23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
ሰባቱ ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች
1. ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
4. ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
አምስቱ ኃዘናት
1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35
2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48
3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1
4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡
ዮሐ 19:17-22
5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42
http://t.me/sraged
Telegram
አንቀጸ ብርሃን ትምህርት ክፍል
ይህ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ነው
የትምህርት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ የተለያዩ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው
የትምህርት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ የተለያዩ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው
❤1
✝✅✝✅❤️💜❤️💜🍏☘🍏
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
👉የጌታችን ትንሳኤ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታንን በቃል አስተምሮናል፡፡ ማቴ 20፡19፣ ሉቃ 18፡31-33፣ ማቴ 27፡62-64 በቃል ብቻ አይደለም ሞቶ መነሣት ትንሣኤን በተግባር በመፈጸም አሳይቶናል ዮሐ 20፡1፣ ማቴ 28፡1፣ ሉቃ 24፡1 ማር 16፡1 ጌታችን ዓርብ በ9 ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በሥልጣኑ ለየ፡፡ ዮሐ 19፡30 11 ሰዓት ሲሆን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀል አውርደው በአይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፍነው ማንም ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ የመቃብሩንም ደጃፍ በታላቅ ድንጋይ ዘጉት ማቴ 27፡57፡61 ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በለየ ጊዜ ሦስት መዐልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፡፡ በነፍሱም ደግሞ ወደ ሲኦል በመውረድ ለነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው ነጻም አወጣቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህን ሲገለጽ ‹‹በሥጋ ሞተ በመንፍስ ግን ህያው ሆነ እርሱም ደግሞ ሄዶ በወህኒ ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ሰበከላቸው›› 1 ጴጥ 3፡18 በማለት ተናግሯል፡፡ ከተዋህዶ በኋላ መለኮትና ትስብእት ለቅጽበተ ዓይን መለያየት የለባቸውምና ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር በመውረድ ሥጋን ሙስና መቃብር ማለት ፈርሶ በስብሶ እንዳይቀር ሲያደርገው በነፍስ ወደ ሲዖል በመውረድ ነፍሳትን ከዲያብሎስ ማርኮ ነፃ አውጥቷል፡፡
👉የትንሣኤ አማናዊነት
