SOA COMMUNITY GEjA 2 CAMPUS
1.11K subscribers
851 photos
40 videos
398 files
90 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ 👉👉👉 @SOA2C
Download Telegram
Forwarded from Tani Gold
Forwarded from Tani Gold
Forwarded from Kolfe education official channel🇪🇹 (Mesfin👩‍👩‍👦‍👦Asnake)
#ጥቆማ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ቀዳማዊ ምንሊክ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2018 ዓ.ም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ይቀበላል፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈቶች የምታሟሉ ተማሪዎች ማመልከት ትችላላችሁ።

መስፈርቶች፦
➫ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች፣
➫ የክልል አቀፍ ፈተና ውጤት አማካይ 80 እና ከዚያ በላይ፣
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የመቀጠል ፍላጎት ያለው/ያላት፣
➫ ምንም አይነት የስነ-ምግባር ችግር የሌለበት/የሌለባት፣
➫ በትምህርት ቤቱ ህግና ስርዓት ለመመራት ፈቃደኛ የሆኑ፣
➫ በቀጣይነት ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አውቀው በትጋት ለመማር ዝግጁ የሆኑ።

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ፦
➫ ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ኮፒው
➫ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሐምሌ 14-18/2017 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ፦
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ቀዳማዊ ምንሊክ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፣ አራት ኪሎ አራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት

@tikvahuniversity
Forwarded from SOA
የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽኝት መርሃግብር
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ስማርት ስልኮችን ከተጠቀሙ የአዕምሮ ጤናቸው ይጎዳል - ጥናት
*******

በዓለም አቀፍ ደረጃ በ163 ሀገራት በተደረገ ጥናት፤ ስማርት ስልኮችን መጠቀም እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን አዕምሮ ሊጎዳ እንደሚችል ጥናት አመላክቷል።

መቀመጫውን በአሜሪካ ቨርጂኒያ ያደረገውና በዶ/ር ታራ ታጋራጃን የሚመራው ይኸው የተመራማሪዎች ቡድን፤ የጥናቱን ውጤት ይፋ አድርጓል።

2 ሚሊዮን በሚሆኑ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች በሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ላይ በተደረገው በዚህ ጥናት መሰረት፤ በዚህ እድሜ ስማርት ስልኮችን መጠቀም በተለይም በሴት ታዳጊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥነ-አዕምሮ ችግር ሊዳርግ እንደሚችል በጥናቱ ተገልጿል።

በተመራማሪዎቹ የጥናት ውጤት መሰረትም በዚህ እድሜ ስልክ የሚጠቀሙ ታዳጊዎች፤ በኢንተርኔት ለሚቃጣ ጾታዊ ትንኮሳ፣ ስሜታዊ የመሆን፣ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት፣ ራስን ዝቅ አድርጎ የማየት፣ ከወላጆች ጋር አለመግባባት፣ ብሎም ራስን ለማጥፋት እስከማሰብ ለሚደርስ አደገኛ የስነ አዕምሮ ችግር ሊያጋልጣቸው ይችላል ተብሏል።

የተመራማሪዎች ቡድኑ አባላት የጥናቱን ውጤት ይፋ ባደረጉበት ወቅት አፅንኦት ሰጥተው እንዳሳሰቡት፤ እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር ለመፍታት በዓለም አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ስማርት ስልኮችንና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ እንዲወጣ መጠየቃቸውንም ሲኤንኤን ዘግቧል።

ዶ/ር ታራ ታጋራጃን ወላጆች ሊወስዱት የሚገባው ትልቅ እርምጃ፤ በተቻለ አቅም ልጆች ከስማርት ስልኮች እንዲርቁ እና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።
©️እጅግ አስተማሪ ታሪኮች
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA