Solomon driving school
397 subscribers
24 photos
8 videos
1 file
6 links
ጀሞ 1 ሩት ህንፃ ላይ እንገኛለን
ስልክ - 09-09-72-72-72
Download Telegram
የማለስለሻ ክፍሎች

ኦይል ፓን(ሶቶኮፓ):-ለሞተር ማለስለሻ የሚያስፈልገዉን በቂ ዘይት የሚይዝና በዉስጡ ማጣሪያ እና ዲፕስቲክ የሚይዝ ክፍል ነዉ።

ኦይል ፓምፕ(የዘይት ፓምፕ):- ዘይትን ከሶቶኮፓ በመሳብና በመግፋት በከፍተኛ ፕሬዠር(ግፊት) በዘይት ማጣሪያ አልፎ የሞተር ክፍሎችን እንዲያለሰልስ ያስችለዋል።

ኦይል ፊልተር:- ከኦይል ፓን ከሚመጣዉ ዘይት ጋር ተቀላቅሎ የሚመጣን ቆሻሻ በማጣራት ንፁህ ዘይት ወደ ዘይት መስመር እንዲያልፍ ያደርጋል።

ኦይል ጋለሪ(የዘይት መስመር):- ዘይት ከሶቶኮፓ እስከ ሞተር ሲሊንደርና የሞተር ቴስታታ ድረስ የሚያስተላልፍ መስመር ነዉ።

ኦይል ስክሪነር(የመጀመሪያ የዘይት ማጣሪያ):- ኦይል ፓን(ሶቶኮፓ) ዉስጥ የሚገኝ የዘይት ማጣሪያ ሲሆን የዘይት ቆሻሻን በማጣራት ወደ ዘይት ፓምፕ የሚያስተላልፍ ክፍል ነዉ።

ዲፒስቲክ(ሊቤሎ):- ኦይል ፓን(ሶቶኮፓ) ዉስጥ የሚቀመጥ ቀጭን ዘንግ ሲሆን የዘይት መጠንን, የዘይት መቆሸሽን, የዘይት ዉፍረትና ቅጥነትን ለማረጋገጥ ይጠቅማል።

ኦይል ኩለር( የዘይት ማቀዝቀዣ):- ዘይት የማስለስ ተግባሩን በሚያከናዉንበት ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሞቅ ሲሆን ኦይል ኩለር ይህን የሞቀ ዘይት እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል።

ሪተርኒንግ ላይን( መላሽ መስመር):- ዘይት የማለስለስ ተግባሩን ካከናወነ በኋላ ከሞተር ክፍሎች ወደ ሶቶኮፓ የሚመለስበት መስመር ነዉ።

የማለስለስ ዘዴ የሚካሄደዉ በሁለት አይነት መንገድ ሲሆን በክራንክ ሻፍት ጭለፋ እና በዘይት ፓምፕ አማካኝነት ነዉ።

ክራንክ ሻፍት በከፊል ሶቶኮፓ ዉስጥ የገባ ከሆነ ዘይትን በመጨለፍ የሲሊንደር ፒስተንና ሌሎች የሞተር ክፍሎች እንዲለሰልሱ ያደርጋል።

የዘይት ፓምፕ ደግሞ ዘይትን በከፍተኛ ሀይል በመግፋት የተለያዩ የሞተር ክፍሎችን ያለሰልሳል

ሰለሞን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

ቁ.1,  ጀሞ ሩት ህንፃ ላይ

ቁ.2,  ሳሪስ ነጋ ቦንገር ህንፃ ጎን

ስልክ:-  09-06-72-72-72/09-09-72-72-72
Oil pan (ሶቶኮፓ )
Dipstick (ሊቤሎ )
Oil pump ( የዘይት ፓምፕ )
Oil filter ( የዘይት ማጣሪያ )
ለጀማሪ አሽከርካሪ የመጀመሪያ ቀን አነዳድ ማብራሪያ...

1,መሪ:- የአሽከርካሪዉ እጅ የሚያርፍበትና ተሽከርካሪዉን ወደፈለገዉ አቅጣጫ የሚያዞርበት ክፍል ነዉ።

2,ፍሬን
2.1 የእግር ፍሬን:- የተሽከርካሪን ፍጥነት ለመቀነስና ሙሉ ለሙሉ ለማቆም የሚያስችል መቆጣጠሪያ ክፍል ነዉ።

2.2 የእጅ ፍሬን:- ተሽከርካሪን ለአጭርና ለረጅም ጊዜ አቁሞ ለማቆየት የሚያስችል የተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ ክፍል ነዉ።

3,ፔዳል
3.1 ነዳጅ መስጫ ፔዳል(አክስለሬተር ፔዳል):- በማንዋል ትራንስሚሽን መኪኖች ላይ በእግራችን ከምንረግጣቸዉ ሶስት ፔዳሎች ዉስጥ በስተቀኝ የሚገኘዉ ሲሆን የተሽከርካሪን ፍጥነት ለመጨመር ይጠቅማል።

3.2 ፍሬን ፔዳል(ብሬክ ፔዳል):- ከለይ እንደተጠቀሰዉ ይህ ፔዳል ከሶስቱ ፔዳሎች መሀል ላይ የሚገኘዉ ሲሆን በቀኝ እግራችን እንረግጠዋለን በዚህ ጊዜ የተሽከርካሪዉ ፍጥነት ይቀንሳል ወይም ተሽከርካሪዉ ይቆማል።

3.3 ፍሪሲዮን ፔዳል(ክለች ፔዳል):- በስተግራ በኩል ያለዉና በግራ እግራችን የምንረግጠዉ ፔዳል ሲሆን የተለያዩ ጥቅሞች አሉት።

4,የፍሪሲዮን ጥቅሞች
4.1 ማርሽ ለመቀየር ይጠቅማል
4.2 ፍሬን ስንይዝ ሞተር እንዳይጠፋ ያደርጋል
4.3 በዳገታማ እና በቁልቁለት ቦታ ስንነሳ ባላንስ ለመስራት ይጠቅማል።

5, ማርሽ
የአይሱዙ ህዝብ አንድ መኪና ማርሽ አገባብ:-

1ኛ ማርሽ:-ወደ ሹፌር አቅጣጫ(ወደራሳችን) ሳብ አድርገን ወደኋላችን በምንስብበት ጊዜ 1ኛ ማርሽ ይገባል።

2ኛ ማርሽ:-ከአንደኛ ማርሽ ቀጥታ ወደፊት በምንገፋት ጊዜ እናገኛለን
3ኛ ማርሽ:-ከሁለተኛ ማርሽ ቀጥታ ወደኋላ በምንስብበት ጊዜ ይገባል።

4ኛ ማርሽ:-  ወደ ቀኝ ማለትም ሹፌሩ ካለበት በተቃራኒ አቅጣጫ ገፋ አድርጎ ወደፊት በመግፋት ማስገባት እንችላለን።

5ኛ ማርሽ:-ከአራተኛ ማርሽ በቀጥታ ወደኋላ አቅጣጫ በመሳብ ማስገባት ይቻላል።

የኋላ ማርሽ:- ወደእኛ አቅጣጫ በመሳብ ወደፊት በምንገፋበት ጊዜ የኋላ ማርሽ እናስገባለን

6, ፍሬቻ
6.1 የግራ ፍሬቻ:- ለሚከተሉት ጥቅሞች ያገለግላል:ከቆምንበት ለመነሳት,ወደግራ ለመታጠፍ,ለመቅደም, ከቀኝ ወደ ግራ ረድፍ ለመለወጥና ወደ ግራ ዞሮ ለመመለስ።

6.2 የቀኝ ፍሬቻ:የሚከተሉት ጥቅሞች ይሰጣል:ወደቀኝ ለመታጠፍ;ለማስቀደም;ከግራ ወደ ቀኝ ረድፍ ለመቀየር

7,ቁልፍ
አራት ደረጃዎች አሉት
ቁልፍ በነዚህ አራት ደረጃዎች ላይ በሚሆንበት ጊዜ:-

7.1 Lock(ሎክ):- በዚህ ጊዜ የተሽከርካሪዉ ክፍሎች በሙሉ ዝግ ናቸዉ ማለትም ሀይል አያገኙም።

7.2 acc(አክሰሰሪ):- ቴፕና ሌሎች የተሽከርካሪዉ አክሰሰሪዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ያገኛሉ።

7.3 on(ኦን):- የዳሽቦርድ ላይ ጠቋሚ ምልክቶች ይበራሉ

7.4 start(ስታርት):- ሞተር ይነሳል።


ሰለሞን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

አድራሻ - ጀሞ 1 ሩት ህንፃ ላይ

ስልክ:-  09-06-72-72-72/09-09-72-72-72
የባላንስ አሰራር ማብራሪያ

አንድ አሽከርካሪ ባላንስ የሚሰራዉ ወደ ዳገት ለመሄድ ከቆመበት ሲነሳ ሲሆን የባላንስ ዋና ጥቅም ተሽከርካሪ ስትራፕ አድርጎ(ተንሸራቶ) እንዳይነሳ ለማድረግ ነዉ።

ዳገት ላይ የቆመን መኪና ፍሬን አሽከርካሪዉ በሚለቅበት ጊዜ የመሬት ስበት ሀይል(Gravity) ተሽከርካሪዉን ወደኋላ እንዲሽከርከር ያደርገዋል። በዚህ ጊዜ ከኋላ በቅርብ ርቀት የቆመ መኪና ካለ የመጋጨት አደጋ ይከሰታል።

በተመሳሳይ የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ቁልቁለት ዙሮ የቆመ መኪና ወደኋላ ለመነሳት ቢፈልግና ባላንስ ሳይሰራ ፍሬን ቢለቅ አሁንም በመሬት ስበት(Gravity) ምክንያት ተሽከርካሪዉ ወደፊት ሄዶ ከፊቱ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር ይጋጫል።

ስለዚህ ባላንስ ይህን ሁኔታ ለመቅረፍ የሚተገበር ነዉ።

የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ዳገት የዞረ ከሆነ እና አሽከርካሪዉ ወደ ፊት መነሳት ሲፈልግ አንደኛ ማርሽ በማስገባት ባላንስ ሰርቶ ይነሳል። ይህ የፊት ባላንስ ይባላል።

የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ቁልቁለት ዙሮ አሽከርካሪዉ ወደኋላ ማለትም ከቁልቁለት ወደ ዳገት ለመነሳትና ለመሄድ ሲፈልግ የኋላ ማርሽ በማስገባት ባላንስ ሰርቶ ይነሳል። ይህ የኋላ ባላንስ ይባላል።

ባላንስ እንዴት እንሰራለን?

ወንበራችንን አስተካክለን የደህንነት ቀበቶ ካሰርን በኋላ ሞተር አስነስተን ጉዞ ለመጀመር ዝግጁ እንሆናለን,ዳገት ላይ ወደፊት የምንሄድ ከሆነ 1ኛ ማርሽ ወደኋላ የምንሄድ ከሆነ ደግሞ የኋላ ማርሽ አስገብተን የእጅ ፍሬን እናወርዳለን።

በዚህ ሂደት በቀኝ እግራችን የእግር ፍሬን ፔዳልን እንረግጣለን በግራ እግራችን ደግሞ ፍሪሲዮን ፔዳልን እንረግጣለን።

ከዚህ በመቀጠል የግራ እግራችንን ከፍሪሲዮን ፔዳል ላይ ማንሳት እንጀምራለን።ቢያንስ እስከግማሽ ድረስ ፔዳሉን ለቀቅ ስናደርግ የሞተር ድምፅ ይቀየራል በዚህ ጊዜ ፍሪሲዮን ፔዳሉን ባለበት ይዘን የቀኝ እግራችንን ከእግር ፍሬን ፔዳል ላይ ሙሉ ለሙሉ እናነሳለን።

በዚህ ጊዜ ተሽከርካሪዉ ያለፍሬን በፍሪሲዮን ብቻ ይቆማል። በመሬት ስበት ሀይል ወደ ቁልቁለት ስትራፕ አያደርግም (አይንሸራተትም)

ከዚህ በመቀጠል የቀኝ እግራችንን ነዳጅ መስጫ ፔዳል ላይ በማሳረፍ ነዳጅ እየሰጠን የግራ እግራችንን ከፍሪሲዮን ፔዳል ላይ ቀስ በቀስ ሙሉ ለሙሉ ስናነሳ ተሽከርካሪዉ ይነሳል(ይንቀሳቀሳል)።


ሰለሞን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

አድራሻ - ጀሞ 1 ሩት ህንፃ ላይ

ስልክ:-  09-06-72-72-72/09-09-72-72-72