የጌታችን ከሞት መነሣት ለክርስትናው ሃይማኖት ወሳኝ ነው፡፡ ትንሣኤ ዓለምን የለወጠ ምሥጢር ነው፡፡ ትንሣኤው ኃይል ነው፡፡ ጌታ ከሞት ባይነሳ ኖሮ ክርስትና ያለፈ ታሪክ ብቻ በሆነ ነበር፡፡ ስለዚህ በትንሣኤው እውነተኝነት ወይም አማናዊነት ማመን በእምነት ውስጥ የማዕዘን ደንጊያ ነው፡፡ በጥንት ዘመን የነበሩ ሁለት ክርስቲያኖች ሲገናኙ‹‹ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ --- እውነት ተነሣ›› በማለት ነበር ሰላምታ የሚለዋወጡት ወይም ደግሞ ‹‹ማራናታ›› በሚል ቃል ሰላምታ የሚመጣው ማለት ነው፡፡ ‹‹ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ … በእውነት ተነሣ›› የሚለው የክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሰላምታ ልውውጥ በብዙ ሐገሮች እስከዛሬ ቀጥሎአል፡፡
እንግዲህ እነዚህ ሰላምታዎች ክርስቲያኖች በክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊነት ያላቸውን ጽኑ እምነት የሚያሳይ ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊ ባይሆን ምን ያህል ከንቱ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲገልጽ ‹‹ ክርስቶስ ከሙታን እንዴት የለም ይላሉ? ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሳማ፣ ክርስቶስ ካልተነሳ እንግዲህስ ስብከታችን ከንቱ ነው፡፡ እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት… በዚህች ህይወት /በምድራዊ ህይወት/ ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን›› በማለት ያለ ክርስቶስ ትንሣኤ በክርስትና ያለው ሁሉ ከንቱ እንደሚሆን ገልጧል፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፡12-29
ዮሐ 20፡6-7 የተልባ እግር ልብሱና በራሱ ላይ የነበረው ጥምጣም ተለያይተው መቀመጣቸው ለጌታ ትንሳኤ አስረጂ ናቸው፡፡ በአይሁድ አባባል የጌታ ሥጋ ተሰርቆ ከሆነ ሰራቂው እንዴት ከፈኑን ከሰውነቱ ማለያየት ቻለ ዓላማውስ ምንድን ነው ጠባቆችስ በጥበቃ ላይ ሳለ እንዴት ከፈኑን ከሰውነቱ ለይቶ ማስቀረት ቻለ
ለዚህ ነው በቁጥር 8 ላይ ‹‹በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደመቃብር የመጣው ሌላው ደቀመዝሙር(ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው) ደግሞ ገባ አየም፣ አመነም›› የተባለው ምክንያቱም ደቀመዝሙሩ የተመለከተው ጌታ ሲነሣ አይደለም ይልቁንም ከፈኑን እንጂ ይህ ደግሞ ለመነሣቱ ማስረጃ ስለሚሆን አየም አመነም፡፡ ምንም እንኳን የክርስቶስ ከሞት መነሣት በብዙ መንገዶች የተረጋገጠ ቢሆንም አይሁድ ግን ያደረጋቸውን ተአምራቶች እንዳሳበሉ/እንደካዱ/ ሁሉ ትንሣኤውን ክደዋል፡፡ ማቴ 27፡63-66፣ 28፡11-15፣ 16-21 ፣ 17፡22-23፣ ሉቃ 24፡23-27፣ 24፡46፣ 24፡7፣
ይቆየን !!!
በቀጣይ ‹‹የአይሁድ ክህደት በትንሣኤውም ላይ›› በሚል ርዕስ እንመለሳለን!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!
https://t.me/sraged

✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ በስመ አብ ወውልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
✅ የአይሁድ ክህደት በጌታ ትንሳኤ
አይሁድ ከመጀመሪያውም የጌታን መምጣት ያልተቀበሉ ናቸው ምክንያቱም የጠበቁት እንደነ ንጉስ ዳዊት ነግሶ በጦርነት ከሮም ነጻ የሚያጣቸው መሲህ ይጠብቁ ስለነበር ነው ። እስራኤላዊያን ከጌታ ልደት አስራ አምስት ዓመት ቀድሞ በሮም ቀኝ ግዛት ስር ነበሩ። እስራኤላዊያን ጌታን እንደማይቀበሉ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ አስቀድሞ ተናግሯል ። ኢሳ 1፥2
