Soccer Ethiopia
86.4K subscribers
63.2K photos
180 videos
6 files
21.1K links
The voice of Ethiopian football

For business enquiries ONLY

Tell: +251940018801
Email: ads@soccerethiopia.net
Download Telegram
የፋሲል ከነማ የቡድን አባላት በህመም ላይ ለሚገኙት የመቐለ 70 እንደርታው ምክትል አሰልጣኝ ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ ድጋፍ አድርገዋል

በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት በኢትዮጵያ እግርኳስ የራሱን አሻራ ያሰፈረው የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያና ዋልታ ፖሊስ ትግራይ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ በአሁኑ ወቅት በካንሰር በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ታሞ ይገኛል።በመሆኑም ህክምናው በሀገር ውስጥ የማይሰጥ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ወጥቶ እንዲታከም የህክምና ባለሙያዎች ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

በመሆኑንም ለህክምናው ውጭ ሀገር በመሄድ እንዲታከም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ የቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላት መዋጮ በማድረግ የ50 ሺ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል።

የክለቡ አባላትም ሌሎች ክለቦች ይህንን መልካም አርዓያ ያለውን ተግባር ተቀላቅለው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፍ ለማድረግ 👇

ወ/ሮ ትብለፅ ገብረመስቀል

👉 የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ | 1000184557375

👉 ወጋገን ባንክ | 0952411530101
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት አጠቃላይ ውጤቶች ፣ የ24ኛ ሳምንት መርሐግብር ፣ የደረጃ ሰንጠረዥ እና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ደረጃ !
ታታሪ ወጣቶች ነገን ዛሬ ይሠራሉ!

የታዳጊ ወጣቶች ቁጠባ ሒሳብ

========

የታዳጊ ወጣቶች ቁጠባ ሒሳብ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ተሰማርተው ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ታዳጊ ወጣቶች ከሚያገኙት ገንዘብ በመቆጠብ ለነገ ስኬታቸው መሠረት የሚጥሉበት ነው።

• ከመደበኛው የቁጠባ ሒሳብ የተሻለ ወለድ ያስገኛል፡፡

• ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች የሚከፍቱት ሒሳብ ነው፡፡

• ከወላጆቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር የሚኖሩ ወጣቶች ይህን የቁጠባ ሒሳብ በወላጆቻቸው ወይም በአሳዳጊዎቻቸው አማካኝነት መክፈት ይችላሉ።ታታሪ ወጣቶች ነገን ዛሬ ይሠራሉ!
#CBE #Teen #saving #youth #bank #Ethiopia
Forwarded from GOFERE
😍 አርቲስቶች ፣ ድምፃውያን ፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮችን በጎፈሬ ማሊያ ለማየት ዝግጁ ናችሁ? 🤩

ጎፈሬ የታዋቂ ሰዎች አዝናኝ የስፖርት ፌስቲቫል ውድድርን አጋር ሆነ

በቅዳሜ ሚዲያ እና አድቨርታይዚንግ አዘጋጅነት በአርቲስቶች ፣ ድምፃውያን ፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች መካከል ደማቅ ስፖርታዊ ውድድር ሊደረግ ቀን ተቆርጦለታል። ውድድሩ እንደ ፌስቲቫልነቱ አዝናኝ ከመሆኑ ባሻገር ለመቄዶንያ የአረጋዉያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ገቢ የማሰባሰቢያ በጎ ዓላማ ይዞ በደማቅ ሁኔታ ሚያዚያ 23 እና 26 የሚከናወን ይሆናል።

የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነው ጎፈሬም ውድድሩን በምርቶቹ እና በሽልማቶች ለማድመቅ የሁለት ዓመት የአጋርነት ስምምነት በዛሬው ዕለት ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድቨርታይዚንግ ጋር ተፈራርሟል።

ዛሬ ቀትር ላይ በሀርመኒ ሆቴል በርካታ የጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ስርዓት እና ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቅዳሜ ሚዲያ ከጎፈሬ ጋር ስምምነቱን ከፈፀመ በኋላ የአርቲስቶች፣ የድምፃውያን፣ የጋዜጠኞች እና የቲክቶከሮችን ቡድን በመወከል የቡድኖቹ አምበሎች ከውድድሩ በፊት የቃላት ጨዋታ የጀመሩበትን ፍልሚያ ከመድረክ ሆነው ጀምረዋል።

@goferesportswear