St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
1.97K photos
23 videos
12 files
458 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 17/2017 ዓ.ም
#Mpox
ኤም ፖክስ
#MPox
____

ምንነቱ! አጠቃላይ እውነታዎች!

ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡

የበሽታው ታሪካዊ ዳራ

የኤም ፖክስ ቫይረስ በዴንማርክ (1958) በዝንጀሮዎች ውስጥ የተገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ላይ የተገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነው፡፡ በቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዘው የዘጠኝ ወር ህጻን ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1980 የፈንጣጣ በሽታን ማጥፋት እና የፈንጣጣ ክትባት በአለም አቀፍ ደረጃ ማብቃቱን ተከትሎ ኤም ፖክስ በመካከለኛው፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ያለማቋረጥ ብቅ እያለ ይገኛል። በ2022-2023 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ተከስቷል። እንደ ሽኮኮዎች እና ጦጣዎች ያሉ የተለያዩ ትናንሽ አጥቢ እንስሳት ለበሽታው የተጋለጡ ናቸው፡፡

ከ1970 በኋላ የኤም ፖክስ በሽታ በመካከለኛው እና ምስራቅ አፍሪካ (ክላድ I) እና በምዕራብ አፍሪካ (ክላድ II) አልፎ አልፎ ተከስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2003 በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተከሰተው ወረርሽኝ ከውጭ ከሚገቡ የዱር እንስሳት (ክላድ II) ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ከ2005 ጀምሮ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የተጠረጠሩ ህሙማን ሪፖርት ይደረጋሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2017፣ የኤም ፖክስ በሽታ በናይጄሪያ እንደገና ብቅ አለ እና በመላ አገሪቱ እና ወደ ሌሎች መዳረሻዎች በሚጓዙ ሰዎች መካከል ተስፋፍቷል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በ Clade I MPXV ምክንያት የኤም ፖክስ ወረርሽኝ በሱዳን ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ተከስቷል፡፡

የበሽታው ምልክቶች

ኤም ፖክስ በሽታ ቫይረሱ ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያለው ሰው የሚከተሉት ምልክቶች በሚታዩበት ወቅት ማለትም ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የእጢ እብጠት፣ የቆዳ ቁስለትና ድካም፣ የጡንቻና የጀርባ ህመም ሲያስተውል በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን የምርመራና ህክምና አገልግሎት ማግኘት ይኖርበታል።

መከላከያ መንገዶች

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ባሉባቸው ታማሚዎች አካባቢ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም፥ የኤም ፖክስ መሰል ሽፍታ የሚታይባቸው ሰዎች ጋር ባለመነካካት እና ታማሚዎቹ የተጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና መኝታ በአግባቡ ሳያጸዱ ባለመጠቀም፣ የግል እና የእጅ ንፅህና በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል።

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በሚገኝበት ጊዜ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርግ ወይም በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