ከጽንሰቱ እስከ ትንሳኤ ድረስ ጌታን ተቃውመዋል ። ሊቀ ካህናቱ ሀናና ቀያፋ የጌታን መነሳት ሲሰሙ በመደናገጥ በከተማው የሐሰትን ወሬ አስወርተዋል ። የጌታን ሥጋ ሰርቀውታል ብለው አስነገሩ ይጠብቁ የነበሩትንም ወታደሮች በሐሰት እንዲመሰክሩ አድርገዋል። ወታደሮቹም አንዱ ጴጥሮስ ወሰደው ሌላው ዮሐንስ ወሰደው ሌላው ከሐዋርያት አንዱ ወስደው አራተኛው ደግሞ ዮሴፍና ኒቆድሞስ ወሰዱት ብለው ተለያይተው በጲላጦስ ፊት መስክረዋል። በመሰረቱ የጌታን ሥጋ ሲወስዱ ታድያ ለምን የተገዘበትን መግነዝ መተው ለምን አስፈለጋቸው ። መግደላዊት ማርያምም ጌታን በአትክልት ስፍራ አግኝታ የጠየቀችውም ይህንን የሐሰት ምስክርነት ይዛ ጌታዬን ወሰደውታል ወዴት እንዳለ ታውቀዋለህ? ወስደኸው ከሆነ ? ብላ ለመጠየቅ አብቅቷታል ።
ሰማዕቱ ቅዱስ ጲላጦስም የጌታን መግነዝ አምጥቶ ለዮሴፍና ኒቆድሞስ አሳየው እነርሱም የገነዙበት እርሱ መሆኑን ነገሩት ። እርሱም ወስዶ እውራንን አበራበት ፤ ድውይን ፈውሰበት ፤ ጎባጣን አዳነበት ። ሙትን አስነሳበት ። ይህን ሁሉ ተመልክተው ግን ሊያምኑ አልቻሉም ይባስ ብለው የቤተልሔሙን ንጉስ ሄሮሥስ አሳምነው ከራሳቸው ጎን አደረጉ ። የጌታን ሥጋ የደበቁበትን ጉድጓድ አገኘን ብለው የሀሰት ፈጠራ በመፍጠር ለጲላጦስ ነገሩት ። የልባቸውን ክፋት የክህደታቸው ጥግ የጭካኔያቸውን ደረጃ ተመልክቶ በማዘን ፍላጎታቸውን ይፈጽም ዘንድ ወድ ጉድጓዱ በመሄድ መግነዙን በሥጋው ላይ ቢያደርግ ሙቱ ተነሳ ። የሚደንቀው ነገር ግን ከሙት የተነሳው ፈያታዊ ዘየማን ጥጦስ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ መሆኑ ነው ። ተነስቶም በጌታችን ኃይል መነሳቱን መስክሯል ። በከተማውም በመዞር የጌታን ትንሳኤ መስክሯል ። አይሁዳውያን ግን ከዓለት የጠጠረ ልባቸውን ከፈርኦን ይልቅ አደንድነው የጌታን መነሳት አንቀበልም ብለው ከሄሮድስ ጋር ተመሳጥረው ፈያታዊ ዘየማንን አንገቱ እንዲሰየፍ በማድረግ ሰማዕት እንዲሆን አድርገውታል ። ጲላጦስ ለሮሙ ቄሳር አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትን ተቀብሏል። ይህን ሁሉ ነገር እያዩ ሊያምኑ ያልቻሉት አይሁዳዊያን ለምን ይሆን ቢባል በምድራዊ ሀሳብ ስለተጓዙ ነው። እውነትም ጌታን አይተው ትንሳኤውን ተመልክተው ያላመኑት አይሁዳውያን ከንቱዎች ናቸው ። ጌታ እንዳለ ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው እውነት ነው። የሐዋርያትን አይን አይን አድርገን አየነው ፥ የሐዋርያትን እጅ እጅ አድርገን ዳሰስነው ስለዚህ አማን ውእቱ ተንስአ እሙታን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን እናምናለን እንመሰክራለን።
ይቆየን.........

🍎🍎🍎🍎ዮሴፍ ዘአርማቲያስ🍏🍏🍏🍏
በሐዲስ ኪዳን በጌታችን ሞት ጊዜ ሆኖ በጀግንነት እና በሥራው ትብብር ምልክት ሆኖ ይቀርባል
✍ ሀብታምና የተከበረ ሰው ነው ማቴ 27÷57
✍ የአይሁድ ሸንጎ( ሲንሃይድረይም) አባል ነበር በዚህም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሽሽግ ደቀ መዝሙር ነበር ዮሐ 19÷38 ይህም በሥልጣኑ የተነሳ ፍራቻ ስለ ነበረበት ነው
✍ አርማቲያ ከተባለች በናዝሬት ውስጥ የምትገኝ ትንሽ መንደር የተገኘ ሰው ነው
🍊🍏 በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቀበር ላይ የነበረው ሚና 🍊🍏
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በመስቀል ላይ ነፍሱን በገዛ ሥልጣኑ ሲለያት ዮሴፍ ዘአርማትያስ ጴንጤናዊ ጲላጦስ ዘንድ በመሄድ የክርስቶስ ሥጋ እንዲሰጠው ለመነው ጲላጦስ ከፈቀደለት በኋላ ሥጋውን ከኒቆዲሞስ ጋር በመሆን ከመስቀል አውርዶ በሐዲስ መግነዝ ገነዙት ውስጥም ለራሱ ባሠራው አዲስ መቃብር ቀበረው ማቴ 27÷60 ይህም የነቢዩን ኢሳይያስን ትንቢት የፈጸመ ነው ኢሳ 53÷9 "ከባለጠጋችም ጋር በሞቱ ...."
🍐 መንፈሳዊ ጠቀሜታው🍏
✍ድፍረትን ያሳያል ሌሎች በፈሩበት ሰአት በአደባባይ በሕዝቡና በሊቀ ካህናቱ ፊት ራሱን አቅርቦ በግልጥ የክርስቶስን ሥጋ ጠየቀ
✍ እምነትና ፍቅርን ይገልጣል ካለው ቦታ አኳያ ያለውን ተጽዕኖ ሳይፈራ እምነትን ፍቅሩን ገለጠ
✍ ለመቀበሩና ለመነሳቱ እውነተኛና ቁልፍ ምስክር ለመሆን በቃ
🍐ቅዱስ ትውፊት🍊
በትውፊት እንደተገለጠው ሐዋርያዊ ተልዕኮን ይፈጽም ዘንድ የወጣ ነበር በምዕራብ ቤተ ክርስቲያን እንግሊዝና አካባቢው እንዳስተማረ ይናገራሉ።
ይቀጥላል

❤️ዮሴፍ ዘአርማትያስ በቀደምት አበው 🌷
#ክፍል ሁለት#
ሀ/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ዮሴፍ ያረፈደ ቢሆንም በእምነት ያለውን ጀግንነት ያሳያል ሐዋርያቱ ፈርተው በሸሹበት ሰአት ዮሴፍ በአደባባይ ተአማኝነቱን አሳየ።
ለ/ ሊቁ አውግስጢኖስ ዘሂፖ
የነቢዩ ኢሳይያስን ትንቢት ያሳየናል ኢሳ 53÷9 ዮሴፍ በዝግታ አምነው ነገር ግን በዓላማ የሚሠሩ አማኞችን ይወክላል ባለጥግነቱን ለክርስቶስ በመጠቀሙ ምድራዊ ሀብት ላላቸው ሰዎች ሁነኛ ምሳሌ ነው።
ሐ/ሊቁ አርጌንስ
በተለይ ምሳላያዊ ምልከታ አለው አዲስ መቃብር ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ያሳያል ዮሴፍ ደግሞ የአማኞች ክርስቶስን በክብርና በንጽሕና መቀበልን ይወክላል።
መ/ ሊቁ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ
ታሪካዊ ፋይዳው ላይ ያተኩራል ። ዮሴፍ የክርስቶስ እውነተኛ ሞት እና እውነተኛ መቀበርን በመመስከር የክርስቶስን ሰውነት ለሚክዱ መናፍቃን ምስክር ይሆናል።
✍ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ✍
ዮሴፍ ዘአርማትያስ
✅ ባለጸጋና የሸንጎ አባል
✅ ድብቅ ደቀመዝሙር
✅ ጲላጦስን የጌታን ሥጋ የጠየቀ
✅ ወደ ሮማዊያን ሥልጣን የተጠጋ
✅ ድፍረት +መስዋዕትነት
ኒቆዲሞስ
✅ ፈሪሳዊና መምህር
✅ ድብቁን ምሥጢር ፈላጊ ዮሐ ፫
✅ የመግነዙን ጨርቅ ያመጣ
✅ ታላቅ ሰው
✅ በእምነት ያደገ
ኒቆዲሞስ በሌሊት በመምጣት የዳግም ልደትን ምሥጢር የተማረ ነው ዮሐ 3 ከዚያም ደግሞ ስለክርስቶስ ጥብቅና የቆመ ነው ዮሐ 7 በመጨረሻም ገንዞ የቀበረ መምህር ነው ዮሐ 19÷39
ኒቆዲሞስ እምነቱ በጥቂቱ እያደገ የመጣ ነው የዮሴፍ ግን በአንድ ጊዜ የተገለጠ ነው።
❇️የምንረዳው ነገር ❇️
የተደበቀ እምነት በሥራ ካልተገለጠ ከንቱ ነው ድፍረት ደግሞ በከባድ ችግር ውስጥ መገለጥ የሚችል ነው ሁለቱም ሰዎች ሁለት የተለያዩ ደቀ መዛሙርትነትን ያሳያሉ እነርሱም በማደግ የሚገለጥና በአንድ ተግባር የሚታይ ናቸው
✅ ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ❇️

✍ዮሴፍ ዘአርማትያስ🍐
ክፍል ሦስት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ
✅ ስለድፍረታቸው
✅ በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
✅ በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።
❇️ ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም
✅ ግልጽ እምነትን ይወክላል
✅ መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
✅ አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
✅ አዲስ መቃብር ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።
✅ መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
✅ ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
✅ ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል
❇️ የጌታ መቀበር ✅
የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
✅ ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል
✅ አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
✅ ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።
❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት ✅
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል
እምነት በሥራ እንደ ዮሴፍ የሚገለጥ እንጂ ተሸሸጎ የሚኖር አይደለም በሥራ ለመግለጥ ትጋት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ያለንን መሆኑን ከዮሴፍ እንማራለን በክርስቶስ መከራው ውስጥ በመሳተፍ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆናችንን መገለጥ አለብን።
የአርማትያሱ ዮሴፍን ከዮሴፍ አረጋዊ ጋር በማመሳሰል አንድ ናቸው የሚሉ አሉ ይህ በፍጹም ስህተት ነው ዮሴፍ አረጋዊ በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደምንመለከተው ያረፈው ጌታችን 25 ዓመት ሲሆነው ነው በዚያ ላይ ሥራው እንጨት ጠራቢ የነበረ ነው ይህ ግን ባለጸጋ የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ ነው።
ዮሴፍ ዘአርማትያስ የሐዲስ ኪዳን ጻድቅ ሲሆን ከኒቆዲሞስ ጋር ሐምሌ 17 ቀን ይከበራል በወንጌል ከተገለጠው ታሪክ በቀር የሚገለጥ ታሪክ ባይኖርም እንግሊዝ ሄዶ እንዳስተማረና መከራን ተቀብሎ ሰማዕት እንደሆነ በትውፊት ይነገራል
ይቆየን
ስለነበረን ጊዜ የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነና የተወደሰ ይሁን
ከትንሳኤው ረድኤት በረከት ይክፍለን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
http://t.me/sraged
ክፍል ሦስት
ዮሴፍ ዘአርማትያስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ሕማሙን መከራውን ከሆሳዕና እኩለ ቀን አንስታ እስከ ዕለተ ዓርብ ዐሥራ አንድ ሰአት ድረስ የሕማማት ሳምንት ብላ ታስበዋለች በዚህም ወቅት ከሚነበበው መጽሐፍ አንዱ ግብረ ሕማማት ነው በዚህም ሳምንት በስቅለት ዕለት ስማቸውን ከሚነሱት መካከል ዮሴፍ ዘአርማትያስ እና ኒቆዲሞስ ይገኙበታል።
ዕለተ ዓርብ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ማዕከላዊ ሚና ወስደዋል ቤተ ክርስቲያን ክብር በመስጠት በንባቡ ትገልጣቸዋለች በዚህም ውስጥ
✅ ስለድፍረታቸው
✅ በሥራ የተተረገመውን ፍቅራቸው
✅ በክርስቶስ መቀበር ባለቤት በመሆናቸው ትልቅ ክብር ሰጥታ ታስባቸዋለች። ሐዋርያት ሁሉ በተበተኑበት ሰአት የተገኙ ሁለት ዕንቁዎች ብላ ትገልጣቸዋለች።
❇️ ሥርዓተ አምልኮአዊና መንፈሳዊ ትርጉም
ዮሴፍ ዘአርማትያስ
✅ ግልጽ እምነትን ይወክላል
✅ መስዋዕት የሆነ ፍቅርን ያሳያል
✅ አዲስ መቃብሩን በመስጠት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ታላቅ ስጦታን ያመለክታል
✅ አዲስ መቃብር ለክርስቶስ የተዘጋጀ ንጹሕ ልብን ነው ።
ኒቆዲሞስ
✅ መንፈሳዊ ዕድገትን ያሳያል
✅ ከድብቅ እምነት ወደ ግልጥ ደቀመዛሙርትነት መሸጋገርን ይገልጣል
✅ ሰበኑ ለጌታ የሚገባ ክብርን ይወክላል
❇️ የጌታ መቀበር ✅
የጌታ መቀበር ጥልቅ የሆነ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ዝም ብሎ ታሪክ ብቻ አይደለም ምሥጢራዊ ትርጉም አለው
✅ ወደ መቃብር መውረዱ ሞትን ድል ሊያደርግ መሆኑን ያሳያል
✅ አዲስ መቃብር በሦስት ወገን ድንግል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ኃጢአት ያልነካው ንጹሕ ልብን ይወክላል
✅ ሁለቱ ሰዎች በመረዳት የሚፈጸም ተግባርና በድፍረት የሚገለጥ ጥበብን ይወክላሉ።
❇️ በዝማሬና ንባብ አገልግሎት ✅
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልግሎቷ ሁሉ ኒቆዲሞስንና ዮሴፍ ታወድሳለች የጌታችንን ሥጋ ስላከበሩ ታከብራቸዋለች በዕለተ አርብ ሕማማት ላይ ሥራቸውን ትገልጣለች። የቤተ ክርስቲያን ጌጧ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ አወድሶ ገልጧቸዋል
ማጠቃለያ